ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ ከኦሮሞ ጠባብ ዘረኘትና ጎሰኝነት ወጥቶ ኢትዮጵያዊነትን የማንነት የታሪኩ አካል ማድረግ አለበት

ከአልማዝ አሸናፊ
ዋዮሚንግ አሜሪካ

ሰብዓዊነት ያለውና ለአገር ደህንነት የሚያስብና የሚቆረቆር : በተለይ እንደእኔ ባልተወለድንበት አገር ማንነታችንና ሰብዓዊ መብታችን ተከብሮ የምንኖር በሰላም ማጣትና በመልካም አስተዳደር ጉድለት ከትውልድ ወደ ትውልድ በድህነት የሚጎሳቀል ሕዝብ ያለባትን አገር ተሻሽሎ ማየት የማንኛውም ሸጋ አሳቢ ምኞት ነው::

እንግዲህ በሰለጠነውና የመልካም መንግስታዊ አስተዳደር በታደለው የአሜሪካ አገር የምንኖር ኢትዮጵያውያን ትምህርት ከመቅሰም : ገንዘብ ማግኘትና ጥሩ ኑሮ ከመኖር ባሻገር ግንዛቤያችን ውስጥ መክተት ያለብን አንድ ነገር ነው:: ይህም እንዴት መጤዎች ተባብረውና ተዋህደው የመጡበትን አዲስ አገር (USA) በ247 ዓመታት ውስጥ የዓለማችን አንደኛ የበለፀገችና በአንፃሩ ሰላምንና የሕዝቦቿን ደህንነትና መብቶች የሚያከብር መልካም መንግስታዊ አስተዳደርን ልምድ ማድረጏ : የመኖሯ መሰረታዊ ምሰሶ መሆኑን ነው:: በእኛ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህ የመልካም መንግስታዊ አስተዳደር ጉድለትና የጎሳ ክፍፍል የችግራችን ዋነኛ መንሴዎች ናቸው:: ትልቁ የሕዝብና የመንግስት ህብረታዊ ትግል መሆን ያለበት እነዚህን ሁለቱን የአገር ሰላም በሽታዎችን ማጥፊያ ዘመቻ ላይ ነው::

መንግስት ሀገራዊነት እንጂ ጠባብ ጎሰኝነትን ማራመድ ተገቢው እንዳልሆነ ማንም ሊነግረው አይገባም:: መንግስት ለሕዝብ ታዛዥና ሕግ አስከባሪ እንጅ ሕዝብን የሚያሰቃይና የሚያስተዳድርበትንና የሚተዳደርበትን ሕግ አፍራሽና ረጋጭ መሆን የለበትም::

ባለሁበት ሀገረ አሜሪካ ወንጀለኞችና የግል ፍላጎታቸው ላይ ያተኮሩ የሕዝብ አካላት አሉ:: በአሜሪካም ሀገርን ለጥቅም አሳልፈው የሚሸጡ አይጠፉም:: ግን እነዚህ ወንጀለኞች የሚፈረጁት ስልጣን ላይ በተቀመጠው አካል ምርጫና ፍላጎት ወይም የአገሪቱ ሕገ መንግስት ላይ የተቀመጠው ፍትሕ ማራመጃ ሕጎች ተጥሰውና ተንቀው አይደለም:: ሕግን ለማስከበር አደራ የተጣለበት ሕግ አስከባሪ አካል : የመንግስት ሕዝብ መጮቆኛ መሳሪያ ሲሆን አገሪቱ ካለችበት የእርስ በርስ መገዳደል ልክፈት አትድንም:: ለምሳሌ JANUARY 6, 2021 በትራምፕ ምክንያት በኮንግሬስ ውስጥ የተፈፀመው የትራምፕ ደጋፊዎች ወረራ እጅግ አሳዛኝና በአሜሪካ ምድር ላይ ይደረጋል ተብሎ ያልተጠበቀ ክህደታዊ ደርጊት ነው:: ከ1000 በላይ ሰዎች በዚህ ጉዳይ ተከሰዋል:: ግን ፍርድ ፊት ቀርበው በሕጉ መሰረት ፍርድ እያገኙ ይገኛሉ እንጂ አገር ከሃዲዎች ተብለው እንደሶስተኛ ዓለም መንግስታት በመንግስት ፍላጎት ያለፍርድ አልታሰሩም:: አልተገደሉም:: እንዲያውም አንዳንዶቹ ባለማወቅ ስህተት ውሥጥ መግባታቸውን ስለተፀፀቱ በይቅርታ ነፃ ሆነዋል:: ይህንን ነው እኛ ለራሳችንም መገንዘብና መንግስትንም ማስገንዘብ ያለብን::

ግን በየመድረኩ የምታዘበው አንዱ ክፍል ድፍን ባለ ሁኔታ “ልጅን ከወደዱ እስከቅዘኑ” በሚል መንፈስ ያለውን የኢትዮጵያ መንግሥት እየደገፈ መላእክ አስመስሎ ተጠያቂ አለማድረግና ሌላው ክፍል ደግሞ መንግስትን በሁሉም ረገድ በመቃወም ፍፁም ሰይጣን ሲያደርግ ነው:: የልጅን ቅዘን የማንፀየፍበትና የማንከፋበት ምክንያት ህፃን ልጅ ለድርጊቱ ኃላፊነትን ለመቀበል ስላልበቃና አውቆ ተንኮል ቀይሶ ቤተሰቦቹን ሆነ አቃፊዎቹን ለመጉዳት አስቦ የሚቀዝን እንዳልሆነ ስለምናውቅ ነው:: ግን የመንግስት ዋናና የመጀመሪያ ግዴታው ስሜታዊ በመሆን እንደፈለገ ሕዝብ ላይ መቅዘንና ተናገራችሁኝ : ወረፋችሁኝ : ተቃወማችሁኝ በማለት እንደህፃን ልጅ ምክንያተ አልባ ትእቢታዊ ቁጣ (TANTRUM) ማሳየት ሳይሆን ለሚሰራው ጥፋት ተጠያቂ መሆን እንዳለበት ተገንዝቦ ሕዝብን ካለበት ከመኖርና ያለመኖር ውዥንብርና ከተሸከመው የችግር ቀንበር ማላቀቅና ሰላምና ደህንነቱን ተቀዳሚ ስራው ማድረግ ይጠበቅበታል::

መንግስት ይህንን ለማድረግ የስራዎች ቅደም ተከተል ተራ ሊኖረው ይገባል እላለሁ:: ይህን ተግባራዊ የማድረግ ፍላጎት ስለሌለው ወይም ፈቃደኝነት ስለማይሳይ መንግስትን በግሌ እቃወማለሁ:: በእርግጥ አንች ምን አውቀሽ ነው ሩቅ ተቀምጠሽ መንግስትን በዚህ አኳያ የምትቃወሚው ብላችሁ : ቢመቻችሁ በካሃዲነት ከሳችሁ ከርቸሌ ለመክተት የምትሹ አትጠፉም:: ይህንን ካሰባችሁ የአመለካክቴን ቅድመ ሁኔታ ካለመረዳታችሁ ነው እላችሗለሁ:: ይህም እኔ የእድሜዬን 3 ተኩሉን ጊዜ ያሳለፍኩት የግለሰብ ነፃ አመለካከትና አስተሳሰብ በሚከበርበት አገር ውስጥ ነው:: ኢትዮጵያን በጥልቅ አውቄ ሳይሆን በቆየሁበት የውጭ አገር ያየሗቸውንና የታዘብኳቸውን የመልካም መንግስታዊ አስተዳደር መንገዶችንና ዘቤዎችን ለተወለድኩባት ታሪካዊ ሀገር የመልካም ታሪኳ አካል ለመሆን የሚቻለውን የመልካም መንግስታዊ አስተዳደር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ አህመድ እንዲነድፈውና እሱም የዚህ መልካም መንግስታዊ አስተዳደር መስራች ሆኖ የታሪኩ አካል ቢሆን ብዬ ነው::

ምን ማስቀደም አለበት ከሚል አንፃራዊ ጥያቄ በመነሳት የገበታ ለሀገር ሀለላ ኬላ ሪዞርት መቅደም አለበት ወይስ ሰላም በአገሪቱ መስፈን አለበት? በዚህ ላይ ግልፅ ማድረግ የምፈልገው የዳውሮ (በበፊቱ ስም ኩሎ ኮንታ) ተወላጅ በመሆኔ ይህ የፓርኩ መገንባትና ተነግሮ የማይታወቀው የዳውሮ ታሪክ የኢትዮጵያ ታሪክ ክፍል መሆኑ ሊያስደስተኝ ይገባል:: ግን ዳውሮ አንፃራዊ ሰላም ቢኖረውም : ሌላው የሀገሪቱ አካል እየታመሰ በሀገሪቱ የሰላም ዕጦት በዳውሮ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚያመጣውን ችግሮች መገንዘብ አይሳነኝም:: ለዚህም ነው ሰላምና የሀገሪቱ የሕዝብ ደህንነት ቅድሚያ ይሰጠው የምለው:: ታዲያ ሰላምንስ የሚያመጣው ማነው? የሰላም አምባሳደር ማን መሆን አለበት? ሰብዓዊ መብቱና ደህንነቱ እንዲጠበቅና እንዲከበር የሚጠይቀውን ሕዝብ መንግስት ካሰረና ከገደለ ልማቱና እድገቱ ለማን ነው? አንዱን ጎሳ የአገር አፍራሽና የአገር ጠላት ብሎ : መሪው የወጣበትን ጎሳ የአገር ህልውና ጠባቂ በማስመሰል ሲያሽሞነምን የሚታይ የመንግስት አመራር አካል : መሪው የመጣውና በሕዝብ የተደገፈው ለአንድ ጎሳ የበላይነት ወይስ ለሁሉም ሕዝብ እኩልነት ለመቆም ነው? በእንዲህ ዓይነት የጎሳ አድልኦ መሪ ሲቆሽሽ የሁሉም ኢትዮጵያውያን መሪ ነው ብሎ ማመን እጅግ ይከብዳል:: ምንም እንኳ በጠባብ ጎሰኞች ቢከበብም የሁሉ ኢትዮጵያውያን መሪ መሆን ከፈለገ ዶ/ር አቢይ አህመድ ከዚህ የጎሳ አድልኦ ስሜት መውጣትና ራሱን ማፅዳት ይገባዋል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የተገረምሁበት የስብሐት ነጋ ቃለመጠይቅ - መንግስቱ ሙሴ (ዶ/ር) ከዳላስ/ቴክሳስ

ዶ/ር አብይ በአጀማመሩ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ታይቶ የማይታወቅ አምራቂና አስደናቂ ሀገራዊ ታሪክ ይሰራል ተብሎ የተገመተ መሪ ነበር:: ጊዜም ይሰጠው ሲባል ሁላችንም ይሰጠው ብለን በአንድነት ከጎኑ ቆመን የስልጣኑ መሰረት ሆነን ያላለአንዳች ጥርጣሬ መቶ በመቶ ተማምነንበት ደግፈነው ነበረ:: ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በአንድ ወቅት ፓርላማ ውስጥ ሲናገር መንግስታችንን ተቃወማችሁ ብለው ከቡራየውና ከአካባቢው ወደ አዲስ አበባ በቁጣ ሊጏዙ የነበሩትን የኦሮሞ ጎሰኞችና ፅንፈኞች (እነዚህ ሁለቱ ቃሎች የእኔ እንጂ ጠ/ሚሩ የተናገሩት አይደሉም) ለማስታገስ ውስጤ ቢከፋም እኔ ለእናንተ ፈገግታ አሳይ ነበር ብሎ የተናገረውን ደጋግሜ ሳስታውስ በእርግጥ ይህ ሰው ለአገር መሪነት ወይስ ሕዝብን አታሎ የአንድን ጎሳ ጠባብነትና የበላይነት እውን ለማድረግ የተላከ ግብዝ መልእክተኛ ነው? የሚል ጥርጣሬና ጥያቄ ተሰማኝ::

ጠቅላይ ሚኒስቴራችን መርሳት የሌለበት በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በዲያስፖራ እየዞረ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ምልክት የሆነውን አረንጏዴ ቢጫና ቀይ ባንዲራችንን ሲያውለበልብ ዛሬ ያቀፉትና እሱ ያቀፋቸው ጎሰኛና ፅንፈኛ ኦሮሞች ዶ/ር አብይ አህመድ አማራ እንጂ ኦሮሞ አይደለም ብለው ሲክዱት ነበር:: ዛሬ ግን እሱ ለጎሳ ደንታ ቢሰጠውም ባይሰጠውም ለስልጣኑ መከታ የሚሆንለትንና የስልጣን እድሜውን የሚያራዝምለትን ጎሰኝነትና ዘረኝነት መሆኑን በመረዳት ሕዝብ ሲያቃጥልና ሲገድል ከነበረው ኦኔግ ሸኔ እየተደራደረ የአማራን ፋኖ እንደ አገር አጥፊ ቆጥሮ አማራዎችን ሰላም ማሳጣቱ : ሰላም ለተወሰነ ሕዝብ ብቻ ናት ወይ? ያስብላል:: ሀገራዊ ሰላም ከተፈለገ በየአካባቢዎች ያሉትን ችግሮች ለመፍታት በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የሰላም ድርድር መደረግ ይገባል:: በጠመንጃና በስለላ ሕዝብን ማስፈራራትና ማንበርከክ ላለፉት የዓለም አምባገነን መሪዎችም አልሆነም:: ለተወሰነ ጊዜ ሕዝብ ሊንበረከክ ይችላል:: ግን ሕዝብ ተቆጥቶ ከባርነት ሞት ይሻለኛል ብሎ ገንፍሎ ከተነሳ ውቅያኖስን እንደሚያናውጥ አጥፊ ማእበል ነው:: ትርፉ እልቂትና የአገር ውድመት ነው:: ይህንን ዶ/ር አብይ አህመድ ይፈልጋል አልልም::

ሁላችንም እንደምናውቀው ዛሬ ከ50 እድሜ በታች ያለው ኢትዮጵያውያን በቁጥር ከመቶው ከፍተኛ ብልጫ ያለው ሲሆን ያደገውም በጎሳ ክፍፍል ፖለቲካ ውስጥ ነው:: ይህም የህዝባችን ክፍል ዛሬ አገሪቱን የሚመራው የጠቅላይ ሚኒስቴሩ ትውልድ ነው:: ወያኔ አገሪቱን በጎሳ የከፋፈለበትን የልዩነት መርዝ ይህ መሪ ማርከሻ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት ነበር:: ያ ተስፋ ደብዙ እየጠፋ ሲመጣ ለካስ የወያኔ ልክፍት በቀላል የሚለቅ እንዳልሆነ መረዳት ችለናል:: ወያኔ ላይ አረመኔው ጁንታ እያለ ውርጅብኝ እንዳላወረደበት ዛሬ የኢትዮጵያን ሕዝብ ስቃይና መከራ ወደጎን ገፍቶ ለወያኔ ስልጣን ሰጥቶ የትግራይን ሕዝብ ድጋሚ የእነዚህ ጁንታዎች ሰለባ እያደረገ : ለሀገር የተሰዋውን አማራ : ፅንፈኛና የውጭ ቅጥረኞች እያለ ሲያስርና ሲገድል መስማት እጅግ ያሳዝናል:: ውጭ ተቀምጠው ልጆቻቸውን በሰላም የሚያሳድጉና የሚያስተምሩ በኦሮሞ ሕዝብ ስም የሚነግዱ ልክስክሶች እንዳሉ : በትክክለኛ የአማራ ትግል ስም የግል ጥቅምን ለማስጠበቅና ሀብት ለመስረቅ ውርውር የሚሉ ተልካሻዎች አይጠፉም:: የዶ/ር አብይ መንግስት ሃቁን ጥርት አድርጎ ያውቃል:: ችግራችሁና ቅሬታችሁ ምንድነው? ቢልስ:: ምንድነው ብሶታችሁ ብሎ ቁጭ ብሎ ከመወያየት የስልጣኑ ተቀናቃኚዎች አድርጎ ስላየ የአማራን ጥያቄ በሰላም ከመፍታት ይልቅ ሕገ መንግስቱን ጥሶ የአገሪቱን የደህንነት : የፖሊስ ኃይሎችና የአገሪቱን መክላከያ የሀገሪቱን ሕዝብ ማፈኛ ማድረጉ ድብቅ የፖለቲካ ዓላማውን በግድያ ለማሳካት እየሄደ ነው ተብሎ ቢታሰብ ስህተት ላይሆን ይችላል::

 

ግን በአፍ የሚናገረው የውይይት አውድ መፍጠርና በእርግጥ የሚፈፅማችው የውይይት ተቃራኒ ድርጊቶች አለመጣማችውን ስገነዘብ ስለ አብይ እህመድ የምጨብጠው ሃቅ ይጠፋኛል:: ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ “በሃሳብ ብልጫ የፖለቲካ ዓላማን የማሳካት አውድ በተፈጠረበት በመገዳደል የፖለቲካን ዓላማ ማሳካት አይቻልም::” ያለውን ስመለከት እጅግ በጣም ጥሩ ግንዛቤ እንደሆነ አየሁት:: ሆኖም ጥያቄው ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የተናገረውን እንደ ሀገር መሪ እንዴት ያሳካዋል? ነው:: የጠቅላይ ሚኒስቴሩ መንግስት ተቃዋሚዎቹን ማሰርና መግደልን የፖለቲካ ዓላማው ማሳኪያ ካደረገ: ከላይኛው የጠቅላይ ሚኒስቴሩ አነጋገር ጋር አይጋጭም? እንዳለው የፖለቲካን ዓላማ የማሳካት አውድ ተከፍቷል የሚለውን በመገንዘብ : ይህ አውድ ምን ዓይነት ነው? የሃሳብ ብልጫ የሚታይበትና የሚከሰትበት የውይይት አውድ ነው ወይ? ይህንን ለማስፈፀም መንግስት በጠመንጃውና በደህንነት አውታሩ ላይ በመተማመን ወይስ እንደሰለጠነው ዓለም : ተሳታፊዎች እስርና ግድያ ሳይፈሩ የሚሰማቸውንና ለሀገሪቱ ሰላም ይጠቅማሉ የሚሉትን ሃሳቦች በነፃ የሚያቀርቡበት የውይይት አውድ ነው? መንግስት ይህንን ግልፅ አድርጎ ለሕዝብ ማቅረብና ለተካፋዮች ደህንነት ዋስትና ማረጋገጥ ቅድመ ዝግጅት መሆን አለበት:: መናገር ቀላል ነው:: ችግሩ የተናገርነውን ማስፈፀሙ ላይ ነው:: ይህ የተደጋገመ ስለሆነ መንግስት የሚናገረውን ስራ ላይ ያውላል ብሎ መገመት አስቸጋሪ ሆኗል:: ዶ/ር አቢይ አህመድ የተናገራቸውን መልካም ንግግሮች ወደ ድርጊት ቢተረጉማቸው ኖሮ ዛሬ ኢትዮጵያ በሰላም በሽበሽ ያለች ሆና የሚተገብራቸውን የልማት ስራዎች በሚገባ ባደነቅናቸው ነበር:: ሰላምና የሕዝብ ደህንነት እየደበዘዘ ልማትን ማጉላት ዘለቄታ የለውም:: ሰላም በጠፋበትና የሕዝብ ደህንነት በጎደለበት ጊዜ ዛሬ የለማው ነገ ድጥማጡ ይጠፋል:: ዛሬ ጎረቤት ሱዳን ያለችበት የውድመት አውድ ሊያስተምረን ይገባል:: ይህ መንግስትን ሊያሳስበው ይገባል::

መፍትሔው በመጀመሪያ ያለው መንግስት የጠባብ ጎሳነቱን ቀለምና ማንነቱን እርግፍ አድርጎ የኢትዮጵያነትን ቀለምና ማንነት ያለምንም ቢሆንና ወይንም ሙሉ በሙሉ ሲለብስ ብቻ መፈራራትና መገዳደል ይቆማል:: ግን ጠቅላይ ሚኒስቴራችን እኔ ከተቀናቃኚዌቼ የበለጠ መሳሪያ ስላለኝ ኑና ሞክሩኝ የሚል ግብዝና ትእቢተኛ መሪ ሆኖ እየታየ ነው:: እኛ ለዲሞክራሲ ክብር ቆመን ይህ መሪ አካሄዱ እንደ ሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን አገሪቱን በርሃብ የደቀቁ : ቆመው ይሂዱ እንጂ በቁም የሞቱ በደመነፍስ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች (ZOMBIES) አገር የማድረግ ሁኔታ እንዳያመጣ ወይንም እንደሶሪያ መሪ ባሽር አል-አሳድ የሕዝብን ችግርና የአገር መፈራረስ የማይገባውና ለሰው ልጆች ደንታ የሌለው በሕዝብ ገንዘብ የተገንባውን መከላከያ እንደግል ጠባቂ በመጠቀም በመሳሪያ ኃይል ስልጣን ላይ ቆይቶ እንደተመኘው እንዳይነግስ ስህተቱን በመጠቆም እንዲታረም ማድረግ ግድ ይለናል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኳ!ኳ!ኳ!ኳ ! አጭር  ልቦለድ  ቅምሻ ለአዲሱ ዓመት

በተለይ ከ20 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ይህ የመልካም መሪነት ተስፋ ተጥሎበት የነበረ መሪ የ49 ቢሊዮን ብር ቤተመንግስት መገንባት ፕሮጀክት የሚያሳየው ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ትኩረቱ ብልጭልጩ ላይ እንጂ ለሰው ልጆች ስብዕና : ሃዘኔታ : የሰዎች ችግርና መከራ የሚሰማው እንዳልሆነ ነው:: ከዚህ በፊት እናቱ ያለሙለትን ወይም ያስጠኖቀሉለትን የንግስና ምኞት ሳቀነቅን: ከቤተመንግስቱ ግንባታ ጀርባ የንጉሥ አቢይ አህመድ ሰርወ መንግስት (DYNASTY) የመመስረት ዓላማ ያለውም ይመስላል:: የአፊሪቃ መሪዎች ጥሩዎችና ብልሆች ተብለው ሲታሰቡ እንዴት መጥፎዎችና ከንቱዎች ሆነው እንደሚገኙ ብዙ ምሳሌዎች አሉ:: ግን ከጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ የቤተመንግስት ግንባታ ጋር ይቀራረባል የምለው በአውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1966 እስከ 1979 ሴንትራል አፊሪቃን ሪፐብሊከ የመራው ጃን በዴል ቦካሳ (Jean-Bédel Bokassa) ነው:: ይህ ሰው የሴንትራል አፍሪካ ሪፕብሊከ አገር ሕዝብ በርሃብ እያለቀ ቦካሳ የናጠጠ ቤተመንግስት ገንብቶ በአልማዝ ያበረሸቀ ዘውድ አስርቶ ራሱን ቦካሳ አንድ ብሎ ነገሰ:: ዶ/ር አብይ አህመድም የጠቅላይ ሚኒስቴርነቱንና የዶክተሬትነቱን ማዕረጎች እርግፍ በማድረግ ቀዳማዊ አብይ አህመድ ሰባተኛው ንጉሠ ኢትዮጵያ በሚል ስያሜ ራሱን ንጉሥ ያደርግ ይሆን?

የሚገርመውና የሚደንቀው ይህ የዛሬው ጠቅላይ ሚኒስቴር በ1 ቢሊየን ዶላርስ ቤተመንግስት እያስገነባ ከዓለም እቀፍ የገንዘብ መዋጮ (IMF) 2 ቢሊዮን ዶላርስ ብድር መጠየቁ ነው:: ይህንን ትክክል ነው የሚል ሰው ካለ አእምሮውን ማስመርመር ይኖርበታል:: የመንግስት መሰረታዊ ተግባር ለሕዝቡ አመራር መስጠት : ስርዓትን ማስጠበቅ : ለሕዝብ አገልግሎት መስጠት : ለሕዝብ ብሔራዊ ደህንነት መስጠት : ለሕዝብ የኢኮኖሚ ደህንነትን የኢኮኖሚ ድጋፍ መስጠት ናቸው። ቤተመንግስት ግንባታ ወይስ 20 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከርሀብ ማዳንና በእስርሽዎች ከአዲስ አበባና ከአካባቢው መንግስት ቤታቸውን በማፍረስ መንገድ ላይ የጣላችውን አማራ : ትግሬ : ጉራጌ : ወላይታ : ሱማሌ ኢትዮጵያውያንና የተቀሩትን ኦሮምኛ የማይናገሩ የኢትዮጵያ ዜጎችን መኖሪያ መገንባት ይሻላል? ይህ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን የእግር ትኩሳት ከሆነባቸው የጎሳና የዘር ፖለቲካ በሽታ ያወጣቸዋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት እንዴት እንደዚህ ለሰዎች ደንታ የማይሰጠው ፋሽስታዊ መሪ መስሎ ሊታይ ቻለ?

ትላንትና የጠባብ ኦሮሞ ጎሰኝነትን ጆከር ካርታ በኢትዮጵያዊነት አረንጏዴ ብጫ ቀይ ባንዲራ ውስጥ ደብቆ ለጊዜው የፖለቲካ ቁማሩን በላን:: ድሮስ ከቁማርተኛ ምን እውነት ተገኝቶ!! የኢትዮጵያ ሕዝብ በአገር ውስጥም በዲያስፖራ አንዴ ተሞኝተናል:: ይህ መሪ ግን ይገላል እንጂ ድጋሚ እንደማያሞኘን ግልፅ ነው:: የሰላም ትርጉም ሳይገባው ወይም ለሰላም የቆመ መስሎ ቁማሩን ተጫውቶ : ዓለምን አሞኝቶ የሰላም ኖቤል ሽልማት ተሸልሞ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ሰላም እያሳጣን ይገኛል:: ስግብግቡ ጁንታ ብሎ የጠራውን እንጀራ አባቱን ወያኔን ሲዋጋ ለኢትዮጵያ ህልውናና ለአገር አንድነት ደግፎት የተዋጋውን የአማራን ሕዝብ ዛሬ እንደአገር አፍራሽ ሲቆጥርና ትጥቅ ለማስፈታት አካኪ ዘራፍ በማለት አገሪቱን ሰላም ሲያሳጣ እያየን ነን:: በጣም የሚገርመው ዛሬ በአብይ መንግስት ውስጥ ተሰግስገው የሚገኙት የኦሮሞ ዘረኞች ክርስትና አባት የሆነውን ኦኔግን አብይ አህመድ ወደ አገር ቤት ሲያስገባ አንዳችም መሳሪያ አላስፈታም ነበር:: የዚያ ጭፍን ወገነኝነት ፖለቲካ ውጤት ላለፉ አምስት ዓመታት በኦሮሞ ክልል ውስጥ በአማራውና በሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመው ጭፍጨፋ ይገልፀዋል:: በሰሜኑ ጦርነት ላይ ተካፍሎ በሰውም ሆነ በንብረት ውድመት ለአንድነትና ለኢትዮጵያዊነት የከፈለውን የአፋር ሕዝብ ዛሬ ዞር ብሎ ችግሩን ማየት የተሳነው ኦሮሞን ከፍ በማድረግ ዘረኛ የኢትዮጵያ ሂትለር ለመሆን እየገሰገሰ ይመስላል:: በጣም ፈርሃ እግዝአብሔር ተስኖት የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት የጀርባ አጥንት የሆነውን የተዋህዶ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለማፍረስ የማይቆፍረው ጉርጏድ የለም:: የሚያሳዝነው በእግዚአብሔር አምናለሁ የሚል ሰው የእግዚአብሔርን ቤት (ቤተክርስትያንም ሆነ መስጊድን) ለማቆሸሽ : ለመበጥበጥና ለማፍረስ ይመኛል ወይም ይሄዳል ብዬም አላስብም ነበር:: የሚመስለው ይህ ሰውና አጋሮቹም ሆኑ ደጋፊዎቹ ሃይማኖትም ሆነ ፈርሐ እግዚአብሔር ያላችው አይመስሉኝም:: ፈጣሪያቸው የስራችውን ይስጣቸው ከማለት እኔ በሃይማኖት በኩል እልዳኛችውም::

መሪ ማለት በጥሩ ስራዎቹ እንደሚመሰገን አገሪቱ በችግር ስትወጣጠርና ሕዝብ ተስፋ ሲቆርጥ አለሁላችሁ በማለት ወደተስፋ ጎዳና የሚመራና የሕዝብ እንባ አባሽ መሆን የሚገባው ነው ብዬ አስባለሁ:: ጥሩ መሪ ብልህ : ታጋሽ : እኩልነትን የሚያራምድ: ወገነኝነት የማይሰማው: ከዘረኝነትና ከጎሰኝነት የራቀ : ሙስናንና አድሎን የማይወድ : የሕዝብ መከራና ችግር የሚያንገበግበው : ልበእሩሩ : የሌላው ጉዳትና ጥቃትን የራሱ አድርጎ የሚያይና ስብዕና የተሞላበት መሆን ይገባዋል:: ዶ/ር አብይ አህመድ እነዚህ የመልካም ሰው ባህሪዎች የተሳኑት ይመስላሉ:: ምክንያቱም ከ2018 እስከ አሁን በተለይ ከ2022 (የሰሜን ጦርነት ካለቀ) ጀምሮ ያሳየን የባህሪዎች ለውጥ ከዚህ በፊት በዓለም ውስጥ ያለፉት አምባገንነንና አረመኔ መሪዎች ወደስልጣን ሲመጡ ሕዝባዊና የሕዝብ መከራና ችግር አሳስቧቸው ለሕዝብ መፍትሔ አምጪዎች መስለው ያሳዩትን ባህሪዎች ነው:: ይህም የመንግስትን አውታር ከጨበጡ በሗላ ሕዝብን ካስለቀሱና ካሰቃዩ አማባገነን መሪዎች ባህሪዎች ጋር ይመሳሰላል:: ተቀናቃኚዎቹን ጋዜጠኞችን መግደል : ማሰር : ማሰቃየትና ስብዓዊ መብቶችን መርገጥ ለአቢይ አህመድ ስልጣን ማጠናከሪያና መቆያ መሳሪያ እየሆኑ ይገኛሉ:: በተጨማራም መንግስት ፍርደገምድልና ገዳይ ሲሆን የያዘው የፖለቲካ ዓላማ በማንኛውም አስፈላጊ መንገድ (BY ANY MEANS NECESSARY) መንፈስ ተጠያቂነት በሌለው ሁኔታ ስልጣን ላይ መቆየትና የሀገር ሀብት በመዝረፍ ጥቂቶችን ቱጃር ማድረጊያ ዘይቤ ነው ሊባል ይቻላል:: ምክንያቱም በስልጣን ለመሰንበት እጋሮቹን ሌቦች : ቀማኞችና በሙስና የበሰበሱ ታዛዥዎችና ሎሌዎች ማድረግ የአምባገነን መሪ አንዱ መንገድ ነው::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከመንግሥት ውጭ ያሉ ተዋናዮች (Non state Actors) ሚና  ከወቅቱ የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁ

ሕዝብ በጎሳ ፅንፈኝነትና ጠባብነት እየተገዳደለ ጧት ማታ ስለእርሻና ስለተሰሩ ፓርኮች በሕዝብ ሚዲያ ላይ ማሰማት አገሪቱ በአምባገነኖች እንደሚመሩ አገሮች ትመስላለች::የሕዝብ ሀብት የሆኑት የአገሪቱ ሚዲያዎች ጎሰኝነትና ዘረኝነት በሀገር ላይ ያመጡትን ትልቅ ጥፋትና ጉዳት በስነስርዓት በተለያዩ የአገሪቱ ቋንቋዎች ማስተማር ይገባቸዋል:: ሚዲያዎች ይህንን እንዲያደርጉ መንግስት መመሪያ መስጠት ይኖርበታል:: የሩዋንዳን ምሳሌ መከተል ይቻላል:: የሕዝብ ንቃት የመልካም መንግስታዊ አስተዳደር መገለጫው አንዱ መመዘኛው ነው:: ስለዚህ የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውያንን ማንነት ማዳበርና ማሳደግ የፖለቲካ ዓላማ አድርጎ ለማሳካት ከመገዳደል የሚያድነው ምንድነው ብንል : መንግስት የሕዝቡን ሰብዓዊ መብቶች አክብሮ ሲያስከብር : መንግስት ከጎሰኝነት ወጥመድ ራሱን አስለቅቆ ሀገራዊነትን ሲያራምድ : ተበድያለሁ የሚለውን የሕዝብ አካል ከመወንጀል ይልቅ በደሉን ሲያዳምጥና የሕዝብን ችግር በቀና መንገድ መፍትሔ ለማምጣት የሚያስችል አውድ ሲፈጥር ነው::

ዶ/ር አብይ አህመድ የመልካም አስተዳደር ጉድለት በግለሰቦችና በቤተሰቦች ላይ የሚያመጣውን ቀውስ ሚስቱና ልጆቹ በአሜሪካ ጥገኝነት ያሳለፉት ሊያስተምረው ይገባ ነበር:: ሚስቱና ታዳጊ ልጆቹ በአሜሪካ ከምኖርበት ዋዮሚንግ ጎረቤት በሆነው ኮሎራዶ ስቴት በስደት በሕይወት የቆዩለት መሪ : በእሱ መንግስት የቤት ማፍረስ ምክንያት ከነልጆቿ ጎዳና የወደቀችውን እናትና የእሱ መንግስት በጨለማ ቤቷን ሲያፈርስ ልጆቿ በጅብ የተበሉባት እናትን ጉዳይ ሲሰማ እነዚያ እናቶች ቀዳማዊት ዝናሽና ልጆቹ የሱ ልጆች ቢሆኑ ምን ይሰማው ነበር የሚለውን ጥያቄ ሳሰላስል : ከያዘው እመራር አንፃር ይህንን ጥያቄ ያስባል : ለሰዎች ሃዘኔታ ይሰማዋል የሚል ግምት የለኝም:: ምክንያቱም ሰዎችን መረዳት የምንችለው በራሳችን ውስጥ ከተሰማን ብቻ ነው። ይህንን ለማድረግ ርሕራሔ ሊኖረን ይገባል:: ርሕራሔ ማለት በሌላ ሰው ዓይን ማየት : በሌላው ሰው ጆሮ ማዳመጥና በሌላ ሰው ልብ መሰማት ነው። ትልቁ የስዎችና በተለይ የመልካም አስተዳደር በዓለምም ሆነ በአገራችን ኢትዮጵያ ችግር የሆነው ርህራሄ ከሰዎች መጥፋት ነው:: መሪዎች ርህራሄ ከሌላቸው የሕዝብ ስቃይና ሰቆቃ ይበዛል:: ይህንን ነው ከመንግስት ወደ መንግስት የምናየው:: የመጣው ለውጥ አዲስ ጨካኝ ጨቋኝና ጎሰኛ መሪ : ሌባና ስግብግብ የመንግስት ቅጥሮችና አሽከሮች እንጂ ርህራሄና ስብዕና የተከናነቡ መሪና የመንግስት ባለስልጣናት አላመጣም::

እያንዳንዳችን ራሳችንን በሌላው ቦታ እያስቀመጥን ይህ ችግር የእኔስ ቢሆን እንዴት አየዋለሁ ብለን ስናስብ መግባባትን እንፈጥራለን:: የሌላው ስቃይ የኔ ስቃይ ቢሆን : የሌላው ለቅሶ የእኔ ለቅሶ : የሌላው እስር የእኔ እስር : የሌላው ግድያ የእኔ ግድያ ብለን እኛ የሌላውን ጫማ እየለበስን ብናሰላስል መረዳዳት ልንፈጥር እንችላለን:: ስንሳሳትም ስህተታችን ለመሸፈን ሌላ ስህተት ውስጥ እንዳንገባ ለራሳችን ሃቀኞች መሆን ከብዙ ችግር ያድነናል:: አንድነትና አብሮ መኖርን መንግስትም ሆነ ሕዝብ የፖለቲካ ዓላማ ካደረጉት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሰላም ዋንጫን በአጭር ጊዜ ይጨብጣሉ የሚል ተስፋ አለኝ:: ዶ/ር አብይ አህመድም ይህንን ተስፋ ይዞ ለመጏዝ ከፈለገ : ከመበታተን አንድነት : ከብቸኝነት አብሮነት : ከጠባብነት ሰፊነት: ከጎሳነት አገራዊነት : ከሁሉም በላይ ሰውነት እንደሚበልጥ ተገንዝቦ የያዘውን የዘረኝነትና የጎሰኝነትን ፖለቲካ ማስወገድ ግድ ይለዋል::

 

ለማጠቃለል ዶ/ር አብይ ሀገሪቱን ለማሳደግና ለማልማት የሚያደርገውን ሥራዎችና ጥረቶች ፍፁም ውድቅ አላደርግም:: የእኔ ቅሬታ የአገሪቱ ህልውና : የሕዝቦቿ አንድነትና : የአብሮ መኖር መንፈስና ሁኔታ ከማንኛውም ልማት ስለሚበልጥ ቅድሚያ አልተሰጠውም ነው:: ከትግራይ : ከአማራ : ከአፋር : ከሱማሌ : ከጋምቤላ ከደቡብ ወዘተ ክልሎች ሕዝቦች ጋር የተናቆር የኦሮሞ ክልል በልፅጎና ለምቶ ሌሎቹን እረግጣለሁ ብሎ ካሰበ መሪዎቹ ዕውነትም ደንቆሮዎች ናቸው:: ጎረቤትን ሰላም ነስቶ በሰላም እኖራለሁ የሚል የአእምሮ በሽተኛ እንጂ ጤነኛ ነው ተብሎ እይታይም:: አዎን የመሳሪያ ኃይልና ብዙ ወታደር ሊኖር ይችላል:: ግን መሳሪያና ብዙ ወታደር የነበራቸው መሪዎች ነበሩ:: ሆኖም ሕዝብን ገደሉ እንጂ አላሸነፉም:: ዶ/ር አብይ አህመድ የታሪክ መፅሐፎች አንባቢ ነኝ ሲል እንሰማለን:: ከሕዝብ ጋር ተጣልቶ ለዘመናት የመራ መሪ እንደሌለ አንብቦ መገንዘብ ይችላል:: የሚያዋጣው ሕዝብን አነጋግሮ አንድነትን በመፍጠርና በማጎልመስ በሕዝብ ፈቃድ ስልጣን ላይ መቆየት ነው:: እንዲያውም በቋንቋ የተከለሉትን ክልሎች በትኖና የተለያዩ ጎሳዎችን ያቀፉ ክልሎች በመመስረት እየመነመነ የመጣውን ኢትዮጵያዊነት አበልፅጎ ማጠናከርና : ሕዝብን በጎሳ መሰለፍ : ራስን ማሳነስና ሗላቀርነት ነው ብሎ ማስተማር የመንግስት ተቀዳሚ ግዴታው ማድረግ ይገባዋል:: በዚህ ረገድ የሕዝብ መቀራረብንና አንድነትን መንግስት የፖለቲካ ዓላማ እያደረገ ልማቱን ሲያስቀጥል እንደግፈዋለን:: ከጎኑ እንሆናለን::

 

 

 

3 Comments

  1. Stop any futile attempts to save a genocider, top-criminal by suggesting various guises under which he should hide. He has to go. He has to face justice. The blood and tears of innocent mothers whose entire family he massacred cries to the heavens.
    Mane-tekel-fares!

  2. አንዳንድ ሰዎች እንዴት እንደሚያስቡ በጣም ይገርመኛል። በብዙ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ያስገደለ፣ እንደ ኦነግ ሸኔ የመሳሰሉ አረመኔዎችን አስታጥቆ አማራውን እንዲጨፈጨፍ ካደረገ፣ ወያኔ እስከ ወሎና አፋር ድረስ ዘልቆ በመግባት በሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻቻን ሲገደሉ ዝም ብሎ ያየን፣ ከወያኔና ከኦነግ ሸኔ አረመኔያዊ ኃይሎች ጋር በሰላም ስም የሚደራደር፣ አሁን ደግሞ በአማራው ልዩ ኃይልና በፋኖዎች ላይ በመዝመት ወገኖቻችንን የሚጨፈጭፈውን አረመኔውን አቢይ አህመድን ልብህን ግዛና ኢትዮጵያዊነትን ማዕከል ያደረገ ፖለቲካ ተከተል ብሎ መማፀን ጤናማ ጭንቅላት ካለው ሰው የሚመነጭ ሃሳብ አይደለም። ውድ እህታችን ከየትኛው ፕላኔት ሆነሽ እንደዚህ ዐይነቱን ተጨባጭ ሁኔታዎችን የማያንፀባርቅ ሀተታ እንደምትጽፊ አላውቅም። አቢይ አህመድና ግብረ አበሮቹ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና የአረቦች ቅጥረኛ በመሆን በህዝባችን ላይ በግልጽ የሚታይ ጦርነት ብቻ የከፈቱብን ሳይሆን የባህልም ጦርነት ነው የሚያካሂዱት። የመጨረሻ ዓላማቸውም ኢትዮጵያ እንደ አገር እንዳትኖር ማድረግ ነው፣ መበታተን ነው። የሚሰሩት ስራ ሁሉ የውጭ ኃይሎች የሚፈልጉትን ነው። ይህ የማይታይሽ ከሆነ አርፈሽ ተቀመጭ። አንድ ሰው ሲጽፍ ከተጨባጭ ሁኔታዎች በመነሳት እንጂ የራሱን ቅዠት አይደለም መጻፍ ያለበት። ሰለሆነም የማይገባሽ ከሆነ አርፈሽ ተቀመጭ። ውዥንብር አትንዢ።

    ፈቃዱ በቀለ

  3. እትዬ አልማዝ የማይድን በሽታ ማከም ራስን ማድከም ነው። ዛሬ በወያኔ እግር ተተክተው ሃገሪቱን የሚያምሷት ያው ልክ እንደ ወያኔ በዘራቸው የሰከሩ፤ ለሰሚ ቢከብድም ከወያኔ የከፉ የኦሮሞ ፓለቲከኞች ናቸው። ሃገሪቱ አሁን ባለው እይታ በአፓርታይድ ፓለቲካ የተጠረነፈች፤ ሰው ሁሉ በግድ ኦሮምኛን ካልተናገርክ ሥራ አታገኝም የሚባልበት የእብዶች ምድር ሆናለች። የዛሬ መቶ ዓመት ሚኒሊክ ፈረሴን ቀማኝ የሚሉ የሙት ፓለቲከኞች ባሉበት ምድር ራስን ከጊዜና ከህብረብሄራዊ እይታ ጋር አስታርቆ ሰውን በሰውነቱ ፈርጆ መኖር ከቀረ ቆይቷል። በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚፈርሱት ቤቶች፤ የኦነግ ሰራዊት ነኝ የሚለው ግፈኛ ቡድን የሚያፍናቸው ሰዎች፤ የዘረፋቸው ባንኮች፤ የገደላቸው የአማራ ተወላጆችና በዚህ ግፈኛ ቡድን ሃበሳ እየቆጠሩ ያሉት ወገኖቻችን እንባና ሰቆቃ እያለ ዛሬ አማራን ትጥቅ አስፈታለሁ በማለት የዘመተው የኦነግ መንግስት በማይድን የዘር ፓለቲካ የተለከፈ ከፍ ሲያረጉት ዝቅ የሚል ቃሉና ሥራው ለየቅል የሆነ እንደሆነ የእለት እለት ስራቸው ይመሰክራል።
    የሚገርመው ዛሬም ወያኔ ጠላቴ አማራ ነው በማለት ሲደነፋ እንሰማለን። ኦሮሞው የሚገድለውና የሚያፈናቅለው አማራን እየለዬ ነው። ለምን ይህ ሆነ ለሚለው መልሱ አንድ ነው። ደም አፍሳሽና ዘረኞች በስልጣን ለመቆየት በጠላትነት የሚፈርጅት ወገን መኖር አለበት። ለዚህ ተግባር ከሻቢያ እስከ ኦሮሞ ፓለቲካ የሃበሻ ህዝብ ጠላት አማራ ነው ተብለው ነው ፓለቲካውን የተጋቱት። ይህ የፈጠራ ትርክት ምዕራባዊያኖችንም በጉቦና በሌላው ነገር ሁሉ አሳምኖ የአሜሪካው መንግስት ወያኔን ወደ ስልጣን ለመመለስ ያልተጓዘበት መንገድ አልነበረም። ከላይ ሃሳብ ሰጪው እንዳለው 3 ጊዜ አማራና አፋር እንዲወረርና በወያኔ እንዲደበደብ የተደረገው የአማራን ህዝብ ለማጥፋትና ለማዳከም ከታለመው የኦሮሞ ሃሳብና የወያኔ ክፋት በአሜሪካኖች እየተመራ ነበር። ያ አልፎ አሁን ሌላ ዘፈን ሆኖ ይኸው እንሆ አስመራ ከራሺያና ከቻይና ጋር ስትጎዳኝ የእኛው ሃገር ደግሞ ጊዜውን በዘር ፓለቲካ መገዳደል በማሳለፍ ላይ ይገኛል። ቆይቶ ግን አስመራም ሆነ ሞቃዲሾ፤ ጅቡቲም ሆነ ኢትዮጵያ የሃያላን መንግስታት ሽኩቻ በሚያስከትለው ሴራ ዳግመኛ መገዳደላቸው አይቀሬ ነው። ሲጀመር ቻይና የአፍሪቃ ሃገሮችን ሊወጡ በማይችሉበት ዕዳ ውስጥ በመዘፈቅ የእድሜ ልክ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የጥቁር ህዝቦች መከራ አብዛኛው ከራስ የሚመነጭ ቢሆንም አረቡ፤ ነጩና ቻይናውም የራሱን ድርሻ በዚህም በዚያም እሳት በማቀጣጠልና ተቀጣጣይ ነገር በማቀበል እንድንተላለቅ ያደርጉናል። ጥቁሩ ዓለም እንዲያድግ፤ በራሱ ቆሞ ከብድርና ከልመና እንዲላቀቅ ጭራሽ አይፈልጉም።
    የኦሮሞ ስመ ምሁራንና ጠ.ሚ በጊዜ ወደ ልባቸው ተመልሰው ነገሮችን መስመር ካልያሲያዙ ዛሬ በሱዳን የምናየው አይነት እልቂት በምድሪቱ ጫፍና ጫፍ ላይ እንደሚነድ ለማሰብ አይከብድም። የኦሮሚያ ክልል፤ የአፋር ክልል፤ የአማራ ክልል እያሉ አጥር ከማበጀት ሰው በፈለገው የምድሪቱ ክፍል ሰርቶ የሚኖርበት ሃገር ለማየት ተስፋ አድርገን ነበር። ያ ግን አልሆነም። የተከመረ የእህል ክምርን የሚያቃጥሉ ጉዶች ባሉበት ሃገር ረሃብ ቢገባ የሚያስገርም አይሆንም። የሳር ጎጆ አቃጥሎ ፎቶ ከሚነሳ ወልጋዳ ስመ ነጻነት ታጋይና ዘራፊ ሞት እንጂ ህይወት አይገኝም። ጊዜው የመሸባት ኢትዮጵያ ስሟ ብቻ በመነሳቱ የሚያንገሸግሻቸው የዘርና የቋንቋ ሰካራሞች ምንም አይነት የትምህርት ደረጃ ላይ ቢሆኑ የሚያስቡት ሁሉ ፉርሽና አፍራሽ ነገር ብቻ ነው። ዶ/ር እከሌ እንዲህ ብሎ ኢንጂኒየሯ እንዲ ብላ ማለቱ ዝም ብሎ ሃሳብን ለማጠናከሪያ የሚጠቀሙበት የስም ልጣፊ እንጂ ከአንድ የሃገራችን ያልተማረ ገበሬ በታች የሚያስቡ እብድ ፓለቲከኞች ናቸው። ስለሆነም በማር የተለወሱ የጠ/ሚ ንግግሮች ሁሉ በመሬት ላይ ከምናያቸው የኦሮሞ ግፈኞች ግድያ፤ አፈና፤ ዝርፊያ ጋር አብረው የማሄድ ከእውነት የራቁ የቃላት ጋጋታዎች ናቸው። ዛሬ ማን ነው በእስር ቤት ያለው? ማን ነው ከምድሪቱ የሚፈናቀለው? ማን ነው ትጥቅ ፍታ ተብሎ የሚሰቃየው። ይህ ሁሉ ሆን ተብሎ የአማራን ህዝብ ለማዳከምና ለጠላት አሳልፎ ለመስጠት የሚሰራ ሴራ ነው። ለመረጃ በቅርቡ በአቶ ጌታቸው ረዳ ሰብሳቢነት በመቀሌ የተደረገውን ህዝባዊ ስብሰባና የተነሱ ሃሳቦች፤ እንዲሁም ትላንት ከተለያዪ ሃገራት የተገኙ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ያደረገውን ውይይት፤ በቅርቡ ጄ/ባጫ ደበሌ የተናገረውን ሁሉ ጨምቀን ስንመለከት አሁን በአማራ ህዝብ ላይ የሚደረገው ሴራ የሁሉም እጅ ያለበት ከፕሪቶሪያው ስምምነት ጋር ለህዝብ ግልጽ ያልሆነ አንድ ሚስጢር እንዳለ ያሳያል። አንድ አረንጓዴ ኮፍያ ያደረገ የስምምነቱ ታዛቢ ሲናገር እንዲህ አለ “ወደ ምዕራብ ትግራይ እንሄዳለን፤ ሁመራን እናያለን” ሁመራ ምዕራብ ትግራይ ሆና አታውቅም። ይህ ግን ሆን ተብሎ በወያኔ ሴራ ውስጥ ገብቶ የተናገረው እንጂ በመረጃ ተመርኩዞ አይደለም። ጌታቸው ኤርትራን እየኮነነ ሃሳብ ሰጭዎቹ ደግሞ ወራሪ አማራ እያሉ በመለፋለፍ ነገሩ ተደመደመ። በአማራ ህዝብ ላይ የተሸረበው ሴራ በግልጽና በህቡዕ ለመሆኑ ከቃላቸው መረዳት ይቻላል። ስለሆነም የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ጠ/ሚሩ ከኦሮሞ እሳቤ ወጥቶ እይታው ሁለ አቀፍ እንዲሆን ማሰቡ የፈሰሰ ውሃ መልሶ እንደማፈስ ይቆጠራል። ችግራችን የዘር ፓለቲካ ነው። ለራስ ሲቆርስ የማያሳንስ የቋንቋና የክልል ፓለቲካ። መንቃት መደራጀት ግፈኞችን መፋለም አማራጭ የማይገኝለት ዘዴ ነው። ሁሌ እየየ ይሰለቻል። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share