December 17, 2022
29 mins read

“ ሿሿው “ ከቀጠለ ፣ ነገ ፣ ልጆቹን የሚበላ አብዮት መፈጠሩ አይቀርም ። ሲና ዘ ሙሴ

Oromo song

የኦሮሚያ ክልል መዝሙር / የአማርኛ ትርጉም /
ኦሮሚያ ( 2)የትልቅ ህዝብ ታሪክ እናት
የኦሮሞዎች እምብርት ፥ የገዳ ስርአት አዳራሽ
የህግና ስርአት መሬት ፥ የጨፌ ኦዳ እናት
የብልጽግና ልምላሜ ፥ ሁሉን አብቃይ እናት
የመቶ አመት እድፍ ፥ በደማችን አጠብንልሽ
በብዙ እልፍ እልቂት ፥ ባንዲራሽን ከፍ አደረግን
ደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ ፥ ስልጣንን መልሰን አገኘን
ሰላምና ዴሞክራሲ ፥ የሰብአዊነት መብት
አስተማማኝ ልማት ፥ ዘላቂ ልማት
ከህዝቦች ጋር ሰላምና ፍቅር
ለመኖር ዋስትና ትልቅ አላማ አድርገን
ኃይላችንን አሰባስበን ፥ ተነስተናል ተማመኚብን
ኦሮሚያ አብቢ ፥ ለምልሚና ኑሪ!

ኦሮሚያ ማናት ? እንደዚህ የተንቆላጰላጠሰችው ?  አንድ ቋንቋ ተናጋሪ እንደ ተፈጥሮ ዛፍ ፤ በ1983 ዓ/ም በአሜሪካ ኢፔሪያሊሥቶች እርዳታ ሥልጣን በያዙ እናቸንፋለን ባዮች ኦሮሞ የተባለ ሰው ፣  ከመሬት የበቀለባት ናት እንዴ ? የዓለም የሣይንሥም ሆነ የኃይማኖት ታሪክ ይህንን ቅጥፈት ፅድቅ ነው በማለት የሚደግፈው ይመሥላቸዋል  እንዴ ? ከሣይንሥ እና ከዳሪዊን ህሳቤ እንኳን ሥንነሳ  የመጀመሪያው ዝንጀሮ ማነው ? ከኃይማኖት አንፃርሥ የመጀመሪያዎቹ አዳምና ሄዋን ኦሮሞች ናቸውን ? ናቸው ከተባለ ፣ የዓለም ሰው ሁሉ ኦሮሞ ነው ። ማለት ነው ።

ደግነቱ በፈጣሪ ዘንድ መላው ዓለም ላይ የሚገኘው በአርያ ሥላሤ የተፈጠረ በሙሉ መጠሪያው ሰው ነው ። ቋንቋ አይደለም ። ፖለቲከኞች ያልነቃውን ህዝብ ለማሞኘት የፈጠሩት የቆዳ ማዋደድ ፖለቲካ ሲኦል እንጂ ገነተ አያሥገባም ። የዛሬ ገንዘብህ በእንኮኮ ኪሊማንጃሮ ሊያሶጣህ ይችላል ። ሆኖም የኪሊማንጃሮን ግዙፍነት አያጎናፅፍህም ። “ ሾሾህን “ እዛ ጣለው ። ከኢትዮጵያ ጠላቶች የተቀበልከውን የቤት ሥራ በቢሊዮን ዶላር በህቡ እንደምታቀሳቅሥ ፣ ባንኩን እንደተቆጣጠርክ ሁሉ ፣ ታንኩን ለመቆጣጠር ና የድሮኑንም ቁልፍ  በእጅህ ለማሥገባት  የተነቃበትን ሿሿ ይዘህ በድጋማ መምጣትህ ያሣፍራል ።

በመጠኑ ሞዲፋይ በሆነ ሿሿ  በአዲስ አበባ ብጥብጥ የፈጠርከው ራሥህ ነህ ። “ What’s Lov got to do , got to do with it?  … But a second hand emotion ? “ ( Tina Turner )  አለች አሉ ፤ትልቁ  ሰውዬ በ1997 ዓ/ም  ምርጫን ተከትሎ  “የአና  ጎሚዝን “ እና የፕሮ ብርሃኑንን መሞዳሞድ አሥተውለው ¡¡

እኔም በአዲሳ አበባ ሉአላዊ አሥተዳደር ውሥጥ የቆዳ ማዋደዱ ፖለቲካ ምን አገባው ? ህዝብ እንደ ዜጋ በፍቅር አብሮ እየኖረ ሣለ ህዝቡን እንደ በግ፣ፍየል፣በሬ ፣ አህያ፣ላም ፣ዶሮ በአጠቃላይ እንደ ግል የቤት እንስሳ መመልከት ጤነኝነት ነው ፤ ትላላችሁን  ? በማለት “ ትምህርት ውሥጥ የክልል አርማ ምን ጥልቅ አደረገው ? “ እላለሁ ። ሌላ ሥውር ነብጥብጥ አጀንዳ ከሌለ በሥተቀር  ። “ ከወንዙ በላይ  ሆነው ነፁህ ውሃ እየጠጡ ታች ከነሱ በታች እየጠጣ ያለውን ፣ ለምን ውሃውን ታደፈርሳለህ ብሎ መቆጣት ፤ ምን ማሐት ነው ? “ሣታሜከኝ ብላኝ ….” አለች …

ይኽ  በማይሙ ና በሥሜት ተነጂው ህብረተሰብ ብቻ ሣይሆን በመላው አሥተዋይ የኢትዮጵያ ህዝብ ማላገጥ ነው ። የሚገርም ማላገጥ ።

የሚገርም ማላገጥ ፣ ያውም በሚሊዮኒ የአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ።   የራስን ትርክት እያዳመጡ የአዲስ አበባ ህዝብ አቋም ይሄነው እያሉ መቀለድ ፣ ከደርግ ጀምሮ ሲተገበር የኖረ የሠለቸን ድራማ እንደሆነ እንዴት የዛሬ ባለሥልጣናት ዘነጉት ? የአዳነችም ሆነ የጃዋር አሥተሳሰብ መንጋውን በመፎገር ቢያንሥ ተንቀባርሬ እኖራለሁ የሚል ደርጋዊ እና ኢህአዴጋዊ በህዝብ ሥም የመቀሐድ አባዜ ነው  ። የህሊና ቢስነት መንገድንም ነው ።  እነዚህ ለጥቅም ሲሉ ብቻ ዘረኛ የሆኑ ፣ ሰውን በሰውነቱ ብቻ እንዳይመለከቱ ገነዘብ ና ምቾት አይናቸውን ያወራቸው እብድ ሰዎች  ፤ ዜጎችን  እንደ ሰው በኩል ደረጀሠ ያለማየት  የአእምሮ ህመም አለባቸው ። ከህመማቸው የተነሳም  ሰዎች እንደ ሰው ተፋቅረው እንዲኖሩ ፈፅሞ አይፈልጉም ። ሰዎች ተደበልቀው  እንዳይኖሩ የሚያደርግ የሤጣን ሥርዓትን ለማንበር ነው ጥረታቸው ።  ይኽ ደግሞ በዓለም የሌለ ሰው ጠል አሥተሣሠብ በመሆኑ ሊተገበር አይችልም ።

ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ 99% ሰውና ዜጋነኝ የሚል ነው ።1% ደግሞ ከሆዱ አኳያ ሰውነቱን ረስቶ ፣ ከዓለም ሥልጣኔ እና የዛሬ እና አሁን ማህበራዊ አኗኗር አፈንግጦ ፣ ለማግበሥበሥ እንደ ጅብ  ተቧድኖ መንጋ በመፍጠር “ እኔ ቋንቋ ነኝ “ ባይ ነው ።

በዘር የተደራጁ ፣ ነፃ ሰው ሳይሆኑ የቋንቋ ባርያ የሆኑ በአገር ውሥጥ ሥልጣን ይዘው ፣  በጫካ ሰው ለማረድ መንጋውን አሠማርተው ፣ በውጪ አገር ( በነቃው እና ሰው መሆኑንን በተገነዘበው የበለፀገ አእምሮ ባለው ህብረተሰብ ውሥጥ እንደሰው ታቅፈው እየኖሩ ፣ ) በኢትዮጵያ ውሥጥ  የእንስሳት ሥርዓትን ለማንበር ሌት ተቀን እየቸፍጨረጨሩ ነው ።

የዓለም ህዝብ   ሰው  ና ዜጋ ነኝ በማለት በጋራ በፍቅር እየኖረ ፤ አሜሪካ በዲቫ አያሌ አፍሪካዊያንን ዜጋዋ እያደረገች ( ዘመናዊ የባሪያ ንግድ ይሉታል ። አንዳንዶች )  ኢትዮጵያውያን ሰውና ዜጋ ሆነው ሣለ ፣ “ አንተ ቋንቋ ና ዘር “ ነህ ማለት ምን ማለት ነው ?

ይህ  የኢንተርሃሙዬ ተግባር ነው ። አዲስ አበባ በደም እንድትታጠብ የፈለጉትም እና ጃዋር እና አዳነች አቤቤ ናቸው ( አዳነች አቤቤ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወይም ደሞ ሥኳር አቅመሰዋት ሊሆን ይችላል ። ጃዋር ግን በዓላማ እና በተላላኪነት እንደሆነ መቶ ፐርሰንት የተረጋገጠ ነው ። )

ጃዋርና ግብረ አበሮቹ ( በመንግሥት መዋቅር ውሥጥ ተሰግስገው ) ሁሌ በቁርጥና በውሥኪ ከርሳቸውን እየሞሉ እና  በጥጋብ እያናፉ ፣ አፍንጫቸው ሥር ያለውን ሞት ዘንግተው   ፤በምት ላይ ያላግጣሉ ። በቀን አንዴ ለመመገብ ጭንቅ የሆነበትን ምንዱባንን ፣ በሽብርተኝነት ይከሳሉ ። የፈረንሳዩን ሪቭሎሺን በገዛ እጃቸው ለማምጣት ይኽን በአሥተዋይነት ዝም ያለ ትውልድ ለምን  በተዋጊ ጥፍራቸው የጎነትሉታል  ? ዝም ያለ ትዕግሥተኛ ሰው ሁሉ ፣ ፈሪ ና ቧቅቧቃ ይመሥላቸዋልን ?  …. አይናቸው በትዕቢት ሥለታወረ  አያዩትም እንጂ ይህ ትውልድ በሁሉም ረገድ እጅግ የነቃ እሳት ትውልድ ነው ።

ወጣቱን አገር ተረካቢውን ፣ የተማረውን ፣ አሥተዋዩን ትውልድ ልቡን አላወቁትም ። አይነ ልቦናቸው ታውሯልና !   የታወረውም አገርን ለማሸበር በተለገሱት ገንዘብ ባፈሩት ሀብትና ንብረት እንደሆነ ይታወቃል ።   ነገን በዕውርነታቸው ከቀጠሉ ፣ ያፈሩት ንብረት ብቻ ሳይሆን እነሱም ያለቀናቸው ትቢያ   ሊሆኑ ይችላሉ ።

ልበ ዕውሮቹ ፣ ህሊና ቢሶቹ ፣ የነገን ጥፋት ማየት አይችሉም እና  ይኽቺን ታሪካዊት አገር ኢትዮጵያን መነገጃ አድርገዋታል ። ህዝቧን ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ እያጭበረበሩት እና እያዘናጉት በሥውር ረብጣ ዶላር እየተቀበሉ አገርን እየሸጡ ነው ። አገር ፈርሳ የት እንደሚኖሩ ባናቅም ፣ ህሊና ሥለሌላቸው   መንጋ በመፍጠር ፣ሰው  ፣ እንሥሣ ሆኖ ሰውነቱን  ረስቶ በቋንቋ ተቧድኖ እንደ  ጥንቱ ኋላ ቀር  ጦርነት በሥለት እንዲጨፋጨፍ እያዘጋጁት ነው ። ይሄንን ያልተረዳ ማንኛውም ኃቀኛ ዜጋ ደግሞ ነገ እጣ ፈንታው ጥርስ ማፋጨት እንደሚሆን ተገንዝቦ ይኽንን የህሊና ቢሶች ሴራ ለመቀልበስ ያለእንቅልፍ መታገል ይኖርበታል  ። …

ለመሆኑ “ ኦሮሚያ “ በኢትዮጵያ  ፣ ሥር ናት  ወይስ ብቻዋን አገር የሆነች ናት ? ከቶስ ይኽቺን ኦሮሚያ የተሰኘች ምድር ማን ጠፍጥፎ ሰራት ?  ኦሮሞ የተሰኘውን ሥያሜ ማነው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጣት  ? እራሥህ መልሥ ? ዞረህ ዞረህ አዳምና ሄዋን ጋ ትሄዳለህ ። አንተ ሰው ነህ በቃ ። ሌላውን የፖለቲካ ዲሥኩርና ትርክት ወደዛ ጣልው ። ትልቅ እግዛብሔር እንጂ የሰው ወይም የዘር ትልቅ የለም ። “ ሁሉም ውሥጡ ሥጋና ደም …” አለ በጣፋጭ ዜማ ፣ አብዱ ኪያር ።

ኦሮሚያ የተሰኘችው ክልል መሆኖን ነው የምናውቀው ። በኢትዮጵያ ጉያ ሥር ያለች  ። በወያኔ ዘመን በነ ኩማ ደመቅሳና በእነ አልማዝ መኮ  ፊት አውራሪነት የኦነግን የፖለቲካ አጀንዳ በኦህዴድ አማካኝነት እንድትተረጉም የተደረገችም ናት ኦሮሚያ  ። የኦነግን አፍ ለማዘጋት በመለሥ ዜናዊ ለአክራሪና  ለጠባብች እንዲሁም “ለቆዳ አዋዳጆች”  የተለገሰች የጥቂቶች ኬክ ናት ኦሮሚያ ። “ አፋን ኦሮሞን “ ከግእዝ ፊደል ወደ ቀኝ ገዢዎቹ የላቲን ፊደል ያሸጋገረች ።  ላቲን በእጅ ብልጫ የፀደቀላት ። ዘጠኝ ሰዎች በሚሊዮኖች የፈረዱባት  … ዛሬ እና አሁን ፣ የቆዳ ማዋደድ ጦሳቸው የዋሁን ዜጋ የሚያሳርድባት ፤ ናት ኦሮሚያ ።

ዛሬ ኢትዮጵያ ” ዩቶጵያ ” ለመሆን እየተንደረደረች ነው ። የምናብ ፣ የተምኔት ኢትዮጵያ ። መንግሥት እንደመንግሥት ሲሆን የማይታይባት ። ለሥልጣን ያበቁኝ ናቸው ውለታቸውን አልዘነጋም በማለት እውነትን አድበስብሶ ለማለፍ የሚጥርበት ። ሥልጣንን እንዳያጣት ንግሥናንን እሥከእርጅና ለመዝለቅ ሃቀኛ ኢትዮጵያውያን ወደ ሥልጣን መወዳደሪያ መድረክ እንዳይመጡ የእሣት አለንጋ መያዙን የሚያሳይባት ናት ይኽቺ አገር ።

መንግሥት ሸንጋይ ሆኖ ፣ “ ላም አለህ በሰማይ ! “ ይልሃል ።  ህዝብን ለማሞኘት በተመሣሣይ የሽንገላ ቃላት ዛሬም ይጠቀማል ። ነገሩ ይገርማልም ያሥቃልም  ። ድራማው በኮመዲ የተጀመረ ትራጀዲ ፍፃሚ ያለው መሆኑ ነው እያሥገረመ የሚያሥቀው ።

ዛሬ ደግሞ  የአሜሪካ መንግሥት ፖለቲካውን እንደ እግር ኮሥ ጫወታ አይቶታል ። እርግጥ ዛሬ እና አሁን ኳሷ በፕሬዝዳንት ባይደን እግር ሥር ናት ። እሳቸው በፈለጉት አቅጣጫ ኢትዮጵያን ለመውሰድ ይችላሉ ። የዛሬው የኢትዮጵያ ሁኔታም ለአሜሪካ መንግሥት አመቺ ነው ። “ ሌቦች የዘረፉትን ሀብት  በአገሪቱ ኢንቨስት  እሥካደረጉ ጊዜ ደረስ አትንኳቸው ። ተባብረን በመበዝበዝ እንበልፅግ ! ! “ ነው ፣ የአሜሪካኖቹ መፈክር ። ( it eat, Let me be soil , USA) ማለት ብቻ ነው የሚያዋጣው ። አፈር ሥህን እያሉ USA ን በአፍ ፣ በአፍዋ ማጉረስ ። …

በተረፈ ዛሬ ማንም ህዝብን ለመሸንገል ብቃት የለውም ። ዓለም ዛሬ በእያንዳንዱ  የኢንተርኔት አጠቃቀም ባወቀ ሰው ሁሉ መደፍ ውሥጥ ናት ። የዓለም መንግሥታት ከሥልጣን ውጪ የተለየ ኃይልና ጥበብ የላቸውም ። በቲዎሪ ደረጃ የሁሉንም ሙያዊ እና ጥበባዊ እውቀት ለማወቅ ወይም ቢያንሥ መሠረታዊውን ዕውቀት ለመጨበጥ  እጅግ ቀላል የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል ። ለበረታ ደግሞ ቲዎሪውን እሥተጥግ ማወቅ ከባድ አይደለም ። እናም ማንም  በትወራ እየሸነገለ  በኢቲቪ ፣ በፋና ፣ በዋልታ ፣ ” እየከደረ ” ህዝብን በደምሳሳው መሸንገል ከቶም አይችልም ። እንደ ኢህአዴግ የአገዛዝ ዘመነሰ( ዛሬም ሹመኞቹ ኢህአዴጎች መሆናቸውን አላጣሁትም ። )  የበዛ  ካድሬ እና የተደናበረ   ግራናቀኙን  የማያውቅ አፋሽ አጎንባሽን  ሰብስቦ  ከኢትዮጵያ ባንዲራ ይልቅ የኦሮሚያ አርማ በአዲስ አበባ ላይ ይንገሥ ማለት ቅዠት ነው ።  ከኤቨረስት ተራራ በላቀ መልኩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ  ታላቅ ነው ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለምን ብሎ ሞተና !! …

ይኽን ያለዕውቀት መንቀዥቀዥ ያመጣው ፣ ሥለዓለም ታሪክ ብቻ ሣይሆን ሥለ ሰው አፈጣጠር ፈፅመው ያለነበቡ ማይም የፖለቲካ ሰዎች በድንገት ፣ ፈፅመው ሳያሥቡት ፣ በ1983 ዓ/ም አራት ኪሎን በጠመንጃ ኃይል ሥለተቆጣጠሩ እንደሆነ በብዙ ጥናት ተረጋግጧል ። ዛሬም ሥልጣን እውቀትና ጥበብ የሚመሥላቸው ናቸው ፤ ራሳቸውን መምራት ሳይችሉ ፣ ህዝብን እንመራለን በማለት ዜጎችን ሠላም የሚያሳጡት  ።

ከ1983 ዓ/ም በኋላ ፣ እውቀት እና ጥበብ  ዓልባ ሰዎች ሚኒሥቴር ሆነዋል ። ባለሥልጣን ሆነዋል ። መኮንኖች ና ጀነራሎች ሆነዋል ። ዲሲፕሊን ገደል ገብቷል ።ሥልጣን  ካለህ በሰማይ መንገድ አለ እና ዲግሪው ፣ ማሥትሬቱ በሲቪል ሰርቪሱ አማካኝነት ታድሏል ።  አንዳንድ የምዕራብ ዩኒቨርሲቲዎችም በዶላር ዲግሪዎችን ሸጠዋል ። እናም መንግሥት በቀጣፊዎች ተሞልቷል ። ዛሬ ደግሞ ቀጣፊ አገርን እንደወረራት  ታውቋል። እናም  ያለዘረኝነት ሥልጣናችን ዘላለማዊ አይሆንም በማለት በቋንቋ ዘረኝነት  የሚያላዝኑትን ሰው መሆኑንን የተገነዘበው አማርኛ ፣ ኦሮምኛ፣ትግሪኛ፣ ሱማሊኛ፣አፋርኛ፣ሲዳምኛ ፣ወላይትኛ፣ሃድይኛ ፣ ዶርዝኛ ፣ ቅማንትኛ ፣ ሐረሪኛ፣ሐመርኛ ፣ ወዘተ ። ተናጋሪው ፣ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ግን ፈፅሞ  አይሰማቸውም ።

ዛሬ ፣ ለኢትዮጵያ ሠንደቅዓለማ  እንሰዋለን የሚሉ ወጣት ጀግና ዜጎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ መሆናቸውን ያስተውሉ ። ከህፃንነት  ጀምሮ የሰው ባልሆነ ዘረኝነት ልጆችን አግልሎ በማሥተማር  ዘላለማዊ ንግሥና እናገኛለን ብሎ ማሰብ በራሥ ላይ እባብ መጠምጠም እንደሆነም  እያሳዮቸው ነው  ። በማህበረሠቡ ውሥጥ እየኖረ ያለን ወጣት እንደ ጋሪ ፈረስ ማድረግ ከቶም አይቻልም ። ለአንተ ለማይሙ እና ነገ ትቢያ ለምትሆነው ፤ ተንቀባሮ መኖር ሲል ሥለ ዓለምና ሥለ ሰውልጅ አፈጣጠር ከአንድ ፕሮፊሰር እኩል የሚያቅ የኦሮምኛ ተናጋሪ ወጣት ልጅ ፣ የአማርኛ ተናጋሪ ወጣት ልጅ ፤ የትግሪኛ ተናጋሪ ወጣት ልጅ ፤  የአፋርኛ ተነጋሪ ወጣት ልጅ ፤ የሱማሊኛ ተናጋሪ ወጣት ልጅ ፣ የአፋርኛ ተናጋሪ ወጣት ልጅ  ።ወዘተ ። እንደትላንቱ  በከንቱ በመንጋነት የሚሰዋልህ እንዳይመሥልህ ።

እርግጥ ነው ፣ ትላንት በቦናፓርቲዝም የተዘፈቀውን  ህወሃትን ገንዘብ እየከፈሉ “ በመንጋ አብዮት “ ከሥልጣን ያሶገዱት የግብፅ ተላላኪዎች ነበሩ ። ህውሃት ከ1983 ጀምሮ በዘረኝነት ፣ በፀረ _ ኢትዮጵያዊነት እና በምሁር ጠልነት የፈፀመው ግፍ  ፅዋው ሞልቶ በመፍሰሱ ፈጣሪ ቅጣቱን ሰጥቶታል ። ጥቂት ፣ የእጃቸውን ያላገኙት  ግፈኞችም የእጃቸውን እንደሚያገኙ   አልጠራጠርም ። በበኩሌ በፈጣሪ ተስፋ ቆርጬ አላውቅም ።

ዛሬ  በአዲሰ አበባ እንገዛለታልን ፣ ገዢያችን ነው ያሉትን ፣ ህገመንግሥቱን በመጣሥ ፣ በማንኛውም ማህበረሳባዊ ግንኙነት የተጣመረውን ፣ አብሮ የሚበላና የሚጠጣውን የአዲስ አበባ ወጣት እርስ በእርሱ በማጋጨት ፣ የቀውስ እና የብጥብጥ ድግሳቸውን  በመላው ኢትዮጵያ ለማዳረስ ጥረዋል ።   ግን ግጭቱን በጠመቁት የኦሮሚያ የመንግሥት ባለሥልጣኖች እና በዘረኛ ፓርቲዎች እና ግጭት በመጥመቅ በታወቁ ግለሰቦች ላይ  መንግሥት እርምጃ አልወሰደም ። የአዲስ አበባ ፖሊሥም ሆነ የፊደራል ፖሊሥ ሹማምንቶችም ከግጭት ጠማቂው የተበረከተላቸው የአፍ መዝጊያ የተቀበሉ ይመሥል ለመብቱ የታገለውን ወደ ማጎሪያ ካምፓቸው ወሥደውታል  ።

ደጎስ ያለ ረብጣ የአፍ ማዘጊያ ና የመተባበሪያ ብር በመቀበል ፣ ባለ ቪላ ቤት ሆነዋል ና ለክፍያቸው እየተገበሩት ያለ አገር የሚያዋርድ ሥራ ነው  ። ባለ መኪኖች ፤ በየከተሞቹም ባለ ቪላዎቹ ከፍተኛ የፊደራል ፖሊሥ ባለሥልጣናት እና የኦሮሚያ ፖሊሥ አባላት ናቸው ። ሥንቶቹ እንደሆኑ ለማወቅ ከፈለግህ ፣ በየ ከተማው  ዙሪያ የተገነቡትን  ቪላ የባለሥልጣናትና የፖየኦሮሚያ ፖሊሥ ና ልዪ ኃይል ቤቶች በላሥቲክ ቤት የሚኖረው ምንዲባን አንድ ሁለት ብሎ ቆጥሮ ይነግርሃል ። በዚች አገር እኮ የደም ነጋዴው ከእሥከ አይባልም ። ጥቂት የማይባልው የየቀበሌውና የየወረዳው ፖሊሥ አዛዥ በአዳዲስ ፎቆች  ውሥጥ ባለ ሱቅ መህኑንም እወቅ ።

ከዚህ አንፃርም  የብልፅግና መበስበስ እውን ሆኗል ማለት እንችላለን  ። ብልፅግና በስብሶል ።  የፖሊሥ አዛዥ ይቅርና ተራ የቀበሌ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ  ሥልጣኑንን ተገን አድርጎ ፣ ከሌባ እና ህሊና ቢስ  ባለሀብት ተብዬ ያሻውን  ይለገሳል  ። ( ቤት ፣ መኪና ገንዘብ ፣ ወዘተ ።) ሁሉም ባይሆን ጥቂት የማይባለው በሚጢጢ ሥልጣኑ አማካኝነት ያልተገባ ጥቅም ያገኛል ። ዛሬ ብዝበዛው እና ዘረፋው  በልማት ሥም የሚከወን ነው ። ብልፅግና ከኢህአዴግ የበለጠ መብስበሱን መሪው በውል የተገነዘበ  አይመሥልም ። ብዙዎች ግን ” አብይ ሿሿ እየተጫወተ ነው  ። ሃቀኛውን ለማ በከንቱ ኮነነው ። ” ይላሉ ። …አንዳዶችም  ”  ከቤቱ ሲወጣ የሚያቸው መልካም ነገሮች እጅግ የበሰበሰውን እና የገማውን የሰፊው ህዝብ መኖሪያና ህይወት  እንዳያይ ጋርዶት ነው እንጂ  እርሱ እጁ ከሌብነት የፀዳ ነው  ። ” በማለት ሿሿ ይጫወታሉ  ። እንዲህ እና እንዲያ  ይባል እንጂ አብይ ከቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ከኮሎኔል  መንግሥቱ ውድቀትም ሆነ ፣ ከኃ/ማርያም እጅ መሥጠት የተማረ አይመሥልም ።

” እንዴት ? ” በሉ ። እንዴት ማለት በጣም ጥሩ ነው ። የጥሩ አድማጭ ና አንባቢም ወግ ነው ።

እሥቲ ዞር ብላችሁ አሥታውሱ ከመጋቢት 24/ 2010 ዓ/ም በኋላ ባሉ 9 ወራቶች በጠቅላይ ሚኒሥቴር ዶ/ር አብይ አማካኝነት ተአምር የተባሉ ክስተቶች የኢትዮጵያ ህዝብ አይቶ ተደሥቷል ። በግፍ የታሰሩ የፖለቲካ እሥረኞች ተፈተዋል ። ከኤርትራ ጋር የኢትዮጵያ ህዝብ ፍቅር እንደሆነ አሳይተዋል ።

ይኽንን የሥርነቀል የለውጥ ጅምራቸውን ጀነራል አሣምነው ፅጌ በማድነቅ ዶክተሩን ፣ ” ኢትዮጵያዊው ሙሴ ” ብለዋቸው ነበር ። ይሁን እንጂ እኝህ ጀነራል  በአምባቸው መኮንን ሞት ሰበብ እንዲገደሉ ተደርገዋል ። የአምባቸው መኮንን  ምሥጢርም    ከጀነራሉ ሞት ጋር ሊቀበር ችሏል  ። እና ይህ እውነት ምንን ያመለክታል ። “ አብዮት ልጆቾን ትበላለችን ? “… ወይስ የሿሿ ጫወታን ?

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop