January 9, 2023
14 mins read

የግማሽ ሚሊዮን የትግራይ ወጣቶችን ደም በወልቃይትና ራያ ለመካስ መሞከር አጓጉል ህሳቤ ነው

Abiy is a killer eየኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያውቀውና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ትልቁ ጉዳይ ሃገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ህሳቤና መንፈስ በሌላቸው መሪዎችና ባለስልጣኖች እየተመራች መሆኑን ነው።

“ከአያያዝ ያስታውቃል ከአነጋገር ይፈረዳል” እንዲሉ ያለፉት 27 ዓመታትና የሰሞነኛው የኢትዮጵያ አራት ዓመታት ስንቦታችን ስንቃኝ በሃገራችን የስልጣን ቁንጮ ላይ ተሰይመው ኢትዮጵያን እያመሱ ያሉ  ባለስልጣን ተብየዎች ከአንድ ብሄር የተቀዱ ፣ በተፋለሰና መሰረት በሌለው የታሪክ ዲስኩር በኢትዮጵያ ና በኢትዮጵያውያን ላይ ቂም የቋጠሩ ናቸው።

እነዚህ ባለስልጣኖች በሻሞ ያገኙት ስልጣን ካላዛለቃቸው እንወክላለን የሚሉትን ሕዝብ/ብሄር/ ይዘው ለመንገጠል የቀቢፀ ተስፋ መርሆ እንግበው የሚወናገሩ በአካለ ስጋቸው የሚንቀሳቀሱ ነገር ግን በቁም ሙተው የሚወጃወጁ ነሆልሎች ናቸው።

የሃገሬ ሰው “ ወይራ ዶግ ይወልዳል” እንዲሉ እነዚህ አጓጉሎች ከኢትዮጵያውያን ማዕፀን ወጠተዋል ቢባልም  የበታችነት የስሜት ዶፍ የዘነበባቸው ቡኩን ፣ ማሰብ የተሳናቸውና ሃገር አፍራሾች ናቸው።

ይህን መሰረት አርገን እኛ ኢትዮጵያዊያን እነዚህ እኩያን በሚያደርጉት ፣ በሚያፀድቁት ፣ በሚወስዱት ፅንፍ የለቀቀ ፣ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊ የማይሸት ህገ አራዊት ውሳኔያቸው መደናገር ፣ መደናገጥና ተስፋ መቁረጥ የለብንም።

የኢትዮጵያ አምላክ ቃል ለገባላት የተስፋዋ ምድር የሚሆናትን ቀብቶና ጊዜው ደርሶ መሪ ሲሾምላት አሁን እያየነው ያለው ጥዮፍ ነገር ሁሉ እንደጉም ይበናል ፣ ኢትዮጵያ ሃገራችንም ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ስሟ የገነነ ምድረ ገነት ትሆናለች።

ነግር ግን አምላክ “ እርዱኝ እረዳችኋለው” እንዳለው በያለንበት ቦታና አጋጣሚ እነዚህን ሃገር አጥፊዎች “ እርጉም ከመ አሪዎስ” እያልን ልናወግዛቸው የግድ ይላል ።

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረጉ ያሉት የሰሞነኛው የአራት ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነቶች በኢትዮጵያ የመንግስት የታሪክ ክዋኔ ታይተውም ተሰምተውም አይታወቅም።

ያለፉት የኢትዮጵያ መንግስታት/ ነገስታት መጠነኝ የእርስ በርስ ግጭት የሚያደርጉት ግብር ባለመክፈል ፣ መሳፍንቶች ሕግን በመጣስ  ኢትዮጵያዊያንን ሲበድሉ እና መሰል በሆኑ መህበራዊ መጎሻሸሞች እንጂ እንደአሁኑ ሕዝብ ከሕዝብ ወይም ብሄር ከብሄር በታንክ ፣ በድሮን ፣ በጀት ፣ በሚሳኤልና ከባድ አገር አጥፊ መሳሪያዎች በመጠቀም ተዋግተው አያውቁም ፣ ታሪክ አልመዘገበውም ፣ አልነበረምም።

የብልፅግና የመንግስት አስተዳደር ከዘመነ መሳፍንት የአገዛዝ ዘመኖች ጋር የሚያመሳስለው ፈርጣማ ጉልበትና ከባድ መሳሪያ ያነገቡ ሚጢጢ መንግድታት በየአካባቢው ብቅ ብቅ ማለታቸው ፣ ተቻችሎ በአንድነትና በኢትዮጵያዊነት መንፈስ የመዝለቅ ፍላጎት እያጡ መምጣታቸውና የሕግ ተገዥ አለመሆናቸው ነው።

የዚህ ሁሉ  “ እንደ ግመል ሽንት “ ሃገራችን ወደኋላ እድትጓዝና ዘመነ መሳፍንት ስርዓት እንደገና እንዲያንሰራራ ምክንያት የሆነበት ምክንያት በኋላ ቀር ፣ ገነጣጣይና ሃያ አንደኛውን ክፍለ ዘመን በማይመጥን ሕገ መንግስት ሃገራችን እንድትመራ ስለተደረገና ስልጣነ ወንበሩ ላይ የተሰየሙት መሪወች ግትልትል ፅንፈኛ ብሄርተኞችና ጊዜውን የዋጁ ባለመሆናቸው ነው።

ቀደም ያሉ ባለ ግርማ ሞገስ ፣ አርቆ አሳቢና ጀግና መሪዎቻችን ከፋም ለማም ጦር የሚሰብቁት ድንበር ጥሶ ከሚመጡ ወራሪዎች ከቱርክ ፣ ከፋሽሽት ጣሊያን ፣ እንግሊዝ ፣ ፖርቸጋል ፣ ሶማሌ ፣ ከሱዳን ድርቡሽ ፣ ከግብፅና መሰሎች ጋር ነበር። የዚያ ወርቅ ዘመን ጦርነቶች ደግሞ በቁጭት ፣ እንዴት ብንናቅ ፣ እምቢ ለሃገሬ ፣ ለድንበሬ በሚያስብል ምክንያታዊ ስሜት መላ የኢትዮጵያ ሕዝብን ለፈቃዳዊ መስዋትነት የሚጋብዙ ነበሩ።  እንዲህ አይነት ምክንያታዊ  የጦርነት ፍልሚያዎች ደግሞ መቋጫቸው በማያዳግም መልኩ ሲሆን በታሪክ መዝገብ የሚወሱና ሃውልት የሚቆምላቸው ናቸው። ።

ትላንት የውጭ ሃገር ወራሪ ጠላትን ሲፋለሙ የነበሩ የኢትዮጵያዊያን ክንዶች በአሁኑ ጊዜ ግን ብሄር ከብሄር ጋር ለሚደረጉ ሰው ሰራሽ ጦርነቶች ሰለባ እየሆኑ ነው።  የሰሞነኛው ጦርነቶች ዓላማ ደግሞ ለስልጣን ማስጠበቂያ ፣ ማራዘሚያ ፣   ባልተጨበጠ ትርክት ወዘተ በምሁራንና በመሪዎች መካከል በሚቆሰቆስ የእርስ በርስ መበሻሸቅ የሚፈጠሩ የልብ ወለድ ፊልም ዐይነት ጦርነቶች ናቸው።

ለእንደዚህ መሰል ዓላማ ቢስ ጦርነቶች የሚከፈለው መስዋዕትነት በጣሙን ያስቆጫሉ ፣ ያናዳልና ያንገፈግፋል።

በኢትዮጵያ ሃገራችን በላህላይ የስልጣን ቁንጮ  ሳይገባቸው ቀብ ባሉት እና ያለ ሕዝብ ድምፅ በግጥምጥሞሽ በተሰየሙት መሪዎች በተጠነሰሰ የእርስ በርስ የስልጣን ሽኩቻና አለመግባባት ሕዝብን ከሕዝብ ካጫረሱት ጦርነቶች መካከል እንደኛው  “ የባድሜ” ጦርነት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ “ሕግ ማስከበር “ በሚል የዳቦ ስም በትግራይ ፣ በአፋርና በአማራ አካባቢ ያሉ እምቅ የኢኮኖሚ ፣ የማህበራዊ ፣ ለግፈኞች አልገዛም ፣  እምቢ ለሃገሬ ኢትዮጵያ ፣ ለባንዴራየና ለጋራ ቋንቋየ የሚለውን የህዝቡን የጋራ እሴት ድምጥማጡን ለማጥፋትና ያለተቀናቃኝ ሕዝብን ደፍጥጦ ለመግዛት በገዥው መደብ ተፈብርከው ታላቅ ውድመት ያደረሱ  ጦርነቶች እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ጦርነቶች ስለመሆናቸው መስካሪ አያስፈልግም።

ቀጣዮ ጦርነት ደግሞ የሚፈበረከው የግብፅና የሱዳን ወራሪ ኃይሎችን ሽንጡን ገትሮ ለዘመናት ተፋልሞ የሃገሩን ድንበር ያስጠበቀውን  ፣ ወያኔን አፈር ድሜ ያበላውን ፣ ለብልፅግና መንግስትና በቅርቡ ከኦሮሚያ ብልፅግና ጋር ዳግም ጋብቻ ሊፈፅም ለተዘጋጀው አርባአይ /አራተኛው/ ወያኔ ስጋት የሆነውን የአማራ ጎንደርና የወሎን ምድር ለማተረማመስ ፣ ለማዳከምና እንዳያንሰራራ ለማድረግ ሊከወን የተዘጋጀው ትውኔታዊ ጦርነት ነው።

ሳይደመሩ ተደምረናል ፣ ኢትዮጵያዊነትን እናገናለን ብለው በብሄር አጥር የታጠሩት እነ ብልፅግና “ወጉ ተወግጓል ምጣዱ ተጥዷል” እንዲሉ ከህውሃት ጋር ድርድር አደረግን ፣ሰላም ወረደና እንግዲህ ፊታችን ወደ ልማት እያሉ መቀሌ ላይ ባደረጉት የጫጉላ ሽርሽር ደስኩረውልናል ፣ ስምምነታቸው” የድመቷና የአይጧ ታሪክ” እንዳይሆን ስጋታችን አየጠቆምን ፣ ያዝልቅላቸው እንላለን።

ያደረጉት ድርድር ግን የሁለት ፓርቲ ማለትም የብልፅግና እና የህውሃት አንጃወች የጨረባ ድርድር እንጂ የድርድር ፅንሰ ሃሳቦችን ያልተከተለ ማለትም አካታች ያልሆነ፣ ግልፅነት የጎደለው ፣ በውስን አጀንዳ የታጠረ ፣ በሸረኞች ምሕራባዊያንና በሆድ አደር ያረጁ ያፈጁ የአፍሪካ መሪዎች ኢትዮጵያን ሆን ተብሎ ወደ ባሰ የማትወጣበት መቀመቅ ለማግባት ያሴሩበት በመርዝ የተለወሰ ድርድር ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ከዚህ አልፎ አስገዳይና ገዳይ ለፍርድ ሳይቀርቡ ሕውሃትን ከትግራይ ሕዝብ ጋር ለማስታረቅና ብልፅግና ነብስ እንዲዘራ ለማድረግ በጓሮ በር ወልቃይትና እራያን ለማይገባው ፣ አግባብ ባልሆነና በማናለብኝነት አዙሪት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሆነውን የአማራን ፣ የአፋርንና የትግራይ  ወጣቶችን ፣ ገበሬዎችን ፣ ልጃገረዶችን ፣ አባቶችንና ሕፃናትን ካፋጅ በኋላ  የትግራይን ሕዝብ ለመካስ በሚል አስተውሎት የጎደለው አካሄድ ያለ ሕዝብ ይሁንታ ይህን የዘቀጠ እኩይ ውሳኔ ለመፈፀምና ለመወሰን መሞከሩ ከድጡ ወደ ማጡ እንደሚያስገባ ብልፅግና ሊገነዘብ ይገባል እንላለን።

ስድስት ሚሊዮን የትግራይን ሕዝብ ማሸነፍ የተሳነው ብልፅግና አምሳ አምስት ሚልዮን የአማራን ሕዝብ፣ ከ25 ሚሊዮን በላይ የሚገመተውን የሌላውን ሃገር ወዳድና ቀና ኢትዮጵያዊ ጦር ሰብቆ ለመውጋት መሞከር “ጥንቸል ከዝሆን “ ጋር ለመግጠም እንደሞከረችው ማለት ስለሆነ አወዳደቃችሁን አሳምሩ ፣ በእናንተ ላይ ሕዝብ የሚሰጠው ፍርድ አስከፊና የመጨረሻውን የውርደት ጥግ እንደምትከናነቡ ከወዲሁ ልንነግራችሁ እንወዳለን።

በመጨረሻም ወልቃይትና እራያን የግማሽ ሚሊዮን የትግራይን ሕዝብ እልቂት ለመካስ በመሞከርና የትግራይ ሕዝብ ይቅር ይለኛል በሚል “ ቀቢፀ ተስፋ “ እንቶ ፈንቶ የሆነ ውሳኔ ለማድረግ መሞከር ትርፉ ኪሳራና “ የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም” እንዲሉ አተርፍ ባይ አጉዳይ እዳትሆኑ በአፅንሆት እንመክራለን።

 

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop