ወደተነሳሁበት አስገራሚ የጋራ ጉዳይ ከመግባቴ በፊት ስለሀገራችን ወቅዊ ጉዳይ ትንሽ ልናገር፡፡ “በማን ላይ ቆመሽ …” እንዲሉ ነውና ከሁሉም የሚቀድመው የሀገር ጉዳይ ነው፡፡
አክራሪ ኦሮሞ ኢትዮጵያ ላይ ካለቆንጣጭ ካለገልማጭ በግልጽ መፈንጠዝ ከጀመረ እነሆ አምስተኛ ዓመቱን ሊደፍን ጥቂት ወራት ይቀራሉ፡፡ በነዚህ ባለፉ አምስት ዓመታት ገደማ አክራሪ ኦሮሞ በአጠቃላይ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በተለይ ግን በአማራ ላይ ያልፈጸመው ግፍና በደል የለም፡፡ አማራም የሚደርስበት መከራና ስቃይ ሁሉ የተመቸው ይመስላል ነገር ዓለሙን ጥሎ ለሽ ብሎ የተኛ ይመስላል፡፡ የተኛ ሁሉ ግና እስከወዲያኛው ተኝቶ እንደማይቀር ሁሉም ሊያውቅ ይገባል፡፡
ወገኖቼ፤ ግፍን መጸየፍ የሁላችንም የሰውነት ባህርይ ሊሆን በተገባው ነበር፡፡ የምንዘራት እያንዳንዷ ግፍና በደል ቀኗን ጠብቃ ወደኛው ትዞራለች፡፡ ማንም የዘራውን ማጨዱ የእውነቶች ሁሉ ቁንጮ ነው፡፡ በሀገራችንም ሆነ በሌላው ዓለም ይህን ነባራዊ እውነት የሚያስረዱ እጅግ በርካታ ታሪካዊ ክስተቶች ተመዝግበዋል፡፡ የቅርብ ጊዜዎቹን የሀገራችንን ግፍና በደል ዘሪዎችን እንኳን ብንመለከት ከነሱ ብዙ በተማርን ነበር፡፡ ሁሉም የዘሩትን ሰብስበዋል፡፡ አንዳቸውም ሳይቀሩ፡፡
ወያኔ በሠራው የግፍ ቁልል ሳቢያ ትግራይና ተጋሩ ምን ያህል እንደተሰቃዩ አሁንም ድረስ የሚታይ ስለሆነ አስታዋሽ አያስፈልገንም፡፡ እልህ ጩቤ ያስውጣል እንደሚባለው ሆኖ ወያኔ በአልሞትባይ ተጋዳይነት አሁንም ድረስ በተለይ በአንደበታዊ ጦርነቷ ትንፈራፈር እንጂ በተግባር ግን ዜሮ ሆናለች – ወደታች ካልሆነ ወደላይ የማይወጣ ዜሮ፡፡ የፈለገችውን ያህል ብትሞክር ከእንግዲህ ወዲያ ወያኔ እንደዱሮ መግነን አትችልም፡፡ አቢይና ሽመልስ የፈለጉትን ያህል ቢረዷትም የትም አትደርስም፡፡ የርሷ አኪር ተገልብጧል፡፡ ያ ሁሉ የደረሰባት ግና ባጠራቀመችው ግፍና በደል ነው፡፡
ከዚያች እርጉም ወያኔ ቅንጣት ያልተማሩት ደደቦቹ ኦነግ/ኦህዲዶች በነቀርሣው ብአዴን ረዳትነት ያልሠሩትና የማይሠሩት ግፍና በደል ባለመኖሩ ከወያኔ በበለጠ እንደሚቀጡ ለመረዳት የማንንም የትንቢት ቃል መጠበቅ አይገባንም፡፡ “ወያኔ ላይ የደረሰው ቅጣት ምሕረት እንጂ ቅጣት አይደለም” እስኪያስብል ድረስ ኦነግ/ኦህዲዶች በእሳት አለንጋ ይገረፋሉ፤ መፈጠራቸውንም እስኪራገሙ የዶግ ዐመድ ይሆናሉ፡፡ ወያኔ በ “ወይ አነ!” ጩኸት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል እንዳጓራች ሁሉ ኦነግ/ኦህዲዶችም በ“አኒ በዴ” እሪታ በያሉበት በድኝ እሳት እንደሰም ይቀልጣሉ፡፡ ይህ የሚሆነው ስለተመኘን አይደለም፡፡ ፈጣሪ ሁሉንም እንደሥራው ስለሚከፍል እንጂ፡፡ መጽሐፉም “ለለአሃዱ በበምግባሩ” ይላልና ይህ የላይኛው ጌታ ፍርድ ጊዜውን ጠብቆ ይመጣል፡፡ ሞት ሲዘገይ የቀረ መምሰሉ እያታለላቸው እንጂ እነሱም ይህን ያውቁታል፡፡ ድንበር ላጣው ጭካኔያቸውና ዕብሪታቸው ተገቢውን ቅጣት ያገኛሉ፡፡ የኬኛ ፖለቲካ ዛሬ እንደጎርፍ እንዳጥለቀለቀንና ሁሉን ነገር እንዳሳጣን አይቀርም፡፡ ጊዜ ባለውሉ ተገለባባጭ ነው፡፡ ግን ግን ጊዜ ሰጠኝ ብሎ እንደኦነግ/ኦህዲድና ወያኔ ይሠሩትን ማጣት ለከፍተኛ ኪሣራ እንደሚዳርግ መረዳት ይገባል፡፡ ተፈጥሮም ሆነች ፈጣሪ ለማንም አያዳሉም፡፡
አማራ አማራ ልሁን ብሎ ፈጣሪን በመማጸን አልተፈጠረም፡፡ ይህን እውነት ሽመልስም አቢይም ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ መገርሣም ያውቃል፤ ደቻሣና ጫልቱ፣ አመንሲሣና ቶሎሣም ያውቃሉ፡፡ አማራን ማጥፋት ምንም ዓይነት ፍላጎት ከግብ እንደማያደርስ ሁላቸውም ይረዳሉ፡፡ ነገር ግን አእምሯቸውን ሰቅዞ የያዘው ሰይጣናዊ ሤራና ተንኮል የ666 ተልእኳቸውን እንዲያስፈጽሙ አስገደዳቸው፤ በዚያም ሳቢያ ወያኔ በሦስት አሠርት ዓመታት አገዛዙ ከጨረሰው አማራ ይልቅ በነዚህ አምስት ዓመታት ብቻ ተቆጥሮ የማያልቅ አማራ በአቢይና ሽመልስ የተናበበ ሤራ ሊያልቅ ቻለ፡፡ ቀን ለሰጠው አጎብዳጁ ብዙ ነውና ከአማራ ከራሱ ወደ አጋሰስነት የተለወጠውን ብአዲናዊ ሆዳም ጨምሮ አጋዣቸውም በዛ፡፡
ልብ አድርግ! እግዚአብሔርን በፍርዱ አይዘባበቱበትም፡፡ የውሻ ደም በከንቱ እንደማያስቀር በአባባል ጭምር የሚነገርለት የሰማይና የምድር ጌታ፣ እርጉዝ ሴትን ሆዷን በመቅደድ ሽሏን አውጥቶ ማስታቀፍና አንገቷን መቅላት የአቢይንም ሆነ የሽመልስን ፍላጎት የኋሊት ያሽቀነጥረው እንደሆነ እንጂ ወደፊት ስንዝር አያስኬደውም፡፡ ያልታጠቁ አማሮችን፣ ሕጻናትንና አእሩግ ሴትና ታማሚ አማሮችን ለስብሰባ በሚል ከጠራ በኋላ ሸሽተውም እንዳያመልጡ ዙሪያቸውን በመክበብ መጨፍጨፍና የዘመናት ጥሪታቸውን መዝረፍ ወይንም ማውደም አንድም ዓላማ ከግብ አያደርስም፤ እንዲያውም በዚህ ድርጊት ፈጻሚዎችና አስፈጻሚዎች ላይ የሚያመጣው ጽልመታዊ የዕዳ ሸክም ትውልዶችም አይችሉትም፡፡
የታጠቀን መግደል ያባት ነው – ይህም ትክክል ነው ባንልም ግዴለም ይሁን፡፡ ለአቅመ ጦርነት የደረሰን ወንድ መግደል ያባት ነው – ምናልባት ለወደፊት ስጋት ሊሆን ይችላል ተብሎ ይታሰባልና እየመረረንም ቢሆን ይህንንም እንቀበለው፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው አማራ በመሆኑ ብቻ በራሱ ጊዜና በራሱ ህመም ሊሞት እያጣጣረ የሚገኝን ሰው መግደል የሚሰጠው ደስታና እርካታ ምንድን ነው ብለን ብንጠይቅ ከሰማይ በታች የምናገኘው ምላሽ የለም፡፡ እንዲህ ያለውን ድርጊት የሚፈጽሙትና የሚያስፈጽሙት እነአቢይና ሽመልስ የጀመሩት ቁማር ምንም ይሁን ምን እነዚህን ጉዶች ሰው ናቸው ብሎ መቀበል ራሱ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሰው የመሆንን ትርጉም የሚያሳጡ ከራሱ ከሰይጣን የባሱ ዐረመኔዎች ናቸው፡፡
አቢይ በሽተኛ መሆኑን ብዙ ጊዜ ተናግረናል፡፡ ዓለማችን እንደአቢይ ያለ ውሸታም፤ እንደአቢይ ያለ ዐረመኔ ጨካኝ፤ እንደአቢይ ያለ አስመሳይ፤ እንደአቢይ ያለ በላኤሰብና ልመለክ ባይ ፈጽሞ እስካሁን አላየችም፡፡ ሂትለርና ሙሶሊኒ ጨካኝ እንደነበሩ ይነገራል፡፡ የነሱ ጭካኔ ግን ምክንያትም ለከትም ነበረው፡፡ የዚህ ሰውዬ ጭካኔና ዐረመኔነት ግን ወደር አይገኝለትም፡፡ የሚገርመው ደግሞ ይህንን ሰው የሚወዱና በገባበት የስብዕና ቀውስ ምክንያት የሚሠራውን ቅጥ ያጣ ነገር ሁሉ ለማየት ባለመፈለግ የሚያዝኑለት በብዛት መኖራቸው ነው፡፡ ትናንት ማታ ከአንድ ሰው ጋር ተጣልቻለሁ – “እርሱ ምን ያድርግ፤ በሥሩ ያሉት እኮ ናቸው አላሠራው ያሉት …” ሲለኝ ብልጭ አለብኝና አለወትሮየ አስጮኸኝ፡፡ ይህን ያለው ደግሞ በዘሩ ከሚታረዱት ወገኖች ሆኖ በሥራውም በፖሊስነት ሙያ ዕድሜ ልኩን በማገልገል በቅርቡ ጡረታ የወጣ ነው፡፡ ያኔ ስለሀገሬ መቼም አዝኜ የማላውቀውን ያህል አዘንኩ፤ ዕዳ ፍዳችንም ትንሽ እንደሚቀረው ተረዳሁ፡፡ ከርሱ እንዲህ ከሰማሁ ሌላውማ በፍቅሩ ቢነድ አይፈረድበትም፡፡ ሰውዬው እኮ አቦይ ስብሃት እንዳለው የሴት ጂኒ ሳትኖረው አትቀርም፡፡
ይህን ሃቅ ደግሞ ልብ እንበል፡፡ ኢትዮጵያና አማራ ነፃ የሚወጡት ብአዴን የተባለ ከርሣም የታሪክ ነቀርሣ በኣቱን ሲይዝ ነው፡፡ ስለዚህ ከዘረኝነት የጸዳ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ብአዴን የተባለውን ሆድ እንጂ አንጎል ያልፈጠረበትን የወያኔና የኦህዲድ የትሮይ ፈረስ ባገኘው ሥልት ሁሉ አጥብቆ መታገል ይኖርበታል፡፡ አማራን እያስፈጀ ያለው ብአዴን ነው፡፡ ብአዴን ጥግ ከያዘ ሌላው ሁሉ ቀላል ነው፡፡ አማራን ያስቸገረው በርሱ ስም የሚነግደው አማርኛ የሚናገር ሕወሓትና ኦነግ ነው – ብአዴን፡፡ ሰውነታችን ውስጥ ነቀርሣ ካለ ያ ነቀርሣው ያለበት የአካላችን ክፍል ተቆርጦ እንዲጣል ይደረጋል፤ ይህን ማድረግ ጽድቅ እንደመሆኑ አማራን አበስብሶ ከምድረ ገጽ ሊያጠፋ ከዱሮ ጀምሮ ከአማራ ጠላቶች ጋር የሚተባበረውን ብአዴንን ቆርጦ መጣልና አማራንና ኢትዮጵያን ነጻ ማውጣት ለነገ የሚባል አይደለም፡፡ የውስጥ ነቀርሣ ሳይነቀል የአማራን ጠላት እታገላለሁ ማለት በራስ ላይ ሞትን መጋበዝና ጊዜን በከንቱ ማጥፋት፣ አጉል መስዋዕትነትንም መክፈል ነው፡፡
አንዳንድ ነገሮች በትኩረት ይታዩልኝ ዘንድ ልጠቁምና ልሰናበት፡፡
- አማራንና ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሲዖልም ድረስ ቢሆን እንደሚወርዱ በቃል አቀባያቸው በአማራው ጌታቸው ረዳ አማካይነት ዘወትር የሚደሰኩሩት ሕወሓቶች እርስ በርሳቸው እስከመገዳደል በሚደርስ የጠብ ክረት ቢጋጩም በአማራ ዕልቂት ላይ ያላቸው አቋም ግን ምን ጊዜም አንድና አንድ ነው፡፡ ለዚህም ነው ጻድቃን ገ/ትንሣኤንና ስዬ አብርሃን የመሰሉ የሕወሓት የቀድሞ ነቃፊዎች አሁን ቁርጡ ቀን ሲመጣ ገነትን የሚያስንቀውን ኑሯቸውን ትተው ገና ሳይሞቱ በቁማቸው ሲዖልን የመረጡትና ጫካ ገብተው ወንድሞቻቸውን በመቀላቀል ፍዳቸውን እያዩ የሚገኙት፡፡ ስለዚህ ሕወሓቶች ሞተውም ቢሆን አማራን እንደማይለቁት ጅላጅልና ጅላንፎው አማራ ቢገነዘብ ለኅልውናው ይበጀዋል፡፡ ይሄ መግነጢሳዊ ኃይል ያለው ኢትዮጵያዊነት የሚባል አፍዝ አደንግዝ ያነሆለለው አማራ እስኪነቃና በማንነቱ ላይ የታወጀበትን የዘር ፍጂት እስኪረዳ ስንት ዓመት ይፈጅ ይሆን ግን? የነቃ ዕለት ግን ምድረ አራጅ ዘረኛ ወዮለት!! አማራ ለጊዜውም ቢሆን አማራነቱን አስታውሶ ከኢትዮጵያዊነቱ ጋር በማዋሃድ አዋጭ ትግል ማድረግ ይኖርበታል፡፡ አለበለዚያ ከእስካሁኑም በባሰ ሊጎዳ ይችላል፡፡
1.1 “አማራንና ኦርቶዶክስን በገቡበት ገብተን እናጠፋቸዋለን፡፡ እነዚህ አካላት የትግራይ ታሪካዊ ዋነኛ ጠላቶች በመሆናቸው እነሱን ከማርናቸው አባታችን ዲያብሎስ አይማረን፡፡” (ከወያኔ ማኒፌስቶ ተሻሽሎ የተወሰደ)፡፡ ይህ መመርያ ለሽዎች አማሮች ዕልቂት መሠረት ነው፡፡
- አክራሪ ኦሮሞዎች በመቶ ጎራም ይደራጁ በመቶ አምሣ፣ እርስ በርሳቸው ይጣሉም ይገዳደሉ በአማራ ዕልቂት ላይ ያላቸው አቋም ግን ልክ እንደወያኔዎቹ ምን ጊዜም አንድና አንድ ነው፡፡ የአማራን ጭፍጨፋ በተመለከተ ወያኔም ኦነግ/ኦህዲድም አንድ ናቸው፡፡ ለዚህም ነው የነሱ ጠብ መሬት ያልያዘና ሥልታዊ የሆነው፡፡ ሁለቱ የምር ጠብ ውስጥ የሚገቡት አማራ ካለቀላቸው ብቻ ነው፡፡ ያ ደግሞ በምኞት የሚቀር ስለመሆኑ መጪው ጊዜ በግልጽ የሚመሰክረው የማይቀር ክስተት ነው፡፡ አንዱ ፌዴራሉን፣ አንዱ ጫካውን ይዘው ቢጨፈጭፉትም አማራ እየበዛ እንጂ እየጠፋ ሲሄድ አይታይም፡፡ ባለቆንዳላ ሴታሴት ሸኔም በሉት ወያኔ፣ ኦነግም በሉት ኦህዲድ በቅርብ ይጠፋሉ፡፡ አንድ ወንድ ቢያገኙ እነዚያ ሕጻናትን በስስት እንደመሳም አጋድመው የሚያርዱ ቆንዳላዎች ይገቡበትን ባጡ ነበር፡፡ ጀግና የሚገድለውን ያውቃል፡፡ የሚገድለውን የማያውቅ ፈሪ ነው፡፡ ፈሪ ደግሞ የሰው ጥላ ቀርቶ የዛፍ ጥላ ቢያይ ሳይታኮስ ገደል ይገባል፡፡ እናውቀዋለን፡፡ ያቺ ጊዜ ደግሞ ቀርባለች …. በሰላም ያድርሰን፡፡
2.2 እኔ as Oromo nationalist let me tell you ….. ያለችዋ ኢትዮጵያ እኛን ገድላ መኖር ስለፈለገች የኛን ሕዝብ ከሞት ለማትረፍ ኢትዮጵያን አሳድገን – ኦሮሞን – [ማለቴ] ኢትዮጵያን ዝቅ አድርገን ኦሮሞን ከፍ የሚያደርግ ዲስኮርስ ተጠቅመናል፡፡ We deconstructed Ethiopia. We want to reconstruct Oromo. (የወያኔው ልጅ ኦነግ በአንዱ ባለሥልጣኑ በቅርቡ ያስነገረው ዳግማዊ የወያኔ ማኒፌስቶ ነው ይሄ ደግሞ) – የሚገርመው ይህን ሁሉ የዘር ማጥፋት መፈክር የሚሰማው አማራ ዝም ብሎ መተኛቱ ነው፡፡ ለነገሩ ጽንስም አለቀኑ አይወለድምና አለመቸኮል ይሻላል፡፡ (https://t.me/ytgebar/185701)
- አማራም ሆነ አጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ “የናቁት ወንድ” ማስረገዙን ያውቅ ዘንድ ከልክ ያለፈ እጅግ ታላቅ መስዋዕትነትን ከፍሎ አረጋግጧል፡፡ እውነተኞቹ ወንዶች እስኪመጡ ብዙ መከራና ፍዳ እያየን መቆየታችን የታሪክ ፍርጃ ነው፡፡ ግን ሁሉም በፈጣሪ ወደቦታው እንደሚመለስ አንጠራጠር፡፡
ይህን እውነት አንርሳ፡፡ መናቅ ያዋርዳል፤ መናቅ ከሰውነት በታች ያውላል፡፡ ይህን ክስተት በተለይ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ አየነው፡፡ አማራውም ሆነ ሌላው ወገን የትም አይደርሱም ሲላቸው የነበሩ የሃያ ዓመት ዕድሜን እንኳ በቅጡ ያልደፈኑ ሰባት ኩታራ ታጣቂዎች በ17 ዓመታት ውስጥ አንዲት ታላቅ ሀገር አፈረሱ፤ ሕዝቧንም በተወሰነ ደረጃም ቢሆን በዘርና በሃይማኖት፣ በጎሣና በጎጥ ከፋፈሉ፤ በክልልና በዞን በታተኑ፡፡ አሁንም ተተኪዎቹ ኦነግ/ኦህዲዶች ሀገርን ገሃነመ እሳት እያደረጉ ባለበት ወቅት የትም አይደርሱም በሚመስል ንቀት ሕዝቡም ነቃ ያለው የኅብረተሰብ ክፍልም ተኝቷል፡፡ የተናቀ ማስረገዙን ለማወቅ ይህን ያህል ከፍተኛ የዘመናት መስዋዕትነት መክፈል አልነበረብንም፡፡ ያሳዝናል፡፡
- ሰሞኑን የዩንቨርስቲ መምህራን የደመወዝ ጥያቄ አንስተዋል፡፡ ጥያቄያቸው ካልተመለሰም የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ ዝተዋል፡፡ ትክክል ናቸው፡፡ የስምንትና አሥር ሽህ ብር ደመወዝ ከኩሽና መሰል የቤት ኪራይ በማያልፍበት የገንዘብ ግሽበት አንድን መምህር በዝቅተኛ ክፍያ ሥራ ማለት በጥይት ከመግደል የማይተናነስ ወንጀል ነው፡፡ እነሱ በኔና ባንተ ገንዘብ በሚገዛ የ10 እና የ20 ሚሊዮን ቪ8 መኪና እየተንፈላሰሱ፣ በምስኪን ዜጎች ሕይወት መቀለድ አግባብ አለመሆኑን ማወቅ ነበረባቸው፡፡ ለነገሩ እነሱ ሆድ እንጂ ጭንቅላት ስለሌላቸው ከእንስሳት ካነሰ እንስሳ ምንም አይጠበቅም፡፡
ለማንኛውም ይህን የአድማ ጥሪ በሚመለከት የጭራቆቹ ንጉሥ ግራኝ አቢይ ተናገረው የተባለው ነገር እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ ይህን ሁኔታ ሲሰማ “ያድርጉትና እንተያያለን” ነው ያለው፡፡ እንዲህ ያለ ንግግር መብቱን ለሚጠይቅ ዜጋ አይሰጥም፡፡ አቢይ በኢትዮጵያ ላይ የሠራው ግፍና በደል የሞት ፍርድ ባለበት አንደኛው የአውሮፓ ሀገር ውስጥ ቢሆን ኖሮ አንድ ሣይሆን አንድ ሽህ ሞቶችን ባስፈረደበት ነበር፡፡ ይህ ሰውዬ የወመኔዎችና የዱርዬዎች መሪ እንጂ የሀገር መሪ ሊሆን እንደማይችል አዘውትረን የምንናገረው ለዚህ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት መልስ ከዱርዬም አይጠበቅም፡፡ በማን ላይ ቆመሽ እንዲሉ ይህ ወፍ ዘራሽ ወጠጤ ጊዜ ሰጥቶት ባዶ ባገኘው ቤተ መንግሥት ቢገባ ይህን መሰል ዕብሪታዊ ምላሽ ሊሰጥ በቃ፡፡ አንድ ሰው የተዋጣለት ማይምና መደዴ ሲሆን እንደዚህ ይሆናል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ዜጋ እየተራበ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ዜጋ እየተሰደደ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ዜጋ በሰው ሰራሽ ጦርነትና መንግሥት ተብዬው አደራጅቶና አስታጥቆ በላካቸው ሸኔዎችና ወያኔዎች በማንነቱ ሳቢያ በየቀኑ እየታረደ፣ እርሱ ግን በሚሊዮን የሚገመት ዜጋ ከቤት ንብረቱ እያፈናቀለ በርስታቸው ላይ የ500 ቢሊዮን ብር ቤተ መንግሥት ይገነባል፡፡ በአማራ ደም ጎርፍ እየዋኘ ይዝናናል፡፡ በውነቱ የዚህ ሰውዬ ሰውነት ሥሪት በጣም ይገርመኛል፡፡ይህ ጨለማ ዘመን ሲነጋ የሚወራው ጉድ መቼም ትንግርት ነው፡፡
ርዕሴን መለወጥ አይቻልም፡፡ “ጊዜ አጥቼ” ወደርዕሴ ሳልገባ በመሰናበቴ ግን አዝናለሁ፡፡ ይቅርታ፡፡
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ