May 3, 2023
6 mins read

ያቶ ኤርምያስ ለገሰና የመሰሎቹ ቅጥፈት፣ እውን አማራ ዘረኛ ነው?

Ermias
#image_title

ጭራቅ አሕመድ የገደለውን ግርማ የሺጥላን አማራ ገደለው ለማስባል፣ አቶ ኤርምያስ ለገሰና መሰሎቹ ግለሰቡ የተገደለው አባቱ ወይም አያቱ ኦሮሞ ናችው እየተባለ ስለሚታማ ነው እያሉ አማራን ዘረኛ ለማስባል ከፍተኛ ዘመቻ ከፍተዋል፡፡  ስለዚህም፣ እውን አማራ ዘረኛ ነው ብሎ መጠየቅ የግድ ነው፡፡

በመሠረቱ አንድን ብሔር እንዲህ ነው እንዲያ ነው ብሎ በጥቅሉ መፈረጅ ትልቅ ስህተት ነው፡፡  ብሔርን በጅምላ መውቀስ ወይም መከሰስ ከተቻለ ግን፣ ከጦቢያ ብሔሮች ውስጥ በዘረኝነት ለመወቀስ ወይም ለመከሰስ የመጨረሻው የሚሆነው አማራ ነው፡፡

ትግሬ በመጀመርያ የሚመለከተውና የሚጠይቀው ትግሬ መሆንን ነው፡፡  ለምሳሌ ያህል አማራ ነው የሚባለው ጌታቸው ረዳ ለወያኔ ያደረገው ማናቸውም ትግሬ ነው የሚባል ሰው ለወያኔ ካደረገው የበለጠ ቢሆንም፣ ጌታቸውን በተመለከት ግን ትግሬወች በመጀመርያ የሚመለከቱት ትግሬ አለመሆኑን ነው፡፡  በወያኔ ላይ የሚደርስን ማናቸውንም ጉዳት የሚያሳብቡት ደግሞ በጌታቸው አማራ መሆን ነው፡፡  በተመሳሳይ መንገድ ኦሮሞም በመጀመርያ የሚመለከተውና የሚጠይቀው ኦሮሞ መሆንን ነው፡፡

በሌላ በኩል ግን ያማራ ሕዝብ ያንድን ሰው አማራነት መጠየቅ የሚጀምረው ፀራማራ ንግግሮችን ሲናገር ወይም ደግሞ ፀራማራ ድርጊቶችን ሲፈጽም ሲመለከተው ብቻ ነው፡፡  ግርማ የሺጥላ ለኦነጋውያን አድሮ አማራን ባይጨፈጭፍና ባያስጨፍጨፍ ኖሮ አሮሞ ይሆን ወይ የሚለውን ጥያቄ የሚጠይቅ አማራ ባለነበረ ነበር፡፡

ጭራቅ አሕመድ ስልጣን ሲይዝ ትግሬ አልደገፈውም፣ የተመለከተው ኦሮሞ መሆኑን ነውና፡፡  ኦሮሞም አልደገፈውም የተመለከተው አማራ ናት ከምትባል ሴት ጋር መጋባቱንና እናቱ አማራ ናቸው መባሉን ነውና፡፡  አማራ ግን ጭራቅ አሕመድ ኦሮሞ ነው የሚባለውን ሙሉ በሙሉ አምኖ ተቀብሎ ሙሉ በሙሉ ደግፎት ነበር፣ የተመለከተው ኦሮሞነቱን ሳይሆን ኢትዮጵያን እወዳለሁ ማለቱን ብቻ ነበርና፡፡  የአማራ ሕዝብ የጭራቅ አሕመድን ኦሮሞነት መመልከት የጀመረው የኦነግን ዓላማ የሚያራምድ አማራ ጨፍጫፊና አስጨፍጫፊ ጭራቅ መሆኑ መረዳት ሲጀምር ብቻ ነው፡፡

አቶ ኤርምያስ ለገሰንም የኦሮሞና የትግሬ ጽንፈኞች ሲያብጠለጥሉት፣ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ሲደግፉት የነበሩት አማሮች ነበሩ፣ ትኩረታችው በማንነቱ ላይ ሳይሆን በምግባሩ ላይ ነበርና፡፡  እነዚህ አማሮች ያቶ ኤርምያስ ለገሰን ኦሮሞነት መጠርጠር የጀመሩት “አማራ፣ አማራ አትበሉኝ” ማለት ከጀመረ በኋላ ነው፡፡

በነገራቸን ላይ ባሁኑ ጊዜ ኦሮሞ ነው ከሚባለው ውስጥ ከዘጠና በመቶው በላይ ኦሮሞ ያለሆነ፣ በሞጋሳና በጉዲፈቻ ማንነቱን እንዲያጣ የተደረገ ስለሆነ፣ ያቶ ኤርምያስ ለገስ አያት ዋቅጅራ ስለተባሉ ብቻ አቶ ኤርምያስ ኦሮሞ ነው ማለት አይደለም፣ ያቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አያት ቂጢሳ ስለተባሉ ብቻ አቶ አንዳርጋቸው ኦሮሞ ነው ማለት እንዳለሆነ፡፡

 

በጦቢያ ምድር ላይ ከጣና እስከ ጫሞ፣ በኦሮምኛ ቃል ያለ ተሰይሞ

ከመስፋፋት በፊት ሁሉም አስቀድሞ፣ አይደለም ኦሮሞ ወይም የኦሮሞ፡፡

በስሙ ኦሮሞ ከሆነው ሕዝብ ላይ፣ ዘጠና በመቶ ወይም ከዚያ በላይ

በደሙ ያይደለ ብሔሩን የረሳ፣ ወይ ጉዲፈቻ ነው አለያም ሞጋሳ፡፡

 

አሮሞን በዚህ እይታ ስንመለከተው ምናልባትም በጦቢያ ውስጥ ከሚገኙት ሕዳጣን ብሔረሰቦች የመጨረሻው አናሳ ነው፡፡  ኬኛነቱን ሙጥኝ ብሎ ማንንም የማላስኖርበት፣ የኔ የራሴ፣ የግሌ ክልል ይኑረኝ ካለ ደግሞ ነገሌ ቦረናም እጅግ ሲበዛበት ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop