የትዕቢተኞች ፍፃሚ ፤  አሰቃቂ ነው – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

መንደርደሪያ ሃሳብ

የፍቅር እስከመቃብሩ ገፀ-ባህሪ ፣ የፊውታራሪ መሸሻ ትዕቢት  ፊውዳላዊ ነው ። ባለማወቅ የተጀቦነ ። የዛሬ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችና ሊሂቃን ትዕቢት ደግሞ ቶማሲዝም ነው ። ″ ሞትን ሞቼ ካልሆነ አላምንም ! ″ ይሉናል ።

  ሰው ልጅ የራሱ የሆነ ውስብስብ አእምሮ ያለው ነው ። ( the most sophisticated computer is  human mind .  ) አንድ ሰው ፣   በ12 ሰዓት ያሰበውን እና የሚተገብረውን ነገሮህ ፣ በ12 ሰዓት ከ 10 ሰከንድ ፣ ሙሉ ለምሉ  ሃሳቤን ቀይሬለሁ ። ሊልህ ይችላል  ። አንተ እንደ ፊታውራሪ መሸሻ የምተስብ  ፖለቲከኛ  ከሆንክ ግን ተከዳው ልትል ትችላለህ ። በግብዝነት ። ወዳጂ ሰው እኮ  ያሳደከው ውሻ አይደለም ። እንዳንተ በአርያ ሥላሤ የተፈጠረ እንጂ !


መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

እንደምታውቁት ፣ በዚች አገር አንድ መንግሥት ነው ያለው ።  ይኽ መንግሥትም  የራሱ ህግ አውጪ አለው ። የራሱ ህግ ተርጓሚ አለው ። የራሱ ህግ አሥፈፃሚ አለው ። ህግ አውጪው ህግ ያወጣል ። ህግ ተርጓሚው ህጉ በትክክል እንዲተረጓም  መደላድል ይፈጥራል ።  ህግ አሥፈፃማው ህጉን ይተገብራል ።  ያሥተገብራል ።  በዚች አገር ከፍተኛው አደራ የተጣለበት ፣ የመሪነት እና በተመጣጣኝ ኃይል የህዝብና የሀገርን ሠላም የማሥጠበቅ ሥልጣን ያለው ደግሞ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒሥትር ነው ።   የአገሪቱን ህዝብና ዳር ድንበር ለመጠበቅ በአገሪቱ ህዝብ ተሣትፎ የተቋቋመውን   የመከላከያ እና የፊደራል ሠራዊት  በባላይነት የሚመራውም  ጠቅላይ ሚኒሥተሩ ነው ።

ጠቅላይ ሚኒሥትሩ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ነው ።  ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒሥተር የበላይነት የሚመራ  አንድ የጦር ኃይል ብቻ ነው ያለት ። ለዚህም ጦር ዘመናዊነት ጥ ካሬ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ትልቅ ብቻ ሣይሆን እጅግ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ።

ወደድንም ጠላንም ኢትዮጵያን እየመሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒሥትር አብይ አህመድ  ናቸው ።  ዛሬ እና ትላንት መልኩን እየቀየረ ራሥ ምታት የሆነባቸውን የጎሣና የቋንቋ ፖለቲካ አደገኝነትም የሚያጡት አይመሥለኝም ። ሆኖም ከኢህአዴግ ህገመንግሥት ጋር ነው እና እየተጓዙ ያሉት ፣ ለትክክለኛው ለውጥ  የአገራዊ ምክክሩን ውሣኔ የሚሹ ይመሥለኛል ። እሥከዛው ቤት ካልፈረሰ የምትሉ ሰከን በሉ ። ማፍረስ ቀላል ነው ። መገንባት እጅግ ከባድ ነው ። የትግራዩ ጦርነትን እና ያሥከተለውን ችግር እና ችጋርም አትዘንጉ ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወያኔ ጠላቴ ነዉ ያለዉ አማራን እንጅ ኢትዮጵያን አይደለም::አንተ ከዬት አምጥተህ ነዉ ወያኔ የኢትዮጵያም ጠላት ነዉ እያልክ የምትጽፈዉ?  - ሸንቁጥ አየለ

እንዳልኳችሁ ፣ ጠቅላዩ  አገራዊ የአገራዊ ምክክሩን እና የአገሪቱን ህዝብ ምላሽ ለማይቀረው ለውጥ የሚጠበቁ ይመሥለኛል ። አገራዊ ምክክሩም  ከሆዳም እና ከራሥ በላይ ነፋሥ ባዮች አሥተሣሠብ የፀዳ እንዲሆንም ይፈልጋሉ ። ይህ ልባዊ ምኞታቸው ይሣካ ዘንድም በመላው ኢትዮጵያና በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን የተቸከለው    የካድሬ አጥር መነቀል አለበት ። የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ምሁራን እና ተማሪዎች ሁሉ ያለአንዳች ሸባቢ በንቃት የምክክር ሃሳብ በሚዘጋጁት መድረኮች ላይ ሁሉ  መሥጠት አለባቸው ።

በበኩሌ “ ዛሬ፣  እና አሁን መጠየቅ ያለበት ጥያቄ የዓለምና የፖለቲካ አካሄድ በመከተል  ፣ ዘመናዋ እና በተጠያቂነት ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲና መልካም አሥተዳደር የሰፈነበት ፣ በመዘጋጃ አገልግሎት ብቻ የሚመራ የመንግሥት ማወቅር እንዘርጋ ና ድህነትን በአጭር ጊዜ ተረት አድርገን ህዝብ በቀን ሦሥቴ እንዲመገብ እናድርግ  ? ወይሥ  አሁን እንደሚታየው ከደርግ ጀምሮ በተዘረጋው ፣  በዓለም በሌለ የቀበሌ ካድሬአዊ ሥርዓት ህዝብን እይንህን ጨፍነህ እያሞኘንህ አንተ በድህነት አረንቋ እየተዘፈቅህ ፣ እኛ ጥቂቶች እንደ ፊውዳል ሥርዓት እያሥተዳደርን በራሣችን የብልፅግና ጓዳና እንገሥግሥ  ? ነው ጥያቄው ። “ እላለሁ ።  ይኽንን ጥያቄ በትክክል መመለሥ አሥፈላጊ ነው ። ለኢትዮጵያ ዜጎች ብልፅግና   የሚበጀው  ዘመናዊው  የአመራር ጥበብ ነው  እንጂ ዘመናዊ የፊውዳልና የጪሰኛ አሥተዳደር አይደለም ።

ያለፉትን አራት ዓመታት የመራውን ግለሰብ አብይ አህመድን ብንመለከት በሕዝብና በአገር ስም የሚሰጠውንም ሆነ በብድርና በእርዳታ የሚገኘውን ገንዘብ እንደ ግል ሃብቱ ሲበትን፣ለምን  እንዲህ ይሆናል ብለው የጠዬቁትን ምን አገባችሁ እያለ ሲሳደብና ሲያንጓጥጥ ማዬቱ የተለመደ ነው

ዛሬ እና አሁን እየተከተልን ያለነው ሥርዓት የትኛው እንደሆነ ግልፅ ነው ። እነረ አውቅልሃለው ባይነት የተፀናወተው ፣ ለጥቂቶች ብዝበዛና ሥርዓተ አልበኝነት የተመቸ የአመራር ሥርዓት ከቀበሌ ጀምሮ በቀድሞው ኢህአዴግ መዘርጋቱ የሚካድ አይደለም  ። ይኽ ሥርዓትም ከዓለም ዘመናዊ አመራር ያፈነገጠ  ሠርዓት ነው ። በኢህአዴግ   ህግ መንግሥት አሥገዳጅነት በህዝብ ሥም ዜጎችን የሚጨቁን ፊውዳላዊ ሥርዓት ተፈጥሮ ይኸው ላለፉት አራት ዓመታት የበለጠ እያመሰን ነው ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትንሽም ብትሆን እውነትን ሳትቀላቅል ዋሽ ….. የሚያዉቁህ ባያምኑህም…... ነገር ግን ዋሽ ….

ይኸው ጦሰኛ ህገመንግስት የአገሪቱ ባለቤት አጠቃላዩ ዜጋ ሆኖ ሣለ ፣ አጥር በማጠር ለእያንዳንዱ ክልል ያልተገባ ጉልበት እየሰጠ እና ፊውዳሎችን እየቀፈቀፈ አገርን ከእድገት በመጎተት ህዝቧን እያሥራበ ነው  ። በፊደራል መንግሥት እሳቤ ላይ ያልተመሠረተ እና ከዓለም የተለየ የቋንቋ ፊደራሊዝም አገሪቱን ከፍተኛ አደጋ ላይ እየጣላት ነው ።

አገሪቱ አደጋ ላይ የወደቀችውም የአገሪቱ ባህላዊም ሆኑ ቁሳዊ ሀብቶች የዜጎች በሙሉ እንዳልሆኑ በመቆጠራቸው እንደሆነ ልብ ማለት ያሥፈልጋል ። የአገሪቱ ቋንቋዎች በሙሉ ከባህላዊ ሀብቶች የሚመደቡ ናቸው ። እናም የሁሉም ዜጋ ሀብት ናቸው ። እናም በየትምህርት ቤቱ እንደተማሪው ምርጫ ያሉን ቋንቋዎች በሙሉ ለትምህርት ቢቀርቡ  ዜጎች እጅግ ደስተኞች  ናቸው ። በቋንቋ ዕውቀት አትራፊ እንጂ ተጎጂ ማንም የለም ።

አርቆ አሳቢያን ሁሉ እንደምታውቁት የዚች፣ የአገራችን  ችግር እንደ በጋ ጉም ብን ብሎ የሚጠፋ አይደለም ። በጥንቃቄ የተሞላ ሥራ እና ሃቀኛ ትግል  ይጠይቃል ። በተለይም የኢትዮጵያ ህዝብ ንቃተ ህሊና ማደግ አለበት ።  ሰውነቱን እና ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን የተገነዘበ ሞጋች እና ጠያቂ ማህበረሰብ መብዛትም አለበት ። ዛሬ እና አሁን ይህ ማህበረሰብ እየበዛ ነው  ። ከደርግ ጀምሮ በቅብብሎሽ እየተካሄደ ያለው የእኔ አውቅልሃለሁ የፖለቲካ መንገድ ያንገሸገሸው ዜጋ በሚሊዮን የሚቆጠር ነው ። በተለይም በትልልቅ ከተሞች ። ዛሬ ይኽ የነቃ ዜጋ ለጥቂት ፊውዳል ፖለቲከኞች ዘላለማዊ መንቀባረር ሢል በመንጋነት እንደማይሞት  የታወቀ ነው ።

እርግጥ ነው  ፣ የነቃውን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያናድዱ ፣ በሥሜት ያልሆነ ሃሳብ እንዲሰጥ እና እንዲፅፍ የሚያሥገድዱ ፣ በክፍያ የሚንቀሣቀሱ ፣ በሥራ አጦት ተገደው ወይም በቀቢፀ ተሥፋ ተሞልተው ለህሊናቸው ሣይሆን ለሆዳቸው  አድረው ፣ ያለአንዳች ፖለቲካዊ ግብ ህዝብን ለማሸበር እና መንግሥት እንዲጠላ ለማድረግ ሰውን በጭካኔ የሚያርዱ ፤ ምናልባትም በታሪካዊ ጠላቶቻችን  የሚደገፉ  አሸባሪዎች  በአገራችን ፣ በተለይም በትግራይ ና በኦሮሚያ ተፈጥረዋል ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እባካችሁን ከሰማችሁ ለአብይ አህመድ የገባህበት ጦርነት አንተንም ከመብላቱ በፊት ወደቀልብህ ተመለስ ብላችሁ ንገሩልኝ

እነዚህን የአገር እድገት እንቅፋቶች ለማሶገድም መንግሥት ፣ በራሱ ማውቅር ውሥጥ ፣ በህቡ ያደፈጡትን የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተባባሪዎች  በጥንቃቄ  እና በህቡ በመመር ር   ሊያሶግዳቸው ይገባል ።

ይኽንን ሃሳብ የማቀርበው ፣ የብዙዎቹን ተከፋይ ዩቲዩበሮችን የሥድብና የዘለፋ ሃሳብ ወደጎን በመተው ነው ። … የኢትዮጵያ መንግሥትን በመሥደብ ፣ በእርግማን እና ባልተገባ ጥላቻ የሚመጣ ለውጥ የለም ። ለአገር ሠላም  ፤ ለህዝቦቾ ብልፅግና የሚመጣው ጉልቻ በመቀያየር አይደለም ። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት በአገር ዘላቂ ሠላም የሚመጣው ህገመንግሥቱ የተከለው በጎሣና በቋንቋ ላይ የተመሠረተ ክልላዊ ማዋቅር ሲፈርስና ዜጎች በዜግነታቸው ሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት አገራቸው መሆኑ በህግ ተረጋግጦላቸው የመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብት ሲኖራቸው ብቻ እንደሆነም አምናለሁ ። ዘመናዊ እና ሥልጡን የፖለቲካ መንገድም ይኸው ነው ። ቻይናም ፣ አሜሪካም፣ሩሲያም፣ኪኒያም፣ጅቡቲም፣ሱዳንም፣ግብፅም፣እሥራኤልም፣ ሲንጋፖርም፣ጃፓንም ( መላው የዓለም ህዝብ ) ዜጋን  የማያበላልጥ የፖለተመካ ሥርዓት ነው ያላቸውና ይኽንኑ  የነቃ ና የዘመነ ፣ ዓለም እየተከተለ ያለውን ፣ የመንግሥትነትን እና  ህዝብን  የማሥተዳደር  መንገድ እንከተል ባይ ነኝ ። …

ሃሳቡ የእኔ ብቻ አይደለም ። እንደ ህልም የሚታየው ይኽ ሃሳብ  የሚሊዮን ዜጎች ሃሳብም ነው ። ይኽ ህልም ያላቸው ፣ የገዘፈ አእምሮ ባለቤቶችም ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው ። ደግሞም ሃሳቡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ተጨባጭ ብልፅግና የሚጠቅም ነውና ቢዘገይም አሸናፊ ሃሳብ ነው ።

 

 

2 Comments

  1. አዳነች (ገደለች) አቤቤን፣ብርሀኑ ነጋን፣አረጋዊ በርሄን የሚያስቆም ስርአት ይጥፋ

  2. አሁን ይህች ሴት ጣት አቀሳሰሯ ትላንት ከአሩሲ የመጣች ትመስላለች? ይበሉህ አዲስ አበቤ አይንህ እያየ ወደ አዳነች አቤቤነት ተለውጠኻል እስክንደር ሲቀሰቅስህ ተኝተህ ነበር ስራህ ያውጣህ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share