ትኩረት ለስነምግባራዊ መሪወች እና ድርጅቶች  ግንባታ!! – በስንታየሁ ግርማ አይታገድ

ታዋቂዊ  የስራ አመራር  ምሁር  ፒተር ድሩከር በእድገት ወደ ሆላ ሀገሮች ይልቅ በስአመራር የተበድሉ ይበዛሉ በሚለዉ አባባሉ በብዛት ይታወሳል ፡፡አባባሉ ለሀገር ወይንም ለድርጅት  እድገትም ሆነ ዉድቀት ወሳኙ የሰዉ ሀይል  በተለይም ስነምግባራዊ መሪወች ወሳኝ መሆናቸዉን ን  ያሳያል፡፡

አስሞለጉ እና ሮቢነሶን why nations fail    በሚል መጥሃፋቸዉ አናዳንድ ሀገሮች የበለጠጉ ልሎች ደግሞ በድህንት አረንቆ የተዘፍኡት በተፈጥሮ፤በአየር ንብረት፤በባሀል ልዩነቶች ሳይሆን አካታች ፖለቲካዊ እና ኢኮናማዊ ስረአት በመሪወቻቸዉ መገንባት መቻል ወይን አለማቻል ነዉ ዪላሉ፡፤በተፈጥሮሀብት ፤በአየር ንብረት፤በባህል መሳስል ቢሆን ኖሮ ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ በተመሳሳ እድገት በተገኙ ነበር፡፤ለልዩነቱ መንስኤ በደቡብ ኮሪ ያ  ፈጠራን የሚያበረታታ የኢኮኖሚ እና የባለስልጣን ሳይሆንን የህግ የበላይነት የሰፈነበት አካታች የፖለቲካ ስርአት መገንባቱ እ ና በጥብቅ ተግባራዊ መድርጉ ነዉ፡፡ለዚህ አይነት አካታች ስረአት ለመገንባት ድግሞ መሪወች በተለይም ስነምግባራዊ መሪወች መኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለዉ፡፤ በስነምግባር አርአያ  የሆኑ መሪወች አካታች ስረአት ይገነባሉ ፡፤ በስነምግባር የዘቀጡ ባለስልጣኖች ደግሞ አግላይ ስርአት በመግንባት ሙሳናን ባህል በማድረግ ማሃባራዊ ካፒታልን በመሠሸርሸር ሀገርን ወደ ዉድቀት አዞሪት ይከታሉ፡፡

በዚህ አለም እንደ ሥነምግባር በመጥፎም ሆነ በጥሩ ለሀገርም ሆነ ለተቋማት ወሳኝ ነገር የለም፡፡ በአለም ላይ ያደጉ እና የለሙ ሀገሮች መሠረታቸው ስነምግባር ነው፡፡ ለምሣሌ የምዕራቡ አለም እድገት “ከኘሮቴስታንት ስነ ምግባር” ጋር ሲያያዝ በ3ዐ አመታት ውስጥ ከግማሽ ቢሊዮን በላይ ህዝብ ከድህነነት ወለል በማውጣት የምትታወቀው ቻይና እድገት አንዳንድ  ኋላ ቀሪ የኮንፈሲየስ ባህላዊ እሰቶች ከመለወጥ ጋር ይያዛል፡፡ በአለም በከፍተኛ ፍጥነት እድገት ያስመዘገቡ የሩቅ ምሥራቅ ኤስያ ሀገራት ደግሞ እድገታቸው ከህዝብ ብሔራዊ መግባባት ጋር ይያዛል፡፡ እንደኰሪያ የመሣሰሉት ሀገራት ሌባ እንኳን ለክቶ የሚሠርቅበት ሀገር ነበሩ፡፡ ለምሣሌ  ለኤክስፖርት በተዘጋጀ ምርት እና አገልግሎት ላይ የጉምሩክ ሠራተኞች ስርቆት አይፈፅሙም ነበር፡፡ መሀንዲሶች በሚገነባው ጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤት፣ መንገድ የራሳቸውን 1ዐ በመቶ ኮሚሽን በመጨመር በጥራቱ፣ በጊዜውናበመጠኑ ላይ አይደራደሩም ነበር፡፡ ይህንን እስቲ ከእኛ ጋር ሌቦች ጋር አወዳድሩት ከዚህ በመነሣት ሥነምግባር ሙስናን ለመከላከል ወይንም ለመከሠት ዓይነት ሚና እንዳለው መረዳት እንችላለን፡፡ማህበረሰቡ ከማንኛውም የመንግሥት ተቋም ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋ፣ ትክክለኛ አገልግሎት ይጠብቃል፡፡ በአሁኑ ጊዜ  “ደንበኛ ሁልጊዜ ትክከል ነው ሉዕላዊ” ነው የሚሉት አባባሎች ከመቸውም ጊዜ የበለጠ ይሁንታ እያገኙ ነው፡፡

ደንበኛ ለማርካት የማይጥር ድርጅት፣ ተቋም፣ ሀገር እራሱን በገመድ አንቆ እንደ መግደል እየታየ ነው፡፡ ምክንያቱም ደንበኛ/ተገልጋይ የሚያማልሉ አገልግሎት ሰጪዎች እንደ አሸን እየፈሉ እና የድንበር የለሽ እየሆኑ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከልማት መጋረጃው በስተጀርባ

ምንም እንኳን በማህበረሰቡ ፍትሀዊ አገልግሎት ቢጠበቅም በማደግ ባሉ ሀገራት ግን ሥነምግባራዊ እሴቶች በመንግሥት አገልግሎት አሠጣጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሸረሸሩ ነው፡፡ ይህ የመንግሥት አገልግሎት አሠጣጥ መላሸቅ በዋነኝነት የሚገለፀው በሙስና መልክ ነው፡፡ ሙስና የህዝብ ስልጣን ለግል ጥቅም ወይም ትርፍ ማዋል ነው፡፡ ጉዳቱ ግን ዘርፈ ብዙ ነው፡፡

ሙስና ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና አካባቢያዊ ተፅዕኖዎች አሉት፡፡ በፖለቲካው መስክ ሙስና የህግ የበላይነት መሸርሸርእና ለዲሞክሪሲ ማበብ ትልቁ እንቅፋት ነው፡፡ ሙስና በተንሠራፋበት የሰዎች እንጂ የህግ የበላይነት በሌለበት ተቋማት አይገነቡም፡፡ ተቋማት ባልተገነቡበት ሁኔታ ደግሞ አካታች ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሥርዓት አይመሠረቱም፡፡ በተቋማት ያልታገዘ  እድገት እና ልማት ዘላቂነት አይኖረውም፡፡

በዳበረ የዲሞክራሲ ባህል ባላቸው ሀገራት ሣይቀር ሙስና የመንግሥት ቢሮዎች፣ ተቋማት፣ መርሆዎች ላይ እምነት በማሣጣት የቅቡልነት ቀውስ ውስጥ ይከታል፡፡

በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች ደግሞ የበለጠ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ሙስና በተንሠራፋበት ሁኔታ እና ቦታ ተጠያቂነት እና ልጓም ያለው የፖለቲካ አመራር ማስፈን አይቻልም፡፡

በኢኮኖሚው መሰክ ሙስና የሀገር ሀብት እንዲወድም ያደርጋል፡፡ በአብዘኛው ውስን የሆነው የህዝብ ሀብት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው/ለድሆች/ ከፍተኛ ባልሆኑ ኘሮጀክቶች ማለትም እንደ ግድቦች፣ የሃይል ማመንጨዎች፣ የቧንቧ መስመሮች፣ አስደናቂ ግን  መሠረታዊ ያልሆኑ አገልግሎቶች ላይ እንዲውል ይደረጋል፡፡ ት/ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ መንገዶች፣ ውሃ ወደ ገጠር አካባቢ እንዳይስፋፋ ያደርጋል፡፡ ከሁሉም የከፋ ደግሞ ውድድሩን በመገደብ የነፃ ገበያ እንዳይስፋፋ ያደርጋል፡፡ ኢንቨስትመንትም ያቀጭጫል፡፡

ሙስና በህብረተሰቡ ማህበራዊ ትስስር ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከሁሉም በላይ ነው፡፡ ህብረተሰቡ በፖለቲካ ሥርዓቱ ላይ ያለውን እምነት ያቀጭጫል፡፡ በተቋማት እና በፖለቲካ መርሆዎች ላይ ያለውን ተስፋ ያጨልመዋል፡፡ ቀድሞ በአገልጋይነት ደካማ የነበረው የሲቪል ሠርቪሱ ላይ ተስፋ መቁረጥ እና ግድሌሽነትን በተገልጋይ ስሜት ያሣድራል፡፡ ይህ ደግሞ በዲሞክራሲ በተመረጡ መሪሆዎች ሳይቀር ህሊና ቢስ በማድረግ የህዝቡን ሀብት ወደ ውጭ ሀገር እንዲያሸሹ ይረዳቸዋል፡፡ ጉቦ መጠየቅ እና መስጠት አፀያፊ ስነምግባር መሆኑ ቀርቶ የተለመደ እና ቅቡልነት ያለው መጥፎ ባህሪ ያደርገዋል፡፡

ስነምግባራዊ መሪ መገንባት ኢትዮፒያ አሁን ለተዘፈቀችበት ብልሹ አሰራር እና የሙስና ማእበል ዋነኛዉ መፍትሄዉ ነዉ፡፡መሪወች ስነምግባራዊ  ሲሆኑ ተከታዮቻቸዉ ስነምግባራዊ ይሆናሉ፡፡ መሪወቹ እና ተከታቻቻ ስነምግባራዊ ባኅል  ይገነባሉ፡፡በቀጣይ ስነምግባራዊ መሪ ምን እነደሆነ፤ስነምግባራዊ መሪ መርሆች ፡ስነምግባራዊ ባኅል  እንዴት   እንደሚገነባ እንይ

ስነ-ምግባራዊ (ግብረ ገብ) መሪ

  • መሪ ማለት ተከታይ ያለው እና መደበኛ ስልጣን ይኑረውም አይነረውም ተከታይ ካለው መሪ ነው፡፡
  • ስነ-ምግባራዊ (ግብረ ገብ) መሪ የሚመራበት መርህ ያለው ለመርሁ የታመነ ትክክል ያለሆነውን እየተወ ትክክል የሆነውን የሚተጋ እውነተኛና ፍትሀዊ የሆነውን ነገር በመስራት ለተከታዮቹ አርአያ የሚሆን ማለት ነው
  • አመራር ሆኖ ግለሰቡ የጋራ ጥቅም የሆነውን የሚያራምድ እና የሚተገብር ሆኖ በማንኛውም የህይወት መመዘኛ ተቀባይነት እና ተገቢ የሆነውን የሚፈፅም አመራር ነው፡፡
  • በማንኛውም ጊዜ ድርጊት እና አመራሩ ሥነ ምግባራዊ የተላበሰ ሲሆን ሥነ ምግባራዊ አመራር ይባላል፡፡ስነምግባራዊ ተቆም እና መሪ ለመገንባት መርሆቹን መከተል እና በጥብቅ  ተግባራዊ ማድረግን ይጠይቃል፡፤በተዋቡ እና በተሰደሩ ቃላቶች ተቆማት አይገነቡም፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  እንደእናቴ ሣይሆን እንደሚስቴ አውለኝ! ብሥራት ደረሰ

 

  • ከአርስቶትል ጀምሮ ያሉ ናቸው፡፡ የእነዚህ መርሆዎች ጠቀሜታቸው በተለያዩ ዲስፒሊን ውስጥ መወያያ ናቸው፡፡
  • ሥነ-ምግባራዊ መሪ ለመፍጠር መሠረቶች ናቸው፡፡

ሀ.ሥነ ምግባራዊ መሪዎች ሌሎችን /ተከታዮቻቸውን/ያከብራሉ፡፡ሌሎችን ያገለግላሉ(ያገለግላሉ)The servant-leader is servant first

 መሪ ማለት ተከታይ ያለው ማለት ነው  ተከታይ ሳይኖር መሪ መሆን አይቻልም እውነተኛ ተከታ ለማፍራት ደግሞ እውነተያ አገልጋይ የመሆንን ይ ጠይቃል”

ለ.ትክክለኛውን ይወስናሉ ይተገብራሉ

ሐ..ሐቀኝነት (honesty) እዉነትን የሚናገር ፤የሚተገብር

መ.ማህበረሰብ ይገነባሉ፤ማሃበራዊ ካፒታል ይገነባሉ

ሰ. አርአያ  መሆን፤መሪወች በቃላቸዉም ሆነ በድርጊታቸዉም አራአያ  ይሆናሉ

ሥነ ምግባራዊ ድርጅት እንዴት ይገነባል?

;

መልካም ስም የአንድ ሀገር ድርጅት ስኬታማነትን እና ውድቀትን ይወስናል፡፡ ለዚህም ነው የአለም ዋረን ቡፌት   ከምንም በላይ ለመልካም ስም /Reputation/ ከፍተኛ ትኩረት እሰጣለሁ ያሉት መልካም ስም ለመገንባት ብዙ አመታት ይፈጃሉ፡፡ ለማፈረስ ግን ሠኮንዶች ይበቃሉ፡፡ በዚህም ነው ጠንቃቃ ድርጅቶች ለመልካም ስም ከፍተኛ ትኩረት የሚሠጡት መልካም ሥነ ምግባር ጥሩ ስም እንደሚገነባ ሁሉ መጥፎ ስነ ምግባር የሠራተኞችን ሞራል ይጐዳል፣ ወጪን ይጨምራል፡፡ ስለዚህ መልካም ሥነ ምግባር ለመገንባት ተቋማት ትኩረት እየሰጡ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ስለሥነ ምግባር ዲዛይን ይሠራሉ፡፡ ሥነ ምግባራዊ ባህል ለመገንባት 4 ጉዳዮች ትኩረት መሰጠት ይገባል፡፡ ግልፅ የሥነ ምግባር እሴቶች መቅረፅ እና መተግበር፣ ሚዘናዊ ፍርድ፣ ማበረታቻዎች እና ተቀጣይነት ያላቸው ባህላዊ ልምዶች መተግበር ናቸው፡፡ እነዚህ አራት የባህላዊ ልምዶች ምሶሶ በመባል ይታወቀሉ፡፡

ግልፅ የሥነ ምግባር እሴቶች መቅረፅ እና መተግበር፣

 

እስትራቴጂዎችና ተግባራት በአግባቡ በግልፅ መርሆዎች ላይ ተመስርቶ መቅረፅ  እና በሁሉም

ሠራተኞች ዘንድ የጋራ ግንዛቤ ሊይያዝ ይገባል፡፡

ስለዚህ ደግሞ በአግባቡ የተቀረፀ ተልዕኮ ያስፈልጋል፡፡ከመርሆዎች ጋር የተጣጠመ ተልዕኮ መቅረፅ ይገባል፡፡ የሚቀረፀው ተልዕኮ አጭር ግልፅ፣ ስሜትን የሚያነሳሳ እና የሚያስተጋባ መሆን አለበት፡፡ ይሁንና የአብዛኛዎቹ ተቋማት ተልዕኮ በምናይበት ጊዜ በጣም ረጅም፣ ከሠራተኞች የዕለት ተዕለት ተግባራት ጋር ያልተቀናጀ እና ሠራተኞች የሚመሩባቸው መነሻ አይደሉም፡፡ የተልዕኮ መግለጫዎች በወረቀት ላይ የሚቀመጡ ቃላቶች መሆን የለባቸውም፡፡ በቅጥር፣ በስንብት በእድገት ወዘተ እንደ ፖሊስ  ማገልገል አለበት፡፡ የፔንታጐን ተልዕኮ በምናይበት ወቅት ምን ያህል ግልፅ፣ አጭር እና የሚያነሣሣ መሆኑን መንዘብ ይቻላል፡፡  ‘’Build the best product  cause no unnecessary harm, use business and implement solutions to the environmental crisis’’.

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትምክህተኛና ጠባብ ማን ነው? - ከአስገደ ገ/ስላሴ መቀሌ

ሚዘናዊ ፍርድ

ብዙ ሰዎች ውሣኔ በሚወስኑበት ወቅት ሥነ ምግባር ግምት ውስጥ የማስገባት ችግር አለባቸው፡፡ በዚህ የተነሣ ሥነ ምግባራዊ ጉድለቶች ይከሰታሉ፡፡

የትኩረት ምንጭም ይሆናሉ፡፡ ለምሣሌ የቅርብ ዘመዳችንን ወይንም ጓደኛ ስንቀጥር በሌሎች በማናውቃቸው ሰዎች ላይ የምናደርሰው ጉዳት ግምት ውስጥ አናስገባም፡፡ ብዙውን ጊዜ የምናሣየው ባህሪይ በአዕምሮአችን ወዲያኑ የመጣውን ተግባር ላይ ስናስታውል ሚዘናዊ ፍርድ የመስጠት እድላችንን ያጠበዋል፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜ ፍርድ ስንሰጥ በምናውቃቻውና በማናውቃቸው መካከል ልዩነት ላለመፍጠር ሁለት ጊዜያት ማሰብ ይገባል፡፡

ማበረታቻዎች

ግልፅ ተልዕኮ ከመቅረፅ እና ከመተግበር ሚዘናዊ ፍርድ ከመስጠት ጐን ለጐን ሥነ ምግባራዊ ተቋማት ለመፍጠር ማበረታቻዎችን ከሥነ ምግባር ጋር ማያያዝ ይገባል፡፡ ውጤት የተመዘገበው ስነ ምግባራዊ መሆን /አለመሆን/ ማገናዘብ ያስፈልጋል፡፡ ሠራተኞች ሥነ ምግባራዊ ስለሆኑ ማበረታቻ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ እነዚህ ማበረታቻዎች የተለያዩ ዓይነቶች /ውጫዊ እና ውስጣዊ/ መሆን ይገባቸዋል፡፡

ከገንዘብ ማበረታቻ በተጨማሪ ሠራተኞች የሚያረካቸውን ሥራ፣ አወንታዊ ተፅእኖ ማሣደር ክብር እና መደነቅን ይፈልጋሉ፡፡ ይሁንና የሥነ ምግባር አመራሮች ከፋይናንስ ውጭ ያሉ ማበረታቻዎችን ትኩረት ሲሰጧቸው አይታይም፡፡  በፎርቹን 5ዐዐ የመጀመሪያ ድርጅቶች እንኳን ስለእነዚህ ማበረታቻዎች የሚሠጡት ትኩረት አናሣ ነው፡፡ ይሁንና ሥነ ምግባራዊ ሠራተኞች እውቅና መስጠት፣ ማመስገን፣ ይገባል፡፡ ተሸላሚዎችን የሚሠጣቸውን ሽልማት ለማህበራዊ አገልግሎት እንዲያውሉት ማድረግ የበለጠ ያበረታታቸዋል፡፡ ሥነ ምግባራዊ ባህሪ ሥነ ምግባራዊ ሥራ ብቻ እንዲሠሩ የሚያበረታታ ብቻ ሣይሆን ጥሩ ስሜትም እንዲሰማን የሚያደርግ ነው፡፡

ባህላዊ ልምዶች

ብዙ መሪዎች ከላይ ላሉት የሥነ ምግባር ስታንዳርድ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ ይሁንና ለመካከለኛው አመራር ጥብቅ ሥነ ምግባራዊ ስታንዳርድ መቅረፅን ችላ ይሉታል፡፡ ይሁንና በመካከለኛው አመራር የሚቀረፅ የሥነ ምግባር ስታንዳርድ የሠራተኞችን ባህሪ በማነፅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ጥሩ መርሆዎች ጥሩ ተከታይ ያፈራሉ፡፡ ይሁንና ሠራተኞች በሚዋሹ በሚያታልሉ በሚሠርቁ መካከለኛ አመራሮች የሚከበቡ ከሆኑ አብዛኛው የሚዋሹ የሚያታልሉና የሚሠርቁ መሆናቸው እድል ከፍተኛ ነው፡፡

መርሆዎች ስነምግባራዊ ባህል ለማበረታታት ጥሩ ሥራዎች ምን ምን እንደሆኑ ያሣውቃሉ፡፡ ስለዚህ የሥነ ምግባር ምልክቶችን /Ethical beacons/ ተግባራዊ ማድረግ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

በአጠቃላ ስነምግባራዊ መሪወች እና ድርጅቶች  ለመፍጠር ትኩረት በመሥጠት ለሁላችንም የተሸለች ኢትዮጵያን  መፍጠር ይገባናል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share