April 27, 2023
7 mins read

ጭራቅ አሕመድ ግርማ የሺጥላን ገድሎታል – መስፍን አረጋ

343055769 185915194316487 4707971056763008681 n

ጭራቅ አሕመድ ግርማ የሺጥላን ገድሎታል፤ እንኳን ገደለው!  ጭራቅ አሕመድ ሆይ፣ ጅማሮህ ጡሩ ነውና ቀጥልበት፣ ሳትጨርስ እንዳታቆም፡፡

አማራን ለሚበላው ለጅቡ ለኦነግ ጥላ ከለላ ስለነበር፣ በሂወት ዘመኑ ግርማ የጅብጥላ ይባል የነበረውን ግርማ የሺጥላን የጅቦቹ አለቃ ጭራቅ አሕመድ ገድሎታል፡፡  የገደለበትን ዋና ዋና ምክኒያቶች ደግሞ ግድያውን ከመፈጸሙ በፊት ባዘጋጀው ወይም ደግሞ አማካሪወቹ እነ ዳንኤል ክብረት ባዘጋጁለትና ግድያውን ከፈጸመ በኋላ በብርሃን ፍጥነት ባወጣው መግለጫ በግልጽ ተናግሯል፡፡  እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡

  • አንደኛው ምክኒያትያማራን ሕዝብ እርስበርሱ ለማጫረስ ነው፡፡  ይህን ዓላማውን የገለጠው ደግሞ “ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ከኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች” በሚለው ሐረግ (phrase) ነው፡፡  ይህን ያለው ደግሞ አማሮች ተወልደው ባደጉባቸው በወለጋና በቤንሻንጉል እንዳይኖሩ ላምስት ዓምታት ያህል ማስጨፍጨፉንና ማፈናቅሉን የረሳንለት መስሎት ነው፡፡  ጭራቅ አሕመድ አማራን በኦነግና በወያኔ ማስጨፍጨፉ ስላላርካው፣ ርስበርሱ ለማጫረስ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል፣ እያደረገ ነው፣ ማድረጉንም ይቀጥላል፣ ያማራ ሕዝብ ጭራቅ አሕመድን ባስቸኳይ ጨርቅ አድርጎ እንዳይቀጥል ካላደረገው በስተቀር፡፡
  • ሁለተኛው ምክኒያትያማራን ሕዝብ በጽንፈኝነት ፈርጆ ባማራ ሕዝብ ላይ የከፈተውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማጧጧፍ ነው፡፡  ይህን ዓላማውን የገለጠው ደግሞ “ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው በስተቀር ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልህ ማሳያ ነው”  በሚለው ሐረግ (phrase) ነው፡፡  የጭራቅ አሕመድ ሸኔ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ አማሮችን አርዶ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ሲያፈናቅል፣ ጭራቅ አሕመድ አንድም ቀን “ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው” ብሎ መዛት ቀርቶ፣ ያንድ ደቂቃ ሐዘን በፓርላማ እንዳይደረግ ከልከሎ ምንም እንዳልተፈጠረ ድምጹን አጥፈቶ ነበር፡፡  አማራን በጽንፈኝነት ለመክሰስ ሲፈልግ ግን፣ እንደ ጅራፍ እራሱ ገርፎ በዚያኑ ቅጽበት እራሱ ጮኸ፡፡
  • ሶስተኛው ምክኒያት ደግሞ ባማራሕዝብ ላይ ለከፈተው መጠነ ሰፊ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በተዛዋሪ መንገድ ገንዘባዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ዲፐሎማሲያዊና ፕሮፓጋንዳዊ ደጋፍ የሚያደርጉለት ምዕራባውያን መንግስታትና ሚዲያወች፣ ያማራን ሕዝብ ባሸባሪነት ፈርጀው የጭራቅ አሕመድን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በግልጽ እንዲደግፉ ምክኒያት (pretex) ለመፍጠር ነው፡፡  ይህን ዓላማውን የገለጠው ደግሞ “ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው” በሚለው ሐረግ (phrase) ነው፡፡  ይህን ያለው ደግሞ እስክንድር ነጋ ሐሳብ በማቅረቡ ብቻ “ጦርነት እንገባለን” ማለቱን የጦቢያ ሕዝብ የሚረሳለት መስሎት ነው፡፡  እሱ ራሱ ዛሬ የተናገረውን ነገ የማይደግም የሾርት ሜመሪ ሰለባ በመሆኑ፣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እንደሱ ሾርት ሜሞሪያም አድርጎ በመቁጠሩ ነው፡፡

 

ጭራቅ አሕምድ ግርማ የሽጥላን የገደለው፣ ባማራ ሕዝብ ላይ የሚያካሂደውን ጭፍጨፋ አጥናክሮ ለመቀጠል ምክኒያት ለመፍጥር ቢሆንም፣  በሌላ በኩል ግን ያማራን ሕዝብ ከውስጥ ሁኖ ይቦረቡር የነበረውን ነቀርሳ ነቅሎ በመጣሉ ላማራ ሕዝብ ከፍተኛ ውለታ ውሎለታል፡፡  ጭራቅ አሕመድ አማራን ቆረጣጥሞ የሚበላ ኦነጋዊ አውሬ ቢሆንም፣ ጥርሶቹ ግን ሙሉ በሙሉ ብአዴኖች ናቸው፡፡  ብአዴኖች በድን ከሆኑ ደግሞ፣ ጭራቅ አሕመድ ጥርስ የሌለው ጭራቅ ስለሚሆን፣ ያማራ ሕዝብ ጭራቅ አሕመድን ባጭር ጊዜ ውስጥ ጨርቅ ይደርገዋል፡፡  ያማራ ሕዝብ ጭራቅ አሕመድን ጨርቅ ካደረገ ደግሞ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ (ቀላል) ነው፡፡

ስለዚህም፣ ጭራቅ አሕመድ ግርማ የሺጥላን በመግደሉ ያወለቀው አማራን የሚቆረጣጥምበትን የገዛ ራሱን ጥርስ ነውና፣ ያማራ ሕዝብ እንኳን ገደልከው ሊለው ይገባል፡፡  በተጨማሪ ደግሞ የቀሩትን ብአዴናዊ ጥርሶቹን (ይልቃል ከፋለ፣ አገኘሁ ተሻገር፣ ሰማ ጡሩንህ፣ አበባው ታደስ ….) ባስቸኳይ እንዲነቅላቸው ያማራ ሕዝብ ጭራቅ አሕመድን ሊያበረታታው ይገባል፡፡  በተለይም ደግሞ ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ የሚዘነጣጥልባቸውን ሁለቱን ክራንቻ ጥርሶቹን (canine teeth) ማለትም ደመቀ መኮንንን እና ተመስገን ጡሩነህን ቢመነግላቸው፣ ያማራ ሕዝብ ለኢትዮጵያ አምላክ ትልቅ ምስጋና ማቅረብ አለበት፡፡  ጭራቅ አሕመድ ሆይ፣ ጅማሮህ ጡሩ ነውና ቀጥልበት፣ ሳትጨርስ እንዳታቆም፡፡

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

 

336041480 190174143897644 5142944496257140045 n

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop