May 15, 2023
5 mins read

ተመጣጣኝ እርምጃ እና አርበኝነት የሚለካዉ በምን እናበማን ነዉ ?

Abiy Ahmed Shine OLF 1

Abiy 122ዛሬ ላይ ዕዉነት የሚናገር እና ለዕዉነት የሚኖር  በምድረ አበሻ  በጥቂት  እንኳ  ለመኖራቸዉ ብቻ ሳይሆን ጥቂቶችን የሚጎዳ  ነዉ ፡፡

ድሮ ድሮ  “ዕዉነት ካልተናገርክ  ዝም በል  “ያሉት  ማን ነበሩ  የህንዱ የነፃነት አባት  ታላቁ ማህተመ ጋንዲ ናቸዉ  አይደለም  እንዴ  ?

ዕኮ  ለምንድን  ይሆን ዝም ማለት ስንችል ዕዉነት  መናገር ሳንፈልግ  ዉሸት ለመናገር መትጋትን ምን  ይሉታል ፡፡

ይህን  የክህደት እና ዉሸት  ሸፍጥ የሞላበት መንፈራገጥ  ለማለት  ከላይ በርዕሱ  ተመጣጣኝ እና አርበኝነት ምን እንደሆነ የሚነገሩት የሚለወጡት ወይም የሚታደሱት መቸ እንደሆነ  የማይጠይቅ  እንዴት ስለ አርበኝነት እና ተመጣጣንኝ ዕርምጃ  ምንነት ለመናገር የሚዳዳዉ መኖሩን ስንሰማ ያማል ፡፡

ብዙ ጊዜ ላለፉት ሶስት አስርተ  ዓመታት በኢህአዴግ  የስልጣን እና ንዋይ  ምኞት በመጋረድ  አገር እና ህዝብ የመከራ እና ጨለማ ዘመን ለማሳጣር  ህዝብ ባደረገዉ  የሞት ሽረት ትግል   የነፃነት እና የመብት  ጥያቄ ማንሳት ጥፋት ሆኖ ለሞት ሲዳርግ ለምን ማለት ሲቻል ተመጣጣኝ እርምጃ ነዉ አይደለም እያሉ  በህአዝብ ቁስል እና በአገር ደህንነት የሚሳለቁ  ብዙዎች  ሆነዋል  ፡፡

ለመሆኑ ሠዉ በሠዉነቱ  ተፈጥሯዉ ማንነቱን ለማስከበር ለምን ሲል መግደል ፣ማግለል እና መበደል  በምን መለኪያ ይሆን የሰባዊ መብት ተቋማት ተመጣጣኝ እርምጃ አይመስልም እያሉ ማለት ዕኮ እንዴት ፡፡

ሠብ ማለት ሠዉ ከሆነ ሠባዊነትም ለሠዉነት ከሆነ አንድ ሠዉስ  በግፍ እና በኃይል ሲሞት ደረጃ እና መረጃ እየተጣቀሰ እና እየተነቀሰ ተመጣጣኝ መረጃ ማለት ድኃ እና ብዙኃን ሲሆን ይሙት  ሌላ ሲሆን ስም ፣ ስልጣን እና ሀብት ለይቶ ማልቀስ የሚቆመዉ መች ይሆን ?

ላለፉት ሶስት ዓመታት በቀን ከሶስት ሞቶ በላይ ሠዎች ዜጎች  በማንነታቸዉ ምክነያት በግፍ ሲገደሉ እና ሲፈናቀሉ  ስለግለሰብ እና ስለ ሌላ አገር የምናነባ እኛ ለራሳችን የማናዝን በየጊዜዉ  አገር እና ህዝብ ሲሞት  ስለጥፋቱ ተመጣጣኝነት  ጥናት ላይ ነን ፡፡

ከዚህም ሌላ ስለ አደዋ ፣ማይጨዉ ፣ ስለ ዳግም ኢጣሊያ  የነፃነት ትግል እና ተጋድሎ ሲነሳ የየዘመናት የጦር አርበኞችን መዘከር እና መመስከር  ከልብ ከሆነ የሚደገፍ ቢሆንም ትዉልዱ የሚነገረዉን የሚያስተጋባ ብቻ ሳይሆን በዘመኑ ለአገር እና ለህዝብ ዋጋ የከፈሉ የዘመን ጀግኖችንም ማወደስ እና ታሪክ ማደስ አለበት ፡፡

ለዚህም በሶማሊያ  ወረራ በሶስት ወር ዝግጂት ለእናት አገራቸዉ ደም ፤ የአካል እና ሞት ዋጋ ለከፈሉት እና በህይወት ላሉት ፣ በባድመ ጦርነት ከፍተኛ ሚና የነበራቸዉ ፣ ከሁለት ዓመት በፊት በትህነግ ወረራ አገራቸዉን እና ህዝባቸዉን ከጥፋት ፣ ፍረሰት እና ሞት ለመታደግ ለህልዉና ትግል ከፍተኛ የትግል እና የአርበኝነት ዋጋ ለከፈሉት ኢትዮጵያዉን የድል እና የነፃነት ተጋድሎ መታሰቢያ ክብረ በዓል ቢደረግ  እንዲሁም በትገህሉ ወቅት ህይወታቸዉ ላለፈዉ እና በህይወት ለሚገኙት ያአገር ባለዉለታዎች ክብር እና መታሰቢያ ሊኖራቸዉ ይገባል፡፡

የትናንቱን እየጠዉን የዛሬዉን እያዳፈን ስለ መቶ ዓመት በፊት የነፃነት ትግል እና የአርበኝነት ተጋድሎ ማቀንቀን አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ ስለሚሆን ለሁሉም ከመናገር ወደ ተግባር ማዘንበል ለአገርም ለህዝብም የሚበጂ ይሆናል ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ !

“በአንድነት እና በፅናት ዘብ መቆም የነፃነት ዋጋ ነዉ!”

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

182560
Previous Story

አቶ ግርማ የሺጥላን የሚተኩት ማን ናቸው? የመከላከያ ሰራዊት ጎጃም መግባት፡ የአቶ ጌታቸው ረዳና የዶ/ር ደብረጺዮን ፍጥጫ

Dr. Fekadu Bekele
Next Story

 በኢትዮጵያውያን ምሁራን ፎረም ላይ ስሜን በመጥቀስና ካለአግባብ በመክሰስ ለዶ/ር ኤሌኒ ገብረመድህን ጠበቃ በመሆን ለወነጀለኝ ለዶ/ር ብርሃኑ አበጋዝ የተሰጠ መልስ!

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop