የተመድ የሠላም አስከባሪ ኃይል ኢትዮጵያ ውስጥ ይግባ!!! ሀርማ ሙራ! ሀርካ ሙራ! ኖርሜ ሙራ!  ከመጠምጠም ትምህርት ይቅደም!

ኢት-ኢኮኖሚ             /ET-  ECONOMY

(ክፍል አንድ) ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

ገለልተኛ የስብዓዊ መብቶች አጣሪ ኮሚቴ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው የዘር ፍጅት፣ የጦር ወንጀልና የስብዓዊ መብቶች ጥስቶችን አጣርተው ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ የኢትዮጵያ ህዝብ ይጠይቃል፡፡የተመድ የሠላም አስከባሪ ኃይል ኢትዮጵያ ውስጥ ይግባ!!! ሀርማ ሙራ! ሀርካ ሙራ! ኖርሜ ሙራ!  ከመጠምጠም ትምህርት ይቅደም! በመንጋዎቹ ወንዶች የሚፈጸመው ጥቃት ሰለባዎች ሴቶች፣ ህጻናትና፣አረጋዊያን ዜጎች መሆናቸው በእውን ኢትዮጵያ ውስጥ አስራዘጠኝ ሚሊዮን ሰዎች የአይምሮ በሽተኞች እንደሆኑ ጥናቶች በማስረጃ አረጋግጠዋል፡፡ መንጋዎቹን የሚያሠማሩ የክልልና የፌዴራል መንግስት ሥልጣን የጨበጡ በሽተኛ ፖለቲከኞች በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ቀርበው ሊዳኙ ይገባል እንላለን፡፡   

የዘር ማጥፋትን የሚፈፅም፣  የስብዓዊ መብት ጥስት ወንጀል፣ የጦር ወንጀልና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚያፍን  የብልፅግና መንግሥት ህዝብ የመግዛት ብቃትና የሟራል ልዕልና የለውም፡፡ ህወሓትና ኦነጋዊው ብልፅግና ከአሜሪካና አውሮፓ አገራቶች እህል እየተሠፈረላቸው  በህዘብ ርሃብ ለፖለቲካ ትርፍ የሚነግድ ባለሥልጣን ወንጀለኞችን በዓለም ፍርድ ቤት አቅርቦ የሚቀጣው አካል ሊኖር ይገባል!!! በአሜሪካ መንግሥት ባወጣው H-R-6600 እና S-3199 ረቂቅ ህግጎች በሰሜኑ ጦርነት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈፀሙ የስብዓዊ መብት ጥስት፣ የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂዎቹን የኢትዮጵያና ኤርትራ ባለሥልጣኖችን በነፃና ገለልተኛ አካላት በሄግ ፍርድ ለፍርድ መቅረባቸው የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡

የዘር ማጥፋት መንስዔው የጥላቻ ንግግር ጥንስስ እርሿ በአድርባይ የዘር ፖለቲከኞች ተሰራጭቷ በህዝቡ ህሊና ውስጥ ሰርፆ በመንጋው በተስተጋባ ጊዜ የሚፈጠር የዘር ግጭት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሃገራችን የዘር ፍጅት (ጀኖሳይድ) የፖለቲካ ሴራ የተወጠነው በሻብያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ በወያኔ መሪ መለስ ዜናዊና በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) መሪ ሌንጮ ለታ በደርግ ዘመን  በወለጋ ውስጥ የዘር ፍጅት ፈፅመው ለኢትዮጵያዊያን የመቶ አመት የዘር ፖለቲካ የቤት ስራ ሰጥተናቸዋል ያሉ ጊዜ ነበር፡፡ ጦርነቱን ከሰሜን ወደ መኃል ሃገር እናሸጋግረዋለን  ያሉት የዛሬ ሠላሳ አመት ነበር፡፡

        ከኖቬል ወደ ሄግ! ሩጫዬን ጨርሻለሁ! ከትግራይ ወደ አማራ ጭፍጨፋ፣ ከመጠምጠም ትምህርት ይቅደም!

{0} ‹‹የዓይናቸው ቀለም ካላማረን እናስወጣቸዋለን!!!›› …..‹‹እንኳን ከእናንተ ተወለድኩ!!!›› መለስ ዜናዊ {1} «ወደ ትግራይ አንድ ማክስ እንጅ አንድት ጥይት አልክም»….«ከ14ዓመቴ ጀምሬ ለኦሮሞ ህዝብ ታግያለሁ»…«ወለጋ ከሄድኩ ይገሉኛል፣ በመጨረሻም ከጅማ ህዝብ ጋር ይጋደላሉ»……ክርስቲያን ማለት አማራ ነው አማራ ማለት ክርስቲያን ነው፡፡›› ዶክተር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት ከተናገሩት ‹‹ለኦሮሞ መሬቱ ማለት ማንነቱ ማለት ነው፡፡  ከአንድ ክፍለዘመን በላይ ሲሰደብ፣ሲጨቆን ሲፈናቀል የነበረው በመሬቱ ምክንየት እንጂ በማንነቱ ምክንያት አይደለም፡፡ በተለይም መሬት ለመምህራን ስንሰጥ፣ ለባለሃብቶች ስንሰጥ የከተማችን የህዝብ ስብጥር አይቀየርም ብላችሁ የምታስቡ ብትኖሩ ሁለት ሶስቴ ደጋግማችሁ አሰቡ፡፡  በዘፈቀደ (መሬቱን) አድለን አድለን ስናበቃ (ዶሞግራፊውን) ሲቀየር ለምን ተቀየረ ብለን መጮህ አንችልም፡፡ በኛው ውሳኔ ነዋ የተቀየረው፡፡ በርካታ ለውጦች የተመዘገበ ቢሆንም የመሬቱ ጉዳይን በተመለከተ ከተሞች ሥራቸውን በጥንቃቄ እንዲያከናውኑ ማሳሰቢያ የሰጡት  ደግሞ  ዶክተር አብይ አህመድ በምክትል ፕሬዜዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ የከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስትር  ናቸው፡፡›› …………………………………(1)

‹አዲስ አበባ ላይ መዝሙር ተዘመረ ኦሮሙኛ እና ተረኝነት ነው የሚል ተረት ነበር፡፡ አዲስ አበባ ላይ ከፍተኛ ኦሮሞ ጠል ኃይሎች ኦሮሞን የሚጠሉ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር የሚያስቡ ሰዎች ኦሮሞኛ ተዘመረ አሉ!!!›› ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ  

‹‹በአንድ ጀንበር መቶዎች፣ መቶ ሺዎች የሚታረዱበትን ትራጀዲ እንፈጥር ይሆናል እንጂ መንግሥት መሆን አንችልም፣ አንችልም፡፡ ለምንድነው ያን ያደረከው ካላችሁኝ እንደሆነ ከቡራዩ፣ ከሰበታ፣ ከለገጣፎ አርሶአደር ወጣት ተደራጅቶ እየመጣ ነው፣ ሊዋጋ እየመጣ ነው፡፡ መንግሥታችን ተነካ ብለው፡፡››  ዶክተር አብይ አህመድ

{2} ‹‹በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን አንገት ቆርጠው ጭንቅላት ጦር ላይ ሰክተው ጋዜጣዊ መግለጫ አሮሚያ ውስጥ ሲሰጡ እያየን ነው፡፡ ድሮ በመኢሶን ዘመን እንደሚባለው ‹የነቃ እና የተደራጀ ህዝብ ያሸንፋል› ህዝቡ በቻለው አቅም ተደራጅቶ ያለውን አቅም በሙሉ ተጠቅሞ ራሱን መከላከል አለበት፡፡ ድሮ አፄዎቹን ‹ሀርማ ሙራ› ‹ጡት ቆራጭ›፣ ‹ሀርካ ሙራ› ‹እጅ ቆራጭ›፣ ነበር የምንላቸው አሁን ደግሞ ‹ኖርሜ ሙራ› ‹አንገት ቆራጭ› መጥቶብናል፡፡ አሁን ላይ ፈጣሪም መንግሥትም ይጠብቀኛል ብሎ መቀመጥ አያዋጣም በተቻለው አቅም ተደራጅቶ ራስን መከላከል ያስፈልጋል፡፡›› ……‹‹መሬት እንጂ ሰው የለም›› ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሞትን የመረጡ ወጣት ሴቶች የመጀመሪያውን ብቻኛ የነፃነት ተጋድሎ ምዕራፍ ከፈቱ። የምዕተ ዓመቱ ማህጸን ተስፋን ሰነቀ!

{3} ‹‹ፊንፊኔ ላይ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ እጅግ በጣም ቀላልና አንድ ነገር ብቻ ናት፡፡ እርሶም ፊንፊኔ በኦሮሚያ አስተዳደር ስር መመለስ ብቻ ነው፡፡ በኦሮሚያ አስተዳደር ስር አልተዳደርም የሚል ዘረና ካለ ወደ መጣበት ክልሉ መሁደረ ይችላል፡፡ አሻፈረኝ የሚል ጥጋበኛ ደግሞ ካለ በህግ ልክ ማስገባት ነው፡፡ ስለዚህ እባካችሁ ማጭበርበሩን ሌብነቱንና ማወናበዱን ተወትና ህጋዊ ስራ ስሩ፡፡ እነርሱ ሲወሩን የእኛን ፍቃድ ጠይቀውና አማክረውን ነው እንዴ?››……. “የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአዲስ አበባ ከንቲባ መሆን ያለበት ኦሮሞ ብቻ ነው” ብርሃነመስቀል አበበ ሰኝ፣

{4} ‹‹ተርቦ አጥንት ሆኖ፣አጥንትና ስጋ ብቻ ሆኖ፣ የወለጋ ህዝብ ተቀብሎ መሬቱን ሰጥቶቸው፣ በሬውን ስጥቶቸው፣……..ሰው ያደረጋቸው የወለጋ ህዝብ ነው፡፡ …….ወደ ወለጋ ሲመጡ እህል ጭነው ነው እንዴ የመጡት ……..ከሞት አፋፍ ላይ የነበሩትን ሙታንን ወስዶ ሰው አደረጋቸው፡፡ ዛሬ ትልቅ ሆኑ፣ ዛሬ ኃብታም ሆኑ፡፡ ዛሬ ትልቅ ሆኑ፡፡ የወለጋ ህዝብ እጁ አመድ አፋሽ ሆነ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ የኦሮሞና የአማራ ደም እንዳላቸው ሳውቅ እኔ……….የኢትዮጵያ ህዝብ ተዘጋጅ፡፡ ዛሬ ኦሮሞብቻ አይደለም አይምሰላችሁ፡፡ ለእያንዳንዳችን እቤታችን ይመጣል፣ ስለዚህ ይሄንን መጠበቅ ነው፡፡››……… ‹‹አትግዙ አትሽጡ አትለውጡ››  በቀለ ገርባ…………………………….(2)

{5} ‹‹የኦሮሞ ወጣቶች አንገት ተቀልቶ ከወለጋ ቡሬ ድረስ ተወስዶሽለላና ፉከራ ሲካሄድበት አይተናል፡፡ ሆኖም ግን የእነሱም ጭንቅላት አንድ ቀን እንደሚቀላ በደንብ አልተረዱትም፡፡ ቲት ፎር ታት፡፡›› ዶክተር ረጋሳ ኦልጅራ………………………….…….(3)

{6} ‹‹ይሄ የአዲስአበባ ህዝብ አጀንዳ አይደለም፡፡ ይሄ የነሸኔ የተለያዩ እነ ጽንፈኞ ፋኖ ከዚያ በኃላ ደሞ ምዕራባዊያን እጅ ያለበት አጀንዳ ነው፡፡›› አዳነች አቤቤ

{7} ‹‹ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጣ!!!››…“Ethiopia out of Oromia!” ….‹‹ዲቃላ›› ጁሃር መሃመድ፣

{8} ‹‹እንደሰባበሩን ሰባበርናቸው›› ‹‹አዲስ አበባን ኦሮሙማ እያደረግናት ነው!!!››ሽመልስ አብዲሳ፣

{9} ‹‹ደማቸው ውስጥ ያለው አማራ ብሔር እንጂ ›› ኩምሳ ዲርባ (ጃል መሮ)

{10} ‹‹ስሜን የቀየረብኝ ምኒልክ ነው!!!፣›› ኮነሬል አበበ ገረሱ፣

{11} ‹‹የኢትዮጵያ ቌንቌ ኢትዮጲኛ ይባል›› ህዝቅየል ጋቢሳ፣

{12} ‹‹ጦርነቱ አልቆል፡፡ ከእንግዲህ ከማን ጋር ነው የምንደራደረው? ›› ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ

{13} ‹‹ያለቀው ሰው ቁጥር አሳዛኝ ነው፡፡ ማለት አሁን (Morbid exitment) የሚሉት አላቸው ፈረንጆች፡፡ በአስክሬን መደሰት ቢኖር ሙሉውን አቅርበሽ ሰው ቆቅ እስኪለው ድረስ ቢያየው እኔ ፐርሰናሊ አንዳንዴ እንደዛ እላለሁ፡፡ እያለቁ እንደሆነ አያውቁም ወይ? ሰው እያለቀ እንደሆነ አያውቁም ወይ?›› ጌታቸው ረዳ

{14} ‹‹ቲፒኤልኤፍ ሰላሙን ማስጠበቅ ችሎል፡፡ That is great! ጥሩ ነገር ነው፡፡ ሌላ ኢትዮጵያ ክፍል በምን እንዳለ እኮ እያየን ነው፡፡ግን ይሄ የትግራይ ህዝብ ጨዋነት ነው፣ ይሄን ያስገኘው፡፡ ያለፈውን በልቡ ይዞ ግን አሁን ይሄ ነገር ማንሳት ጊዜው አይደለም ብሎ፣በሆደ ሰፊነት ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ ውስጡ ነገሮችን አምቆ እየሄደ ያለው፣ ይሄ ሊያታልል አይገባም፡፡ ትዕግሥት ድንበር አለው፡፡ የትግራይ ህዝብም ይታገሳል፣ አስተዋይ ነው፡፡ ትልቅ አክብሮት ያስፈልጋል፡፡ ይገባዋል፡፡ ግን ደሞ የሚጠብቀው ነገር አለ፡፡››…….‹‹ኢሳያስ አፈወርቂ ጦርነት እንደማንፈራ ደግመን እናስታውሰዋለን››  ስዬ አብርሃ

{15} ‹‹ከባድ የሆነ ተፅዕኖ ነበር፣ ከዛ አማርኛ ለመማር ያጠፋሁት ጊዜ በህፃንነቴ በጣም ይቆጨኛል!!!››ሜ/ጀ ተክለብርሃን ወ/አረጋይ

{16} ‹‹ኢትዮጵያዊነት ራሱን በራሱ ያጠፋ ተነተከሲስ የሆነ ማንነት ነው!››  ‹‹ኢትዮጵያዊ የሆነ ማንኛውንም ሰው ሰላም እንዳትሉ!›› አሉላ ሰለሞን (ቲኤምኤች)

{17} ‹‹አረመኔያዊ ድርጊት እንደፈፀሙባችሁ፣ እናንተም አረመኔዊያዊ ድርጊት ፈጽሙባቸው ›› አንዳርጋቸው ፅጌ

{18} ‹‹የአማራ ናሽናሊዝም የሚባል የለም ነው እኔ የምለው፡፡ ከኖረ ግን ከኖረና እግዚአብሄር አይቅናው፡፡ ቀንቶት ስልጣን ከያዘ የአማራ ናሽናሊዝም የሂትለርን የሚመስል ፋሽዝም ነው፣ እዚህ አገር የሚወለደው፡፡ ናሽናሊዝም ሁሉ ዲስቲኔሽኑ ፋሽዝም ነው፡፡ ›› ዶክተር ደረጀ ዘለቀ

ተጨማሪ ያንብቡ:  አዟሪና አከፋፋዮች ለምን አንድ ለአምስት አይደራጁም? (ጽዮን ግርማ)

{19} ‹‹አንደኛ በምንም ዓይነት የአማራና ኦሮሞ ግጭት አይደለም፡፡ይሄ የተወሰኑ የአበዱ ሰዎች ስልጣን ለማግኘት ስልጣን ላይ ለመቆየትና በምንም መንገድ ቢሆን ይሄን ጥቅማችንን እናስከብራለን ብለው የሚያስቡ ኃይሎች ከሁሉም ሳይድ ያሉ ኃይሎች የሚያደርጉት እንትን ነው፡፡………….የሰው ልጅን አንገት ቆርጦ በዱላ ማሳየት ወይም እሳት አንድዶ ከዛ በኃላ ፎቶ ስልፊ መነሳት ይሄ የሰው ልጅ ባህሪ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊፈጠር የሚፈለገው አንድ እንትን መንግሥት የለም ነው፡፡›› ፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ

{20} ‹‹በጊዜዊ ማጎሪያ ካንፕ መቆየት አለባቸው!!!›› መሳይ መኮንን (ኢሳት)

{21} ‹‹ በጣም ቀላል እኳ ነው፡፡ አየር ኃይል ያላት አገር ናት፡፡ ዝም ብለህ እያንዳንዱ ከተማ ላይ አስር አስር ቦንብ አፈንድተህ መጨረስ ትችላለህ ጦርነቱን በሁለት ቀን፡፡ ምን ይሄን ያህል ይከብዳል! ይሄን ያህል እኳ ከባድ አይደለም፡፡›› ሙሐዘ ጥበባት ዳይቆን ዳንኤል ክብረት

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሹማምንቶቹ ከመቦተልካቸው በፊት መጀመሪያ ጽፈው የጻፉትን እንዲያነቡ አዋጅ መታወጅ አለበት፡፡የአይምሮ ህመም በከፍተኛ ጥላቻ ውስጥ ሰምጠው በተግባር ማድረግ ያልቻሉትን በቃላት የሰው ዘርን፣ ብሄሮችን የሚጨፈጭፉበት የጥላቻ ስለት ሆኖል፡፡ እናንተም አክሉበት፡፡

 

 

ኢት-ኢኮኖሚ             /ET-  ECONOMY

የተመድ የሠላም አስከባሪ ኃይል ኢትዮጵያ ውስጥ ይግባ!!! ሀርማ ሙራ! ሀርካ ሙራ! ኖርሜ ሙራ!  ከመጠምጠም ትምህርት ይቅደም!

(ክፍል ሁለት) ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

 

በዶክተር አብይ አህመድ አገዛዝ ዘመን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኦነግ ሸኔ የተገደሉ አማራዎች ከሰባት ሽህ ቁጥር በላይ አሻቅቦል፣የቆሰሉ ሰዎች በሽህ ይቆጠራሉ፣ የተዘረፉ የቁም ከብቶች አራት መቶ ሽህ በላይ ይገመታል፣ የተቃጠሉ ቤቶች ብዙ ሽህ ይቆጠራል፣ 68 (ስልሳ ስምንት) ቤተክርስቲያኖች ተቃጥለዋል፣ 46 (አርባ ስድስት) መስጊዶች ተቃጥለዋል፣ 84 (ሰማንያ አራት) ወፍጮ ቤቶች 163 (መቶ ስልሳ ሦስት) ትምህርት ቤቶች ወድመዋል፣ ብዙ መኪኖች ተቃጥለዋል፣ 756 (ሰባት መቶ ሃምሳ ስድስት) ትምህርት ቤቶች ተዘርፈዋል የትምህርት ማስረጃዎች ተቃጥለዋል፡፡325 (ሦስት መቶ ሃያ አምስት) ሽህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ 5227(አምስት ሽህ ሁለት መቶ ሃያ ሰባት) አስተማሪዎች ከስራ ውጪ ሆነዋል፡፡ በወለጋ 500 (አምስት መቶ) ሽህ ህዝብ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በተመሳሳይ በምዕራብ ሸዋ ዞን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች 647 ንፁሃን አማሮችን መግደላቸው ተገልፆል፡፡ 1252 (አንድ ሽህ ሁለት መቶ ሃምሳ ሁለት) የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 85 (ሰማንያ አምስት) ሽህ ህዝብ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ 26.7 (ሃያ ስድስት ነጥብ ሰባት)  ሚሊዩን ብር የሚገመት ንብረት ወድሞል፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት በጦርነቱ 11.6 (አስራአንድ ነጥብ ስድስት) ሚሊዮን ህዝብ አስቸኮይ የስብዓዊ እርዳታ ድጋፍ  እንደሚያስፈልጋቸው ተገልፆል፡፡ ከዚህ ውስጥ  9.3 (ዘጠኝ ነጥብ ሦስት) ሚሊዮን ህዝብ በሰሜኑ ጦርነት በእርሻ ዘርፍ እንዳያመርቱ የተገደዱ ገበሬዎች ናቸው፡፡ 2.3 (ሁለት ነጥብ ሦስት) ሚሊዮን ህዝብ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆኑ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች የተጠለሉ የነፍስ አድን ድጋፍ ምግብ፣ መድኃኒት፣ መጠለያ ወዘተ የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡ የአማራ ህዝብ በተለይ በወለጋ ኦሮሚያና በመተከል ቤኒሻንጉል ክልሎች   ያሉት ህዝብ ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ቆስለዋል፣ ንብረታቸው ተዘርፎል  ምንም የቀረን ነገር የለምና ከነዚህ የሰዎች እርድ ቄራዎቸ ስቃይና መከራ ተላቀን ወደፈለግንበት በሰላም እንድንሄድ የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ድምፅ ተነስቶ ነፍሳችንን እንዲያድን በህፃናቶች፣ በእናቶችና በአረጋዊያኑ ስም እንጠይቃለን፡፡

‹‹ኢሰመኮ በርካቶች የተቀጠፉበትን የሰሞኑን ጥቃት ጨምሮ ከሐምሌ 2014 ዓ.ም እስከ ኅዳር 2015 ዓ.ም የደረሱ ግድያዎችን፣ የአካል ጉዳቶችን፣ እንዲሁም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ስለተፈናቀሉባቸው ግጭቶች እና ጥቃት ዛሬ ኅዳር 28/2015 ዓ.ም. ሪፖርት አውጥቷል።በእነዚህ ዞኖች ከሰላማዊ ነዋሪዎች በተጨማሪ የመንግሥት የፀጥታ እና የአስተዳደር አባላት መገደላቸውን፣ የመንግሥት እና የሲቪል ሰዎች ንብረቶች መዘረፋቸውን እንዲሁም ወድማቸውን አመልክቷል።››

‹‹በስድስት ወራት የደረሱትን ግጭቶችና ጥቃቶች ያስከተሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም በመገምገም፣ በሰብዓዊ መብቶች መርሆችና ድንጋጌዎች መሠረት እጅግ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች (grave violation of human rights) ተብለው የሚመደቡ መሆናቸው በርካታ አመላካቾች አሉ ብሏል።››

‹‹በዚህም መሠረት ጥቃት እና ግጭት እየደረሰባቸው ያሉ ስፍራዎችን በሪፖርቱ አካቷል። እነዚህም ጥቃቶች በሆሮ ጉድሩ፣ በምሥራቅ፣ በምዕራብ ዞን፣በቄለም ወለጋ ዞኖች፣ እንዲሁም በሰሜን ሸዋ፣ ኢሉ አባቦራ ዞን፣ በቡኖ በደሌ ዞን፣ በምሥራቅ ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና በአርሲ ዞን መሆኑም ተጠቅሷል።››በተጨማሪም በሁለቱ የጉጂ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በተለይም በኪረሙ፣ ጊዳ አያና፣ አልጌ፣ ሁሩሙ፣ በአሙሩ፣ ሆሮ ቡሉቅ፣ ጃርደጋ ጃርቴ፣ ቦሰት፣ ግንደበረት፣ ጮቢ፣ ደራ፣ ኩዩ፣ መርቲ ጀጁ እና የአርሲ ዞን አጎራባች ወረዳዎች እያጋጠሙ ያሉ ግጭቶች እና ጥቃቶችን በመከታተል ላይ እንደሚገኝም ገልጿል። እነዚህ ጥቃቶችና ግጭቶች የሚከሰቱባቸው አካባቢዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ እንደሆነና እያስከተሉት ያለው የሰብዓዊ መብቶች ቀውስ ደረጃ አስከፊ ነው ብሏል።››

‹‹ዚህም መሠረት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች፣ በመንግሥት እራሳቸውን እንዲከላከሉ በሚል የታጠቁ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ከሌሎች ክልሎች ጭምር እንደመጡ እና በተለምዶ በአካባቢው የአማራ ታጣቂዎች መሆናቸውን የሚነገር የታጠቁ ቡድኖች እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ወይም መንግሥት ሸኔ ብሎ የሚጠራው ኃይል ይንቀሳቀሳሉ ብሏል።››

‹‹ታጣቂ ቡድኖች አካባቢዎችን በሚቆጣጠሩበት ወቅት መንግሥትን ወይም ሌላኛውን ታጣቂ ቡድን ትደግፋላችሁ በሚል በርካታ ግድያዎችና ጥሰቶች ይፈጸማሉ ብሏል። በተጨማሪም ዝርፊያዎች፣ በግዳጅ የሚጠየቁ የገንዘብ ክፍያዎች ነዋሪዎችን ለከፋ ስቃይ መዳረጋቸውም ኮሚሽኑ ጠቅሷል። በሌላ በኩል በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችም እንዲሁ ታጣቂ ቡድኖችን ትደግፋላችሁ በሚል ከፍርድ ውጪ ግድያዎች መፈጸማቸውን መረጃዎች አግኝቻቸለሁ ብሏል። እንዲሁም መንግሥት ታጣቂ ቡድኖችን ኢላማ በማድረግ በሲቪል ሰዎች የመኖርያ ሰፈሮች አቅራቢያ በሚፈጽማቸው የአየር ጥቃቶች፣ ሕገ ወጥና የዘፈቀደ እስሮች፣ ተጠርጠሪዎችን የማሰቃየት ተግባራት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ እንደሆነም ከኢሰመኮ ሪፖርት መረዳት ይቻላል። የፖለቲካ አመለካከትን ወይም ታጣቂ ቡድኖችን ትደግፋላችሁ ከሚሉ ግድያዎች በተጨማሪ ብሔርን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ሆን ተብለው መፈጸማቸው አሳሳቢ እንደሆነም ገልጿል።››

‹‹ኢሰመኮ የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥቱ ተቀናጅተው በአፋጣኝ እና በሙሉ ትኩረት በመሥራት ዘላቂ ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥቷል። የነዋሪዎችን ደኅንነት ማስጠበቅ፣ አፋጣኝ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲቀርብ ሁሉንም ባለድርሻዎች ማስተባበር እንዲሁም በቂ የፀጥታ ኃይልም ሊሰማራ እንደሚገባም አሳስቧል። የፀጥታና የደኅንነት ሁኔታ የመፍጠሩን ኃላፊነት ጨምሮ በአካባቢዎቹ መድረስ የሚገባውን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ማስተባበር የሚችል መዋቅር እንዲዘረጋ ጠይቋል።››

“በእነዚህ ዞኖች ውስጥ በአሁኑ ወቅት የሚገኙ ነዋሪዎች ያሉበት በተዋጊ ቡድኖች መካከል መውጫ የሌለው አጣብቂኝ ውስጥ መጠለፋቸው ቢያንስ በተሟላ መልኩ ለመግለጽ/ለማስተጋባት የሚያስችል ሁኔታ እንኳን አለመኖሩ ከደረሰው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተነጥሎ ሊታይ የማይገባ ሲሆን አጠቃላይ ሰቆቃው ከዚህ የበለጠ ሊቀጥል ስለማይችል ሳይውል ሳያድር ሰላማዊና ዘላቂ መፍትሔ ሊደረግለት ይገባል” በማለት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ መግለፃቸው በመግለጫው ሰፍሯል።……………………….(4)

 

መደምደሚያ

ኢንተርናሽናል ሪስክ ኮሚቴ ሪፖርት መሠረት በ2023 እኤአ ዓለም አቀፍ ስብአዊ ቀውስ በአንደና ደረጃ ሱማሊያ በሁለተኛ ደረጃ ኢትዮጵያ በሦስተኛ ደረጃ አፍጋኒስታ እንደሚሆኑ ተገምቶል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከአነጋገር ይፈረዳል ከአያያዝ ይቀደዳል - ጥላሁን ዛጋ

“ International Rescue Committee (IRC) Somalia, Ethiopia and Afghanistan top IRC’s list of countries most at risk of deteriorating humanitarian crises in2023.Climate, economic turmoil and conflict deepen humanitarian crises worldwide.”…………………………………….(5)

‹‹በኢትዮጵያ በአጠቃላይ 21.2 (ሃያ አንድ ነጥብ ሁለት) ሚሊዮን ዜጎች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ፣ ከእነዚህ ውስጥ 16 (አስራስድስት ሚሊዮን ህዝብ) በድርቅ የተጎዱ፣ እንዲሁም 4.6 (አራት ነጥብ ስድስት) ሚሊዮን የተፈናቀሉ መሆናቸው ተገልፆል፡፡ በጦርነቱ አንድ ሚሊዮን ወጣቶች አልቅዋል፣ በመቶ ሽህ ወጣቶች አካላቸው ጎሎል፣ እንዲሁም አንድ ትሪለየን አምስት መቶ ቢሊዮን ብር የሚገመት የመሠረተ-ልማት ውድመት በሁለቱ ዓመት ጦርነት ተመዝግቦል፡፡  በዚህም የተነሳ አራት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ህዝብ ከቀያቸው ተፈናቅለው በተለያየ መጠለያ ጣቢያ ይገኛሉ፣ አስራስድስት ሚሊዮን ዜጎቻችን በድርቅና ርሃብ ቸነፈር እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡ በመላ ኢትዮጵያ ለደረሰው ስብዓዊና ቁሳዊ ጉዳቶች ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው የፖለቲካ ድርጅቶችና ሹማምንቶች ተጠያቂ እስካልሆኑ ድረስ ፍትህና ርትህ በኢትዮጵያ ምድር አይኖረውም፡፡ በህወሓት ኢህአዴግ መንግሥት ዘመን የተቀረጸው ህገ- መንግሥት ምን ይላል፡-  ‹‹ማንኛውም ሰው ስብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና፣ የነጻነት መብት አለው፡፡››አንቀጽ 14 …….‹‹ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው፡፡ ማንኛውም ሰው በሕግ  በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡›› አንቀጽ 15……‹‹ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ መብት አለው፡፡›› አንቀጽ 16  ተፈፃሚ ለማድረግ ተጠያቂነት መቅደም አለበት እንላለን፡፡ መንግሥት ህግ ማስከበር ባለመቻሉ ምክንያት ነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሠላም አስከባሪ ኃይል እንዲገባ የሚጠየቀው፡፡ በወለጋ በኦነግ ሸኔ ተከበው በህይወትና በሞት የሚገኙ ከሃምሳ እስከ ሰባ ሽህ ሰዎች የመኖር ተስፋ በተመድ የሠላም አስከባሪ ኃይል በመግባት እንጂ በፌዴራል ሠራዊት ወይም ልዩ ፖሊስ ኃይል ወይም በኦነግ ሸኔ እንዳልሆነ ህዝብ ይናገራል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጸሙ የዘር ፍጅት፣ የጦርነት ወንጀልና የስብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂዎቹን ለህዝብ ማሳወቅና ለውይይት ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት፡-

 

1ኛ/ ህወሓት ኢህአዴግ ለሃያ ሰባት አመታት ግንባር ሆነው የገዙ ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴድ በዋነኝነት አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሎቹ  ም/ሊቀመንበሮች  እና ካቢኔያቸው ውስጥ በፊትና አሁን የሠሩ ሁሉ፤ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡

2ኛ/ ህወሓት፣  በዋነኝነት ህውሃት እና አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሉ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱን ከመለኮስ ጀምሮ እስከአሁን ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና ቁስዊ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡

3ኛ/ ገዥው ፖርቲ ብልጽግና እና አመራሮቹ፤ በዋነኝነት ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱ ተጀምሮ እስከ ተጠናቋል በተደጋጋሚ ጊዜ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ ከደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ የተደረገው የሰላም ስምምነት ድረስ በንጹሀን ዜጎች ላይ ለደረሰው የህዝብ እልቂት፣ ሞት፣ መደፈርና ስደትና  ሰቆቃ፣ ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡

4ኛ/ የኤርትራ መንግስት፤ በተለይም ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፎወርቂ፤ በወታደሮቻቸው ለተፈጸመው ዝርፊያ፣ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር፤ እነዚህ አካላት በአንድ ወይ በሌላ መልኩ ለተፈጸሙት የመብት ጥሰቶች፣ ጭፍጨፋዎች እና ግጭቶች፤ ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ይሁን፤ ማድረግ የሚገባቸውን ባለማድረግ ተጠያቂ ናቸው፡፡

 

ምንጭ

  • Ethio 360 Zare Men Ale “እንባ ወደ ደም ሲቀየር የተሰወረው እንባ ጠባቂ” Thursday April 08, 2021 – YouTube
  • ‹ኩሽሚዲያ ኔትወርክ አቶ በቀለ ገርባ/ በወቅታዊ ጉዳዬች ዙሪያ ልዩ ቆይታ
  • ኩሽሚዲያ ኔትወርክ / የኦሮሞ ህዝብ እራሱን የመከላከል መብት አለው፡፡ /ዶክተር ረጋሳ ኦልጅራ/ በውጭ ሀገራት የኦነግ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ
  • በኦሮሚያ ክልል ‹እጅግ ከፍተኛ የስብዓዊ መብት ጥስቶች› እየተፈጸሙ እንደሆነ ኢሰመኮ አስታወቀ/ ቢቢሲ አማርኛ/ 7 ታህሳስ 2022
  • Somalia, Ethiopia and Afghanistan top IRC’s emergency watchlist 2023. https://www.rescue.org

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share