የመርገም አርማ የጥላቻ ዜማ! – ከቴዎድሮስ ሃይሌ

ኦህዴድ/ኦዴፓ የሕወሃት አሮጌ የሞት ሌጋሲ ወራሽ:: ወያኔ እንደ ጭቃ አቡክቶ እንደ ኩበት ጠፍጥፎ የተዛባ ትርክት አስታቅፎ ነብስ የዘራበት አዛውንት ግን ጨቅላ ድርጅት:: ኦዴፓ ሕወሃት ያስታጠቀውን የርዕዮት ጥብቆ ያሥጨበጠውን የጥላቻ ምርኩዝ ያጠመቀውን የበታችነት ስሜት ጥሎ ዘመኑን መዋጀት ያልቻለ ገባር:: በባርነት የተሸለመውን የመርገም አርማ የጌትነቱ ማሳያ ሰንደቅ ያደረገ ሞኝ ::

ሃገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል መሬት ሲያረጅ መጅ ያበቅላል አበው እንዲሉ:: ፖለቲካችን የሃገር ማርጀትና የሞራል ቁልቁለት ላይ መሆናችን ማሳያ ሆኗል:: ገበታ ሙሉ ጮማ ቀርቦ ስለ ፍርፋሪ የሚጨነቅ : ጽዋ ሙሉ ወይን ጠጅ አስቀምጦ ቅራሪ መፈለግ ጤነኝነት ነውን? ጠቅላይ ሚንስትሩ ከንቲባው ማርሻሉ ባንኩም ታንኩም ሌላው ሌላውም ኦሮሞ ሆኖ: የሃገሪቱ የፖለቲካ ስልጣን የሚዘወረው በኦሮሞ ሆኖ ማለቃቀስ ምን ማለት ነው:: ኢትዮጵያን ያህል ሃገር ይዞ እንዴት አንድ ከተማ በስርዐት ማስተዳደር ያቅታል::

የኦሮሞ የፖለቲካ ኤሊቶች በትልቁ ማሰብ አልሆነላቸውም እንጂ ዛሬ በታሪክ አጋጣሚ እጃቸው ላይ የወደቀውን ሃገር የመምራት እድል ከዛም በላይ አሻግረው የአፍሪካ መሪ አሰባሳቢና ተምሳሌት መሆን በቻሉ ነበር:: ነገር ግን አልሆነም :: ወርደው ወርደው ሃገራዊ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ የሆነውን በሃውርታዊ ከተማ አዲስ አበባን የእኛና የእኛ ነው የሚለው አጉራ ዘለልነት ያሳፍራል:: የመርገም ሰንደቅ ስቀሉ የሚለው ዋይታ የጥላቻ ዝማሪያቸውን አዚሙልን ማለት በእርግጥ ዘመኑን የሚዋጅ ተግባር ነው:: ሃገር እየመሩ ለመንደር አርማ ሃገር ማሸበር ተማሪዎችን ማንገላታት አለመሰልጠን የመሪነት ብቃት ማጣት ወይስ ጨልምተኝነት:: ይሄ ተግባር እንወክለዋለን የሚሉትን ሕዝብ ይመጥናልስ ወይ ? ኦዴፓ ከሕወሃት የወረሰው የገለማ ዜማና የሻገተ ሰንደቅ ኦሮሞስ እንደ ብሄር በጋራ ይስማማበታል:: ቢያንስ ቢያንስ እንኳ የኦነግ የኦፌኮን እና ደርዘን የሚሞሉት የኦሮሞ ድርጅቶች የጋራ ተግባቦት የሌለበትን ቡቱቶና የጥላቻ ዜማ ልጆቻችን በምን እዳቸው ነው የሚቸገሩበት::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመረራ ጉዲና እና የዳውድ ኢብሳ ነገር (ሰማነህ ጀመረ)

የሞኝ ዘፈን ሁሌም ሆሆይ ነው እንዲሉ የኦሮሞ ብልጽግና /ኦዴፓ/ ትልቅ ሃገር ይዞ መንደር የሚፈልግ ቤተመንግስት ገብቶ በረት የሚያምረው ዙፉን ላይ ተቀምጦ ድብዳብ የሚናፍቀው; ጮማ እየቆረጠ በቂጣ የሚጎመጅ.:: ግራ የተጋባና የተሳከረ ከየት እንደመጣ ወዴት እንደሚሄድ ምን እንደሚፈልግ በቅጡ የማያውቅ ጮርቃ ድርጅት ከሕወሃት ውታፍ ነቃይነት ወደ መሪነት ማማው ላይ ቢደርስም ዛሬም ያው እርጥብ ::ከስነልቦና ስብራቱ ያልተፈወሰ ሞራለ ቢስ ድኩማን ቡድን ነው::

የበታችነት ስሜት ከኤድስ ይልቅ የሚያመነምን: ከትራኮማ ይብስ የሚያሳውር ሐብት የማያረክሰው እውቀት የማያሽረው ስልጣን ሹመትና መሪነት የማይፈውሰው ከባድ ደዌ ነው:: አሁን ያለው ሁኔታ የሚያንጸባርቀው ይህንን እውነታ ነው:: እስቲ አሁን ምን የሚሉት ተግባር ነው አዲስ አበባ ላይ የሚደረገው:: ያለው ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግር ሳይፈታ የደፈረሰው የሰላም እጦት ያስክተለው ከባድ ብሄራዊ ቀውስመፍትሄ ሳያገኝ ሌላ ሕዝብን የሚያለያይና የሚያጫርስ አጀንዳ ማራገብ ሃገር ከሚመራ ገዢ ፓርቲ አይጠበቅም::

ሕግ አስፈጻሚ ሆነው ሕግ የሚያፈርሱ ማህበራዊ መሰረታቸውን የሚያናጉ ፖለቲካዊ ፉይዳ ማህበራዊ ጥቅምየሌለው በአንጻሩ ግጭት የሚጭር እጅግ የወረደ አጀንዳ ማራገቡ የበላይነትን ለማሳየት በሌሎች ላይ ያለን ጉልበት ለመፈተሽ የስነ ልቦና ቀውሳቸው ማሳያ ከመሆን ውጪ አንድም ምክንያት የላቸውም::

የሕወሃት አልጋ ወራሾች የሆኑት የኦዴፓ ኦነግ ኤሊትች ሕዝባቸውን የማይመጥኑ ሗላ ቀሮች ሃገር ለመምራት የተሰጣቸውን እድል ለብጥብጥና ሃገር ለማፍረስ እያዋሉት ነው:: በተዛባ ትርክት ጠላ ሰክረው ጥላቻና ውድመትን ስራ አድርገውታል:: ኦሮሚያ ንጹሃን ዜጎች አቅመ ደካሞችና ሕጻናት በማንነታቸው ብቻ እየተለዩ በግፍና በጅምላ የሚጨፈጨፉባት የሰው ቄራ አድርገዋታል:: ኦሮሚያ ዛሬ ወደ ጥንታዊ ጋርዮሽ ዘመን ተመልሳለች:: ዜጎች ወጥተው የማይገቡባት ለነዋሪዎቿ ገሃነብ የሆነች ነጋዴና ባለሃብት የማይደፍራት የአራጆችዋሻ የዘራፊዎች መሸሸጊያና የፖለቲካ ነጋዴዎች የደራ ገበያ ሆናለች::

ተጨማሪ ያንብቡ:  አዲሱ የህወሓት ዕቅድ እና “ጠንቋይ” አክቲቪስቶቹ! - ስዩም ተሾመ

ይህ ሁሉ የኦሮሚያ ክልል ቀውስ ሕዝቡ የፈጠረው አይደለም:: 50 አመታት ኦነግ አንዲት ቀበሌ ሳይዝ ዶሮ ከመስረቅና አሮጊት ከመግደል ውጪ የከፉ ችግር መፍጠር ያልቻለው በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው የኦሮሞ ሕዝብ ጸጥታውን ማስከበር በመቻሉ ነው:: ያ የኦሮሞ ሰላማዊና ኢትዮጵያዊ ባህልና ጨዋነት ዛሬ ልጆቹ ነን የሚሉት ተረኞች ሃገር ሲመሩ የበለጠ ጎልቶ መታየት እንዳይችል ወያኔ ባሪያ አድርጋ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ያሰማራችው የሌጋሲዋ ወራሽ ኦዴፖ ኦሮሞን ሳይሆን ሕወሃትን በመምሰሉ ስርቆት ውሽት ዝርፊያና ቅሚያ የኦሮሚያ መገለጫ አድርጎታል::

ሕዝቡ አሁንስ በዛ ገለማን ታከተን ስለ ሰላምና ፍቅር ችግሮችን ሁሉ ማለፉችን የፍርሃት አይደለም እያለ ነው:: የነገ ሃገር ተረካቢ ልጆች የተሻለ ትምህርት የሚያቀራርብ ተግባር ስብዕናቸው በትላንት ሳይሆን በነገ ላይ እንዲገነባ ማድረግ ሲገባ የባርነት ዜማ ተቀኙልኝ ማለት ያሳፍራል:: ትንሾቹ ልጆች ከኛ ተሽለው የመለያየትን ግንብ ሲንዱት ቆም ብሎ እንደማሰብ ጉልበትን ሕጻናት ላይ መጫን ቃላት ሊገልጹት የማይችሉት የምዕተ አመቱ ድንቁርና ነው:: የኦሮሞ ብልጽግና ሰዎች እባካችሁ ተመከሩ እንደ እናንተ ሕዝቡ አልተመቸውም የኑሮ ውድነቱ በልቶ ማደርን አክብዶበታል:: የዜማና የቡቱቶ ችግር የለበትም:: እናንተው ተሰብስባችሁ የፈለጋችሁትን ሰንደቅ ስቀሉ አዚሙ ጨፍሩ ልጆችን ግን ከቆሻሻችሁ እንዲጎነጩ አትጫኑ:: አለያ ወዳጃችሁ መራራ እንዳለው የተራበ ሕዝብ መሪዎቹን ይበላል::

የመጣችሁበትን መንገድ ዞር ብላችሁ አስተውሉ :: ይህ ሕዝብ ከተነሳ እንኳን በቁማርና ግርግር ለስልጣን የበቃ ሻጋታና ገባር ድርጅት አይደለም የአውሮፓን ብካይ ግራዚያንን ያዋረደ የዚያድባሬን አክርካሪ ስብሮ ዳግም ያንበረከከ ህዝብ ነው:: ጦርነት ባህሌ ነው ባዩን ትምክህት ያሳበጠውን ጠመንጃ ነካሹ ጌታና ፈጣሪያችሁሕወሃት እንዳ አሮጌ ጎማ ተንፍሶ የተንበረከከው በኢትዮጵያውያን ክንድ እንጂ በልፍስፍሱ የኦዴፓ አራጅ ቀማኛና የመንደር ድስት ገልባጭ አይደለም::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሰለማዊ ትግል ፋይዳ (ከአብርሃ ደስታ)

አዲስ አበቤው መላው ኢትዮጵያውያን ይህንን ጉግማንጉ የብጽግና እንኩቶ በቃህ ሊለው ይገባል:: ኦሮምኛን እንደ ቋንቋ መማር ተጨማሪ እውቀትና ሃገራዊ ጌጣችን ነው:: ይህን የሚቃወም ማንም ጤነኛ እይምሮ ያለው ዜጋ የለም:: ችግሩ የመርገም እርማና የባርነት ዜማችው ጋር ነው:: ሌላው የኦሮሞ ኤሊቶች ችግር ከአማራ ጋር ብቻ የመሰለው ካለ ተሳስቷል:: እንኳን ለሌሎች ብሄሮች ለእራሱ ለኦሮሞ ሕዝብ የማይመጥንና ቅቡልነት የሌለው ሽብር ጠማቂ ቀውስ ፈልፉይ ድርጅት ነው:: በጨዋነት ስለ ሰላም ሲል የመረጠውን የአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ ፉሽስታዊ አጀንዳ ለመጫን የተንቀሳቀሰ ቡድን በሌሎች ብሄሮችና አካባቢዎች ላይ ምን አይነት ግፍሊፈጽም እንደሚችል ቀላል ማሳያ ነው:: ስለዚህም ሳይመሽ ይህንን የመከነ ቡድን ሊታገለውና ከጫንቃውሊያወርደው ይገባል:: ከዚህ በላይ ጊዜና እድል ካገኘ ሃገሪቷን የጦር አውድማና የእርስ በርስ መፋጃ ከማድረግአይመለስም:: ስለዚህም መላው ሕዝባችን በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ ሊታገለው ይገባል:: ለሃገሪቷም ለአሃጉሩም ለዓለምም የማይጠቅም ዘመኑን መዋጀት የማይችል ኤክስፓየርድ ያደረገ ቡድን ሃገር ሳያረክስ ማምከን ግድ ይላል::

እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!አሜን!

4 Comments

 1. ማንነትንና ምንነትን “መግለጽ” ከተባለ ቴወድሮስ የኦሮሙማን ማንነትና ምንነት በሚገባ አሳምረህ ገልጸህልናልና ምስጋና ይግባህ፡፡
  ስሙን ‘ኦዴፓ’ ይበሉት ‘ኦህዴድ’ ወይንም “ኦነግ” ይበሉት “ኦፌኮ” ውይንም “ሼኔ” ይበሉት ቄሮና ቆሮቆር ወዘተ…ወዘተ…. የጥላቻና የመስፋፋትእንደዚሁም የዘረፋና የሌብነት ቡድን ነው፡፡
  ይህ ዘራፊና ተስፋፊ አፋኝና አጭበርባሪ ቡድን ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ ይወክላል ማለት አይደለም፡፡ ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ ግን ወደ ትክክለኛው ኢትዮጵያዊነቱ እንዳይመለስ አድርጎ እየበከለው ነው፡፡
  መፍትሄ፦ ጠንክሮና አንድ ሆኖ መታገልና ጠባብነታቸውን ለአለምና ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ እያጋለጡ ተገድደው ከስልጣን ተሽቀንጥረው እንዲባረሩና ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ ብቻና ብቻ ነው፡፡
  የፋኖ የተጋድሎ አርማ ድል በድል እየሆነና በነጻነት ጉዞው እያንጸባረቀ ይሄዳል፡፡ ማረጋገጫውም ከውስጡ ያሉትን የኦሮሙማ ገባሮች (የአማራ ሆዳም ሹመኞች) አስቀድሞ መቀጣጫ ለማድረግ ማጽዳት መጀመሩ ነው፡፡
  አማራ ለዚህ ትግል ግንባር ቀደም ሆኖ እየተዋደቀ ይገኛል ፡፡ ሌላውም ኢትዮጵያዊ ይህንኑ አውቆና አምኖበት ወደ ጸረ ኦሮሙማ የትግሉ ኝባር በቶሎ መግባት አለበት፡፡ አለበልለዚያ አገሪቱ ለማንም ሳትሆን መክና ትቀራለች፡፡

 2. የጭራቁና የሰው ደም የሚጠጣው የአብይ አህመዳ አሊና የሸሪኮቹ የኦሮሙማ “”ከብቶች”‘ ህልም አንድና አንድ ነው፡፡ ከአገሪቱ ህዝብ በቁጥር በመሪነት ደረጃ የሚገኘውን ትልቁን የአማራ ህዝብ ብዛት ቁጥሩን ከኦሮሞ ህዝብ ቁጥር ያነሰ ነው በሚል <> እንደ እውነት ወስዶ አማራን አሳንሶ በማየት በኢትዮጵያዊነት መቃብር ላይ ታላቋን ኦሮሙማን መገንባት ነው፡፡
  ይህ ቅዠትነው፡፡ የማይሳካ ህልም፡፡
  ወያኔ “የአማራ ክልል” ብሎ ከሰየመው ክልል ውጭ የሚኖረው የአማራ ህዝብ ብዛት ቢያንስ ቢያንስ ከ15 ሚሊዮን በላይ ነው፡፡ ይህንኑ እውነታ ቆጠራ አድርጎ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ነገር ግን በወያኔም ሆነ በኦሮሙማይህ እውነት በነጻ ቆጠራ ዉጤት እንዲረጋገጥ አይፈለገም፡፡ ብዙ ጉዶችና ጥቅሞች አሉትና!!!
  ለጊዜው ነው እንጅ 15 ሚሊዮን ህዝብን ፈጅተህ አትጨርሰውም፡፡ ያውም አማራን!!!ጭራቁ አብይ አህመዳ አሊ ቀኑ እየጨለመበት ነው፡፡

 3. ፅሁፍ ብዙ እውነቶች አሉት መከላከያንና ጄኔራሎችን ከፀረ ኢትዮጵያ ኤሊቶች ባትደምራቸው መልካም ነው በአደባባይ መከላከያ ብሄር የለውም ያሉ ቆራጥ ወገኖች ናቸው: የአማራን ብሄር የሚወክሉ ሹሞች በአዲስ አበባ ጉዳይ አፋቸው ለምን እንደተዘጋ ሊገባኝ አልቻለም በዘር ቅርጫም ከሆነ አአ የተመዝገበው ኦሮሞ 19% ሲሆን ጉራጌው 16% ሌሎች 65% ይሆናሉ ማለት ነው በምን ሂሳብ የኦሮሚያ ክልል አርማ አአ ላይ ለምን ይጫናል ብለው ያለመጥየቃቸው ከዚያም ተጨማሪ በህገመንግስታቸው ህገወጥ መሆኑንእያወቁ መሰለባቸው ለአማራ ውርደት ነው: ብዙ ኢትዮጵያውያን ጠሚ ዐቢይን እየደገፍን ይህን ህገወጥ ተግባር እንዲያስቆም እንጠይቃለን

 4. አቶ ቴዎድሮስ ቋንቋን መማር በፍላጎትና ይጠቅመኛል ተብሎ ሲታሰብ ነው።

  የኦሮሞ ያልተማሩ ምሁራን ግን በገዳ ፍልስፍናቸው ሌሎች ቋንቋዎችን አሁን በያዙት መልኩ ማጥፋት ነው። ኦሮምኛ ለምን ከሌሎች ተመረጠ ?ትግርኛ፣ሶማሊኛ፣ሀደርኛ፣ጉራጊኛስ ምን ልታደርጋቸው ነው? ኦህዴድ ተረኛ ስለሆነ እሳቤያቸውን መፈጸም አለብን ማለት ነው? የትክክለኛው ኦሮሞ ቁጥር እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን ብዛቱ ከ፮ ሚሊዮን አይበልጥም። እኛም እነሱ የሚፈልጉትን በክንድ ጥምዘዛ ፖለቲካ ባንፈጽምላቸው መልካም ነው እውነታውም መስተካከል ይገባዋል። ከደፈሩ ጣጥ ጣጥ የሚሉትን አክራሪዎች የዲ ኤን ኤ ምርመራ አድርጎ ፋይሉን መዝጋት ነው። በምን ተአምር ነው በቀለ ገርባና ጁዋር መሀመድ ከሌንጮ ለታና ዳውድ ኢብሳ ጋር የሚመሳሰሉት? አረ አንጋሳም አለልህ ጎበዝ ከስም አወጣጡ ጀምሮ ገርባ ማለት እኮ ባሪያ ማለት ነው የአቶ በቀለ አባት ማንነታቸው ተለውጦ የተሰጣቸው ስም ነው። መቼም ሰው ወዶ ማንነቱን አይለውጥም። በእርግጥ ተስፋዬ ገ/አብ ወዶና ፈቅዶ በሞጋሳ ባህል ኦሮሞ ሁኛለሁ ማለቱን አስታውሳለሁ ሲንቀዠቀዥ የሰው ደም እሱንም ጠራው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share