የትዉልዱ ችግር ለቃሉ የሚታመን ማጣት /መጥፋት ብቻ ነዉ 

#image_title

ላለፉት ሶስት  አሰርተ ዓመታት በኢትዮጵያ ላይ እየሆነ ባለዉ መጠነ ሰፊ ግፍ እና ክህደት እያዩ እንዳላዩ የሚያልፉ የቀልድ ዕምነት እና ስብዕና የተላበሱ ሁነቶቸ መበራከት ትዉዱ ችግሩን የሚሰማለት እና የሚመሰክርለት ሠዉ ማጣት ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ለአገሩ ፣ ለዕምነቱ ፣ ለባህሉ እና ለታላለቆቹ ከፍተኛ ክብር እና ፍቅር ነበረዉ ፤ አለዉ ፡፡ ሆኖም  ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት የጥቃት ኢላማ ከሆኑበት  እና በጠላትነት የተፈረጁበት ግንቦት ሀያ ቀን አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ጀምሮ የዕምነት  እና የአካባቢ  ተቀባይነት የነበራቸዉም በተለያየ ምክነያት እንዲገለሉ እና እንዲገደሉ ሆኗል፡፡

ከዚህ በተቃራኒ ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶች የኢህአዴግ የፖለቲካ እርሾ  በአድር  እና በሆድ አድር ባይነት መጠቅለሉ ትዉልዱ በከፋፋይ ፖለቲከኞች ላይ ያጣዉን ዕምነት በአስመሳይ እና ዕዉነት በካዱ የድመት ምንኩስና በተቀበሉት የቀበሮ ባህታዉያን ላይ መሳ ለመሳ የሆነ  አመኔታዉን አንስቷል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ “ክፉን የሚነቅፍ ፤ በጎን የሚደግፍ ” ሠዉ ማጣት እንጂ ታለቆችን ቀርቶ ጠላቱን ይቅር ብሎ የሚያፍቅር ታላቅ ህዝብ እና ትዉልዱም የዚህ ታላቅ ህዝብ ልጆች ናቸዉ ፡፡ከረጂም ዘመናት የጨለማ ዘመናት ጀምሮ የዜጎች በድህነት ፣ በሞት እና በስደት እንዲሁም በኢትዮጵያዊነት እና በማንነት ምክነያት መፈናቀል ፣ መገደል እና ጂምላ ፍጂት በአገር እና በህዝቦች ላይ ምን ዕንደምታ ምን ሊሆን እንደሚችል እያዩ  እንዳላዩ ለሚያልፉ የዕምነት እና የአገር ሽማግሌዎች በዜጎች ላይ ተቀባይነት እና ዕምነት ማጣት “ጨለማን ጨለማ ላለማለት ከጨለማ ጋር መስማማታቸዉን” መሆኑ የሌሉ ወይም ከህዝቡ መሃል እየኖሩ አለመሆኑን ነዉ  ፡፡እናም እኛ ኢትዮጵያዉያን ታላለቆችን እናከብራለን ፤ እንሰማለን፣ እንቀበላለን …ነገር ግን ለአገር እና ህዝብ ስትሉ ህዝብ የመኒኖረዉን ኑሩ ፤ ህዝብ የሚለዉን ተናገሩ ፤ በህዝብ እና በአገር የደረሰዉን እና እየደረሰ ያለዉን የዘመናት ግፍ እና ግርድፍ  ለዓምላክም ፤ለአለምም ተናገሩ ፤መስክሩ ፡፡ ዕዉነት ለሚናገሩ ፤ ስለ ዕዉነት ለሚመሰክሩ ፤ለቃላቸዉ ላደሩ ዛሬም የሚሰማ የሚስማማ ተከታይ ህዝብ አለ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  [ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን] በማሸነፌ ተደስቻለሁ፣ በማሸነፌ አልተደሰትኩም !!

“ከጨለማ ስራ ጋር አትተባበሩ ይልቁንስ ገስጡት እንጂ ” አፌ .5፡11

Allen Amber

Unity is Power!

United Ethiopia!

Unity is strength,

United Ethiopian Win!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share