December 2, 2022
4 mins read

የመከራ ቤተ ሙከራ ከመሆን እንዉጣ !

Amharaአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ አስከሆነች ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ህዝብ በመሆኑ አንድብሄራዊ ሠንቀደቅ ዓላማ ፣አንድ አገር እና አንድ መዲና መኖር ዉድ ሳይሆን ግድ ነበር ግን ገላጋይ ጠፋ ፡፡

አንዲሁም ኢትዮጵያ የራሷ ሆሄ ፣ ቋንቋ ታሪክ ያላት  አገር መሆኗ  ከዉስጥ ቢካድም በዉጭ እንደሚታወቅ አይካድም ፡፡

እንኳንስ ኢትዮጵያ የሶስት ሽ ዓመታት ታሪክ ፣ ባህል፣ቋንቋ እና ሠንደቅ ዓላማ ያላ አገር እና ህዝብ ቀርቶ ቅኝ ተገዥዎች የነበሩት እና በኢትዮጵያዉያን የነፃነት ትግል ተምሳሌት ነፃ የወጡት ከምዕራብ እነ አሜሪካ፣ካናዳ…፤ከአፍሪካ ብዙዎች ፣ ከምስራቅ እነ ህንድ ፣ቻይና…የራሳቸዉን ባህል ፣ቋንቋ ፣ ሠንደቅ ዓላማ ይዘዉ ቀጥለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ስንል የኢትዮጵያን የቆየ በጎ ነገር በመካድ እና ኢትዮጵያዊነትን በማሳደድ የሚሆን የሚመስለን ካለ ሞኝነት ነዉ ፡፡

በአገር ጉዳይ ከእኔ በላይ ላሳር በማለት የቀደመዉን ኢትዮጵያዊነት እና ማንነት ገሸሽ አድርጎ ለሚያልፍ ጊዜ መጥቶ ጊዜ ሲያልፍ እንዳንተዛዘብ ሊተኮርበት ይገባል፡፡

ያለፈዉ እና የሆነዉ የመከራ ቀንበር ሳይበቃ በአዲስ አበባ ት/ቤቶች አጥር ግቢ የአንድ ክልል ባንዲራ  እንዲዉለበለብ ለማድረግ ማሰብ ምክነያቱ ባይታወቅም ለዓመታት በአገሪቷ ላይ ሲካሄድ ከነበረዉ የመከራ ሙከራ ድርጊቶች ከማስቀጠል እና ከማግለል እና መገለል ዉጭ ለኢትዮጵያም ሆነ ለህዝቧ የሚበጂ አይደለም፡፡

ኢትዮጵያ አገራችን የሁላችን ጎጆ አስከሆነች አዲስአበባ የሁላችን መንበር እና መንደር ናት፡፡ ይህ ከሆነ ኢትዮጵያ አንድ አገር ፤ ህዝቧም በብዙ ቀለማት ዉህደት አንድ ህዝብ እንደመሆኑ በአንድ ሉዓላዊት አገር እና ሉዓላዊ ህዝብ አንድ ነገር የግድ ነዉ ለአንድ አንድ ነዉ ፡፡ ይህም በአንድነት እና አብሮነት ልዩነት የለም ማለት አይደለም ፡፡

ኢትዮጵያ እና ህዝቧ በአንድነት ዉስጥ ፩ነት ፩ ነፃ አገር ፣ ነፃ ህዝብ፣ ሠንደቅ አላማ፣ ቋንቋ፣ ባኅል…..ያላቸዉ መሆኑን ዓለም የሚመሰክረዉ ሆኖ በዚህ በጋራ ታሪክ እና ማንነት እኛ ካልተስማማን “የፍክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል እንዲሉ  ” በተከፈተዉ አጉል ፍክክር በተከፈተ በር ለጂብ እንዳንሆን የ12 ክልሎች ባንዲራ በአዲስ አበባ ት/ቤቶች ይቁም እና እንደምንለዉ  ዉጤየቱን እንየዉ ፡፡ ኢትዮጵያ የእኛ ፤አዲስ አበባም እኛ ከሆን በአንድነት እና በመስማማት የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ከፍ ማድረግ ካልቻልን በተናጠል መቆም እና ማቆም ምን እንደሆነ ስናይ ከወረቱ ስንቁ ሲሆን ወደ ዕዉነተኛዉ ማንነት እና አንድነት ለመመለስ ትምህርት ይሆነናል  ፡፡

እኛም ሆነ አገራችን  የመከራ ቤተ ሙከራ ከመሆን ወጥተን ከህልም ዓለም እንወጣ ዘንድ መትጋት እና በህብረት ዘብ መቆም አለብን፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ ፡፡

Allen Amber!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop