December 17, 2022
12 mins read

ከፊውዳላዊ ህሳቤ እንውጣ ! ፊታውራሪ መሸሻነት ብዙ ርቀት አያሥጉዘንም !! – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

በዚች አገር አንድ መንግሥት ነው ያራል ። ያሥተገብራል ።

በዚች አገር ከፍተኛው አደራ የተጣለበት ፣ የመሪነት እና በተመጣጣኝ ኃይል የህዝብና የሀገርን ሠላም የማሥጠበቅ ሥልጣን ያለው ደግሞ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒሥትር ነው ።   የአገሪቱን  ህዝብና ዳር ድንበር ለመጠበቅ በአገሪቱ ህዝብ ተሣትፎ የተቋቋመውን   የመከላከያ እና የፊደራል ሠራዊት  በባላይነት የሚመራውም  ጠቅላይ ሚኒሥተሩ ነው ።

ጠቅላይ ሚኒሥትሩ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ነው ። ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒሥተር የበላይነት የሚመራ  አንድ የጦር ኃይል ብቻ ነው ያለት ። ለዚህም ጦር ዘመናዊነት ጥ ካሬ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ትልቅ ብቻ ሣይሆን እጅግ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል  ።

ወደድንም ጠላንም ኢትዮጵያን እየመሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒሥትር አብይ አህመድ  ናቸው ።  ዛሬ እና ትላንት መልኩን እየቀየረ ራሥ ምታት የሆነባቸውን የጎሣና የቋንቋ ፖለቲካ አደገኝነትም የ ሚያጡት አይመሥለኝም ።  ሆኖም ከኢህአዴግ ህገመንግሥት ጋር ነው እና እየተጓዙ ያሉት ፣  ለትክክለኛው ለውጥ  የአገራዊ ምክክሩን ውሣኔ የሚሹ ይመሥለኛል ።  እሥከዛው ቤት ካልፈረሰ የምትሉ ሰከን በሉ ።  ማፍረስ ቀላል ነው ። መገንባት እጅግ ከባድ ነው ። የትግራዩ ጦርነትን እና ያሥከተለውን ችግር እና ችጋርም አትዘንጉ ።

እንዳልኳችሁ ፣ ጠቅላዩ  አገራዊ የአገራዊ ምክክሩን እና የአገሪቱን ህዝብ ምላሽ ለማይቀረው ለውጥ የሚጠበቁ ይመሥለኛል ። አገራዊ ምክክሩም  ከሆዳም  እና ከራሥ በላይ ነፋሥ ባዮች አሥተሣሠብ የፀዳ እንዲሆንም ይፈልጋሉ ። ይህ ልባዊ ምኞታቸው ይሣካ ዘንድም በመላው ኢትዮጵያና በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን የተቸከለው    የካድሬ አጥር መነቀል አለበት ። የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ምሁራን እና ተማሪዎች ሁሉ ያለአንዳች ሸባቢ በንቃት የምክክር ሃሳብ በሚዘጋጁት መድረኮች ላይ ሁሉ  መሥጠት አለባቸው ።

በበኩሌ “ ዛሬ፣  እና አሁን መጠየቅ ያለበት ጥያቄ የዓለምና የፖለቲካ አካሄድ በመከተል  ፣ ዘመናዋ እና በተጠያቂነት ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲና መልካም አሥተዳደር የሰፈነበት ፣ በመዘጋጃ አገልግሎት ብቻ የሚመራ የመንግሥት ማወቅር እንዘርጋ ና ድህነትን በአጭር ጊዜ ተረት አድርገን ህዝብ በቀን ሦሥቴ እንዲመገብ እናድርግ  ? ወይሥ  አሁን እንደሚታየው ከደርግ ጀምሮ በተዘረጋው ፣  በዓለም በሌለ የቀበሌ ካድሬአዊ ሥርዓት ህዝብን እይንህን ጨፍነህ እያሞኘንህ አንተ በድህነት አረንቋ እየተዘፈቅህ ፣ እኛ ጥቂቶች እንደ ፊውዳል ሥርዓት እያሥተዳደርን በራሣችን የብልፅግና ጓዳና እንገሥግሥ  ? ነው ጥያቄው ። “ እላለሁ ።  ይኽንን ጥያቄ በትክክል መመለሥ አሥፈላጊ ነው ። ለኢትዮጵያ ዜጎች ብልፅግና   የሚበጀው  ዘመናዊው  የአመራር ጥበብ ነው  እንጂ ዘመናዊ የፊውዳልና የጪሰኛ አሥተዳደር አይደለም ።

ዛሬ እና አሁን እየተከተልን ያለነው ሥርዓት የትኛው እንደሆነ ግልፅ ነው ። እነረ አውቅልሃለው ባይነት የተፀናወተው፣ ለጥቂቶች ብዝበዛና ሥርዓተ አልበኝነት የተመቸ የአመራር ሥርዓት ከቀበሌ ጀምሮ በቀድሞው ኢህአዴግ መዘርጋቱ የሚካድ አይደለም  ። ይኽ ሥርዓትም ከዓለም ዘመናዊ አመራር ያፈነገጠ  ሠርዓት ነው ። በኢህአዴግ   ህግ መንግሥት አሥገዳጅነት በህዝብ ሥም ዜጎችን የሚጨቁን ፊውዳላዊ ሥርዓት ተፈጥሮ ይኸው ላለፉት አራት ዓመታት የበለጠ እያመሰን ነው ።

ይኸው ጦሰኛ ህገመንግስት የአገሪቱ ባለቤት አጠቃላዩ ዜጋ ሆኖ ሣለ ፣ አጥር በማጠር ለእያንዳንዱ ክልል ያልተገባ ጉልበት እየሰጠ እና ፊውዳሎችን እየቀፈቀፈ አገርን ከእድገትበመጎተት ህዝቧን እያሥራበ ነው  ። በፊደራል መንግሥት እሳቤ ላይ ያልተመሠረተ እና ከዓለም የተለየ የቋንቋ ፊደራሊዝም አገሪቱን ከፍተኛ አደጋ ላይ እየጣላት ነው ።

አገሪቱ አደጋ ላይ የወደቀችውም የአገሪቱ ባህላዊም ሆኑ ቁሳዊ ሀብቶች የዜጎች በሙሉ እንዳልሆኑ በመቆጠራቸው እንደሆነ ልብ ማለትያሥፈልጋል ። የአገሪቱ ቋንቋዎች በሙሉ ከባህላዊ ሀብቶች የሚመደቡ ናቸው ። እናም የሁሉም ዜጋ ሀብት ናቸው ። እናም በየትምህርት ቤቱ እንደተማሪው ምርጫ ያሉን ቋንቋዎች በሙሉ ለትምህርት ቢቀርቡ  ዜጎች እጅግ ደስተኞች  ናቸው ። በቋንቋ ዕውቀት አትራፊ እንጂ ተጎጂ ማንም የለም ።

አርቆ አሳቢያን ሁሉ እንደምታውቁት የዚች፣ የአገራችን  ችግር እንደ በጋ ጉም ብን ብሎ የሚጠፋ አይደለም ። በጥንቃቄ የተሞላ ሥራ እና ሃቀኛ ትግል  ይጠይቃል ። በተለይም የኢትዮጵያ ህዝብ ንቃተ ህሊና ማደግ አለበት ።  ሰውነቱን እና ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን የተገነዘበ ሞጋች እና ጠያቂ ማህበረሰብ መብዛትም አለበት ። ዛሬ እና አሁን ይህ ማህበረሰብ እየበዛ ነው  ። ከደርግ ጀምሮ በቅብብሎሽ እየተካሄደ ያለው የእኔ አውቅልሃለሁ የፖለቲካ መንገድ ያንገሸገሸው ዜጋ በሚሊዮን የሚቆጠር ነው ። በተለይም በትልልቅ ከተሞች ። ዛሬ ይኽ የነቃ ዜጋ ለጥቂት ፊውዳል ፖለቲከኞች ዘላለማዊ መንቀባረር ሢል በመንጋነት እንደማይሞት  የታወቀ ነው ።

እርግጥ ነው  ፣ የነቃውን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያናድዱ ፣ በሥሜት ያልሆነ ሃሳብ እንዲሰጥ እና እንዲፅፍ የሚያሥገድዱ ፣ በክፍያ  የሚንቀሣቀሱ ፣ በሥራ አጦት ተገደው ወይም በቀቢፀ  ተሥፋ ተሞልተው ለህሊናቸው ሣይሆን ለሆዳቸው  አድረው ፣ ያለአንዳች ፖለቲካዊ ግብ ህዝብን ለማሸበር እና መንግሥት እንዲጠላ ለማድረግ ሰውን በጭካኔ የሚያርዱ ፤ ምናልባትም በታሪካዊ ጠላቶቻችን  የሚደገፉ  አሸባሪዎች  በአገራችን ፣ በተለይም በትግራይ ና በኦሮሚያ ተፈጥረዋል ። እነዚህን  የአገር እድገት እንቅፋቶች ለማሶገድም መንግሥት ፣ በራሱ ማውቅር ውሥጥ ፣ በህቡ ያደፈጡትን የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተባባሪዎች  በጥንቃቄ  እና በህቡ በመመርመር   ሊያሶግዳቸው ይገባል ።

ይኽንን ሃሳብ የማቀርበው ፣ የብዙዎቹን ተከፋይ ዩቲዩበሮችን የሥድብና የዘለፋ ሃሳብ ወደጎን በመተው ነው ። … የኢትዮጵያ መንግሥትን በመሥደብ ፣ በእርግማን እና ባልተገባ ጥላቻ የሚመጣ ለውጥ የለም ። ለአገር ሠላም  ፤ ለህዝቦቾ ብልፅግና የሚመጣው ጉልቻ በመቀያየር አይደለም ። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት በአገር ዘላቂ ሠላም የሚመጣው ህገመንግሥቱ የተከለው በጎሣና በቋንቋ ላይ የተመሠረተ ክልላዊ ማዋቅር ሲፈርስና ዜጎች በዜግነታቸው ሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት አገራቸው መሆኑ በህግ ተረጋግጦላቸው የመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብት ሲኖራቸው ብቻ እንደሆነም አምናለሁ ። ዘመናዊ እና ሥልጡን የፖለቲካ መንገድም ይኸው ነው ። ቻይናም ፣ አሜሪካም፣ሩሲያም፣ኪኒያም፣ጅቡቲም፣ሱዳንም፣ግብፅም፣እሥራኤልም፣ ሲንጋፖርም፣ጃፓንም ( መላው የዓለም ህዝብ ) ዜጋን  የማያበላልጥ የፖለተመካ ሥርዓት ነው ያላቸውና ይኽንኑ  የነቃ ና የዘመነ ፣ ዓለም እየተከተለ ያለውን ፣ የመንግሥትነትን እና  ህዝብን  የማሥተዳደር  መንገድ እንከተል ባይ ነኝ ። …

ሃሳቡ የእኔ ብቻ አይደለም ። እንደ ህልም የሚታየው ይኽ ሃሳብ  የሚሊዮን ዜጎች ሃሳብም ነው ። ይኽ ህልም ያላቸው ፣ የገዘፈ አእምሮ ባለቤቶችም ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው።  ደግሞም ሃሳቡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ተጨባጭ ብልፅግና የሚጠቅም ነውና ቢዘገይም አሸናፊ ሃሳብ ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop