ጠላትህ ሲጀምር ራሱን ማጋለጥ፣ እስከሚጨርስ ታዘብ ብለህ ጸጥ
(Never interfer with your enemy while he is destroying himself, Napoleon Bonapart)
ወያኔ አዲሳባን ተቆጣጥሮ በጦቢያ ላይ አዛዥ ናዛዥ መሆኑን እንዳረጋገጠ በመጀመርያ ያደረገው፣ ባዲሳባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሚያስተምሩትን፣ የወያኔን ፀራማራ ጎጠኛ ፖሊሲ ይቃወማሉ የሚላቸውን ታላላቅ የአማራ ምሁራን በብጣሽ ወረቀት ማባረርና ወደ ዩኒቨርስቲው ዝር እንዳይሉ በጥብቅ መከልከል ነበር፡፡ በዚህ ድርጊቱ በግልጽ ያረጋገጠው ደግሞ በወያኔ ዘመን አማራዊነት የሚሰማቸው፣ ለአማራ ሕዝብ የሚቆረቆሩ ምሁራን፣ በማናቸውም ዩኒቨርስቲ ውስጥ (በተለይም ደግሞ አዲሳባ ዩኒቨርስቲን በመሰሉ ትላልቅ ዩኒቨርሲቲወች ውስጥ) ቦታ እንደማይኖራቸው ነው፡፡ ጭራቅ አሕመድ የነገሰበት የኦነግ ዘመን ደግሞ ሌላ ምንም ሳይሆን የወያኔ ፀራማራ ፖሊሲ እጅግ በከፋ ሁኔታ የቀጠለበት የአማራ ሰቆቃ ዘመን ነው፡፡
ስለዚህም በወያኔና በኦነግ ዘመን በረዳት ፕሮፌሰርነት (assistant professor)፣ ተባባሪ ፕሮፌሰርነት (associate professor) ወይም ሙሉ ፐሮፌሰርነት (full professor) ባዲሳባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዲያገለግሉ የወያኔንና የኦነግን እሽታ ያገኙ ሰወች ሊሆኑ የሚችሉት ከሚከተሉት ካራቱ ውስጥ አንዱን ነው፡፡
- የወያኔንና የኦነግን ፀራማራ ሕገመንግስሥት በሙሉ ልባቸው አምነውበት የተቀበሉ፣ የአማራን ሕዝብና አማራዊነትን አምርረው የሚጠሉ የትግሬና የኦሮሞ ፀራማራ ጽንፈኞች፡፡
- ያለም አገሮች እንዴት እንደተመሠረቱ የማያውቁ፣እንጨት ሳይቆረጥ ቤት እንደማይሠራ ያልተገነዘቡ፣ የራሳቸውንና ያገራቸውን ማንነት በቅጡ ያልተረዱ በመሆናቸው የተነሳ፣ በወያኔወችና በኦነጎች ስብከት የጥፋተኝነት ወይም የዝቅተኝነት ስሜት እንዲያድርባቸው ተደርገው፣ የራሳቸውን አማራነት ከመጥላት አልፈው የአማራን ሕዝብ አምርረው እንዲጠሉ የተደረጉ፣ ስለ ብሔር ምንነት ሳይማሩ ስለ ብሔር ጭቆና የሚደሰኩሩ፣ በማርክሲዝም ጥራዝ የነጠቁ፣ ቢከፍቱት ተልባ የሆኑ የዋለልኝ መኮንን ቢጤ ግልብ አማሮች፡፡
- ለሆዳቸው ሲሉ ለወያኔና ለኦነግ ያደሩ ሆዳደር አማሮች፡፡
- ወያኔና አነግ አሸናፊወች ስለሆኑ ብቻ፣ ከወያኔና ከኦነግ ጋር ለመሥራት የመረጡ (ወይም ደግሞ ከወያኔና ከኦነግ ጋር ከመሥራት ውጭ ምርጫ የሌላቸው) አልአማራ(አማራ ያልሆኑ) ግለሰቦች፡፡
በተራ ቁጥር (1) ከተገለጹት ፀራማሮች ውስጥ ለአማራ ሕዝብ እጅግ አደገኛ የሚሆኑት ትክክለኛ ስማቸው አማራዊ የሆነው ወይም ደግሞ የአማራን ሕዝብ ማታለል ይችሉ ዘንድ (ልክ እንደነ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋና ከበደ ጫኔ) ስማቸውን ወደ አማራዊ ስም የቀየሩት ናቸው፡፡
በተራ ቁጥሮች (2) እና (3) የተገለጹት ፀራማሮች ለአማራ ሕዝብ እጅግ አደገኛ የሚሆኑት፣ አማራ ስለሆኑ ብቻ የአማራን ሕዝብ ለጉዳት አይሰጡም ብሎ የአማራ ሕዝብ እምነት ካሳደረባቸው ብቻ ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ፣ የአማራ ሕዝብ አስቀድሞ መታገል ያለበት፣ በተራ ቁጥር (1) የተገለጹትን የግንባር ጠላቶቹን ሳይሆን፣ በተራ ቁጥር (2) እና (3) የተገለጹትን የጉያ ጠላቶቹን ነው፡፡ አብናቶቻችን (አባቶቻችን እና እናቶቻችን) ጠላትማ ምንግዜም ጠላት ነው፣ አስቀድሞ መግደል አሾክሿኪውን ነው የሚሉት፣ የውጭ ጠላትን ማሸነፍ የሚቻለው የውስጥ ጠላትን አስወግዶ ውስጥን በማጠንከር ብቻ መሆኑን አጽንኦት ለመስጠት ነው፡፡
በተራ ቁጥር (4) የተገለጹት ግለሰቦች በነፈሰበት የሚነፍሱ (ወይም በነፈሰበት ከመንፈስ ውጭ ምርጫ የሌላቸው) በዋል ፈሰሶች ስለሆኑ፣ የአማራ ሕዝብ እነሱን ከጎኑ ማሰለፍ የሚችለው፣ ወያኔንና ኦነግን በማያዳግም ሁኔታ ድል በማድረግ አሸናፊነቱን ሲያረጋግጥላቸው ብቻ ነው፡፡
በወያኔ ዘመን የአዲሳባ ዩኒቨርስቲ አስተማሪወችና ሹሞች የነበሩትንና አሁንም በኦነግ ዘመን የሆኑትን እንደነ እንድርያስ እሸቴ፣ ገነት ዘውዴ፣ ዳኛቸው አሰፋ፣ ደረጀ ዘለቀ እና በለጠ ሞላ ያሉትን ግለሰቦች፣ የአማራ ሕዝበ መመልከት ያለበት በተራቁጥሮች (1)፣ (2) እና (3) በተገለጹት መነጽሮች መሠረት ነው፡፡
አማራዊ ስም ያላቸው፣ ወይም ደግሞ አማራን ለማታለል ሲሉ ስማቸውን ወደ አማራዊ ስም የለወጡ የትግሬና የኦሮሞ ፀራማሮች፣ ወይም ደግሞ አማራ ሁነው አማራነታችን የሚጠሉ ፀራማሮች፣ ወይም ደግሞ ለሆዳቸው ሲሉ ላማራ ጠላቶች ያደሩ ሆዳደር ፀረማሮች፣ የአማራን ሕዝብ ከሚያጠቁባቸው የተለያዩ መንገዶች ውስጥ የሚከተሉት ሁለቱ ዋናወቹ ናቸው፡፡
አንደኛው መንገድ፣ ለአማራ ሕዝብ በሚታገል አብንን በመሰለ ድርጅት ውስጥ ተሹለክልከው በመግባት ያመራር ቦታወችን ይዘው፣ በድርጅቱ ላይ የአማራ ሕዝብ ትልቅ ተስፋ ማሳደር እስከሚጀምርና፣ ለአማራ ሕዝብ በቅን የሚታገሉት የድርጅቱ ሰወች በግልጽ እስከሚታወቁ ድረስ ከጠበቁ በኋላ፣ ድርጅቱን በማፈራረስ የአማራን ሕዝብ ተስፋ ማስቆረጥና ቆራጥ ታጋዮቹን ማስመታት ነው፡፡ ለንደዚህ ዓይነቶቹ ፀራማሮች ዓይነተኛው ምሳሌ በለጠ ሞላ ነው፡፡ በለጠ ሞላ የአማራ ሕዝብ ብዙ መስዋዕትነት የከፈለበትን ትግል አቅልጦ አበጠ እንጅ ስላልቀለጠ፣ ቀለጠ ሞላ ሊባል አይገባውም፡፡
ሁለተኛው መንገድ ወያኔንና ኦነግን በጽኑ የሚቃወሙ መስለው ከፍተኛ ያማራ ተከታይ ካፈሩ በኋላ፣ በድንገት እጥፍ ብለው በወያኔና በኦነግ ሚዲያወች ላይ በመቅረብ፣ የአማራን ሕዝብ ወያኔወችና ኦነጎች ከሚወቅሱትና ከሚከሱት እጅግ በከፋ ሁኔታ በመውቀስና በመክሰስ፣ የአማራ ሕዝብ መሪወቹን ሁሉ እንዲጠራጠርና ከእውነኛ መሪወቹ ጋር በሙሉ ልቡ እንዳይቆም ማድረግ ነው፡፡ ለንደዚህ ዓይነቶቹ ፀራማሮች ዓይነተኛው ምሳሌ ደረጀ ዘለቀ ነው፡፡ ደረጀ ዘለቀ ወያኔና ኦነግ ሲጣሉ ካደፈጠበት ወያኔና ኦነግ ሲታረቁ በድንገት ብቅ ያለው ያማራን ሕዝብ የሕልውና ትግል ለማጥለቅ (ወይም የማጥለቅ ተልእኮ ተሰጥቶት) ነው፡፡ የደረጀ ዘለቀ ፀራማራ ዓላማ የሚሳካው ደግሞ፣ የአማራ ሕዝብ ዋና ትኩረቱን በዋና የሕልውና ጠላቱ በጭራቅ አሕመድ ላይ ከማድረግ ይልቅ፣ በደረጀ ዘለቀ እንቶ ፈንቶ ላይ ካደረገ ብቻ ነው፡፡
የአማራ ሕዝብ፣ የሱ ወገን ይመስሉት የነበሩት ሕቡዕ ጠላቶቹ ራሳቸውን በራሳቸው ገሃድ አውጥተው ይፋ ጠላቶቹ መሆናቸውን ሲያረጋግጡለት ተስፋው ሊለመልም እንጅ ሊከስም አይገባም፡፡ ጠላቶችህን ማሸነፍ የምትችለው ጠላቶችህን በደንብ አውቀኻቸው ራስህን ከጠላቶችህ ሙሉ በሙሉ ስታጸዳ ብቻ ነው፡፡ ጠላቶችህ ራሳቸውን በራሳቸው ካጋለጡልህ ደግሞ ትልቁን ሥራ ራሳቸው ሰርተውልህ የራሳቸውን ሽንፈት ራሳቸው አቃረቡልህ ማለት ነው፡፡ ታላቁ ናፖሊዮን እንዳለው ጠላትህ ሲዋከብ ራሱን ሊያጠፋ፣ አንዳታውከው ድምጽህን አጥፋ (Never interfer with your enemy while he is destroying himself)፡፡ ደረጀ ዘለቀም ራሱን እያጠፋ ስለሆነ፣ የአማራ ታጋዮች ከሱ ጋር አታኻራ ገጥመው ራሱን ከማጥፋት ሊያውኩት አይገባም፡፡
መስፍን አረጋ
https://youtu.be/oMjj__OWE4s