የ3ቱን ክልሎች ክልላዊ የህዝብ መዝሙሮች – የአማርኛ ትርጓሜ አንብቡና – ፍርዱን ለህሊናችሁ ስጡት! – ሄርሜላ አረጋዊ

1. የትግራይ ክልል መዝሙር /የአማርኛ ትርጉም 
የማንወጣው ተራራ
የማንሻገረው ወንዝ የለም ፤
ፍፁም ወደኋላ የለም
መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም!
በፀሀይ ሀሩር እና በቁር
ነፍሳችን ውሀ ይጥማት
አለት ይሁን ትራሳችን
ዋሻ ይሁን ቤታችን
ሌትም ቀንም ጉዞ ይድከመንም ይራበንም
ሆኖም መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም፤
በጅቦች እንከበብ መሬት ይክበበን
የጠላቶቻችን ጥርስ ስጋችን ውስጥ ይቀርቀር!
ስጋችን ላሞራ ደማችን እንደ ጎርፍ ይፍሰስ፤
አጥንታችን ይድቀቅ ዱቄት ሆኖ ይበተን
መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን
በፍፁም አንሸነፍም፤
የጦር መሳሪያ መርዝ ፋሽስታዊ ንዳድ
ሚሊየን ጠላቶቻችን ፊታችን ላይ ይጉረፉ
መስዋዕትነት መቁሰል እና ኪሳራም እንከፍላለን፤
የከፋ መከራም ቢመጣ ወደን እንከፍላለን
መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን፤
በዚህ ሁሉ ጉዞ ግን አሸናፊዎች እኛ ነን።
☞ በማለት የትግራይ ክልል መንግስት በትግራይ ባሉ ትምህርት ቤቶች ላለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እስካሁን ድረስ ይዘምራል ።
2. የኦሮሚያ ክልል መዝሙር / የአማርኛ ትርጉም /
ኦሮሚያ //2// የትልቅ ህዝብ ታሪክ እናት
የኦሮሞዎች እምብርት ፥ የገዳ ስርአት አዳራሽ
የህግና ስርአት መሬት ፥ የጨፌ ኦዳ እናት
የብልጽግና ልምላሜ ፥ ሁሉን አብቃይ እናት
የመቶ አመት እድፍ ፥ በደማችን አጠብንልሽ
በብዙ እልፍ እልቂት ፥ ባንዲራሽን ከፍ አደረግን
ደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ ፥ ስልጣንን መልሰን አገኘን
ሰላምና ዴሞክራሲ ፥ የሰብአዊነት መብት
አስተማማኝ ልማት ፥ ዘላቂ ልማት
ከህዝቦች ጋር ሰላምና ፍቅር
ለመኖር ዋስትና ትልቅ አላማ አድርገን
ኃይላችንን አሰባስበን ፥ ተነስተናል ተማመኚብን
ኦሮሚያ አብቢ ፥ ለምልሚና ኑሪ!
☞ በማለት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እንካሁን ድረስ በኦሮሚያ ክልል ይዘመራል ። አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ካልተዘመረ እየተባለ በተደጋጋሚ እየተነሳ ነው ።
3. የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መዝሙር
የታታሪ ህዝቦች የታሪክ ማህደር
የአኩሪ ባህል አምባ የድንግል ሀብት አፈር
የህዝቦችሽ ተስፋ ለሟ ክልላችን
በሰላም በፍቅር በልማት ጉዟችችን
ተባብረን በስራ እንገነባሻለን
የአማራነት ክብር ደማቅ አርማ ይዘን ፥
ከሌሎች ህዝቦች ጋር እኩል ተከባብረን
በፍቅር በአንድነት አብረን እንዘልቃለን ።
☞ በማለት የአማራ ክልል ህዝብ መዝሙር ይቋጫል ፡፡ ይህ መዝሙርም ላለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እስከአሁን ድረስ በክልሉ ይዘመራል ።
ለትውልዱ የጥላቻና የክፋት መርዝ እየጋተ ፥ ሀገርን የሚያፈርሰው ማን እንደሆነ ፥ የህዝብ ህሊና ፍርዱን ይስጥ!
ተጨማሪ ያንብቡ:  ከድጡ ወደ ማጡ! በፈቃዱ ሀይሉ ከፍትህ መፅሔት ላይ የተወሰደ - … - ትረካ ብሩክ!

3 Comments

  1. No wonder the trouble makers have come from Tigray and Oromia. It clearly shows how Amhara has been responsible and once can understand why Tribalists hate Amhara as they hate Ethiopia too.

  2. አብይ አህመድን ተጠግተሽ ቁነኛም ዝነኛም ለመሆን የምትዋትቺው የ”NO-MORE” የህዝብ ጩሀትን ከህዝቡ ነጥቀሽ ለአብይ አህመድ ኦሮሙማ “ባላ”” ማለትም መሰላል” ያደረግሽው ሄርሜላ፦ የሆንሽውን ሁኚ፡፤ካዋጣሽም ቀጥይ፡፡ ነገር ግን እስኪ ስለመዝሙሮቹ አንቺ ራስሽ አስተያየትሽን /የሜሰማሽን ለህዝቡ ቀድመሽ ግለጪ????
    መግቢያ ይሆንሽ ዘንድ የእኔን አረዳድ ላጋራሽ; ሶስቱም መዝሙሮች ነውሮች ናቸው፡፡ የነውረኞች እንጉርጉሮወች ናቸው፡፤ በተለይ የኦሮሙማውና የወያኔው ራሳቸውን ለውርዴት አሳልፈው የሰጡበት የማንነት መገለጫወቻቸው ናቸው፡፡ አንዱ ባንዳ ሌላው ከብት(እንሰሳ)፡፡ በድምር ዉጤቱ የቂሎች ድርሰቶች ትብታቦች ናቸው፡፡
    አገራችን ኢትዮጵያ አሁን ከደረሰባት የኦሮሙማና የወያኔ የተሾረበ ተንኮል አሸናፊ ሆና ትወጣ ዘንድ የየራሳችንን ጥረት እናበርክት፡፡ የውጭ ጠላቶቿን የተቀነባበረ ሴራ በጣጥሳ ወጥታና ከውስጥም ከውጥንቅጡ በአሸናፊነት ጅቦችን፣ ተረኞችንና ሆዳሞችን ድል አድርጋለገራሙና ለየዋሁ ህዝቧ መልሳ “ኢትዮጵያ” ትሆን ዘንድ ፈጣሪ አማላክ ይርዳት፡፡

  3. ሄርሜላ የትኛው የተሻለ ሁኖ አገኘሽው? እውነቱ ቢሆን ይህንን ታላቅ እንቅስቃሴ ያቆመው አብይ ነው የራሷ የሆነ ግንዛቤ ቢኖራትም ለዚህ ግን ተወቃሹ አብይ ይመስለኛል በዚህ አስተያየትህ እውነቱ ጻፈ ሳይሆን አማራ ጻፈ ነው የሚሉህ ፈርዶብህ።a

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share