የሰላም ስምምነቱና ሰላምን የመገንባት ተግዳሮች ከምርምር ጥናቶችና ከልምድ ስነጽሑፎች ስልታዊ ቅኝት

December 25, 2022
97 mins read
313974159 3008290862797145 7073638281151725210 n

313974159 3008290862797145 7073638281151725210 nበዶክተር ሰዒድ ሃሰን እና በአቶ አንዱ ዓለም ተፈራ

፩. መግቢያ 

በአገራችን በኢትዮጵያ፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት አለመረጋጋትና ግጭቶች ጎልተው ታይተዋል። በቅርብ ጊዜ አገራችንን ከፍተኛ አደጋ ላይ የጣለ አስከፊ የርስ በርስ ጦርነት ተካሂዷል። አሁን በፊታችን የምናየው፤ ይሄንን የርስ በርስ ጦርነት ለመግታት የተደረገ የሰላም ስምምነት ሂደት ነው። ይሄንን የሰላም ስምምነት ሂደት መላ ኢትዮጵያዊያን እጃችንን ዘርግተን የምንቀበለው ነው። በዚህ የሰላም ስምምነት ሂደት ዙሪያ፤ የሰላሙ መደፍረስ መሠረታዊ ምክንያቶች፣ የሰላም ስምምነቱ ሂደትና የሰላም ስምምነቱ እንዳይሳካ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉትን በትክክል መረዳት አስፈላጊ ነው። ሰላም ማለት የጦርነት አለመኖር ብቻ አይደለም። ይህ አንጻራዊ ሰላም ነው። ሰላም በጥቅሉ፤ ለጦርነት መንስዔ ሊሆኑ የሚችሉ ረመጦችና አቀጣጣዮቻቸው አለመኖራቸው ነው። በዚህ በአገራችን በተደረገው የርስ በርስ ጦርነት በዋናነት የተሰለፉት፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር እና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት ናቸው። የርስ በርስ ጦርነቶች፤ አስቀያሚ፣ ዘግናኝና የተንዛዙ ሆነው፤ መጠነ ሰፊ ሁከት የሚፈጥሩ፣ የሰዎች ሕይወት የሚቀጠፍበት፣ እና አስከፊ ውድመት የሚከተልባቸው ናቸው። በተጨማሪ፤ እንደ ተላላፊ በሽታ፤ ወደ ጎረቤት አገሮች የመዛመት ዕድላቸው ሰፊ ነው።

በሌሎች አገሮች እንደ ተከናወኑት የርስ በርስ ጦርነቶች ሁሉ፤ የአሁኑ የኢትዮጵያዊያን የርስ በርስ ጦርነትም፤ ብዙኀንን ለዕልቂት ዳርጓል። ይህ ብቻ ሳይሆን፤ ግዙፍ የሆነ የምጣኔ ሀብት ውድመት አድርሷል። የሰብዓዊ መብቶች ተጥሰውበታል። በሰዎች ላይ ግፍና በደል ተፈጽመውበታል። ብዙዎች ተፈናቅለዋል። ከለጋ ሕጻናት እስከ አዛውንት ድረስ መደፈርና ፆታ ተኮር ጥቃቶች ደርሷል። ቤተሰብ፣ መንደርና የአካባቢ ኅብረተሰብ ተበታትነዋል። የአየር ንብረት ብልሽቱ በጣም አሽቆልቁሎ ወርዷል። የኅብረተሰብ መጠቀሚያ አገልግሎቶች ተጓድለዋል (የሕክምናና የትምህርት ስርዓትን ጨምሮ)። የምግብ ማምረቻ መዋቅሮች ከስመዋል። ሰላማዊውን ኅብረተሰብ አቅፎ የያዘው ማሰሪያ ዕሴትም እንዳልሆነ ሆኗል። ኢትዮጵያዊያን እና ቀሪው ዓለም፤ ለዚህ እና ከዚህ ጋር ለሚመሳሰሉ ግጭቶች፤ ባጠቃላይም ለነዚህ አፍራሽ ጦርነቶች ፍጻሜ መፈለግ አለባቸው። በብዙ ሰዎችና የአገር መሪዎች ጥረት፤ በአሁኑ ሰዓት ከፊታችን የተጋረጠውን የርስ በርስ ጦርነት የሚገታ ስምምነት ተቀምጧል። ለዚህ ይረዳ ዘንድ፤ ይህ ጽሑፍ፤ በሌሎች አገሮች የተደረጉ የርስ በርስ ጦርነቶችንና የደረሱባቸውን የሰላም ስምምነቶች በማጣቀስ፤ ይሄን የተደረሰበትን የሰላም ስምምነት ሂደት ሊያስተጓጉሉ የሚችሉ አደናቃፊዎችን በመመልከት፤ እኒህን ለማስወገድ መደረግ ያለባቸውን ጥረቶች ይጠቁማል። አሁን በተጨባጭ የምናውቀው፤ ተፋላሚዎቹ ጦርነት አቁመው፣ በሰላም መንገድ መፍትሔ ለማስገኘት መስማማታቸውን ነው። ይህ የመጀመሪያው እርምጃ ሲሆን፤ ይሄን የተደረሰበትን ስምምነት በተግባር ማዋሉ ቀላል አይደለም። ሆኖም ግን፤ የጉዳዩ ባለቤቶችና ይሄ ጉዳይ እኔንም ያገባኛል የምንል በሙሉ፤ ኃላፊነቱን ተቀብለን ጥረት በማድረግ፤ ግብ ይመታል ብለን እናምናለን።

. የርስ በርስ ጦርነቶችና የተደረጉ ስምምነቶችን እንመለከት፤ ከመስኩ ስነ ጽሑፎችና ልምዶች ጨረፍታ

ሀ. የርስ በርስ ግጭቶች፤ በመንግሥታት መካከል ከሚደረጉ ጦርነቶች በተለዬ፤ በስምምነት የሚጠናቀቁት በጣም ጥቂቶቹ ናቸው። የርስ በርስ ጦርነት ስምምነቶች አስቸጋሪ ከሚሆኑበት ምክንያቶች ከፊሎቹ፤

ሀ1. የተደራዳሪዎች መካከል የጉልበት አለመመጣጠን መኖሩ፤

ሀ2. ጦርነቱ ቢቀጥል አቸናፊው ወገን የበላይነት ማግኘቱና ይሄ ለሌላው ስጋት መፍጠሩ፤

ሀ3. በጋራ ሊስማሙባቸው የሚችሉ ጉዳዮች ማጠራቸው፤

እኒህ ተደራዳሪዎችን ስምምነት ላይ ለመድረስ ችግር ይፈጥራሉ። ለምሳሌ፤ በአንድ አገር፤ አንድ መንግሥትና አንድ የጦር ሠራዊት ብቻ ነውና ሊኖር የሚችለው፤ ይሄን ሀቅ ሁሉም ከተቀበለ፤ ያመጸው ወገን ትጥቁን መፍታት ይኖርበታል። ሌላው ደግሞ፤ በመካከላቸው የማይታረቁ ልዩነቶች መኖራቸው ነው። ድርድሩን ለማጠናቀቅ፤ አስቸጋሪ የሆነ የመሥጠትና የመቀበል ግዴታ በሁለቱም ወገን አለ። በመሥጠቱ በኩል ተዋጊዎች ትጥቅን መፍታትና ማስረከብ ይኖርባቸዋል። ይሄን ከማድረግና ከመተባበር ይልቅ፤ ሽውዶ የመጠቀሙን ግኝት ሊያመዛዝኑ ይችላሉ። በሌላው በኩል ደግሞ መንግሥት የአማፂያንን ሙሉ መብት ተቀብሎ ማስተናገድ አለ። ከዚህ ይልቅ ለመበቀል ጉልበትን መጠቀም ማሰብ ይኖራል። እናም ይሄን ሁሉ ለማስተካከል በሰላም ስምምነት ሂደቱና በአፈጻጸሙ ወቅት ሶስተኛ አካል መሳተፉ ግድ ይሆናል።

ለ. በመንግሥታት መካከል የሚደረጉ ጦርነቶች፤ በአብዛኛው ግልጽ በሆነ የስምምነት ውሎች ይጠናቀቃሉ። የርስ በርስ ጦርነቶች ግን ይሄን አያደርጉም።

ሐ. የርስ በርስ ጦርነቶችን ስንመለከት፤ ሁለት ዓይነት የርስ በርስ ጦርነቶች አሉ። የመጀመሪያዎቹ ርዕዮተ-ዓለምን መሠረት ያደረጉ ሲሆኑ፤ ሌሎቹ ደግሞ ዘውግን መሠረት (ethnic based) ያደረጉ ናቸው።

ሐ1. ዘውግን መሠረት (ethnic based) ያደረጉ ጦርነቶችን መፍታት የተወሳሰበና ክትትሉ አስቸጋሪ የሆነ ነው። ለዚህም ዋናው ምክንያት፤ ወዲያና ወዲህ ሆነው የማይገናኙ አካላት መሆናቸው፤ የየራሳቸው የዘውግ  (ethnic) የኔ ባይነቶቻቸው ገትረው ስለሚይዟቸው (በተፈጥሯቸው ሠጥቶ መቀበልን የኔ የማይሉ፤ ከልብ የሚመነጩ ስሜቶችና ዕሴት-ተኮር ግጭቶች)፣ የምጣኔ ሀብት ስምሪት፣ እና በመደብ የተመሠረተ ክፍፍል፣ ፖለቲካዊ (ርዕዮተ-ዓለማዊ)  አለመግባባቶች – ባህል፣ መደብና በዘውግ ላይ (ethnic) ያተኮሩ ግጭቶች።

ሐ2. ዘውግ (ethnic) ተኮር ግጭቶችን በተመለከተ፤ ባለሙያዎችና ልምዱ ያላቸው ባጠቃላይ፤ ራስን በራስ የማስተዳደርን ወይንም የመገንጠልን ሃሳብ እንደመፍትሔ ያቀርባሉ።

ሐ3. የርዕዩተ-ዓለም ተኮር ጦርነቶችን ለመፍታት፤ የሥልጣን መጋራትንና መንግሥታዊ መዋቅሮችን ወደ በለጠ ዴሞክራሲያዊ አሰራር መምራት፣ ተመጣጣኝ የቁሳቁስ ምንጭ ክፍፍል ማድረግና ተጠያቂነትን በቦታው ማስቀመጥ ዋናዎቹ ሃሳቦች ናቸው።

መ. አብዛኞቹ አመጾች፣ በተለይም በማደግ ላይ ባሉ አገሮች የሚነሱት፤ የዘውግ (ethnic) ወይንም የሃይማኖት ገፅታ ያላቸው ናቸው።

ሠ. አብዛኛዎቹ የአገር ውስጥ የርስ በርስ ጦርነቶች የተጠናቀቁት፤ ተቸናፊውን ክፍል በማጥፋት፣ በመደምሰስ፣ ወይንም በቁጥጥር ሥር በማዋል ነው። በወታደራዊ ኃይል በቀጥታ በማውደም የሚጠናቀቁ ጦርነቶች፤ በድርድር የሚደረጉ ስምምነቶች ከሚያመጧቸው የበለጠ የተረጋጋ ሁኔታን ይፈጥራሉ።

ሰ. ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ፤ የቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን (Cold-War era) ተብሎ በሚታወቀው ጊዜ በነበሩት ጦርነቶችና ከዚያ በኋላ በመጡ ጦርነቶች መካከል የጎላ ልዩነት አለ። በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን የተደረጉ ጦርነቶች ከዚያ በኋላ ከተደረጉ ጦርነቶች አኳያ ሲመረመሩ፤ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው በስምምነት የተጠናቀቁት። ለዚህ ምክንያቱ፤ ዩናይትድ ስቴትስና ግብረ-አበሮቿ በአንድ በኩል፤ ሶቪየት ኅብረትና ግብረ-አበሮቿ በሌላ በኩል በመሆን፤ የርስ በርስና በመንግሥታት መካከል የሚደረጉ ጦርነቶችን፤ ከተፋላሚ ወገኖች ግራና ቀኝ በመቆም፤ ለሚደግፏቸው ወገኖች የቁሳቁስ ድጋፍ በማበርከት፤ አቸናፊ እንዲሆኑላቸው በማበረታታቸው ነው። ይሄ እየቀዘቀዘ የመጣው፤ ከሞላ ጎደል በኒህ ልዕለ-ኃያላን አገራት መካከል ጦርነቱን ለማቆም ስምምነት በመደረጉ ነው። በርዕዮተ-ዓለም ላይ የተመሠረቱ ጦርነቶች በፍጥነት ያቆሙበት ከፊል ምክንያት፤ በልዕለ-ኃያላኑ መካከል ያለው የርዕዮተ-ዓለም ልዩነት አነስተኛ በመሆኑ፤ ወይንም ጦርነቶቹ “ለሚጋሯቸው” የዓለም አቀፍ ደህንነት እንዳያስጋ ሲሉ ነው። በአብዛኛው በዚህ ዙሪያ ያሉ ጦርነቶቹ የሚቆሙት፤ በተባበሩት መንግስታት በኩል ነው።

ሸ. የርስ በርስ ጦርነቶች፤ በመንግሥታት መካከል የሚደረጉ ጦርነቶች ከሚያደርሱት ውድመቶችና ከሚያስከትሏቸው ግፍና በደሎች እጅግ የበዙና እንዲሁም ደግሞ ለማረጋጋትና ለመጨረስ ረጅም ጊዜ የሚወስዱ ናቸው፤ ለዚያውም ካለቁ ነው!

ቀ. በርስ በርስ ጦርነቶች የተሰለፉትን ማደራደርና ለስምምነት አብቅቶ ውጤታማ ማድረግ አስቸጋሪ ነው። በቁጥር አነስተኛ የሆኑ ድርድሮች ናቸው ለመፈራረም የሚበቁት። ቢፈራረሙም ቢሆን የመተግበር ዕድላቸው አስተማማኝ አይደለም። ለመተግበር ቢጀመሩም እንኳን፤ ሳይሳኩ የመቅረታቸው ሀቅ ከፍ ያለ ነው። ለኒህ ዋና ምክንያት ሆነው የሚቀርቡት፤ ተፋላሚዎቹ ለመወያየት ቢስማሙም፤ ስምምነቱን ከግቡ ለማድረስ የሚኖረው ትብብርና ተረጋጋጭነቱ ችግር ስላለበት ነው።

በ. ለትዝብቱ፤ አንዱ ወገን በወታደራዊ ጉልበት የሚያቸንፍባቸው የርስ በርስ ጦርነቶች ጥቂት ጊዜ ነው የሚጠይቁት። የሚከተለውም የሰው ሕይወትና የንብረት ጥፋት አነስተኛ ነው። እናም ለምን ብለው ወደ ሰላም ድርድሩ ያምሩ!

ተ. ለጦርነቱ የሚደረገው የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት መባከን ከፍተኛ ሆኖ ካልጎዳቸው በስተቀር፤ የርስ በርስ ጦርነቶች አይቆሙም።

ቸ. የፖለቲካ ሊቃውንት (political scientists) እና የኅብረተሰብ፣ የባሕልና የባሕል ዕድገት አጥኚዎች (anthropologists)፤ የርስ በርስ ጦርነቶችን የሚገፏቸው፤ ፖለቲካዊና የዘውግ (ethnic) ልዩነቶች ናቸው ብለው ያምናሉ። በሌላ በኩል ደግሞ፤ የምጣኔ ሀብት ሥርጭት ፅንሰ ሃሳብ መላ መቾች (economic theorists)፤ የግጭቶች መነሻ የምጣኔ ሀብት ሥርጭት ነው ሲሉ ያቀርባሉ። በኒህ ሊቆች እምነት፤ ግጭቶቹ በአብዛኛው፤ ለገበያ መቅረብ በሚችሉ የተፈጥሮ ቁሳቁሶች ባለቤትነት ዙሪያ ይገፋሉ። በተሳሳተ የመንግሥታዊ የምጣኔ ሀብት ሥርጭት መመሪያ ምክንያት በሚፈጠረው የገበያ ትርምስ የሚሰፋው ድኅነትም፤ ሌላው ምክንያት ነው። ይህ በአየር ጠባዩ መለዋወጥ ምክንያትም ይባባሳል።

፫. የሰላም ስምምነቶች ለምን ብዙ ጊዜ ይፈርሳሉ?

ሰላም ስምምነቱን በሥራ ላይ ከማዋልና ላሁኑም ሆነ ለወደፊቱ ከሚፈጠሩ አደናቃፊዎች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፤ (አደናቃፊ የሚሆኑ ችግሮችን በሚመለከት ጠቃሚና ዝርዝር ምርመራዎችን ለማግኘት፤ የሰላም አደናቃፊዎች ይመልከቱ።)  በአገራችን ለተከሰተው የርስ በርስ ጦርነት መንስዔው ናቸው የሚባሉትን ማጥናቱ ተገቢ ነው። ትሕነግ በአገሪቱ ላይ ያስቀመጠው ሕገ መንግሥት ምን ያህል ለዚህ ጦርነት መቀስቀስ አስተዋፅዖ አድርጓል? የየክልሎች መንግሥታት መጠንከር ማዕከላዊ መንግሥቱን አዳክሞታል ወይ? እኒህ የክልል መንግሥታት የየራሳቸው የየክልል ኃይሎች እንዲኖራቸው መደረጉ ምን ያህል አስተዋፅዖ አድርጓል? በማዕከላዊ መንግሥቱና በክልል አስተዳዳሪዎች መካከል ያለው መዋቅር ዝርዝሩ ምን ያህል ለዚህ ጦርነት አስተዋፅዖ አድርጓል? የራሳቸው የክልሎች መኖርና አሁን ባሉበት መቀጠል ምን  አስተዋፅዖ አለው? ትሕነግ ለዚህ ዝግጅት ሲያደርግ ማዕከላዊ መንግሥቱ ምን ያህል ዝግጅት ነበረው? ብዙ ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎች አሉ። እኒህን መመልከት ይገባል። ስምምነቱን በሚመለከት ዋናና የመፍትሔዎቹ ሁሉ መሥረት፤ ለሚደረስበት ስምምነት በሁሉም ወገን ያለው ተቀባይነትና ወገኖቹ ያላቸው ቁርጠንነት ነው። ሙሉ ለሙሉ ቁርጠኛ ሆነ መቀበላቸው ብቻ ነው አሰማማኝ በሆነ መንገድ ስምምነቱን ሊያሳካው የሚችለው።

ደናቃፊ ጉዳዮች – ውስጥ በኩል (ከተፋላሚ አካሎች ጋር የተያያዙ)

ሀ. ገዥው ፓርቲ ወገን፤ 

 1. በስምምነቱ ለሚደረስበት ውጤት የቁርጠኝነት ዕጥረት፤ለስምምነቱ የባለቤትነትና የተገዥነት ችግሮች -እያንዳንዱ ወገን ራሱን በአቸናፊነት የሚያስቀምጥ ውጤት መፈለጉ፣ ሰላም እንዲገኝ፤ በሁሉም ወገን ሠጥቶ መቀበል መኖሩን ያለመረዳት
 2. አቅል ማጣት (ለወደፊቱ አስጊ የሆነ) የሰላም ስምምነት ሂደት ጊዜ የሚወስድና አዝጋሚ ጉዞ መሆኑን ያለመረዳት
 3. የሰላም እንቅፋቶችን መቆጣጠር አለመቻል፤(ኒውማን እና ሪችመንድ፤ሪችማንድ ይመልከቱ) እና የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የሰላም ስምምነቱን ለማደናቀፍ የሚጥሩ የስምምነቶች ተሳታፊዎች
 4. በሌላው ወገን ያሉ ተሳታፊ መሪዎችን ወይንም ሙሉ ሥልጣን (የወደፊት አዘናጊ ነጥብ) የፈለጉትን ስጋት፤ በበቂ ለማረጋጋት አለመጣር (ለወደፊት አስጊ የሆነ)፤ እናም ሥልጣን ከማጋራት መቆጠብ ወይንም ለሚያነሷቸው ቅሬታዎች ቦታ አለመሥጠት፣ የዜና ማሠራጨቱን በተመለከተ፤ የተለያየ አቅም ኖሯቸው በእኩል ዜናቸውን ማሰማት አለመቻላቸው (ዝርዝሩን በ  ማቴዝስ እና ሳቩንላይ ይመለከቱ)
 5. ለትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ በይቅርታ ሂደቱ ካቀረባቸው መስማሚያዎች መካከል የተወሰኑ እንኳን ማግኘቱ፤ ሌሎች ቡድኖች ተመሳሳይ ጠቀሜታዎችን ለማግኘት፤ ይሄንን መንገድ እንዲከተሉ ይገፋፋቸው ይሆናል! የሚለው ስጋት
 6. የሰላሙን ጉዳይ በተመለከተ፤ በፌዴራልና በክልል ደረጃ ያሉትን አለመግባባቶች ጭምር፤ በራስ ፓርቲ ውስጥ፤ ውስጣዊ ግጭቶችን መቆጣጠር አለመቻል
 7. በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከደረሰው ከፍተኛ ውድመት አንጻር፤ የባከነ ንብረት ወይንም ሊመለስ የማይችል ወጪ (አናቂ ወጥመድ ሆኖ) የተሳሳተ ውሳኔ ማድረግን አስከትሏል። እስካሁን የፈሰሰው ደምና የወደመው ንብረት፤ ግጭቱን ወደፊት ለማስቀጠል ምክንያት መሆን የለበትም።

ለ. ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መሪዎች

 1. 1. በድርድር የሚደረስበት ስምምነት፤ በሁለቱም ወገኖች በኩል መሥጠትም ማጣትም መኖሩን አለመረዳት
 2. 2. የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ለምሳሌ በማጓተት፣ በማደናቀፍ፣ ሽብርንና ግድያዎችን በመጠቀም የሰላም ስምምነቱን አደናቃፊዎች መቆጣጠር አለመቻል (ለዝርዝሩ ኒውማን እና ሪችመንድን ይመልከቱ)። ይሄ የሰላም ግንባታውን ለሥልጣን ቦታቸው ያስጋናል ብለው የሚያስቡ የጦር አለቆችን፣ ሹሞችን፣ ወይንም ተሰሚ የበላዮችን ይመለከታል። በራሳቸው ወገን መካከል (በራስ ፓርቲ) የሚነሱ አለመግባባቶችን፣ የሰላም ስምምነቱን የሚቃወሙ ቀንደኛ አባላት፣ ክፍል መሪዎች፣ በውጪ አገራት የሚኖሩ ደጋፊ አባሎቻቸው፤ ሁከትን በመጠቀም ስምምነቱን ለማክሸፍ የሚያደርጉትን ጥረት መግታት አለመቻል
 3. ተፋላሚዎቹ ሰላምን ለማምጣት የሚደረገውን ሂደት፤ መልሰው ለመሰባሰብና የበለጠ ለመታጠቅ የጊዜ መግዢያ አድርገው መውሰድ
 4. በሰላም ስምምነቱ ለሚደረስበት ውጤት የቁርጠኝነት ዕጥረት፤ ለስምምነቱ ባለቤት የመሆንና ተገዥ የመሆን ተግዳሮች – እያንዳንዱ ወገን ራሱን በአቸናፊነት የሚያስቀምጥ ውጤት መፈለግ፣ ሰላም በሁሉም ወገን መሥጠትም መቀበልም መኖሩን ያለመረዳት
 5. የሰላሙ ስምምነት ሲከሽፍ፤ ውጤቱ እንወክለዋለን በሚሉት ወገናቸው እና በራሳቸው ላይ የበለጠ  አስከፊ አደጋ እንደሚያስከትል አርቆ አስተዋይነት ማጣት (ምንም እንኳን ጦርነት የተሻለ መንገድና ክፍፍልን የሚያስወግድ፤ የሰላሙ መንገድ ደግሞ የፖለቲካ ቁጥጥርንና ጠፍርቆ መያዝን የሚሻ መስሎ ቢገኝም)
 6. 6. የጦርነቱን ተጠቃሚዎች ለይቶ አለማወቅ (በራሳቸው ድርጅት ውስጥም ወይንም ውጪ ቢሆኑ)፤ እኒህ፤ ጦርነቱ ቢቀጥል፣ ግጭቱ ቢስፋፋ፣ ሰላም ቢደፈርስና ኅብረተሰቡ ሰላም ቢያጣ፤ ጥቅማቸው ከጦርነቱ መካሄድ ጋር የተሳሰረ በመሆኑ፤ ግድ ሳይኖራቸው፤ የሰላም ስምምነቱ ሂደት እንዳይሳካ ይዘይዳሉ
 7. በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከደረሰው ከፍተኛ ውድመት አኳያ፤ የባከነው ንብረት፤ የተሳሳተ ውሳኔ ማድረግን አስከትሏል። እስካሁን የፈሰሰው ደምና የወደመው ንብረት፤ ግጭቱን ወደፊት ለማስቀጠል ምክንያት መሆን የለበትም።
 8. 8. ለጋ ወጣት ታጣቂዎችን መልምሎ ያሳተፈው ጣራ የነካው የጦርነቱ ወንጀለኝነት፤ ለጋ ወጣቶቹ ሰላምን ተቀብለው ለመኖር ችግር ስለሚገጥማቸው፤ ሥራ ማጣት፣ የመንገድ ተዳዳሪ መሆን፣ በውጊያው ጊዜ የነበራቸውን የማኅበራዊ ደረጃ ማጣትና ያልተረጋገጠ የወደፊት ኑሮን ከመጋፈጥ ይልቅ፤ ጦርነቱን መቀጠሉን ይመርጣሉ። (ሲስክን ይመለከቱ);

የሰላም ስምምነቶች እነዚህን በወቅቱ ሊጣሱ የሚችሉ ሁኔታዎች ዕውቅና የሚሠጡ ሆነው ሊዋቀሩ ይገባቸዋል። በተጨማሪ ደግሞ በአብዛኛው ጉዳይ፤ ለተጎዱ ወገኖች ፍትኅን ማስገኘት አለባቸው።

ሐ. ውጭ ወገኖች

 1. 1. ለስላም ስምምነቱ የመታረቅና ሠጥቶ የመቀበል እውነተኛ ፍላጎት የሌላቸው፣ የሚደረስበትን ዕርቅ በቁም ነገር ተግባራዊ ለማድረግ ውል የማይገቡ፣ በድርድሩን ሂደት ዕውቅናንና ሕጋዊነትን ለማግኘት፣ ጊዜ ለማግኘትና የቁሳቁስ ጥቅም ለማግኘት፣ ወይንም ማዕቀብ እንዳይጣልባቸው፣ እናም “የተሸፋፈነ አጀንዳ” ያላቸው ተብለው ሊገለጹ ይችላሉ። (ማጣቀሻውን ኒውማን አና ሪችመንድዘንድ ይመለከቱ)
 2. 2. የሕዝብ ዜና መለዋወጫዎችን በመጠቀምና የእንቶ ፈንቶ ወሬዎችን በመንተራስ በቀላሉ የገንዘብ ድጋፍን ወደ አገራቸው ለመላክ የሚችሉ፤ ከሰላም ስምምነቱ የተገለሉ አካላት ወይንም በውጪ አገር የሚኖሩ የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች።
 3. 3. በተመሳሳይ ጉዳዮች ትኩረታቸውን ያደረጉ ልዕለ-ኃያላንና ጣልቃ ገቦች፤ የሰላም ስምምነቶች ለስኬት የሚበቃው፤ ልዕለ ኃያላን ሲተባበሩ ነው። የወቅቱ የልዕለ-ኃያላን ተቃርኖ ወይንም የየግላቸው የጥቅም ጣልቃ ገብነት፤ ትልቅ ችግር ሊሆን ይችላል።
 4. 4. የውጪ ጣልቃ ገቢዎች፤ (ለግጭቱ ቀጥተኛ ወይንም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በመጠቀም) በግጭቱ መቀጠል ስለሚጠቀሙ፤ ይሄ ገንቢ የሆነ የሰላም ሂደቱን ያደናቅፈዋል።

መ. ከአስታራቂዎች (በመሐል ከሚገቡ አካላት) ሊኦከሰቱ የሚችሉ ስህተቶች

 1. ለግጭቶቹ መንስዔ የሆኑ ጉዳዮችን ወይንም ጦርነቱ እንዲካሄድ የተንተራሰባቸውን መሰረታዊ ብሶቶችአለመረዳት፤ ግለሰቦች ለሚደርሱበት አመፅን የመጠቀም ምርጫ እንዲወስዱ ያደረጋቸውን፤ የፖለቲካ፣ የምጣኔ ሀብት ሥርጭትና የኅብረተሰብ ዑደት በተገቢ አለመረዳት። በፖለቲካው ልሂቃን መካከል የሚደረግ የሥልጣን ሽኩቻ ብቻ ነው? በቁሳቁስ ምንጮች ባለቤትነት? በዘውጎች መካከል (inter-ethnic) ግጭት ነው? በውጪ ኃይሎች ቆስቋሽነትና ደጋፊነት የሚካሄድ ነው? ሌሎች ጥቅማቸው ስለተጋጨ መጠቀሚያ ያደረጉት ተዘዋዋሪ ጦርነት ነው? በየክልሉ የየራሳቸው የታጠቁ ኃይሎች፤ በፖለቲካ፣ በሃይማኖትና በርዕዩተ-ዓለም የተበከሉ የታጠቁ ኃይሎች መፈልፈል፤ ግጭቱን አራጋቢ ሆነዋል ወይ?
 2. ተፋላሚዎቹ በተሳሳተ መንገድ አዝማሚያዎችን እና ገፊ ምክንያቶችን በመረዳት፤ ምናልባትም በቀና መንገድ ሁሉን ነገር ካለማየት አኳያ
 3. ወገን አፍቃሪነትና አድሏዊነት (በርግጥ በዚህ ላይ ሁለት አመለካከቶች ይቀነቀናሉ!) ለሰላም ስምምነቱ በስኬት መጠናቀቅ፤ በሸምጋዩ ወገን ዕምነትን መጣል በጣም ወሳኝ ነው
 4. የጉዳዮችን መነሻ ምክንያቶች አለመረዳትና በትክክል ተረድቶ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው አለመጣር
 5. በቂ ያልሆነ ወይም ተገቢ ያልሆነ እጅ መንሻ መሥጠት ወይንም ማስገደድ (ካሮትና አለንጋ) በሁለቱም ተፋላሚዎችና አደናቃፊዎች፤ ለምሳሌ ደጋፊዎቻቸውናአጎራባች አገሮች ላይ ያለመጠቀም
 6. ወደፊት ቀጣይ ጦርነት የመከተሉን ዕድል ለማሳነስ፤ በቂ የሆነ ፍርሃትን የሚቀንሱና ዋጋ የሚያስከፍሉ ድንጋጌዎችን በስምምነቱ ላይ አለመጨመር። በተደራዳሪዎች መካከል ፍርሃትን የሚያሳንሱ ድንጋጌዎች፤ የጋራ ደህንነት እንዲኖር አስተማማኝ ናቸው። ዋጋው እየናረ እንዲሄድ የሚያደርጉ ድንጋጌዎች፤ ማንኛቸውም ወገን ተመልሰው ወደ ጦርነት የመግባቱን ጉዳይ እና ዕዳ ከፍ ያደርግባቸዋል።
 7. “በሰላም ስምምነቱ ተሳታፊ ዕጩዎች ዘንድ፤ የብቃት ጉድለት፣ ወልዋይነት፣ መጨቃጨቆች” አደናቃፊዎችን ለመቋቋም የተቀናጁ ስልቶች አለመኖር
 8. ግልፅ ያልሆነ የሰላም ስምምነት ውል፤
 9. አስጊ የሆኑ የሰላም ስምምነቱን አደፍራሽ አካላትን መጨመር፤ እና የሰላም ስምምነቱን የሚፈልጉ አካላትን፤ በተለይም የሰላም ስምምነቱን የማጽደቅና የመሻር መብት ያላቸውን አለመጨመር
 10. አደናቃፊዎች ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ግምት በማስገባት የስምምነት ውሉን አለማዘጋጀት

፬. ቡ ማገርሸት ደካማ የሆኑ ጎኖች፤ በኢትዮጵያው ሁኔታ እውነት ሊሆኑ የሚችሉ የተጠናቀሩ ሀቆች  

 1. የንብረት ምንጭ ማጠር፤

ሀ. ድህነት ዋናው ጉዳይ ነው። የግለሰቦችን ድህነት በተመለከተ፤

ሀ1. ድህነት በሕዝቡ መካከል ተስፋ ማጣትንና ጨለምተኝነትን ፈጥሮ፤ በአገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋትን ያስከትላል።

ሀ2. ድህነት ግለሰቦች ስለወደፊታቸው ከማሰብ ይልቅ፤ ዛሬን ውሎ ለማደር የሚያስችላቸውን ማንኛውንም መንገድ እንዲመርጡ ይመራቸዋል።

ሀ3. ድህነት ጦርነት የማካሄጃን ዋጋ የመናር ዕድል ይቀንሳል፤ እናም የሰላም እንቅፋቶች የሆኑት ተዋጊዎችን በቀላሉ መመልመል ያስችላቸዋል።

ለ. የአገራችንን የንብረት አቅም በተመለከተ፤

ለ1. ኢትዮጵያ፤ የቀድሞ ታጣቂ አባላትን ካሉበት ሁኔታ አውጥቶ በሰላም ኅብረተሰቡን እንዲቀላቀሉ ማድረግ የሚያችል በቂ የንብረት አቅም አላት ወይ? ይህ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ አባላትን፣ የአማራ ፋኖዎችን፣ አና የአፋር ታጋዮችን ያካትታል።

ለ2. ኢትዮጵያ፤ የተፈናቀሉትን መልሶ ማቋቋሚያ፣ በአገር ውስጥ የተበታተኑትን ሰብስቦ ወደነበሩበት እንዲመለሱና ኑሯቸውን እንዲገነቡ መርጃ፤ አቅም አላት ወይ?

ለ3. ኢትዮጵያ፤ የኅብረተሰቡን መረጋጋት እና የአገሪቱን የምጣኔ ሀብት ግንባታዎችን ለማከናወን አቅም አላት ወይ?

ሐ. በአገራችን ያለው የሕዝብ ቁጥር ከፍ እያለ መሄዱ አንዱ አስተዋፅዖ አድራጊ ነው።

መ. አገራችን ዝቅ ያለ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ደረጃ ላይ መሆኗ ሌላው ጉዳይ ነው።

ሠ. ቀደም ያለ የርስ በርስ ጦርነት ታሪካችን አስተዋፅዖ አለው።

ረ. በአገራችን የፖለቲካ አለመረጋጋት መኖሩ አስተዋፅዖ አለው።

ሰ. በጉዳዩ አቅላቸው የገነፈለ በውጪ ያሉ አባላትና ደጋፊዎች ጎጂ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ።

ሸ. በአንድ አገር ውስጥ የፖለቲካ ስርዓቱ ሲዳከም፤ ወይንም የአገዛዝ ስርዓቱ በቂ ሕዝባዊ ድጋፍ ሲያጣ

ሸ1. በሕዝቡ ውስጥ አለመርካትን ይፈጥራል። ይህ ደግሞ በበኩሉ አለመረጋጋትን አስከትሎ ግጭቶችን ይጋብዛል።

ሸ2. የውጪ ኃይሎች ወይንም ወዳጅ ያልሆኑ የጎረቤት አገሮች፤ ይሄን ሁኔታ ከራሳቸው ጉልበትና ደህንነት አንጻር አመዛዝነው፤ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

ጉዳዩ የሚታየው የአስተዳደር ሥርዓት ሲዳከም ወይም የአንድ አገር የፖለቲካ ሥርዓት ሲዳከም ይህ ዓይነቱ ሁኔታ በዜጎች መካከል እርካታን እንዲፈጥርና ግጭት እንዲፈጠር ሊያደርግ ብቻ ሳይሆን የውጭ ኃይሎችና ወዳጅ ያልሆኑ ጎረቤቶችም ሁኔታውን ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ያንን አለመረጋጋት የሚመለከቱት በራሳቸው ስልጣን እና ደህንነት ፍላጎት ነው።

 1. በዘውጎች መካከል ልዩነቶች (ethnic cleavages) እናየዘውግ (ethnic) ገፅታ ያላቸው ግጭቶች

ግጭቱ በርዕዩተ ዓለም ሳይሆን በዘውግ ላይ የተመሠረተ ነው። (ይሄን በሚመለከት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ዳውንስ ን ይመልከቱ) የመስኩ ስነ ጽሑፍ፤ በዘውግና በደንበር የተነሱ ግጭቶችን ለሰላም ስምምነት ማብቃት አስቸጋሪ እንደሆነ ይጠቁማል። በስምምነት ከሚጠናቀቁት ሁለት ሶስተኛዎቹ ተመልሰው ያገረሻሉ። በመስኩ ጥናት በተሰለፉና መመሪያ አውጪ በሆኑ አካላት ዙርያ፤ በዘውግ የሚነሱ ጦርነቶችን ለማቆም ከሁሉም የተሻለ ተብሎ ተቀባይነት ያገኘው ግንዛቤ እንዲህ ነው። እንገንጠል ብለው ለተነሱ፤ የአካባቢ የራስ አገዛዝ እንዲያገኙ በማድረግ፤ የሥልጣን ጥያቄ አንስተው መንግሥቱን ለመቆጣጠር ያፈነገጡትን ሥልጣን በማጋራት ይላሉ ( ዳውንስ2007፡1)።

 1. ተጠያቂነት (ተጠያቂ መሆንን መፍራት) ለውጥረት ምንጭ የሚሆን የሰብአዊ መብት ረገጣ
 2. አለመተማመን ( በግጭቱ ውስጥ ያሉት ባህሪያቸው) የትሕነግያም ይጥፋ ይህም ይጥፋ አስተሳሰብን የማጭበርበር፣ የመሸወድ፣ የእማታለል፣ የተንኮለኝነትና አልጨበጥ ባይነት ታሪኩ፤ ሰላምን ለመፍጠር፤ የታወቁና ግልጽ መሪዎች ያላቸውና አንጻራዊም ቢሆን ቋሚ የሆነ አቋም ያላቸው ለሰላም የቀረቡ አካላትን ግድ ይላል
 3. የኃላፊነት መስክ ክልል፤

5ሀ. የበወታደራዊ ጉዳዮች እና ትጥቅን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ፤ የፌዴራሉ መንግሥት ነው ወይ ሙሉ ባለሥልጣን የሆነው

5ለ. ለመሬት ይዞታን በተመለከተ ባለቤቱ ማነው? ለምሳሌ ወልቃይን እና ራያን በመሳሰሉት

 1. ጦርነት ጥቅም ይገኝበታል፤ ጦርነት በቦታው ለተሰማሩ ተዋጊዎች በተለይም በዲያስፖራ ላሉ ሰዎች በጣም ትርፋማ ሊሆን ይችላል።
 2. በዘውግ ላይ የተመሠረተው ሕገ መንግሥት አንድም ለግጭቶች መነስዔ መሆኑ አለዚያም ግጭቶችን ቀስቃሽ መሆኑ
 3. እያንዳንዱ ክልላዊ መንግስት የራሱ የሆነ ቋሚ ሰራዊት ያለው መሆኑ፤ ለምሳሌ ለዘላቂ ሰላም እንቅፋት ሆኖ ማገልገሉ
 4. የሰላም ስምምነቱ ጊዜ የሚፈጅ በመሆኑ፤ በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነቱ ስለሚያንስ የሚያስከትለው ቅሬታ
 5. የመንግስት የሁሉ የበላይነትና ስር የሰደደ ሙስና በተጨማሪም የፖለቲካ ተቋማት ደካማነት ብስጭቱንማባባሳቸው
 6. የሁለት ተቃራኒ ጥጎች መፈጠርና ከልዕለ ኃያላኑ በታች የመሐል ኃያላን መስፋፋት (እንደ ቱርክ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ ህንድ፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታንያ ወዘተ ያሉ) እያንዳንዳቸው ለየራሳቸው ተጽዕኖ መጫኛ መፈለኛይሄ ደግሞ በተደራዳሪዎች ላይ ልዩነታቸውን አጉልቶ፣ ለሶስተኛ አስታራቂ ችግር ፈጥሮ ግጭቶችን ለመቆጣጠር ማስቸገሩ

. አሁኑ የሰላም ስምምነት አበረታች ምልክቶች እና ባህሪያት  

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አሕመድና በአቶ ጌታቸው ረዳ በሠጧቸው መግለጫዎች መሠረት፤ “ለሰላም  የሁኔታው አመቺነት” ወይንም “ጎጂ የሆነ መፋጠጥ” ላይ መሆናቸውን ሁለቱም ወገኖች አምነው፤ ጦርነቱን መቀጠሉ በጣም አክሳሪና  ግባቸውን ለማሳካት ሊረዳቸው የማይችል መሆኑን መገንዘባቸውን ነው። እናም በሰላም ስምምነቱ የበለጠ ሊጠቀሙ መፈለጋቸውን (የሰላም ስምምነቱን ሕዝቡ ከመቀበሉ በተጨማሪ) አስታውቀዋል።

 1. ከተፋላሚዎቹ መካከልአንዱ አቸናፊ ሆኖ ወጥቷል፤ ማለትም የፌዴራል መንግሥቱ። ይሄን የመሰለ አንዱ አቸናፊ ሆኖ የሚወጣበት ውጤት፤ ከሌለው አቸናፊው ካልለየለት የድርድር ስምምነት የበለጠ የተረጋጋ እንደሚሆን ይታወቃል።
 2. የፖለቲካ፣ ወታደራዊ እና የክልል ጉዳይ በግልጥ በስምምነቱ ላይ ተዘርዝረው መስፈራቸው
 3. 3. ማናቸውም ወገን፤ አንዱ ሌላውን ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን አለመፈለጉ፣ ሙሉ ሥልጣኑን ለብቻው ወስዶ ሁሉን መቆጣጠሩን አለመሻቱ፣ በአገሪቱ ሙሉ የአገር ጥፋትና የፖለቲካውን፣ የምጣኔ ሀብት ሥርጭቱን፣ የኅብረተሰብ ሥርዓቱን በነውጥ ለመለወጥ አለመፈለጉ፤ ይሄን የመሰለው ሁለቱን ወገኖች የድርድር ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ያመቻችላቸዋል
 4. ባጠቃላይ ሕዝቡ የሰላም ስምምነቱን ውል መቀበሉ፤ በተለያዩ የዜና ማሠራጫ ተቋማት እንዳመለከቱት የትግራይ ሕዝብን ጨምሮ
 5. የአንዳንድ ጎረቤት አገራት ፈቃደኝነት፤ በተለይም ሱዳን፤ የሰላም አደናቃፊዎችን ማገዷ እና/ወይንም ለውክልና ጦርነት ተካፋይነትን መንፈጓ
 6. በቀላሉ ለገበያ የሚውሉ እንደ ወርቅ፣ አልማዝ፣ ዘይት፣ ማዕድንና የጣውላ እንጨት ያሉ ሸቀጣ ሸቀጦች አለመኖራቸው፤ እናም ግጭቱን ከስግብግብነት ይልቅ የግጭቱን መንስዔ ባብላጫው የተጎጅነት ያደርጉታል
 7. 7. ግጭቱን ለማሸማገልናለመፍታት በዓለምአቀፍ ተሳታፊዎች ያለው ከፍተኛ አንጻራዊ ፍላጎት። ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ ተሳታፊዎች (ልዕለ-ኃያላን) የኢትዮጵያን ግጭት በተመለከተአንድነት ባይኖራቸውም፤ ግጭቱን በመፍታት ደረጃ ልዩነት አይታይባቸውም። በኢትዮጵያ ጉዳይ፤ አሜሪካ ብቻ ነች በድርድሩ በጥልቅ የተሳተፈችው። ሌሎች ልዕለ-ኃያላን አገሮች እሷ ብቻዋን እንዳደረገች ታድርገው ብለው እጆቻቸውን አጣጥፈው ግጭቱ ብቻ ይቁም ብለዋል። ቻይና በሀገሪቱ እና በመላው አህጉር ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰሷ መረጋጋት ትፈልጋለች። እንደ ሩሲያ እና ቻይና ያሉ ኃያላን ሀገራት ከጣልቃ ገብነት የተቆጠቡባቸው በርካታ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ሩሲያ በዩክሬን ጦርነቶች ተጠምዳለች። ጠርጣራ ሰው፤ ሩሲያ የምታደርገው ነገር ቢኖር የልዕለ-ኃያላን የበላይነት ተወዳዳሪነቷን ለማስጠበቅ፤ የጦር መሣሪያዋን መሸጥና ቅጥረኛ ወታደሮቿን ወደ አፍሪካ መላክ ብቻ ነው፤ በማለትም ይከራከር ይሆናል። ቻይና ጣልቃ ላለመግባት የወሰነችው፤ በቂ ጫና የማድረግ አቅም ስለሌላት እና በዋነኛነት የዩኤስ የሚመራው ሽምግልና ካልተሳካ ተቀባይነቷን ማሳደግ ስለምትፈልግ ነው። ዩናይትድ ስቴጽ ኦፍ አሜሪካ፤ ጦርነቱን የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር እንደቀሰቀሰው እያወቀች፤ ለምን ከዚሁ ግንባር ጋር ተለጥፋ ቆመች? የአሜሪካን በኢትዮጵያው ጦርነት ላይ በትኩረት እና ባጠቃላይ ደግሞ በኢትዮጵያና በአፍሪካ አህጉር ሙጭጭ ያለ ፍላጎት ብዙ ምክንያቶች አሉት። የዚህ መነሻው ደግሞ፤ የአሜሪካ ብሔራዊ የስለላ ምክር ቤት ከረጅም ጊዜ በፊት ሲተነብይ የነበረው፤ በብቸኝነት ዓለምን የማሽከርከር አባዜው ዋጋ ማጣቱ ነው። ፕሬዝዳንት ባይደን፤ ቻይና በአፍሪካ ያላትን ተቀባይነት ማምከንና በቦታው በማንኛውም መንገድ የአሜሪካንን ፍላጎት በአፍሪካዊያን ላይ መጫን የሳቸው ተልዕኮ አድርገውታል። ለዚህም በኢትዮጵያ የተነሳው የርስ በርስ ጦርነት ሊጠቀሙበት የሚችሉበት ዕድል ነው። ትሕነግ ካሸነፈ፤ አሜሪካ ጥቅሟን አስጠባቂ አሽከር አድርጋ ልትጠቀምበት ትፈልጋለች። ትሕነግ ካለተሳካለት፤ አሜሪካ ትሕነግ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተጫዋች እንዲሆን ትፈልጋለች። የሰላም ስምምነት ከተፈረመና ውጤታማ ከሆነ፤ ይሄን የመሰለ ውጤት፤ የአሜሪካን ዝና ከፍ ያደርገዋል። እናም ግጭቶችን የመፍታት ችሎታ ያላት “ብቸኛ አውራ!” መሆኗን ያመለክታል። በሌላ በኩል ደግሞ፤ እንዲህ ዓይነቱ ውጤት፤ የበላይ ልሁን ባይ ተፎካካሪዎቻቸውን ፍላጎት፤ በተለይ የቻይናውያንን ሊቀጭ ይችላል። በፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር፤ ቻይናን በሚመለከት፤ በዚህ አጣቃሽ በዚህ የውጪ ፖሊሲ አንቀጽ እንደሚታየው እስከመጨረሻው ድረስ መግፋት፤ በሚል የተጣለ ስልት አካል ነው። እውነታ ግን፤ አሜሪካ በአፍሪካ ውስጥ ምንም ዓይነት የተወዳዳሪ የበላይነት (ተነጻጻሪ የሚሆንም) የላትም።
 8. 8. መንግሥት ራሱን እናየሰላም ውሉን በሚመለከት እያደረገ ያለው ጥሩ የሚያስብል አያያዝ፣ የሰላም ውሉን እውን ለማድረግ ቁርጠኝነቱን በተደጋጋሚ ማሳወቁ፣ የሚያስገርም ነው፤ ፊት ለፊት በሚታየው ሲመዘን። ባጭሩ፤ ከውጭ ሆነን ስናየው፤ መንግሥት ዝም ብሎ ሂደቱን መከታተሉ አበረታትቶናል። በአንጻሩ የትሕነግ መሪዎች ጩኸትና በውሉ ላይ ወዲያ ወዲህ ማለት አስገርሞናል።

፮. ጠቃለያ  

 1. 1.  ተፋጦ መቆም!አሁን ጦርነቱ ያለው ተፋጠው የቆሙበት ላይ ነው። በአንድ በኩል፤የትሕነግ መሪዎች አጅግ ብዙ አረመኔያዊ ተግባር መፈጸማቸውን ስለሚያውቁ፤ ለሕይወታቸው ሊሰጉ ይችላሉ። ከተጠያቂነት ለማምለጥና የስምምነቱን ሂደት ለማጓተት፤ የአማራ እና የኤርትራን ኃይላት ከትግራይ ይውጡ የሚለውን እንደ መደራደሪያ ይጠቀሙበታል። ይሄን ሲያደርጉ፤ ሠራዊታቸው በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ብቻ ሊቸነፍ እንደሚችል ጠንቅቀው እያወቁ ነው። በሌላ በኩል፤ መንግሥት በትሕነግ ሊሠጠኝ ይገባል ላይ እንዳይስማማ የሚያደርጉት በርካታ ምክንያቶች አሉ። አንዱን ለመጥቀስ፤ ገና ተመርምሮ ውሳኔ ያላገኘው፤ ሁለቱን ወገኖች ወደ ጦርነቱ  የማገደው ምክንያት(የትሕነግ ጠብ ጫሪነት)። ሁለተኛው ሕጋዊ ምክንያት፤ መንግሥት በትሕነግ መሪዎች ላይ እምነት ማጣቱ ነው። ይሄም የሆነው፤ በታሪካቸው የተዘገበው አለመታመናቸው ነው። መንግሥት፤ ይሄን የሌሎች ኃይላት ከትግራይ ይውጡ ጥያቄ፤ ትሕነግ ጦርነቱን ጊዜ በመግዛት ለመታጠቅና እንደገና ለመጀመር ሊጠቀምበት ነው! ብሎ ሊሰጋ ይችላል። ሶስተኛው ዋና ምክንያት፤ መንግሥት ለትሕነግ አላስፈላጊ የሆነ እጅ መሥጠት አደረገ ተብሎ በከፍተኛ ደረጃ የመወቀሱ ፍራቻ ነው። አራተኛውና ዋናው ምክንያት፤ እኒህ ሁለቱ፤ ማለትም የአማራ ልዩ ኃይልና ፋኖ ባንድ በኩል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራ ኃይል፤ ለመንግስት የግጭቱን የበላይነት የሠጠው መሆኑ ነው። ይሄ የመንግሥት የኃይል የበላይነት ነው የትሕነግ መሪዎችን ወደ ድርድር ያመጣቸው። ታዲያ ለምን ብለው ይሄን ወደ ጎን ይላሉ? መንግሥት በምንም መንገድ ይሄንን “የሌሎች ኃይሎች ከትግራይ ይውጡ!” ጥያቄ ማስተናገድ የለበትም። ይህ ሙሉ በሙሉ የመንግሥት ጉዳይ እንጂ የትሕነግ ጉዳይ አይደለም። ከሌላ መንግሥት ጋር የሚያደርገውን ማናቸውንም ግንኙነት የሚወስነው ፓርላማው እንጂ፤ አንድ የክልል አካል አይደለም።
 2. 2. እናም ከዚህ አጣብቂኝ ለመውጣትና ተፋጦ ከመቆም ለመገላገል፤ መንግሥትናተደራዳሪዎቹበጥንቃቄ ከዚህ የሚወጡበትን መንገድ መቀየስ አለባቸው። ከዚህም መገላገያ ሁለት የተዛመዱ መንገዶች አሉ።

2ሀ. የዋናዎቹን የትሕነግ የጉዳዩ ባለቤቶች የደህንነት ፍርሃት ማስወገጃ መንገድ መፈለግና  መንግሥት ለሰላም ውሉ ቁርጠኛ መሆኑን ማረጋገጥ፤ (የሰላም ስምምነቶች፤ ወሳኝ የሆኑ ተሳታፊዎችን የግል ጥቅም እስካስጠበቁ ድረስ ነውና ሊተገበሩ የሚችሉት) እናም ቁርጠኛነቱ ዘለቄታነት ይኖረዋል። መንግሥት በግልጥም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ፤ አስፈላጊና ጠንካራ የሆነ መልዕክት ለሰላም ደርድሩ ዋና ተሳታፊዎች ሊልክ ይችላል። ና ለትሕነግ መሪዎች ሊያስተላልፍ ይችላል። በዚህ ሂደት ለሰላም ድርድሩ ቁርጠኛ እንደሆነና የትሕነግ መሪዎች ደህንነትም የተጠበቀ እንደሚሆን በአንጻሩ ደግሞ፤ ከሰላም ውሉ ወደኋላ ቢያፈገፍጉ ወይንም ለማጓተት ቢቃጡ፤ ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው ሊያሳውቃቸው ይገባል።

2ለ. የሰላም ውሉን ለመጠበቅ፤ መንግሥት የራሱን ትጥቅ ሳይፈታ የበላይነቱን ይዞ ጦርነት ያነሱትን ሊያስወግድ የቻለበትን፤ ከአማራ ልዩ ኃይል፣ ከአማራ ፋኖና ከኤርትራ ኃይሎች ጋርም ያለው ትስስር ወሳኝ ነው።

 1. 3.  በሁሉም መንገድ፤ ወደ ሰላም የሚደረገው ጉዞ ፀጥታን ማረጋገጥ፣ አስተዳደሮችን በቦታቸው ማስቀመጥ፣ የመሸጋገሪያ ፍትኅ በቦታው መሟላት ስላለባቸው፤ ውጊያ የለም፣ ሰላምም የለም! በሚሆንበት ሀቅ፤ ብጥብጦች፣ ጭንቀት፣ ሲዋጉ በነበሩ አካላት መካከል መከፋፈል፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት ቀጣይ ሊሆኑ እንደሚችሉ መጠበቅ አለብን። በሌሎች አገሮች እንደሆነው ሁሉ፤ በሰላም ግንባታው ሂደት፤ ሽብር ሊካሄድ ይችላል።

ሰላምነትን ማስገኘትና ሰላምን ማስፈን፣ ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድና ብዙ ግዴታዎችን ይጠይቃል። በዚህ ከሚጠቃለሉት ውስጥ፤ ከተዋጊነት ለወጡትና ትጥቃቸውን ለፈቱት ወደ ኅብረተሰቡ ተመልሰው በሰላም እንዲኖሩ ማደላደል፤ የተፈናቀሉት ወደ ቦታቸው ተመልሰው እንዲሰፍሩ ማድረግ፣ በሕጋዊ መንገድ ስምምነቶችን ማከናወን፣ የሰርዓቱን ሂደት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ማሻሻል፣ ሰብዓዊ መብቶችን ማስጠበቅ፣ ለተፈጸሙት በደሎች ፍትኅን ማስሄድ፣ ሕግና ደንብን ማስከበር፣ በየትኛውም የኢትዮጵያ መሬት የዜጎችን ከቦታ ቦታ በነፃ የመንቀሳቀስ መብት ማስከበር ይገኙበታል።

 1. 4. የሰላም ውሉመሳካት አስቸኳይነቱ፤

4ሀ. በብዙ አገሮች፤ በየርስ በርስ ጦርነቶቹ ከደረሱት የሰው ሕይወት ዕልቂትና ወሰን የለሽ አውዳሚ ጥፋቶች የበለጠ፤ ከሰላም ስምምነቱ ውል በኋላ ደርሷል። ለመጥቀስ ያህል፤ አንጎላና ሩዋንዳ።

4ለ.  የግጭቱ ዳግም መከሰት፤ ከነሱ አካባቢ አልፈው ወደ ሌሎች አካባቢዎች የመዛመታቸውን ዕድል ከፍ ያደርገዋል።

4ሐ. መላ ኢትዮጵያዊያን እና ቀሪው ዓለም እኒህን ረዳት የጦርነቱ አበረታች ጎኖች የመጠቀሚያ መንገድ መፈለግ አለባቸው።

4መ. አለመታደል ሆኖ እንዲህ ያሉ ማጭበርበሮች የሚጠበቁ ይሆናል የሰላም ስምምነቶች ለነዚህ የተጋለጡ ስለሆነ) እናም በሁለቱም ወገን በውሉ ላይ ማጭበርበርን ለመታገል ዋነኛ ትኩረት የሚሠጥ ስልት ማብጀት አለባቸው።

4ሠ. ትዕግሥት ፀጋ ነው። ምንም ትሕነግ ትጥቅ መፍታቱን ቢያጓተቱና የተወሰኑ የስምምነቱን ሕጎች ቢጥሱም፤  መንግሥት መታገሥ ይኖርበታል። የመንግሥት ትዕግሥት፤ ጠቡን ከማቀዝቀዙም በተጨማሪ፤ ትዕግሥት፤ ከአደፍራሹ ይልቅ ለመንግሥትና ባጠቃላይ ለሕዝቡ የብለጠ ይጠቅማል። ልብ በሉ፤ ጦርነቶች ከሞላ ጎደል የስምምነት ውሎቹ እንደተፈረሙ ወዲያውኑ ያገረሻሉ። ይህ በንዲህ እንዳለ፤ መንግሥት ለትሕነግ ተዋጊዎችና መሪዎቻቸው ጥበቃ እንዲደረግላቸው፣ ውሉ እንደሚተገበር፣ የገባቸው ቃሎችን እንደሚጠብቅ ቁርጠኛ መሆን አለበት።

4ረ. ለወደፊትም ይረዳ ዘንድ፤ ትሕነግ ያስቀመጠውና አሁን እየተሠራበት ያለው ሕገ መንግሥት፤ ምን ያህል አሰዋፃዖ አደርጓል የሚለው መመርመር አለበት። ኢትዮጵያዊነት እንዲገንና የየአካባቢ ወገናዊነት እንዲቀንስ፤ ሕገ መንግሥቱ ኢትዮጵያዊ እንዲሆን መደረግ አለበት።

. ሰላም ማስፈን፡ የአፍሪካ ልምድ

 1. ሌሶቶ(የቁርጠኝነት ችግሮች እና ወደ ሥር የሰደደየተበላሸ የፖለቲካ ሂደት ትሩፋቶች ተመልሶ መግባት) እንደ ፖል ናንቱልያ (ፖል ናንቱልያ) ከሆነ፤ ሌሶቶ አደጋው የከፋ የፖለቲካ ቀውስና መፈንቅለ መንግሥቶች አጋጥሟታል፤ በ1970፣ በ1986፣ 1991፣ 1994፣ አና 1998። ይህም የሆነው፤ በየአካባቢው እያንዳንዱ መራጭ አንድ ድምፅ ብቻ በመሥጠትና ከፍተኛ ቁጥር ያገኘው ተመራጭ አቸናፊ ሆኖ ለውክልና የሚሄድበት አሰራር፤ (the-first-pass-the-post election system-ዛሬ በዩናይትድ ስቴጽ ኦቭ አሜሪካ የሚጠቀሙበት መንገድ)  የአንደኛው ፓርቲ የበላይነት አጥቶ ሌሎችን ተወካይ በመንፈጉ ነው።  የደቡብ አፍሪካው ዕድገት ኅብረተሰብ፤ – [Southern Africa Development Community (SADC)] የሌሶቶን የአለመረጋጋት እሽክርክሪት ለመስበር፤ የሽግግር የፖለቲካ ኃይል-[Interim Political Authority (IPA)] አቋቋመ። የተሻሻለው የምርጫ ስርዓት 120 መቀመጫዎች ያሉት ነው። 80ዎቹ (ከሚወክሉት ወገን ጋር ተያይዞ) የአንድ መራጭ አንድ ድምፅ ብቻ በመሥጠትና ከፍተኛ ቁጥር ያገኘው ተመራጭ አቸናፊ ሆኖ ለውክልና የሚሄድበትን አሰራር ተቀብሎ ይከናወናል። 40ዎቹ ደግሞ ውክልናውን በተመጣጣኝ መንገድ የሚያሥጠብቅ ይሆናል። ብርቱ ብጥብጦችና መፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች እንደገና በ2007፣ 2014፣ 2015፣ 2017 አገረሹ፤ ከድምፅ የመሥጠት ስርዓቱ ከተሻሻለና የሰላም ስምምነቶች በኋላም። ይህ የሆነው፤ ፖለቲከኞች እያንዳንዱን የተገኘ ቀዳዳ በመጠቀም፤ ወደ ራሳቸው ሥልጣን ማሳደጊያ የሸፍጥ ተግባር በማካሄዳቸው ነው (ለምሳሌ፤ ትልልቅ ፓርቲዎች ከትንንሾች ጋር የትብብርና ጥምረት መሳይ ውክልናቸውን ለማግኘት የሚያደርጉት መመሳጠር፤ አንድን ተወዳዳሪ በተለያዩ ሁለት የምርጫ ቦታዎች ላይ አስመዝግቦ ማቅረብ፣ ሌላም ከውድድር በኋላ በፓርላማው መድረክ ላይ የፓርቲ ለውጥ እንዲያደርጉ መዘየድ፣ ወዘተ. )
 2. ቡሩንዲ (የቁርጠኝነት ችግሮች እና ወደ ሥር የሰደደ የተበላሸ የፖለቲካ ሂደትትሩፋቶች ተመልሶ መግባት) ለግጭቱ መንስዔ የሆነው፤ የአናሳዎቹ ቱትሲዎች አብላጫውን የፖለቲካ ሥልጣን በበላይነት መጨበጣቸው ሲሆን፤ ይህ በበኩሉ ሥር የሰደድ ጥላቻን እና አመጻን በሁቱዎች ቀሰቀሰ። የቱትሲው ጦር ሠራዊት የሁቱዎችን አመጽ ሰፋ ያለ አረመኔያዊ ግፍ በመፈጸም ለብዙ ዓመታት መቆጣጠር ችሎ ቆየ። በ1994 የሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ ዘር የማጽደት ተግባር ተካሄደ። ለቡሩንዲ ስምምነት፤ ከሌሶቶው ውል የተቀዳ ለቡሩንዲ እየተመላለሱ የሚደረጉ የግጭት ድግግሞሽ ፍጻሜ ለመሥጠት የአሩሻ ዕርቅና ሰላም ስምምነት ተደረገ። ይህ እንግዲህ ሁለት የዘር የማጽዳት ሂደቶችንና አስራ ሶስት ዓመታት (13) የቆየና የሶስት መቶ ሺህ (300,000) ሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈውን የርስ በርስ ጦርነት ይጨምራል። የአሩሻ ዕርቅና ሰላም ስምምነቱ ሥራ ማካሂያጃ ያስቀመጠው፤ ሥልጣን ማጋራት፣ ክትትል እና አስፈላጊ ማስተካከሎችን ማድረግ፣ ሁሉን ያካተተ ሚዛናዊ የመንግሥት ተሳትፎ፣ በሠራዊቱ ውስጥ የሁሉም እኩል ውክልና ደንብ፤ በዘውጎች መካከል ትብብር እንዲፈጠር፣ መረጋጋት እንዲመጣ ደግሞ አናሳዎች ከድምፃቸው የበለጠ ውክልና እንዲያገኙ ማድረግ እና ተጠያቂነት ያለበት አስተዳደርን ለማበረታታት ነበር። ሠራዊቱ ከአድሏዊነት ውጪ፣ መሠሪ ባለሥልጣኖች እንዳሻቸው የማይጠመዝዙትና ነፃ ሆኖ ተዋቀረ። በዚህ በኩል የተወሰን ስኬት ተገኝቷል። በ2006 አና በ2010፤ የተወሰኑ የሠራዊቱ አባላት ሰላማዊ ሰልፍ በወጡት ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ፣ እና በ2015 ብዙዎች ባንድ ላይ ታጅለው የተቀበሩበት ቦታ ሲገኝና ለዚህም ባለሥልጣናትና ወታደራዊ መሪዎች እጃቸው ያለበት በመሆኑ፤ ችግር ተፈጠረ። ከገዥው ፓርቲ ጋር የተቆራኘ የመንግሥት ሸንጎ፤ የፕሬዘዳንቱ የሥልጣን ዘመን ገደብ ተነስቶ ወደ አብላጫ ድምፅ ያገኘ የሚያስተዳድርበትን ስርዓት መለሰና ፕሬዘዳንት ፒየር ኑኩሩንዚዛ ለሶስተኛ ጊዜ በ2016 ለፕሬዘዳንትነት እንዲወዳደሩ ተፈቀደላቸው። ከዚያ በኋላ ሁኔታው በጣም ተባባሰ። የፖለቲካው ሻጥር ደግሞ የሠራዊቱን ከወገናዊነት ነፃ የመሆን ጉዳይ ደመሰሰው። ይህ ሠራዊት ደግሞ፤ የግንቦት (May 17, 2018) ወሩን ሕዝበ ውሳኔ ተጠቅሞ፤ በሕግ ተፈቅዶላቸው የተቋቋሙትን የታጠቁ የዘውግ ኃይሎችን (militia)፣ እና ኢምቦነራኩሬን [(በአገሪቱ በሚገኘው የኩሩንዲ ቋንቋ ኢምቦነራኩሬ ማለት፤ “የሩቁን የሚያይ” – አርቆ አስተዋይ” ማለት ነው።) ነገር ግን አብዛኛው በአገር ቤት ውስጥና በውጪም ያለው ሁሉ ቃሉን፤ የገዥው ፓርቲ ወጣት ክንፍ አባል ለሆኑትና በ2010 ለተነሱት ወጣቶች፤ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ከተደረጉ የቀድሞ ተዋጊዎች የተውጣጡት፤ “የታጠቁ፣ ገዳዮች፣ ወታደራዊ ጥንካሬ ያላቸው፣ ወገንተኞች፣ ጉልበተኞች፣ ማንም የማይጠይቃቸው፣ ያልተማሩ፣ ለሚለው ነው የተጠቀሙበት)] ወደ ጸጥታው ክፍል እንዲቀላቀሉ ያደረገ ነው። ዓለም አቀፍ ጫናዎችና አገሪቱን እንድትገለል መደረጉ፤ ባገሪቱ ውስት ያለውን ድኅነትን አሳደገው። ይህ ደግሞ በተራው፤ በሰኔ 2018፤ ፕሬዘዳንት ንኩሩንዚዛን፤ የሥልጣን ዘመናቸው በ2020 ሲያልቅ፤ ቦታቸውን እንደሚያለቁ እንዲያስታውቁ አደረጋቸው። እሳቸውም፤ የሥልጣን ዘመናቸውን ከመፈጸማቸው ከጥቂት ቀናት በፊት ሕይወታቸው አለፈ።

ማሳረጊያው፤ በአውሮፓ ኅብረትና በተባበሩት መንግስታት ድክመት፤ በተጨማሪም በምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ (የአገሮቹ መሪዎች ስብስብ) አባላት መካከል የነበረው አለመግባባት፤ ፕሬዝዳንት ንኩሩንዚዛ እና የትልቁ ዘውግ ፓርቲያቸው፤ ወደ ቀድሞው የአገዛዝ ስርዓታቸው ልምድ እንዲመለሱ አስቻላቸው። ይህ ማለት፤ ከአውሮፓ ኅብረት፣ ከተባበሩት መንግስታትና ከምሥራቅ አፍሪካ ኅብረት የሚረጨው ድንፋታ፤ የፖለቲካ አሻጥሩንና የፕሬዘዳንት ንኩሩንዚዛን መንግሥት ማፈንገጥ ሊቋቋም አልቻለም። ከዚህ ውድቀት አገራችን ኢትዮጵያ ትምህርት መውሰድ ትችላለች፤

2ሀ. ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ከቆምንና መንግሥት ለምዕራባዊያን ተጽዕኖ አልሰግም ካለ፤ ኢትዮጵያ ታቸንፋለች። ሌላም

2ለ.  ለወደፊቱ ከሁሉ አበዛለሁ ባይ ዘውግ፤ በሚቀመጠውና በተግባር በሚውለው ሁሉን አቀፍ ስምምነት ላይ የማደናቀፍ ዕድሉን መዝጋቱ

 1. የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ፤(የቁርጠኝነት ችግሮች እና ወደ ሥር የሰደደ የተበላሸ የፖለቲካ ሂደትትሩፋቶች ተመልሶ መግባት) በ1997 ሎረን ካቢላ፤ ከዩጋንዳ፣ ሩዋንዳና ከቡሩንዲ ጋር በመተባበር በጆሴፍ ሞቡቱ ሴሴ ሴኮ ላይ ጦርነት ከፈቱና ሥልጣን ያዙ። ከዚያ ተከትለው የመጡት የኮንጎ ዴሞራሲያዊ ሩፓብሊክ ጦርነቶችና በጎረቤት አገሮች የተደረጉት ጦርነቶች፤ ዘውግ ተኮር የሆኑ፣ የዘር ማጽዳት የተከናወነባቸውና የተወሰኑ አገሮችን ያሳተፉ (እናም ሌሎች በጅ አዙር በውክልና የተጠቀሙባቸው) ነበሩ። ለአካባቢው ግጭቶች የማይፈታ ምንጭ የሆነውና አሁንም እንዲቀጥል ምክንያቱ፤ የኮንጎ የበለጸገ የተፈጥሮ ሀብት ነው። ይህ ገበያው የደራ ሀብት፤ በተለምዶ በመንግሥት ባለሥልጣናትና ወታደራዊ መሪዎች ውስጥ ሙስናን አስከትሏል። እኒህ መሪዎች፤ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው፤ ለውጪ ኩባንያዎች እንቅስቃሴ ጉቦ መቀበያ በማድረግ፤ በዘውጎች መካከል ግጭትንና የግለሰቦችን መግደያዎችን የሚያስፋፋ ወጪ ሸፈኑ። ለምሳሌ ሶኮ ዓለም አቀፍ ( SOCO International – ዛሬ ስሙን ቀይሮ ፋሮስ የኃይል ማመንጫ ኩባንያ የሚባል ሲሆን፤ ሎንደን ዋና መሥሪያ ቤቱን ያደረገ ነው።) አራት የሰላም ስምምነቶች ተፈራርመው ነበር፤ በሉሳካ፣ ሉዋንዳ፣ ሰንሲቲ እና የፕሪቶሪያ ውል ስምምነቶች። የተባበሩት መንግሥታት እና አጎራባች አገሮች እኒህን የስምምነት ውሎች ተጠቅመው፤ ለኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሩፕብሊክ ቋሚና የተረጋጋ ዴሞክራሲ ቀየሱ። አለመታደል ሆኖ፤ ከላይ ከተዘረዘሩት ችግሮች በተጨማሪ፤ ጆሴፍ ካቢላ፤ በሥልጣን ላይ ለመቆየት፤ ከሁለት የሥልጣን ዘመናቸው በኋላም ሥልጣናቸውን ላለመልቀቅ፤ የተለያዩ አሻጥሮችን ተጠቀሙ። እኒህ የውዴታ ግዴታ ችግሮች፤ በዘውጎች መካከል ያለውን ውጥረት፣ ሙስናን፣ እና በተዘዋዋሪ የሚደረጉትን የውክልና ጦርነቶች አባብሰዋቸዋል።
 2. 4. ላይቤሪያበ1989 የገና ዋዜማ በቻርለስ ቴይለር የሚመራው አማፂ ቡድን፤ የላይቤሪያ ብሔራዊ አርበኞች ግንባር (NPFL)፣ ጎረቤት ከሆነችው የአይቮሪ ኮስት ምሽጉ ተነስቶ፤ በሰሜን ማዕከላዊ የላይቤሪያ ግዛት ላይ ወታደራዊ ጥቃት ሰነዘረ። ይህ በአገሪቱ መሪ ፕሬዘዳንት ሳሙዔል ኬዮን ዶ ሠራዊት፤ የአጸፋ ጥቃትን አስከተለ። በተዋጊ ኃይሎች መካከል በተደረገው የ1995 የአቡጃ ስምምነት ካቀፈው መካከል፤ የሠራዊቱን የወታደር ቁጥር መቀነስ፣ የቀድሞ የሽምቅ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታትና ወደ ኅብረተሰቡ ሰላማዊ ሆነው እንዲቀላቀሉ ማድረግ፣ እና በአገሪቱ ውስጥ የምዕራብ አፍሪካ የአንድነት ገበያ ጥቅም መንግሥታት ኅብረት Economic Community of West African States – ECOWAS) ሰላም አስጠባቂ ኃይል እንዲሰማራ ነበር። ዝግምተኛውና የተሽመደመደ ትጥቅ የማስፈታት ሂደቱ አስቸገረ። የቴይለርና የክሮማ ጥምር ኃይሎች፤ ከሽግግር መንግሥቱ ውስጥ የጆንሰንን ወገን ካስወጡ በኋላ ጦርነት ተቀሰቀሰ። የቴይለር እና ክሮማህ ጥምር ጦር የጆንሰን ቡድንን ከጊዚያዊ መንግስት ካባረሩ በኋላ ጦርነት እንደገና ተቀሰቀሰ። ከላይ የተጠቀሰው የኅብረቱ ግጭት መቆሙን ተቆጣጣሪው ቡድን (ECOWAS Cease-Fire Monitoring Group ECOMOG)። በሚያዝያ 1996 ቀውስ በዋና ከተማዋ የተደረገውን ዘረፋ ጭምር፤ ማስቆም ሳይችል ቀረ። የምዕራብ አፍሪካ የአንድነት ገበያ ጥቅም መንግሥታት ኅብረት Economic Community of West African States – ECOWAS)፣ የአካባቢው የአፍሪካ አገሮች ድርጅቶች፣ብጥብጡን ለማስቆም ጣልቃ ገቡ። የአቡጃው ሁለተኛ የስምምነት ውል ጊዜው ተፈጸመ። ከዚያ አስራ ስድስት ሰላምን የማስገኘት ሙከራዎች ተደረጉና ደም መፋሰሱ ውል ተደረገለት። ሌሎች ጥረቶች ሁሉ ዋጋ አጥተው ሲቀሩ፤ የአቡጃው ሁለተኛ የስምምነት ውል እንዴት ሊሳካ ቻለ? አንድ የስኬት ጎኑ፤ የቀድሞ ተዋጊዎች በፍጥነት ትጥቅ ፈተው ወደ ኅብረተሰቡ በመቀላቀል፤ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ራሳቸውን ማስተዳደራቸው ነው።
 3. 5. ሞዛምቢክ (1992–1995)፤ክላር ፔድሪክ ( ክሌር ፔድሪክስ 1992 ) እንደገለጠው፤ሰላም የተሳካው፤ ለዲፕሎማሲ ዓለም እንግዳ በሆኑት፤ በሮም ሳፒያንዛ ዩኒቨርሲቲ የክርስትና ታሪክ ፕሮፌሰርና የክስቶሊኮች በጎ ፈቃደኝነት ድርጅት አቋቋሚ በሆኑት አንድሬ ሪካርዲ፣ በሮም ከተማ ስደተኞችንና ኤድስ የያዛቸው ግለሰቦችን በመርዳት የሚታወቁት ቄስ ዶን ማቲዮ ዙፒ፣ እና በሞዛምቢክ የቤይራ ሊቀ ፓፓሱ ጀሚ ጎንሳልቬስ ነው። ጥረታቸው የታገዘው፤ በሶሺያሊዝም/ኮሚኒዝም መጨናገፍ፣ የካቶሊክ ድርጅት በፖለቲካው ውጤት ጥቅም የማግኘት ፍላጎት የሌለው ሆኖ መገኘቱ፣ እና በዲምሎማሲ ክንውን ወቅት ቦታ ባልተሠጠው የሰዎች ተሳትፎና የግጭቱ ተዋናይ በሆኑት መካከል፤ በጊዜ ሂደት የመተማመን መንፈስ መስፈኑ ነው። ሆነም ቀረም፤ በሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ እና በደቡብ አፍሪካ የሰላም ውሎች የተሳኩት፤ መሪዎቹ ለውሎቹ የሠጡትን ቃል በመጠበቃቸው ነው።
 4. አንጎላአንጎላ 1 እና አንጎላ 2 (1991 እና 1994) የሰላም ውሎችሳይሳኩ ሲቀሩ፤ አንጎላ III (2002) ግን ተሳክቷል። ለምን? ከፖርቱጋል ነፃ ለመውጣት የነፃነት ትግል በኋላ፤ ሶስቱ ተቀናቃኞች ኃይሎች፣ ማለትም፣ የአንጎላ ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር  (National Liberation Front of Angola – FNLA)፣ ለአንጎላ ነፃ የሕዝብ  ንቅናቄ አውጪ (People’s Movement for the Liberation of Angola – MPLA)፣ እና ብሔራዊ ህብረት ለአንጎላ ጠቅላላ ነፃነት (National Union for Total Independence of Angola – UNITA)፤ በቀዝቃዛው የጦርነት ዘመን (Cold War)፤ የርስ በርስ ጦርነት አደረጉ። ይህ ጦርነት የውክልና ጦርነት ነበር። በ1994 ድምጥማጡ ሊጠፋ ተቃርቦ የነበረው ብሔራዊ ህብረት ለአንጎላ ጠቅላላ ነፃነት  (UNITA)፤ በዓለም አቀፍ የመሳሪያ ድጋፍ (በተለይም በወቅቱ የዩናይትድ ስቴትስ ኦቭ አሜሪካ ፕሬዘዳንት በነበሩት ሮናልድ ሬገን አስተዳደር)፤ እና በስምምነቱ የፈረመበትን ውል አፍርሶ በተቆጣጠረው የአልማዝ ምንጭ ተረድቶ፤ ራሱን እንደገና አጠናከረ። ውሉን ማፍረሱ፤ ያቸነፈ-ሁሉን-አጠቃሎ-ይውሰድ በሚለው የምርጫ መመሪያ፤ የአንጎላ ነፃ የሕዝብ  ንቅናቄ አውጪ (MPLA) አቸንፎ ተጠቃለለ። የብሔራዊ ህብረት ለአንጎላ ጠቅላላ ነፃነት (UNITA) መሪ የነበሩት ሳቪምቢም በ2002 ከመንግሥት ኃይል ጋር በነበረው ግብግብ ሕይወታቸው አለፈ። ከዚያ ተከትሎ የመንግሥት ሠራዊቱ እና አማፂዎቹ ግጭቱን ለማቆም የተኩስ አቁም ስምምነት አደረጉ። ይህ ክንውን፤ ወታደራዊ ድል፤ የርስ በርስ ጦርነትን ለፍጻሜ ያበቃል ለሚለው ቀኖና ድጋፍ ይሠጣል።
 5.  ሱዳን፤ በ1972የሱዳን አና የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ከሸፈ። የ1972ቱ፤ በሱዳን የርስ በርስ ጦርነቱን የሚያስቆም ስምምነት፤ የሱዳን መንግሥት የሻሪያን ሕግ በተግባር ላለማዋል የገባውን ቃል በማጠፉ፤ ፈረሰ። ይህ፤ ከስምምነት ውሉ በኋላ፤ የኃይል ብልጫ ያለው ወገን በግሉ ውሉን ሲጥሰው የሚታየው የታወቀው የቁርጠኝነት አለመኖር ማሳያ ነው። የአፍሪካ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት በዳርፉር ተረዳድተው የገቡበት የሰላም ጉዳይ፤ (ለሰዎች መንቀሳቀሻ በር የሚከፍቱ፣ ታዛቢ ልዑካን እና አጠቃላይና አግባቢ ስምምነቶችን የሚፈልጉ የሰላም ቡድኖችን ከሚፈቅደው የሰላም ስምምነት ክፍል ውጪ) ሳይሳካ ቀረ። ይሄም ሳይሳካ የቀረው በከፊል፤ መንግሥቱ የአፍሪካ ኅብረትን አና የተባበሩት መንግሥታትን አስታራቂነት በደስታ እጁን ዘርግቶ ባለመቀበሉ አና ከተወሳሰበው የሰላም ስምምነት ውሉ ውጪ የሆኑ ብዙ ተስፈንጣሪ ሚሊሽያዎች በመኖራቸው ነው። የአፍሪካ ኅብረት የገንዘብ አቅም ማነስ፤ የሰሜን አትላንቲክ የስምምነት ድርጅት (North Atlantic Treaty Organization-NATO) ኃይሎች፤ የሰላም አስጠባቂ ኃይሎችን እንዲያጓጉዙ፤ ግብዣ እንዲያቀርብላቸው አስገደዳቸው። የሰሜን አትላንቲክ የስምምነት ድርጅት (NATO) በቦታው መቆየት፤ (እናም ወዲያና ወዲህ የሆኑ የፖለቲካ አመለካከቶች፣ የሰላም ግንዛቤያቸው፣ እና ቅደም ተከተል አቀማመጣቸው) የሊቢያውን መሪ፤ ሞዓመር ጋዳፊን ከሥልጣን በማውረድና በመግደል እንዲሳተፉ መንገድ ከፈተላቸው። ይህ በተራው፤ የአፍሪካ ኅብረትን የሰላም አስገኚ ድርጅትነት ውሃ አፈሰሰበት። የተባበሩት መንግሥታትም በዳርፉር የአፍሪካ ኅብረት ቅይጥ የተግባር እንቅስቃሴ (United Nations – African Union Hybrid Operation in Darfur (UNAMID)፤ የሱዳን የሽግግር መንግሥት የዳርፉሩን ግጭት በሚመለከት ያደረገውን ግስጋሴና ከአማፂያን ጋር ያደረገውን የሰላም ውል መፈረሙን በመጥቀስ፤ ተልዕኮውን ዘጋ። ግጭቶቹ፤ በተለይም በደቡብ ዳርፉር፤ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ በመገደል፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በመፈናቀል፤ እንደገና አገረሹ።
 6. ሶማሊያ፤የ1990ቱ የሰላም ውሉ፤ ሶማሊያን ከሶስት የተቆራረጠችና ያልተሳካላት አገር አድርጓት አረፈ። ለምን? የአፍሪካ ኅብረት የመፍትሔ መንገድ፤ የመረጋጋት፣ የዓለም አቀፍ አስማሚነትን ሕጋዊነትን አረጋጋጭ፣ ለወደፊቱ የሚደረጉ ሰላም የመገንባት ኃላፊነትን ከሰላም ተልዕኮዎች የሚረከብና የውይይት ማዕከል የሚሆን ተቋምን ማቋቋም ግድ ይላል። የአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ በየፖለቲካ ውይይት፣ ሕገ-መንግሥት ማስቀመጥ፣ እና   ተስፋ ሠጥቶ በሕዝቡ ውስጥ እምነት እንዲኖር ማድረግ ነው። ሶማሊያ ያልተሳካላት አገር እና ደካማ መንግሥት በቦታው የሚገኝ በመሆኑ ይህን በተግባር ማዋል አስቸጋሪ ሆነ። አል-ሸባብ በቦታው ተንቀሳቀሰ። እናም አል-ሸባብ የሽብር ድርጅት ተብሎ ተፈረጀ። ይህ ደግሞ የዓለም አቀፍ ኃያላንን ጣልቃ ገብነት አስከተለ። በምሥራቅ አፍሪካ የሕብረ-መንግሥታት የዕድገት ባለሥልጣን (Intergovernmental Authority on Development -IGAD፤ ይህ ድርጅት በ1996 የተቋቋመና 8 አገሮችን ያቀፈ ነው። ጂቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ዩጋንዳ፣ ኤርትራና ደቡብ ሱዳን ይገኙበታል) ደካማነት ላለመሳካቱ አስተዋፅዖ አደረገ፤ በማድረግም ላይ ነው። የግጭቱ ዘውግ/ጎጥ ተኮርነትና የውጭ ዓለም አገራትን ተሳትፎ ማስከተሉ፤ ላለመሳካቱ አስተዋፅዖ አድርጓል።
 7. ሩዋንዳ፤ የ1993 የሩዋንዳ የሰላም ስምምነት፤ የሰላም ውሉን በመተግበር በኩል ቁርጠኝነት አለመኖሩ ውድቀቱን እና የዘር ማጽዳትን አስከተለ። በጥቅምት ወር (October 1, 1990)(ይሄን ሀረግ ተጠቅመው ይመልከቱ፤  ዩጋንዳ ጦርነት)የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር (Rwandan Patriotic Front– RPF) ከዩጋንዳ ተነስቶ ከሩዋንዳው ጦር ሠራዊት (Rwandan Armed Forces – RAF) ጋር ግብ ግብ በመግጠም አገሪቱ ወረረ። ይሄ ግጭት፤ ብዙ የኖረና ሥር የሰደደ፤ በሩዎንዳ ውስጥ ያሉት የሁቱዎችና የቱትሲዎች መቋሰል ነው። ከሳምንታት በኋላ ተጋጣሚዎቹ ግጭቱን በሰላም ለመጨረስ ጥረት አደረጉ። ይህ ጥረት፤ የሁለቱን ወገን ወታደሮች መቀላቀልን እና የሥልጣን መጋራትን በተባበሩት መንግሥታት አነሳሽነት የታቀደውን የአሩሻ ስምምነትን አስከተለ። ሆኖም ግን፤ ስምምነቱ በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የተለያዩ አካላትን መፈጠር አስከትሎ፤ በሩዋንዳ አርበኞች ግንባርና በሩዋንዳ መንግሥት መካከል ደግሞ፤ ትጥቅ አስፈትቶ ወታደሮቹ በሰላም ወደ ኅብረተሰቡ በመቀላቀሉበት መንገድ፣ ከሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ምን ያህሉ ወደ መንግሥቱ ሠራዊት ይቀላቀሉ በሚለው፣ ወዘተ ሥር የሰደደ አለመግባባት ተፈጠረ። ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ፤ ትጥቅ የማስፈታቱን፣ ከውትድርና ዓለም ማስወጣቱን፣ ትጥቃቸውን የፈቱትን ወደ ኅብረተሰቡ በሰላም ማቀላቀሉን፣ እና ለዚህ ተግባር የሚውለውን ወጪ የማስገኘቱን ኃላፊነት ተሠጠው። ሆኖም ግን፤ ይኼ ክፍል ምንጩም ሆነ ማከናወኛ ልምዱ አልነበረውም። (ይሄን ሀረግ ተጠቅመው ይመልከቱ፤  የሩዋንዳ ጥናት  )። መተማመን በመካከላቸው ባለመኖሩ፤ ትጥቅ ማስፈታት፣ ከውትድርና ዓለም ማስወጣት፣ እና በሰላም ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረግ (disarmament, demobilization and reintegration – DDR) በሚለው ላይ መሪዎቹ አልስማማ አሉ። በተጨማሪ ደግሞ፤ ከውትድርናው ዓለም የወጡትን ትጥቅ የፈቱ ተዋጊዎች መርጃ ገንዘብ ጠፋ።  ከዚያም ሌላ፤ ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግሥት ማቋቋም አልቻሉም። ሁለቱም ወገኖች፤ ስምምነቱን በሥራ ላይ ከማዋል ይልቅ፤ የየራሳቸውን ወታደሮች እንደገና ማስታጠቅ ጀመሩ። ዚህም እዚያም ከሚደረገው ግድያ ጋር ፍጥጫው ጣራ ነካ። በግንቦት/ሚያዝያ (April 6, 1994) የፕሬዘዳንት ሃብያሪማና አውሮፕላን ተመቶ መወደቅ ለፍርሻው የመጨረሻውን ድወል አሰማና፤ የዘር ማምከኑ ተግባር በግልጥ ተጀመረ።
 8. ደቡብ ሱዳን፤ለምን ሳይሳካ ቀረ? ለስምምነት ውሉ ከፊል ምክንያቱ፤ በአካባቢው ባሉ አገሮች መካከል ያለው የርስ በርስ ውድድር ነው። ይህ ሀቅ፤ በምሥራቅ አፍሪካ የሕብረ-መንግሥታት የዕድገት ባለሥልጣን (Intergovernmental Authority on Development -IGAD) የዕርቅ ደጋፊ ቡድኑ ኃላፊ የሆኑት አሉ ጋራንግ በ2015 ባደረጉት የደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደት የሁለት ዓመታት ጥናት (ከታህሳስ እስከ ነሐሴ December 2013 to August 2015) ታይቷል። በምሥራቅ አፍሪካ የሕብረ-መንግሥታት የዕድገት ባለሥልጣኑ፤ በመጀመሪያ የዩጋንዳን ዋና ዋና ሕንፃዎችና ድልድዮችና መንገዶች እንዳይፈራርሱ ጣልቃ መግባቱን ተስማምቶበት ነበር፤ ቆይቶ ግን ሃሳቡን በመቀየር፤ ለኢትዮጵያና ለሱዳን አቋም ድጋፉን አደረገ። የሰላም ስምምነቱ አለመሳካት የተባባሰው፤ ተደራዳሪዎቹ ከሌሎች ጉዳዮች በተጨማሪ፤ ሰላምን ለማምጣት እውነተኛ ፈቃደኝነቱ ስላልነበራቸው ነው።

የርስ በርስ ጦርነትን ባንድ ወገን ወይንም በሌላው ወገን ሆኖ ለመደገፍ፤ የውጪ ኃይሎችን የሚስቧቸው ሰፋ ያሉ የተለያዩ ጉዳዮች ሊኖሯቸው ይችላሉ። እኒህ እንግዲህ፤

ሀ. የደገፉት ወገን ካቸነፈላቸው፤ እውነተኛ ጥቅም የማግኘት ዕድል ይከፍትና ተባባሪ ወይንም ወታደራዊ ምሽግ መጣያ ማስከተሉ

ለ. የኋላ ኋላ የነሱን ጥቅም የሚያስጠብቅላቸው “ወኪል” የሚያፈሩበት፣

ሐ. ይሄን በመሰሉ ግጭቶች ላይ ተፅዕኖ የመፍጠር ችሎታን በማሳየት፤ ሊከተል የሚችለው ያገር ውስጥ ወይንም ዓለም አቀፍ ዝና

ወይንም

መ. ሌላውን ወገን የሚደግፉትን የውጪ ኃይሎች ይኖራቸው ይሆናል የሚሉትን ጥቅም ለማደናቀፍ

ጦርነቱ ተራዝሞ ሲቀጥልም፤ ጦርነቱ በተፋፋመበት አካባቢ ያለው ኅብረተሰብ የበለጠ ጉዳቱ ያይላል። እናም ያገር ውስጥ ተፈናቃዩና የስደተኛው ቁጥር ያድጋል። እኒህ ስደተኞች የደህንነት አደጋ ተደርገው ይታያሉ። ይህ ደግሞ አንዳንድ አጎራባች አገሮች፤ ስምምነቱ በፍጥነት እንዲካሄድ ሰፊ ጥረት እንዲያደርጉ ይገፋፋቸዋል። በትን መንገድ እንዲፈልጉ ያደርጋቸዋል። ነገር ግን፤ ባንድ ላይ የውስጥና የውጪውን ፍላጎት የሚያሟላ የድርድር ስምምነት ውስብስብነትን ሀቅ በማጤን፤ ስደተኞቹን የሚቀበሉ አገሮች አንዱን ወገን ወይንም ሌላውን ወገን ለመደገፍ ይገፋፉ ይሆናል።

 

የውጪ ኃይሎች የሰላም ጠባቂነት ጥቅሙንና ጉዳቱን ማመዛዘን ያስፈልጋል

የወታደራዊ ኃይልን የሚጠቀም ወይንም ማስፈራሪ የሚያደርግ የውጪ ጉዳይ መመሪያ አደገኛ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Amhara cry
Previous Story

የሚበላውን እና የሚለብሰውን ያጣ ደኻ፣ የተወለደበትን አገር የሚወድ የአገሩ መንግሥት ሊታደገው ካልቻለ ሊጠፋ ይገባል

320928136 455645626719207 8314142195454687233 n
Next Story

የገሞራ ሙሽራ የሰዶም መንገደኞች!- ከቴዎድሮስ ሐይሌ

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop