‹‹መዋቅራዊ ማሻሻያ መርሃ-ግብር!!!›› ከዓለም ባንክና አይኤምኤፍ ሆድቃ፣ ዶላር ፍለጋ በጨረቃ!!! (ክፍል 2) – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

ክፍል 2
ሚሊዮን ዘአማኑኤል(ኢት-ኢኮኖሚ)

ዶላር ፍለጋ በጨረቃ!!! ላም አለኝ በሠማይ፣ ወተቷንም አላይ!!!

የኢንተርናሽናል ግሮውዝ ሴንተር የፖሊሲ ተመራማሪ ዶክተር ቴዎድሮስ መኮንን፤‹‹የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት በኢትዮጵያ›› በሚል ርእስ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ባቀረቡት ጥናታዊ ድምዳሜ መሠረት ‹‹የአንድ አገር ማክሮ ኢኮኖሚ የተረጋጋ ነው የሚባለው (1)ተገማችና የማይዋዥቅ ግሽበት፣ (2)ትክክለኛ የወለድ ምጣኔ፣ (3)የተረጋጋ የፊስካል ፖሊሲ፣ (4)የተሸለ የክፍያ ሚዛን፣ (5)ተወዳዳሪና ተገማች የምንዛሪ ተመን ምን ይመስላል በሚሉት መመዘኛዎች ነው፡፡ ከዚህም በመነሳት በተለይም አገሪቱ ከዓለም አቀፍና አገራዊ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የሚያስከትሉትን ጉዳዩች ጋር ተያይዞ ፣ የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ የተረጋጋ አይደለም ተብሎ የሚገለፅበት ድምዳሜ ላይ ተደርሶል፡፡››……………………………..(1)

ኢትዮጵያ የዓለም ባንክ መዋቅራዊ ማስተካከያ (ስትራክቸራል አጀስትመንት) ፕሮግራም ተቀብላ እየተገበረች እንደሆነ በዚህም መሠረት የብርን የመግዛት አቅም ማዳከመ (Devaluation) የመንግሥትን ወጪ መቀነስ የታክስ መሠረቱን ማስፋት፡ የአገሪቱን የታክስ መሠረት ያሰፋሉ ተብለው እየተተገበሩ የሚገኙ አዳዲስ የታክስ ዓይነቶችም የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ያዘዛቸው የፖሊሲ አቅጣጫዎች ውስጥ የሚመደቡ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

ሊብራላይዜሽን (ኢኮኖሚውን ክፍት ማድረግ) በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ግዙፍ የመንግሥት ሚና ወደ ግሉ ዘርፍ ማሻጋገር ባለመቻሏ  እና መንግሥት የሚያደርገውን ኢኮኖሚያዊ ድጎማ ማቆም የዓለም ባንክ ፈጣን ስትራክቸራል አጀስትመንት እንድትተገብር ማዘዙን፣ ይህንንም የኢትዮጵያ መንግሥት ተቀብሎ በመተግበር ላይ እንደሚገኝ የኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ያሬድ ኃይለ መስቀል ገልፀዋል፡፡

 

የብልፅግና መንግሥት የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ ዘርፈ ብዙ ፈርጆች በፊሲካል ፖሊሲና ሞኒተሪ ፖሊሲ መናበብ አለመቻላቸው ለኢኮኖሚ ቀውሱ መባባስ በር ከፍቶል፡፡ የሃገሪቱ ፊሲካል ፖሊሲ፤ (Fiscal Policy) የግብርና ታክስ እንዲሁም የመንግሥትን ወጪ ሥርዓትን እቅድና አፈፃፀም ፖሊሲን ያሳያል፡  የመንግሥትን ገቢና ወጪና የበጀት ጉድለትና ትርፍ ያሰላል፡፡ የመንግስት የታክስና የግብር ገቢ አሰባሰብ ሥርዓትና ፖሊሲን እንዲሁም የመንግሥታዊ ዘርፍ ወጪን ይቆጣጠራል፡፡  የመንግሥትና የብሄራዊ ባንክ ፊሲካል ፖሊሲ፤ የግብርና ታክስ ስርዓት ፍትሃዊ ባለመሆኑ ምክንያት በሃገሪቱ የግብርና ታክስ መቀነስ ቀይ መብራት መሆኑን መገንዘብና ማሻሻል አስፈላጊ ነው፡፡

የሃገሪቱ ሞኒተሪ ፖሊሲ፤ (Monetary Policy) የመንግሥትና ብሄራዊ ባንክ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የገንዘብ ዝውውር፣ ገንዘብ ፍላጎትና አቅርቦት በመቆጣጠር የዋጋ ግሽበት መከላከልና የወለድ መጠን በመወሰን የገንዘብ ሥርዓት የሚቆጣጠርበት ሲሆን ከዓለም ዓቀፍ ኢንስቲቲውሽን ማለትም ከዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ ከዓለም ባንክ እንዲሁም የሃገራቱን የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የማህበረሰብ ልማት ፖሊሲዎች ጋር አዛምዶ መስራት ያካትታል፡፡ ሞኒተሪ ፖሊሲ ከሚያካትታቸው ውስጥ፤ የገቢ ፖሊስ፣ የሸቀጣ ሸቀጦችና ምርት የዋጋ ቁጥጥርና የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችትን ያካትታል፡፡ ዘለቄታዊ የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ እንዲኖር የውጭ ንግድ ገቢን መጨመር፣ የዲያስፖራ የሃዋላ ገቢና የዲያስፖራ የቤት ሥራ ገንዘብ በአግባቡ መሰብሰብ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡

‹‹በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴርም ሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ቴክኒካሊ ነው የሚመሩት ብለው እንደሚያምኑ የገለፁት ፣ የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ (1) የውጭ ምንዛሪ ችግሯን መቅረፍ ባለመቻሏ እንዲሁም (2) በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ግዙፍ የመንግሥት ሚና ወደ ግሉ ዘርፍ ማሸጋገር ባለመቻሏ የዓለም ባንክ ፈጣን ስትራክቸራል አጀስትመንት እንድትተገብር ማዘዙን፣ ይህንንም የኢትዮጵያ መንግሥት ተቀብሎ በመተግበር ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡››…………………………………(2)

ተጨማሪ ያንብቡ:  በላተኛው አባ-መላ ከያሬድ አይቼህ

‹‹የአገሪቱ የብር መጠን በየጊዜው በተከታታይ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ምርትና አገልግሎት ለማዘዋወር ከሚያስፈልገው መጠን በላይ መንግሥት ከብሄራዊ ባንክ በሚወስደው ብድር መልክ እያሳተመ ገበያው ውስጥ እንዲገባ የሚያደርግበት አሠራር ሌላው ነው፡፡ ይህ የአጠቃላይ የኢኮኖሚው እድገት ምጣኔ ያላገናዘበ (Excess Money Supply) የገንዘብ ፖሊሲ በሕወሐት ዘመን የተጀመረ ቢሆንም፣ በኦሕዴድ / ብልፅግና ዘመን በከፍተኛ ደረጃ ተባብል፡፡ መንግሥት ይህን የሚያደርገው የበጀት ጉድለቱን ለማሟላት ነው፡፡ መንግሥት የበጀት እጥረቱን ሲያሟላ የቆየው በአገር ውስጥ ብድር፣ ከውጭ በሚገኝ ብድርና እርዳታ ነው፡፡ በአገር ውስጥ የመንግሥት ብድር የሚሸፍነው ከንግድ ባንክ በሚገኝ ብድርና ቀሪው በብሔራዊ ባንክ አማካይነት አዲስ ገንዘብ ታትሞ ለመንግሥት የመደበኛ ወይም የካፒታል በጀት መሸፈኛ እንዲውል በማድረግ ነው፡፡

ለምሳሌ በአገራችን  ከዛሬ 15 ዓመታት በፊት ማለትም በ2000ዓ/ም በኢትዮጵያ ውስጥ በሰው ኪስ፣ በትራስ ውስጥ የተደበቀው፣ በግልና በመንግሥት ድርጅቶች ሒሳብ ውስጥ የነበረው ጠቅላላ የብር መጠን 67 ቢሊዮን ብር ብቻ ሲሆን፣ከአስራ ሦስት ዓመታት በኃላ ማለትም 2013 ዓ/ም  በኢኮኖሚው ውስጥ ሲዘዋወር የነበረው ገንዘብ 870 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ይህም የገንዘብ አቅርቦቱ (Money Supply) 1298 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን ያመላክታል፡፡  ባለፈው እኤአ በ2021 የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ላይ መንግሥት ብሔራዊ ባንክን በማዘዝ በአዲስ እንዲታተም ያደረገው የብር መጠን 83.5 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ይህም ከ2020 ከነበረው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር የ169.4 በመቶ ዕድገት እንደነበረው የብሔራዊ ባንክ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የገንዘብ አቅርቦቱ ከአጠቃላይ ብሔራዊ ምርት (GDP) ከ12 በመቶ በላይ ከሆነ ውጤቱ የዋጋ ንረትን መጨመር እንደሆነ የኢኮኖሚ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ በኢኮኖሚው ውስጥ እየናረ  ለመጣው የዋጋ ንረት አንዱ ዓይነተኛ ምክንያት ይህ በየጊዜው እየታተመ ወደ ገበያ ውስጥ እንዲሠራጭ የሚደረገው በምርትና አገልግሎት ያልተደገፈ ሌጣ ብር ነው፡፡ ›› አመሃ ዳኘው ተሰማ…………………………(3)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዘመን ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2015 ዓ/ም፤ የአጠቃላይ የኢኮኖሚው እድገት ምጣኔ ያላገናዘበ (Excess Money Supply) የገንዘብ ፖሊሲ በኦነግ ኦሕዴድ / ብልፅግና ዘመን በከፍተኛ ደረጃ ተባብሷ ለመቀጠሉ ዝርዝር መረጃዎች እንሆ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶክተር  አብይ  አህመድ  ዘመን ከጁን 30 ቀን 2021 እኤአ ድረስ፣ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ 2.4 (ሁለት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን  ብር  ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአገር ውስጥ  ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.14 (አንድ ነጥብ አስራ አራት) ትሪሊዮን ብር እንዲሁም የውጭ አገር ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.29 (አንድ ነጥብ ሃያ ዘጠኝ) ትሪሊዮን ብር ሆኖል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዘመን ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2014 ዓ/ም፤የአገር ውስጥ የመንግሥት ዕዳ ከ449.7 (አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ነጥብ ሰባት)  ቢሊዮን ብር ወደ 1.14 (አንድ ነጥብ አስራ አራት) ትሪሊዮን ብር ተመንድጎል፡፡ በሌላ በኩል በአብይ ዘመን የሚገነባው የጫካው ከተማ ፕሮጀክት አንድ ትሪለየን ብር ወጪ የገንዘቡ ምንጭ ምስጢር  ከኢትዮጵያ የብድር ግምጃ ቤት በብድር ስም የተመዘበረ ሊሆን እንደሚችል ይጠረጠራል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአዳነች አቤቤ ተቺዎች ኢትዮጵያዊ ከሆናችሁ አስተውሉ - ሰርፀ ደስታ

የባንኩ ባለቤት፣ የዓሳውም ባለቤት ነው!!! (who owns the bank owns the fish)(የራሽያን ተረትና ምሳሌ)

ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2011ዓ/ም፤በብልፅግና ፓርቲ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዘመን፡- የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ  የማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ  449.7 (አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ብር ነበር፡፡ በ2013 ዓ/ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዘመን የአገር ውስጥ የመንግሥት ዕዳ 945 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ተጠቅሷል።  ከዚህ ውስጥ  525 (አምስት መቶ ሃያ አምስት) ቢሊዮን  ብር የሚሆነውን ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቆማት ያበደረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው፡፡ ከመጋቢት  2010 እስከ 2013ዓ/ም የአገር ውስጥ የመንግሥት ዕዳ ከ449.7 ቢሊዮን ብር ወደ 945 ቢሊዮን ብር ደረሰ፡፡  መንግሥት ተጨማሪ 495.3 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ከብሔራዊ ባንክ፣ በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ፣ ከመንግሥት ሠራተኞችና ከግል ሠራተኞች የጡረታ ፈንድና ተወስዶ ያልተከፈለ ዕዳ መሆኑን ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ  መንግሥት የአራት አመት አገዛዝ ዘመን ከመጋቢት 2010 እስከ 2014ዓ/ም የአገር ውስጥ ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.14 (አንድ ነጥብ አስራ አራት) ትሪሊዮን ብር መድረሱ ተገልፆል፡፡ የአገር ውስጥ የመንግሥት ዕዳ ከ449.7 ቢሊዮን ብር ወደ 945 ቢሊዮን ብር ብሎም ወደ 1.14 (አንድ ነጥብ አስራ አራት) ትሪሊዮን ብር ደረሰ፡፡  መንግሥት ተጨማሪ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ከብሔራዊ ባንክ፣ በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ፣ ከመንግሥት ሠራተኞችና ከግል ሠራተኞች የጡረታ ፈንድና ተወስዶ ያልተከፈለ ዕዳ መሆኑን ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዘመን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የአገር ውስጥ ዕዳ 386.8 (ሦስት መቶ ሰማንያ ስድስት ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ብር በላይ ዕዳ እንዳለባቸው መረጃው በዝርዝር ያመለክታል፡፡ ብድሩ የተሰጠው ከኢትዮጵያ አየር መንገድና ከኢትዮ ቴሌኮም ወጭ ያሉትን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የሚመለከት እንደሆነ ሰነዱ ያመለክታል፡፡ ከመንግሥት ልማት ድርጅቶቹን የተናጠል ዕዳ ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር ያለባቸው የአዲስ አበባ የቤት ልማት መርሃግብር 50 (ሃምሳ) ቢሊዮን ብር እዳ፣  የስኳር ኮርፖሬሽን 70 (ሰባ) ቢሊዮን ብር እዳ፣  የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል 300 (ሶስት መቶ) ቢሊዮን ብር እዳ፣ የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን፣ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ወዘተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር ያለባቸው ድርጅቶች ናቸው፡፡

‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ከጥቂት ወራት በፊት ይህንኑ ሁኔታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስረዳታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በወቅቱ ባደረጉት ንግግርም መን ሥታቸው ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው የኢኮኖሚና  የፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርም  ፈጥኖ ባይደርስ ኖሮ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመውደቅ አደጋ ተጋርጦበት ነበር ማለታቸው አይዘነጋም።  (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቶ ባጫ ጊኒ በአብይ አህመድ ከተሸሙ በኃላ የባንኩን ገንዘብ ሰማንያ አምስት በመቶ ለኦሮሞ ኢንቨስተሮች በማበደር የኦሮሞ ኢንቨስተሮች  በአንድ ምሽት የመፈልፈል ‹‹የኦሮሙማ እቅድ›› ተተግብሮ ባንኩን ለኪሳራ ተዳረገ፣በዛን ጊዜ ባጫ ጊኒ እንዳይጠየቅ አብይ አህመድ አንባሳደር አድርጎ በሾም ዋነኛውን ሙሰኛ አሰናብቶ አሁን ስለሙስና  ) መንግሥት እያደረጋቸው ከሚገኙ ሪፎርሞች መካከል የመንግሥት ልማት ድርጅቶች፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልከፈሉትን ዕዳ ቀስ በቀስ ወደ መንግሥት ማዘዋወር አንዱ ተግባራዊ መደረግ የጀመረ የመፍትሄ አማራጭ መሆኑን  ታውቆል፡፡›› ኮነሬል አብይ መንግሥታቸው ዋናው ተበዳሪ ሆኖ እያለ  የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ያልተከፈለ  የተቆለለ እዳ ቀስ በቀስ ወደ መንግሥት ማዘዋወር አንዱ አማራጭ ተደርጎ ተቀምጦል፡፡ የመንግሥት የትየለሌ እዳ እያለበት እየታወቀና ያለገደብ ከብሔራዊ ባንክ ያለህግ እየመነተፈ የልማት ደርጅቶችን እዳ ወደ መንግሥት ማጠቃለል ማለት እዳቸውን መሠረዝ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  "ህይወት አጭር ጣፋጪ ና በሥቃይ የተሞላች ናት።" መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዘመን ከጁን 30 ቀን 2021 እኤአ ድረስ፣ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ 2.4 (ሁለት ነጥብ አራት) ትሪሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአገር ውስጥ ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.14 (አንድ ነጥብ አስራ አራት) ትሪሊዮን ብር እንዲሁም የውጭ አገር ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.29 (አንድ ነጥብ ሃያ ዘጠኝ) ትሪሊዮን ብር ሆኖል፡፡ መንግሥት በዘንድሮው በጀት አመት 73.1 (ስባ ሦስት ነጥብ አንድ) ቢሊዮን ብር ወይም 1.8 (አንድ ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ዶላር ለውጭ አበዳሪዎቹ ከፍሎል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዘመን  ከ2022እኤአ የእርቁ ስምምነት ከተፈረመ በኃላ የተገለፀ የጫካው ፕሮጀክት ምስጢር ሲገለጥ፤ አንድ ትሪሊየን ብር ወጪ የሚገነባ ስማርት ከተማና ቤተ-መንግሥት፣ 3700 ሔክታር የግንባታ ቦታ ያካትታል፤ በዚህ ፕሮጀክት ሁለት ቢሊዮኝ ደላር በዓመት ይገኛል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ወደፊት በሙሉ አቅሙ ሰርቶ ኤሌትሪክ ወደ ጎረቤት ሃገሮች ተሸጦ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስገኝ የዓለም ባንክ መረጃ ገልፆል፡፡ የኢትዮጵያና ትግራይ የጫካው ጦርነት ፕሮጀክት ምስጢር ሲገለጥ ደግሞ፤ አንድ ሚሊዮን ወጣቶች ህይወታቸውን አጥተዋል…! የመሠረተ ልማቶች ቁሳዊ ውድመት ደግሞ አንድ ትሪለየን አምስት መቶ ቢሊዮን ብር ኪሳራ በሃገሪቱ ላይ ደርሷል፡

 

ምንጭ፡-

የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ከዓለም አቀፍ መመዘኛዎች አንፃር‹‹ያልተረጋጋ›› መሆኑን ምሁራን ተናገሩ/ ሪፖርተር ጋዜጣ ሴፕቴምበር 4/2022

ኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ያዘዘውን መዋቅራዊ ማስተካከያ እየተገበች እንደሆነ ተጠቆመ/ ሪፖርተር ጋዜጣ ጁላይ 6/2022

የኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ የኢኮኖሚ ችግሮች ምክንያቶቻቸውና መፍትሔዎቻቸው/ ሪፖርተር ጋዜጣ / በአመሃ ዳኘው ተሰማ/ ኖቨንበር 20/2022

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share