January 21, 2023
24 mins read

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ላልተወሰነ የቆይታ ዘመን የተቆቆመ ድርጅት!!!

eet576768598ሚሊዮን  ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

‹‹የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን ላልተወሰነ የቆይታ ዘመን የተቆቆመ ድርጅት ነው፡፡›› አዲስአበባ ጥር 23 ቀን 2014 ዓ/ም ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር  የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን በአዋጅ ቁጥር 1263  የተቀቀመ ድርጅት መሆኑን በአዋጅ በ2014ዓ/ም ደነገጉ፡፡ ‹‹የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና ተቆጣጣሪ ኤጀንሲን ስልጣንና ኃላፊነት ለመወሰን የወጣ ደንብ ቁጥር 445/2011 እና ሌላ ይህን ደንብ የሚቃረን ማንኛውም ህግ ፣ደንብ፣ መመሪያ ወይም አሠራር በዚህ ደንብ በተሸፈኑ ጉዳዩች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡››………………….(1)

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ (Ethiopia Investment Holdings (EIH))

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፍሪካ ትልቁ ሉዓላዊ ኃብት ሲሆን 150 ቢሊዮን ዶላር ቆሚ ሃብትና ንብረት  በአስተዳደሩ ስር ያሰባሰበ እና ተጨማሪ የገቢ ክፍፍል ፍሰት ያለው ድርጅት ነው፡፡ በ2022 እእአ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከአፍሪካ አቻ ድርጅቶች ጋር ተዋህዶል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሚወክለው የኢትጵያን የረዥም ጊዜ የኮሜርሽልና ኢንቨስትመንት ፍላጎትን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው የተሸሙት ልጅ እግሩ አቶ ማሞ ምህረቱ ሲሆኑ በፊት የምጣኔ ኃብት አማካሪና የኢትዮጵያ ዋና የንግድ ተደራዳሪ የነበሩ ሲሆን አሁን ደግሞ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው ተሾመዋል፡፡ አቶ ማሞ ምህረቱ የዓለም ባንክ ከፍተኛ ሠራተኛ ነበሩ፡፡ በእጃቸው መዳፍ ላይ የሚገኘውን የሃገሪቱን ኃብት በአዲስ ኢንቨስትመንት አትረፍርፈው፣በየዓመቱ ለሚሊዮን ወጣቶች የስራ እድል ከፍተው በዘላቂ ልማት ያፋጥኑ ይሆን? ወይስ የሃገሪቱን ኃብት ይቸበችቡት ይሆን? ፈጣሪ ይርዳቸው፡፡   ‹‹ Ethiopian Investment Holdings (EIH) is the largest sovereign wealth fund in Africa, with over $150 billion in assets under management and additional dividend income inflow. It recently joined its African peers in January 2022. EIH represents Ethiopia’s long-term commercial and investment interest.›› የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዙ ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር ያሉ ኃብትና ንብረቶችን ሁሉ ያስተዳድራል፣ይቆጣጠራል፡፡ ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ኃላፊነት በላይ ሪል-ስቴት፣ መሬት፣ መሠረተ-ልማቶች፣ የመሳሰሉትን ኃበቶች ጨምሮ ይቆጣጠራል፡፡ በአዋጁ መሠረትም፡-

‹‹የተቀናጀ  ስትራቴጂያዊ  ቁጥጥር  በማከናወን በመንግሥት ባለቤትነት የተያዙ ሪል-ስቴት፣ መሬት፣መሠረተ  ልማቶች፣የመንግሥት የልማት ድርጅቶች እና የመሳሰሉት ሀብቶችን የተሟላና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲሰጡ ማድረግ የሚቻልበትን ተቌማዊ አደረጃጀት መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ›› ‹‹የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒሰትር ጽህፈት  ቤት ይሆናል፡፡›› ‹‹ የኢትዮጵያ  ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን የተፈቀደ ካፒታል ብር አንድ መ ቶ ቢሊየን ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር ሃያ አምስት  ቢሊየን በጥሬ ገንዘብ እና  በዓይነት ተከፍሎል፡፡››

‹‹የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት  ሆልዲንግስን የገንዘብ ምንጭ የሚከተሉት ናቸው፡- (1) በዚህ ደንብ በተደነገገው መሠረት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን እንዲያስተዳድራቸው   የተደረጉ የተለያዩ የመንግሥት ሀብቶች  (2) ከሃብቶቹ የሚገኝ ገቢና የኢንቨስትመንት ትርፍ  (3) ከሃብቶቹ ወይም ከተቆማቱ ሽያጭ የሚገኝ ገቢ (4) ከቦንድ  እና ከሌሎች የፋይናንስ ሰነዶች ሽያጭ የሚገኝ ገቢን ጨምሮ ከብድር እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚገኝ ገቢ  (5) በዳይሬክተሮች ቦርድ ፀድቆ የሚመደብ ከሌሎች ምንጮች የሚገኝ ገቢ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሥራ ተግባራት መኃከልም፡-

‹‹ከአገር ውስጥ እና ከውጭ አገር  ምንጮች ይበደራል፣ገንዘብ ይሰበስባል፣የእዳ ሰነዶችን ያወጣል፣ ዋስትና  ይሰጣል፣ እንደ አስፈላጊነቱም ማንኛውንም እዳ ወይም ግዴታ ይሰርዛል፡፡›› ‹‹ለሃገራዊ ኢንቨስትመንት፣ የእዳ ክፍያ፣ ለበጀት እና ሌሎች የፖሊሲ ዓላማዎችን ለማሳካት የሚያስፈልገውን ሀብት ጨምሮ ቀጣይነት ያለውን ትርፍ ለመንግሥት ማስገኘትን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን የወደፊት ኢንቨስትመንት የሚሆን ተቀማጭ ገንዘብ መያዝን ባመጣጠነ መልኩ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን እና ተቀጥ ዎቹን የትርፍ አከፋፈል ፖሊሲ ይወስናል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን በባለቤትነት ከያዛቸው ድርጅቶች የሚያገኘው የትርፍ ድርሻ ከማናቸውም ግብር ቀረጥና  ተመሳሳይ የክፍያ ግዴታ ነፃ ነው፡፡››

‹ኦዲተሮች የሩብ ዓመትና የዓመታዊ የሂሳብ መግለጫዎችን ይመረምራሉ፡፡›› ‹‹ማንኛውም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን ስር ያለ ሀብት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባላቸው ደረጃዎች መሠረት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን የሒሳብ መዝገብ ውስጥ መመዝገብ አለበት፡፡›› ‹‹ቆሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ይገዛል፣ ይሸጣል፣ይከራያል፣ያከራያል፣ይጠቀማል፣ይገለገላል›› ይላል አዋጁ፡፡

ኢትዮጵያ ስቶክ ኤክስቼንጅ( Ethiopian Stock Exchange (ESX))

የኢትዮጵያን  ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶችን› ፕራይቬታይዝ የሚያደርግ በትንሹ ሃምሳ ካንፓኒዎችን ስም ዝርዝር በኢትዮጵያ ስቶክ ኤክስቼንጅ (ESX) በሚቀጥለው ሁለት አመት ውስጥ በግልፅ እንደሚጀመር ተገልጾል፡፡ ኢትዮጵያ ስቶክ ኤክስቼንጅ የጋራ ፕሮጀክት ሲሆን  በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ (Ethiopia Investment Holdings (EIH))፣ የገንዘብ ሚኒስቴርና፣መሠረቱን ናይሮቢ ያደረገው ፋይናንሻል ሴክተር ዲፕኒንግ አፍሪካ (Financial Sector Deepening Africa (FSDA)) በጋራ ፕሮጀክቱ መረጃ መሠረት የኢትዮጵያ ስቶክ ኤክስቼንጅ ከ25 እስከ 55 በመቶ  ድርሻ የሚሸጠው ለኮርፖሬሽኖች፣ ካፒታል ማርኬት፣ ኢንተርሚዲአርሪስና ኦፕሬቶርስ ኦፍ ኢንተርናሽናል ሴኩሪቲስ ኤክስቼንጅስ ሲሆን የመንግስት ድርሻ ከሃያ አምስት በመቶ እንደማይበልጥ ተገልፆል፡፡ በ2021እኤአ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ (EIH))፣ በስሩ የሚቆጣጠረው ንብረትና ኃብት $38bn (የሠላሳ ስምንት ቢሊዮን ዶላር)  ወይም 34% (ሠላሳ አራት በመቶ) የኢትዮጵያን ጂዲፒ ኃብት ሲሆን በዚህም የሚያመነጨው አመታዊ ገቢ $6.2bn.(ስድስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር) ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ ትልልቆቹ ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶችን› ፖርትፎሊዮ ውስጥ የኢትዮጵያ አየርመንገድ፣የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኢትዮቴሌኮም መሳሰሉት ድርጅቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ስር ሆነው ኢኮኖሚውን ነፃና ክፍት በማድረግ ጎዳናውን በመጥረግ የፕራይቬታይዤሽኑን ሽያጭ ያሳልጣሉ፡፡ “At least 50 companies are expected to list on the Ethiopian Stock Exchange (ESX), set to launch in two years. The ESX is a joint project between the country’s giant new sovereign wealth fund, Ethiopia Investment Holdings (EIH), Ministry of Finance and Nairobi-based Financial Sector Deepening Africa (FSDA). Between 25% and 55% of the ownership of the ESX will be for corporations, capital market intermediaries and operators of international securities exchanges, while government will not own more than 25%. Meanwhile, the establishment of EIH, one of Africa’s biggest sovereign wealth funds, could be the start of a massive turnaround in Ethiopia’s long-established economic heterodoxy. It was set up in late 2021 and will control assets worth some $38bn, or 34% of Ethiopia’s GDP, generating annual revenues of $6.2bn. It has some of Ethiopia’s largest and most productive state-owned enterprises in its portfolio, such as Ethiopian Airlines, the Commercial Bank of Ethiopia or Ethio Telecom, and with its active participation in the establishment of the country’s first securities exchange, is likely to pave the way for the liberalization of the economy and increase the pace of privatization.”

SOURCE: NORTH AFRICA POST……………………….(2)

ሊብራላይዜሽን፡- በአሜሪካና በአውሮፓ ህብረት አገሮች የሚዘወረው አይኤምኤፍና የዓለም ባንክ ታዳጊ አገሮችን ኢኮኖሚያችሁን ክፍት አድርጉ! ሊብራላይዝ አድርጉ በማለት ያስገድዳሉ፡፡ የብልፅግና መንግሥት   ኢኮኖሚውን ክፍት ለማድረግ  የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ ለመሸጥ የተያዘው ዕቅድና የቴሌኮም ሊብራላይዜሽን ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ከሚችሉት ጉዳዮች አንዱ የፋይናንስ ዘርፉን ክፍት  በማድረግ የውጭ ካንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ማድረግ በመሆኑ የአገር ውስጥ ባንኮችና ኢንሹራንሶች ከፍተኛ ውድድር እንደሚጠብቃቸው ተናግረዋል፡፡ ሌላው የዓለም ባንክ ስትራክቸራል አጀስትመንት በሊብራላይዜሽን  ፕሮግራም ሥር እንዲፈጸም የሚጠይቀው ለውጭ ኩባንያዎች ዝግ የነበሩ ዘርፎች ተከፍተው የውጭ ተወዳዳሪ ኩባንያዎች እንዲመጡ የሚያስገድድ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ስቶክ ኤክስቼንጅ ከ25 እስከ 55 በመቶ ድርሻ የሚሸጠው ለዓለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖች፣ ካፒታል ማርኬት፣ ኢንተርሚዲአርሪስና ኦፕሬቶርስ ኦፍ ኢንተርናሽናል ሴኩሪቲስ  ኤክስቼንጅስ ሲሆን የመንግስት ድርሻ ከሃያ አምስት በመቶ እንደማይበልጥ ተገልፆል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ (EIH))፣ በስሩ የሚቆጣጠረው ንብረትና ኃብት $38bn (የሠላሳ ስምንት ቢሊዮን ዶላር)  ወይም 34% (ሠላሳ አራት በመቶ) የኢትዮጵያን ጂዲፒ ኃብት ሲሆን በዚህም የሚያመነጨው  $6.2bn.(ስድስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር) አመታዊ ገቢ አለው፡፡  “The Prime Minister of Ethiopia has set up in August 2018 an Advisory Council, which oversees the process of privatizing large state-owned enterprises. The establishment of the Council aims to implement the decision of the Executive Committee of the ruling party, EPRDF in June 2018 to open major state-owned enterprises for private and foreign investors. The decision includes to partially or fully transferring the shares of companies such as railways, industrial parks, hotels, sugar and manufacturing industries. The Committee also decided to sell minority shareholdings in some other state companies, including Ethiopian Airlines, Ethio Telecom (the only telecommunication service provider in the country), as well as the Ethiopian Shipping & Logistics Services Enterprise.” …………………………..(3)

አይኤምኤፍና የዓለም ባንክ በፕራይቬታይዤሽን ስም የታላቆ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ ኢትዮቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንና ሌሎችም በሙሉና በከፊል ለሽያጭ  የሚቀረቡ ድርጅቶች በእጅ አዙር እንዲሸጡ በመደለል ላይ ይገኛሉ፡፡ ለሃገራችን ውድቀት እንጂ እድገት ይዞ አይመጣም እንላለን፡፡ ሃገር በቀል የሆኑ የሃገር ውስጥና ዲያስፖራው ወገኖች እነዚህን ድርጅቶች በአክሲዮን እንዲገዙ በማድረግ ሁኔታውን ማመቻቸት ያስፈልጋል፡፡

ኢኮኖሚውን ክፍት በማድረግ (ሊብራላይዤሽን) ለውጭ ኩባንያዎች ፈቃድ መስጠት መጀመሩንና ከቴሌ ኮሙዮኒኬሽን ዘርፍ በተጨማሪ መንግሥት ወደ ግል የሚዛወሩትን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን 13 የስኳር ፋብሪካዎች፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንና ሌሎችም በሙሉና በከፊል ለሽያጭ  የሚቀረቡ ድርጅቶች ናቸው፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕራይቬታይዤሽን አማካሪ ካውንስል 21 አባላት  ያሉት ተቆቁሞል፡፡ የፕራይቬታይዤሽን በሙሉና በከፊል ለሽያጭ የሚቀርቡት ድርጅቶች ከሽያጩ የመንግሥት ከፍተኛው ድርሻ እንደሚሆን በስብሰባቸው ላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ገልፀው ነበር፡፡ በሚቀጥሉት ሁለት አመታት ውስጥ በፕራይቬታይዤሽን ከ25 በመቶ  እስከ 55 በመቶ  ድርሻ የሚሸጡት ካንፓኒዎች ለዓለም አቀፍ ንግድ ድርጅቶች ጨረታ ይቀርባሉ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት 25 በመቶ ድርሻ ብቻ ይኖረዋል፡፡ “The Executive Committee of the EPRDF unanimously voted to partially privatise some of the most profitable state enterprises in early June, with the government retaining majority stakes. They included Ethio telecom, Ethiopian Airlines, Ethiopian Shipping & Logistics Services Enterprise and Ethiopian Electric Power, as well as state-owned railways, sugar factories, industrial parks, hotels and manufacturing plants. The Prime Minister has since told parliament that the majority of the shares the government relinquishes will be offered to non-national investors.”………………………(4)

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ፡-

በኢትዮጵያ የፕራይቬታይዤሽን ፍሪዳ ለቅርጫ ተጥሎል የአሜሪካ፣ የአውሮፓ፣ የኤሽያ ሙልቲናሽናል ኮርፖራሽኖች በርግደው ባስከፈቱት ‹ሉዓላዊ ሃገር› በር ትርፋማ የሆኑትን የሃገሪቱን ካንፓኒዎች በሙሉ ወይም በከፊል ለመግዛት ቆምጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ኃብትና ንብረቶች ውስጥ፡- ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶችን›  ፕራይቬታይዝ የሚያደርግ በትንሹ ሃምሳ ካንፓኒዎች  ኃብትና ንብረት  $38bn (የሠላሳ ስምንት ቢሊዮን ዶላር)  ወይም 34% (ሠላሳ አራት በመቶ) የኢትዮጵያን ጂዲፒ ኃብት ሲሆን በዚህም የሚያመነጨው አመታዊ ገቢ $6.2bn.(ስድስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር) ነው፡፡ ሃምሳ አትራፊ ካንፓኒዎች የሚሸጡት ብድርና የእዳ ወለዳችንን ለመክፈል እንደሆነ ይገመታል፡፡  የፕራይቬታይዤሽን ፍሪዳ ለቅርጫ ተጥሎል፡፡ መንግሥት ተበድሮ፣ ተበድሮ መክፈል ስላቃተው፣ አትራፊ ካንፓኒዎቹን ሸጦ የእዳውን ወለድ ለመክፈል እንደሆነ ይታመናል:: የሃገሪቱ አንጡራ ሃብት ተዘርፎ ውጭ ሀገር ከዘራፊዎቹ ጋር ተሰዶል፣ በኢህአዴግና ብልፅግና መንግሥት ዘመን ከ30 እስከ 70 ቢሊዮን ዶላር ከሃገር ተዘርፎ ባህር ማዶ እንደኮበለለ በማስረጃ ተሰንዶ ተቀምጦል፡፡ ከሃገሩ ሌላ ሃገር የሌለው ዜጋ የተረፈው እዳው ብቻ ነው፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም Ethio Telecom:-  የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የብልጽግና መንግስት ስም፣  ከአይኤም ኤፍና ዓለም ባንክ ብድር በማግኘትና ኢኮኖሚውን ክፍት ለማድረግ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ላይ ያለውን 45 (አርባ አምስት) በመቶ ድርሻ ለግል ባለኃብቶች ኢንቨስተሮች የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ሸጦል፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮቴሌኮም ከፊል 45 በመቶ ድርሻ የኬንያ ሳፋሪኮም 850 (ስምንት መቶ ሃምሳ) ሚሊዮን ዶላር በመሸጥ እንዲሁም በሚቀጥሉት አስር አመታት ውስጥ የ8.5 (ስምንት ነጥብ አምስት) ሚሊዮን ዶላር ወጪ ኢንቨስትመንቱን ለማስፋፋት እቅድ ነድፎል፡፡ “At the end of May, one of the licenses was awarded to a consortium led by Kenya’s Safaricom, which offered $850 million and also plans to invest $8.5 million over ten years, according to the authorities.” የኢትዮ ቴሌኮም ሶስተኛውን የቴሌኮም አገልግሎት ፍቃድ ለባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ለመሸጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም  ያለውን 55 (ሃምሳ አምስት) በመቶ ድርሻው ላይ ስንቱን ቀንሶ እንደሚሸጥ ገና አላሳወቀም 25 በመቶ እስኪቀር ሽጦ መንግሥት የእዳውን ወለድ ለመክፈል ተገዶል ማለት ነው፡፡ የብልፅግና መንግሥት በገባው እዳ የተነሳ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ኢትዮ ቴሌኮም ለሦስተኛ አካል ፍቃድ ለመስጠትና ለመሸጥ ተገዶል ማለት ነው፡፡የኢትዮ ቴሌኮም ከሳፋሪኮም 850 ሚሊዮን ዶላር ሽያጭ ገንዘብ ለምን አላማ እንደዋለ ህዝብ የማወቅ መብት አለው፡፡ “A key pillar in the reform agenda is the commercialisation and privatisation of Ethiopia’s SOEs, which we expect to continue in the coming years and to contribute to external financing in the form of government receipts and higher FDI inflows. Earlier in 2022, the government completed the sale of a license to operate telecom services in the country and is proceeding with both the partial sale of Ethio Telecom and the tender of a second telecom license. The government is also moving ahead with the sale of several enterprises in the sugar sector.”

‹‹የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ላልተወሰነ የቆይታ ዘመን የተቆቆመ ድርጅት›› ቆይታ አንቀፅ 19 ከአዋጁ

 

ምንጭ፡-

Reg  487 investment holding objec & duty. Pdf/  Ethiopian-Investment-Holdings-Regulation-No.-487_2022Download

A Platform for the Privatization of Ethiopia’s State-owned Enterprises – Africa.com (www.africa.com) / October 29, 2022 / By Editor

Advisory Council on Privatization of State-owned Companies Establis

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop