ሲና ዘ ሙሴ
የዛሬዎች የኢትዮጵያ ገዢዎች ከቀድሞዎቹ ያልተማሩ በመሆኑ ፣ በዚህ በ11ኛው ሰዓት ለመማር ና ከዘረኝነት አስተሳሰብ ተመልሰው ፣ ዓለማቀፋዊ ህሳቤን በመንግስታቸው ውስጥ ካላነበሩ ፣ ፍፃሚያቸው ከቀኃሥ ፣ ከደርግ እና ከህወሓት ውድቀት እጅግ የከፋ ይሆናል ።
ቀኃሥ ( ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ) ” ዙፋኑን እና መንግሥታዊ ሥርዓትን አጣምሬ የህዝብን ነፃ አእምሮ ተቆጣጥሬ ፤ አገርን ከሰማይ በታች አስተዳድራለሁ ። ወይም ገዝቼ ዘለዓለሜን እኖራለሁ ። ” በሚል ገደብ በሌለው የሥልጣን ጥማት ፣ እስከ እርጅና ዘመናቸው ” ሰልጣን ወይም ሞት ! ” ብለው ሲንገዛገዙ ፣ 60 ባለስልጣናቶቻቸውን ( በውስጣቸው ታላላቅ ምሁራን አሉበት ።) በሐሰተኛ ዘዴ ጠርተው ካሰራቸው በኋላ ፣ እዛው እስር ቤት ውስጥ እንዲረሸኑ አደረጉ ። እራሳቸው ቀኃሥ በትራሰሰ ታፍነው ወይም ታንቀው ተገደሉ ። ከንጉሱ ና ሹመኞቻቸው ውጪ ደርግ በእጅ ብልጫ ና በነፃ እርምጃ ሞት የፈረደባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ መሆናቸውን ታሪክ ዘግቦታል ።
ደርግ ከጅምሩ ፣ ለሚሊቴሪው ጥቅም የተቋቋመ የወታደራዊ ኃይል ስብስብ ቢሆንም ፣ በህቡና በግልፅ የተቀላቀሉት ምሁራን ፣ የደርግን የጥቅም ጥያቄ ወደ ” ዙፋን ግልበጣ ” አሸጋገሩት ።
” ቁማር ጫዎታ ተጫውቼ
አጨብጭቤ ወጣሁ ተበልቼ ።
ምንኛ ዕድሌ በሰመረ
ዘውዱን ገልብጨው በነበረ ። ”
በምሁራን ደጋፊነት ዘውዱ ተገለበጠ ። ቁማሩ በደርግ ተበላ ። ዘውድ የመገልበጥ ቁጭት ተሳካ ። …
እናም ኢትዮጵያችን በማሌ ማርክሲዝም ና ሌኒንኢዝም ሪዮት መምራት ጀመረች ። ብዙ በስሜት የተነዱ ተግባራት ብቻ ሣይሆኑ ከፍተኛ የልማት ተግባራትም በአሥራሰባት ዓመት ያልተቋረጠ ጦርነት ውስጥ ደርግ ቢያከናውንም ምስጋና አላገኘም ። በ17 ዓመቱ በአሜሪካኖች ቀተቀነባበረ ሤራ ተገፋ ። መንጌ ወደ ዙምባብዌ ወታደራዊ ተሰደዱ ። የደርግ መንግስት ተንኮታኮተ ።
…የደርግ መንኮታኮት ፣ ትልቁ ሰበብ የሰሻሊዝም ካምፕ መፈረስ ነው ። ዕድሜ ለጎርቫቾቭ ። ሶቬት ህብረትን 17 ቦታ ሲያሸነሽኗት ፣ ጎን ለጎን የወደፊት የኢትዮጵያ 77 ቦታ ሽንሸና ንድፍ እየተሰራ ነበር ። በአሜሪካና በአውሮፓ ቱጃሮች ። ደርግ እንደ ዋዛ ከግዙፉ ጦር ሠራዊታችን ጋር ተንኮታኮተ ። የጠላቶቻችንን አንጀት ራሰ ። አርበኞቹ ኢትዮጵያውያን እርር ጭስስ አሉ ።
በደርግ እግር የገበሬው ጦር የወያኔ ሠራዊት ቤተመንግሥቱን ተቆጣጠረ ። መንግስቱ ወደ ሐራሬ ሂዶል ሲባልም ፣ ” በየት አቅጣጫ ነው ፤ መንገዱን አሳዩን ። አንገቱን አንቀን ይዘን ፣ ለፍርድ እናቀርበዋለን ። ” በማለት ጦር የአራት ኪሎን ነዋሪን የሐራሬውን መንገድ አሳዩን ሲል ጠየቀ ።
ውሎ ሲያድር ፣ ኋላቀር አስተሳሰቡን ፣ አመለካከቱን ና ድርጊቱን በዘመናዊነት ለመቀየር ጣረ ። እናም ጀግናው ፣ የኢህአዴግ ሠራዊት የሽግግር መንግሥት አቋቁሞ ፣ ለጥቂት የጥቅም ተጋሪዎች ገነት የመሰለች አገርን ፣ ለብዙሃኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የችግርና የችጋር አገርን ለመገንባት ፣ በብርቱ መጣርን ” ሀ ” ብሎ በ1983 ጀመረ ። ” አንድነት ፣ ፍቅር ፣ መተሳሰብ ፣ ሰው የእኔ ብጤነው ማለትን ፤ ህግን ማክበርና ማስከበር ፣ ጨዋነት ፣ አኩሪው የቤተሰብ ባህል ፣ ጡርን የመፍራት ወይም የልተገባ ነውረኛ ድርጊት በማንም ሰው ላይ ያለመፈፀም ። ወዘተ ። ” ከህዝብ ህሊና እንዲፋቅ ፣ ሰውን በጥርነፋ ( በአንድ ለአምሥት ) እርስ በእርሱ እንዲሳለል በማድረግ የአንድ ክልልን ህዝብ ከአንድ ፋብሪካ የወጣ የኮካ ጠርሙስ እንዲመስል በቋንቋና በጎሣ ፋብሪካ ውስጥ አስተሳሰብ እና አመለካከቱ እንዲቀየር በብርቱ ጣረ ።
ተጠራጣሪነትን ፣ ሥግብግብነትን ፣ መከፋፈልን ፣ ዘር መቁጠርን ፣ በጎሣ ማመንን ፣ ቆዳ ማዋደድን ፣ ቋንቋን አምላክ ማድረግን ፣ ” እኔ ሰው ነኝ ። ሌላው ከትል ያነሰ ፍጥረት ነው ። ይኼ የእኔ መሬት ነው ። ሌላው መጤ ነው ።… ” የሚል ህሳቤን የሚያዳብር እና የሚያነበር የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ሥርዓትንም ገነባ ። ልማታዊ እና ኪራይ ሰብሳቢ በሚሉ ቃላት ማደናገር እንደጀመረ ግን ሥልጣኑ አከተመ ።
ራሱ ኪራይ ሰብሳቢና ራሱ ኢ – ልማታዊ ሥራ እንደሚከውን ተረጋግጦ ለ27 ዓመት ከገዛበት ወንበሩ ህውሓት ኢህአዴግ ተሽቀነጠረ ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ” አገዛዙ በቀኛ ! ህገ አራዊት አገዛዝ ይውደም ! ” ብሎ ለለውጥ ተነሣ ። ኢህአዴግ በህዝብ በመጠላቱ እና የቀደመ ድጋፉ በመመናመኑ ፣ እንዲሁም ዋልታ ረገጡ ፣ የአክራሪ ና የጎሰኞች ተቃውሞ እያየለ በመምጣቱ በመንግሥት ውሥጥ ሹክቻ ተፈጠረ ። የኢህአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲ መንግስት ለሁለት እና ለሦስት ተሰነጠቀ ። በዋነኝነት የተሰነጠቀው የግንባሮቹ ” መሪ ግንባር ” ህውሃት ነው ። እናም ” ህውሃት የመሰዋት በግ ” ሆነ ።
ህውሃት ተሰዋ ። ከመሪነት ወረደ ። አራቱ ግንባሮች በኦሆዴድ ዋና ተዋናይነት የኢትዮጵያን ህዝብ በቅንነት በማገልገል ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ እናበቃዋለን አሉ ። ጠ/ሚ እንዲሆኗቸው አብይ አህመድን ( ዶ/ር ) ሊቀመንበራቸውና ጠ/ሚ አደረጓቸው ።
እሳቸውም እኛ ነበርን አሸባሪ ከእንግዲህ ሣናጣራ አናስርም ። ቶርቸር አንፈፅምም ። የማሰቃያ ካፕ አንገነባም ። ወዘተ ። ” መግለጫ ሰጡ ። …
ከዛስ ፣ ከዛማ ፣ ሰነባብተው ፣ ጠ/ሚሩ በራሳቸው መንገድ ” ብልፅግና ” የተሰኘ ፓርቲ መሠረቱ ። በፓርቲው ምሥረታና ሂደት የነበረውን ድራማ ፣ ብዙ ስለተባለበት ለታሪክ እንተወው ።
ዛሬ ብልፅግና በምናብ ደረጃ እንጂ በኢትዮጵያ ምድር በተግባር እንደሌለ እያየን ነው ።
ያለው ብልፅግና ሳይሆን የብልግና ሥርዓት ነው ። በዓለማዊ ነገሮች ፣ በፖለቲካ ጉዳዮች ፣ ጥንብ በሆነው ዘረኝነት ሰበብ ፣ ኢትዮጵያዊያን ከቀደመው ኢህአዴግ በባሰ መልኩ ፣ ከንቱ መሰዋትነት እንዲከፍሉ ያደረገው ብልፅግና የተሰኘ ፓርቲ ነው ። ዛሬ ደግሞ መላው የኦርቶዶክስ ምዕመናንን ለማጋጨት በመንፈሳዊ ቤት ውስጥ ሤጣናዊውን ዘር ለማብቀል ቆርጦ ተነስቷል ። ሰውነት እንዲጠፋ እና ጥንቡ ዘረኝነት እንዲፋፋ እና ህዝብ እርስ በእርሱ እንዲጫረስ መንገድ እየጠረገ ነው ።
ይኽንን ዳቢሎሳዊ ድርጊት ፣ ከአክሱም እሰከ ሞያሌ፤ ከሙስታሂል እስከ ጉባ ። ከጨው ባህር እሰከ ዳሎል … ። ከኦጋዴን እስከ መተከል። ከቦንጋ እሰከ ወለጋ ። …ከአዲስ አበባ እሰከ ድሬደዋ ። ከጅማ እሰከ ቴፒ ። ከአርባምንጭ እሰከ ጎጀብ ። ከባህር ዳር እሰከ ሑመራ ። ወዘተ ። ያለ የኦርቶዶክስ አብያተ ቤተክርስቲያን ምዕመን ሁሉ ተቃውመውታል ። የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶችም ጥንብ በሆነው ዘረኝነት ኃይማኖትን ለመክፈል የተደረገውን ጥረትን አውግዘዋል ። ቅዱስ ሲኗዶስም መንግስት መራሹን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ደም ሥር ቆራጩን ” የኃይማኖት ፖለቲከኞችን ” ስብስብ ወደ አቶነት አውርዷል ። የሚከተላቸውንም አውግዟል ። በዚህም ህዝበ ክርስቲያኑ በእጅጉ ተደስቷል ።…
የህዝበ ክርስቲያኑ ደስታ ግን ዘላቂ አልሆነም ። ሤጣን ይኽቺን በአንድነቷና በአቃፊነቷ የምትታወቀውን ፣ ለጎሣና ለነገድ ደንታ የሌላትን ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ማፈራረስና ህዝቡ በእምነቱ ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረጉን በጠብመንጃ እየተገዘ ቀጥሏል ። ይኽ ጠመንጃ የያዘ ኃይል እየተባበረ ያለው ከቅዱስ መንፈስ ጋር ያለመሆኑንን ህዝበ ክርስቲያኑ አውቋል ። የመነኮሱ ፣ ዓለምን የተለዩ ቅዱስ ግለሰቦች የመሳሪያ እጀባ አያስፈለጋቸውም ። ከኒኩለር እጅግ በጣም የሚበልጥ ኃይል ያለው እግዚአብሔር ጠባቂያቸው መሆኑንን አሳምረው ያውቃሉና ። …
ይኽንን ክፉ ፣ አሳፋሪ ድርጊትን በህዝበ ክርስቲያኑ ላይ እየፈፀመ የሚገኘውን ፣ የሤጣን ሠራዊት ፈጣሪያችን በቅርቡ እንደሚቀጣው አምናለሁ ። የዚህ እኩይ ሠራዊት ተባባሪዎችም ፣ ዘግናኝ ቅጣቱ አይቀርላቸውም ።
ህዝብ የሰጣቸውን የማገልገል ሥልጣን በተገቢው መንገድ ሣይጠቀሙበት በመቅረት የቤተክርስቲያን አባቶችን እንዲሰቃዩ ያደረጉት ሁሉ ፣ ተገቢውን ቅጣት በቅርቡ እንደሚያገኙ አልጠራጠርም ። አገርን እና መንግስትን በፈጣሪ ፈቃድ ፣ በታላቅ እምነትና ፀሎት ያቆየች ፣ ጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊ ቤተክርስቲያን ከፍሎ ፣ ለራሱ የክፋት ዓላማ ሁለት ፖትርያርክ መመስረት ፣ መንግስት አገርን ለማፍረስ ቆርጦ መነሳቱን ያመለክታል ። ” ሆሆ !!ዴድ !! ሸኔ ! አበልፃጊው ! ” ( እየዘረፉ ፣ እየገፈፉ ፤ እያፈኑ እና ከሚሊዮን እሰከ 200ሺ እየተቀበሉ የበለፀጉ ዕድሜ ለአብልፃጊው መንግስታችን ስለሚሉ ነው ፣ አበልፃጊው የተባለው ፣ ብልፅግና ። ) መንግስት ።
“ሆሆ !!ዴድ !! ” እነዚህ የተወገዙ እና አቶ የተባሉ ግለሰቦችን አክብሮ ሆቴል እስቀምጦ በመቀለብና በጠመንጃ በማስጠበቀ ፣ ህዝበ ምዕመኑን የተወገዙ ተራ ሰዎች መሰቀል እንዲያሳልሟቸው ፤ የእምነት አባቶች እንዲሆኑት ወደ አድባራቱ በአጀብ መውሰድ ፣ ለፈጣሪያችን ለእግዛብሔር ስድብ ነው ። እናም ይኽቺን የተቀደሰች ቤተክርስቲያን ማፍረስ እንደማይቻል በማይመረመር ችሎታና ኃይሉ ያሳያቸዋል ።
ይኽቺ ቤተክርስቲያን ፈረሰች ማለት አገር ፈረሰች ማለት ነው ። በበኩሌ ይኽ መላቅዱሱ የጠፋበት መንግስት ” በሬ ካራጁ እንደሚውል ዓይነት አደገኛ ጫዎታ ሥለሚጫወት ከአገራችን በፊት የሚፈርሰው እራሱ ነው ።
በተቋም ደረጃ ያለን አማኝ ሁሉ ፣ በሆሆ ዴድነት ጨፍልቄ ፣ ያንን ትንታግ መከላከያ ሠራዊት ሳይቀር ፣ እሳት የታጠቀውን ሁሉ ፤ ብዙሃኑንን ኦርትዶክሳዊ ፣ በሆሆዴድነቴ ፣ ” በቡድን ሃሳብ ብቻ እቆጣጠረዋለሁ ። ” ብሎ የሚያስብ ከሆነ ፣ በዘግናኝ ሁኔታ የሚፈርሰው ፣ የሚነደው ፣ የሚቃጠለው የመንግስትን ስልጣን የያዘው እና ግብረ አበሩ ሁሉ ይሆናል ።
ዛሬ መንግስትና ህዝብ ሆድና ጀርባ ናቸው ። የቱንም ያህል ኢህአዴግአዊ / አንድ ለአምስት ካድሬአዊ ስብከት በካድሬ ደረጃ ፣ አበል እየተከፈለ ቢያካሂድ ብልፅግና የህዝብን ልብ ወደራሱ መመለስ ከቶም አይችልም ።
ከእንግዲህ ባለሥልጣናት ( ቁርስ ፣ እራት ምሳችሁ ከባለአምስት ኮኮብ ሆቴል የሆነ ፣ እርስ በእርሳችሁ ትጫረሳላችሁ እንጂ ህዝብ ለእናንተ ለግብዞች ሥልጣን ሲል በሞኝነት ፣ በየዋህነት ፣ በጅልና በጅላፎነት አያልቅም ። ) እወቁ ፣ የትም ክልል ውስጥ ያለ ህዝብ የእምነቱን ነፃነት ፣ በገዛ እጁ ለማግኘት እንደሚንቀሳቀስ እወቁት ። …
ሰው እኮ የፈጣሪ ሥራ ነው ። የማያምን ፣ ፀረ እግዚአብሔር ሁሉ ፣ ይኸንን እውነት ከወዲሁ ይገንዘብ ። በግል የማሰብ ችሎታ ምን እንደሆነ የዘነጋም ፣ ከነ ጀነራል ሠዓረ አሳዛኝ አሟሟት ቀጥተኛ መልዕክቴን ይረዳ ።
እያንዳንድሽ ከኢንጅነር ሥመኘው እስከ አምባቸው መኮንን እና ጀነራል አሳምነው ድረስ ብቻ ሣይሆን ፣ በሥልጣነ ዘመንሽ በፈሰሰው የንፁሐን ደም በፈጣሪ ፊት ተጠያቂ ነሽ ። በሰው ላይ ጨለማን ተግን አድርገሽ ግፍ ስትሰሪ ያየ ዓምላክ ” እንዲሁ አፉ ይለኛል ፣ ባላየ ላሽ ይላል ” ብለሽ በእምነተ ቢስነት አትገበዢ ። ዘግናኝ ፍፃሜሽ በደጅሽ ነው ።
ልብ በሉ እኔ እያስፈራራሁ አይደለሁም ። እኔ እንደ ” ሲናው ሙሴ የፈጣሪ መልዕክተኛ ነኝ ። ” የታጠቀ ዜጋ አእምሮ ያለው መሆኑንን በቅንነት ላሳስብህ ነው ። ከአባትና ከእናት መወለዱን እና ዘመደ ብዙ መሆኑንም ፈፅሞ መርሳት የለብህም ። ጠመንጃ እንደያዝና በጠመንጃው ምን ማድረግ እንደሚችል ተረዳ ። በአእምሮው ጎዳ ሁሌም የሚያብሰለሰለው አንተን የኢትዮጵያ መሪ ስለሆንክ አንተን ስለመታደግ ፣ ስለአንተ ሲል ህይወቱን ስለመስጠት ብቻ አይደለም የሚያስበው ። ከዜጎች ፣ ከአባቶቹ ፣ ከእናቶቹ ፣ ከወንድሞቹ ፣ ከእህቶቹ ዘወትር በሚሰማው ብሶት የተነሳ ፣ አንድ ቀን ፣ ” ይህ ነው የህዝቤ አንድነት ነቀርሳ ፣ ለምን እሱን ወደ ሲዖል ሸኝቼ ሥሜን በታሪክ አሥጠርቼ አላልፍም ? ሞት እንደሆን ለሁላችንም የማትቀር ፀዋ ናት ። ” ብሎ ቃታውን ሊስበብህ ይችላል ። የሰውን አእምሮ እንደ ግልህ ሮቦት ልትቆጣጠረው አትችልምና !
መቆጣጠር የምትችለው ፣ ግኡዛኑን የቅስቀሣ ና የፕሮፓጋንዳ መሣሪያዎችህን እና ቱሉትላ ወይም ለፍላፊ ዶሮ የሆኑ ካድሬዎችህን ብቻ ነው ። ” እንደአንተ ምሳ ሳትበሉ የምሳችሁን ቆጥቡ ። ለማለት ወደኋላ አይሉምና ! ምሳ ሁሌም የሚያበላ ደሞዝ ነው እንዴ መምህሩ ሲጀመር ያለው ? ዛሬ አንድ ሽሮ ፣ በደረቅ እንጀራ ስንት ነው ? … ። ጉሮሮው ለሚነድ አስተማሪ አንድ ሌትር ውሃ ለአራት ፔሬድ ይበቃዋልን ? አንተ እዚህ ተማሪ ወደቀ ። ሾቀ ። ትላለህ የሾቀ አስተማሪ የሾቀ ተማሪ ነው የሚያመርትለህ ። አሥተማሪነት ላብህን ብቻ የምታንቆረቁርበት ሙያ አይደለም ። የዘወትር የአእምሮ ትጋትን እና ጤነኛ አእምሮን ይጠይቃል ።
ይኽን መሠፈርት የሚያሞሉ የበቁ ፣ በእውቀታቸው የማይታሙ ሥንቶች ናቸው ? ከግማሽ በላይ ከተማሪው ያነሰ ዕውቀት ያላቸው አስተማሪ ተብለውልናል ። በቋንቋ አጥር አይደለም እንዴ ምድረ ማይም በኦሮሚያ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ማይምነትን እያስተማሩ ያሉት ። ማትስ ፣ ኬሚስቲሪ፣ ባዮሎጂ ፣ ሂስትሪ ፣ ኢኮኖሚክስ ወዘተ። ድብልቅ ቋንቋ የሚናገሩ ልጆችን ( ተማሪዎችን ) ለማስተማር የግድ ኦሮምኛ ማወቅ የቅጥር መስፈርት በመሆኑ ቋንቋውን እንደ ፒኤችዲ በመቁጠር በዜጎች ላይ ጢባጢቤ ይጫወታሉ ። ። እልም ያለው መሃይም በጮርቃዎቻችን ላይ እንዲቀልድ በአስተማሪነት እንዲቀጠር ሽፋን የሰጠው ይኼ ጥንብ የሆነ ዘረኛ ሥርዓት አይደለም እንዴ ?
ወዳጄ ቀልድህን አቁም ። ምን ያልጨመረ ነገር አለ በኢትዮጵያ ? ርካሽ የተባለው ሙዝ እንኳን አንዱ 10 ብር ሆኗል ። ከአምስት ብር ወደ አሥር ብር ማደግ ማለት ምንማለት ነው ? ኢኮኖሚስቶችን ጠይቅ ።
ወዳጄ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችህን በፈለከው መንገድ በውሸት ሰበካ ፣ ለእኩይና ሠናይ ፍላጎቶችህ መገልገያ ልታድርጋቸው ትችላለህ ። ሆኖም ነፍስ ያላቸው ማሰብ የሚችሉ ሰዎችን ሁሌም ከእኔጋር በባርነት ይኖራሉ ብለህ እንደ ግኡዝ ካሰብክ ተሳስተሃል ። በውድም ሆነ በግድ ፣ መንግስት ስለሆንክ ብቻ ምሁራንንም ሆነ ማይማንን ፣ በአውቅልሃለሁ እና በአውቃለሁ ባይነት ልታወራቸው ፣ ጥያቄያቸውን ፣ በመምህር አብራራውነት ልትመልስላቸው ፤ አይንህን በማጉረጠርጥ ፣ እጅህን በማወናጨፍ ፣ የነኤዞፕን ተረት ልተርት እና ከአለቃ ገብርሃነ እበልጣለሁ ልትላቸው ትችላለህ ። እነሱም በህሊናቸው እየሰደቡህ ወይም አድናቆት እየቸሩህ ሊያዳምጡህ ይችላሉ ። ሆኖም ማወቅ ያለብህ እንደመንግስት የሰራኸው ፣ የህዝብን ሰላም እና ፀጥታ የማስከበር አንዳችም ተጨባጭ ሥራ ባለመኖሩ በህዝብ ልብ ውስጥ ከመንግስትነት ወርደሃል ።
የኢትዮጵያ መንግስት ምድር ላይ በተግባር የለም ። ያለው የትግሬ ፣ የኦሮሞ የአማራ ፣ የሶማሌ ፣ የጋምቤላ ፣ የሲዳማ ፣ ወዘተ ። የሚባል ፣ ከፊደራሉ መንግስትና ከተካዮች ምክር ቤት አቋም ውጪ ህዝብን ቁም ሥቅል የሚያሳይ መንግስት ነው ያለው ። ዛሬም ፣ ቤተሰባቸውን መምራት የማይችሉ ግለሰቦች ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ከፍተኛው አመራር ፣ ህዝብን እንዲያስተዳድሩ ሥልጣን ሰጥተሃቸዋል ። ዛሬ ደግሞ በኃይማኖቱ ጣልቃ በመግባት ከቀኖናው ና ዶግማው ውጪ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ሌላ ፓትርያርክ በመሾም ቤተክርስቲያኗን በዓለማዊ መንገድ ለመምራት ቆርጠው የተነሱ አይነኬዎች በሥርህ በቅለዋል ። ዓለማዊ ፀረ ክርስቶሶች በኢትዮጵያ እንዲነግሱ ከለላ እየሰጠሃቸው ነው ። በእግዚአብሔር ሥራ ጣልቃ በመግባት ። ደፋር ነህ ። ። ይኽ ድፍረትህ የሚያጣለህ ሰውን ከፈጠረው ዓምላክ ጋር ነው ። ይኽ ቀጥታ እግዚአብሔርን መዳፈር ነው ። ይኽ የግብዞች ድፍረት የሚያስከትለው ቁጣ ለፃድቃንም እንደሚተርፍ እወቅ ። … ፈጣሪያችን መድሃኒያለም ሆይ አስበን ።