February 1, 2023
5 mins read

ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን መጥላት ፤ ማጥላለት ኢትዮጵያዊነት ሊሆን አይችል!!!

abiy divider

abiy dividerወገን ሆይ አስቀድሞ የሚልስህ ቆቶ እንደሚያቆስልህ ዛሬም ላይ አለማወቅ  ድንቁርና እና ብልግና ብቻ ሳይሆን ኃጢት ነዉ ፡፡

አበዉ አካሄዱን አይቶ ስንቁን ይቀሙታል እንዲሉ ትናንት ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት አስቀድሞ በተተከለዉ ሶስቱን የኢትዮጵያ አምዶች በመነቅነቅ ፣ በማሻማቀቅ እና በማማቀቅ የሆነዉ ሁሉ አሁን ለተደረሰበት ዉብስብ ችግር ድንገተኛ ሁነት አይደለም ፡፡

ኢትዮጵያን በጠላቶች መንጋጋ ለማኘክ ይቻል ዘንድ ዉስጥ ጥርስ እንድትገባ እና ጠላቶች የዕግር ዕሳት እና ሰንሰለት የሆኑት ኢትዮጵያ ፣ኢትዮጵያዊነት እና የኢትዮጵያዊነት መገለጫዎች እነዚህ ሶስቱ የኢትዮጵያ ዕሴቶች ዕምብርቶች ነበሩ ፡፡

እነዚህም በጊዜዉ ፀረ-ኢትዮጵያዉያን  የጥፋት መዝገበ ቃላት በጠላትነት ሲፈረጁ ኢትዮጵያ ፣ዓማራ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን መሆናቸዉን ከረጂም ዓማታት አስቀድሞ ኢትዮጵያን ለማዳከም ኢትዮጵያዊነትን ማክሰም የጥፋት ዕሾክ በመትከል ኢትዮጵያዊነት ወንጀል ሆኖ የዜጎች መኖር ዋስትና በጠላቶች መዳፍ ስር ሆኖ ቆይቷል፡፡

በገዚዉ በ1983 ዓ.ም መጀመር የነበረበት አገርን እና ጠላትን የመከላከል ስራ ችላ ብሎ ማፈግፈግ ዛሬ እየሆነ ያለዉን ለሚረዳ በሽሽት መከራ እና  ጦርነት የማይቀር መሆኑን ነዉ፡፡

ኢትዮጵያን ለማዳን ዋጋ የከፈሉት ነፃነት እና ሠላም እንጂ ባርነት እና ከፊል ሠላም ፤ሠላም እንዳልሆነ ስለሚታወቅ በቀሚያ ረፊያ ሲያወጡ ፤ ሠዎች በማንነታቸዉ እና በበጎ ስራቸዉ ቁም ቅምጥ ሲነሱ፤ ለአገር የኖሩ ሲነወሩ፤ የአገር ጠላቶች በአገር የሚጦሩባት አገር መሆን፣ በዕምነት እና አመለካከት ልዩነት ሲደነቀር፣ የኢትዮጵያን ባንዲራ መያዝ ወንጀል ሲባል…ለምን ብሎ አለመጠየቅ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ከደረሱበት አረንቋ ለማዉጣት ትልቅ ዋጋ እየተጠየቀ ነዉ ፡፡ ዋጋ ጠያቂዉ ደግሞ የኢትዮጵያ ጠል አስተሳሰብ በሚሸከሙ ጠላቶች መሆኑ በቸልተኝነት የመጣ ባርነት እና ገባርነት ሆኗል፡፡

ትናንሽ ምት ዝግባን እንደሚጥል ትናንት በህዝብ እና በአገር ላይ የነበረዉን መከራ እና ስቃይ ለምን የሚል ባለመኖሩ ዛሬ ላይ በተቋም ደረጃ በኢትዮጵያ ቤ/ክርስቲያን ላይ የሚሆን የመጨረሻ መጀመሪያ እንጂ አዲስም ፤እንግዳም አይደደለም፡፡

ኢትዮጵያ አገራችን የሁላችን ከሆነች ቤተ ክርስቲን ላይ ጥፋት መመኘት የጋራ ጎጇችን ዕምየ ኢትዮጵያን ከአመታት በፊት ጎልላቷን ፤በመኃል ዕምብርቷን ዛሬ መሰረቷን መናድ ኢትዮጵያን ስረ መሰረቷን ማናጋት፣ማጥፋት ወይስ ማፅናት ?  ኢትዮጵያን መናድ እና መካድ ኢትዮጵያን መዉደድ እንዴት አንድ እንደሆነ ማብራሪያ መጠበቅ የምናየዉን እና የሆንዉን አለማወቅ ስለሚሆን እያዩ መሞት ፅድቅ ስለማይሆን የሆነዉ ፤እየሆነ ያለዉ እና የሚታሰበዉ ሁሉ ኢትዮጵያን ማቁሰል እና ኢትዮጵያዊነትን ማግለል በመሆኑ አገር ለማዳን የተደረገዉ ተጋድሎ ዋጋ ከማንም ፣ከምንም በላይ ዛሬም ለአፍታ ሳይረሳ ሁሉም ራሱን እና አገሩን የሚወድ ከዕንቅልፉ ሊነሳ እና ለአገሩ እና ለመፃኢ ህልዉናዉ ዘብ መቆም አለበት ፡፡

“ሁሉም በአገር ነዉ ፤የጨዉ ክምር ሲናድ ሞኝ ይስቃል ፤ ጠቢብ ሠዉ ያዝናል ፡፡”

የጥፋት ጎርፍ አንገት ላይ ሲደርስ ዋናትመኛ መሆን ከጎርፍ አያድንም ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ ፡፡

Allen Amber

1 Comment

  1. The PM Reminds Of Mobutu Sese Seko. “Ruthless And Cunning As He Was, Mobutu, Indeed, Used His Showmanship, Braggadocios Buffoonery And Eccentricity To Fool Everybody Himself Included” “He Can Be Ranked High Among Worst Managers Africa Has Ever Has In Running The Business Of The State”. “; Taken From Book ” Africa’s Worst And Best Presidents”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

matias
Previous Story

አባታችን አቡን ማትያስና የጭራቅ አሕመድ ሲሳይ አጌና ዘዴ

matiastt5t 1
Next Story

DC- ዐቢይ አህመድ የመከፋፈል ሴራ ብቻ ነው ያለው

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop