November 9, 2022
7 mins read

ኢትዮጵያ – ትናንት እና ዛሬ !

ETHIOPIAN INTELትናንት ኢትዮጵያ በአስራ አራት ክ/ሀገራት  ምሰሶች ተዋቅራ  የሠላም ምድር እና የአበሻ ስም በየትኛዉም የዓለም ክፍል የሚከበርበት ነበረች ፡፡

የራሷ የባህር በር የነበራት፣  ዜጎች በችሎታ እና ለአገራቸዉ እና ለህዝባቸዉ ባደረጉት በጎ ዉለታ ለኃላፊነት እና ሹመት የሚታጩባት አገር ነበረች ፡፡

እንደዛሬዉ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ በአገር ዉስጥ አይደለም በዉጭ አገር በቀን ብርኃን ቀርቶ በድቅድቅ ጨለማ ማንም የማይደፍረዉ ነበር ፡፡ ዛሬ በዉጭ አይደለም ከቀበሌ ቀበሌ በባይታዋርነት እና በባዕድነት የሚታይበት ፤ዜጎችን በማንነታቸዉ ለይቶ ማገት፣ ማጉላለት፣ መግደል….. ቀላል ከመሆን አልፎ በህግ የተፈቀደ አስከመሆን ተደርሷል፡፡

ይህ ሁላ የሆነዉ ሁሉም የቀበሮ ባህታዊ መሆን እና የአገር ጉዳይ  እኔ ፤የእኛ ጉዳይ ነዉ ዕምነቱም፣ ወጉም ሁሉም በአገር ነዉ የሚል እና ታሪክን ከኋላ የማየት ችግር ያስከተለዉ  ሰንኮፍ ነዉ ፡፡

የኢትዮጵያን የነበረዉን የቀድሞ የግዛት አስተዳደር አድበስብሶ በማለፍ ታላቋን ኢትዮጵያ ማሰብም ሆነ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ማለት ከከንቱ ዉዳሴ ዉጭ ዘጭ እምቦጭ ነዉ ፡፡

የኢትዮጵያ ታላቀነት እና ገናናነት ከኢትዮጵያ ህዝብ ሉዓላዊ  ጥቅም እና ስም ዉጭ ማሰብ ከአሳ አልባ ባህር አሳ እንደመጠበቅ ነዉ ፡፡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለዘመናት ያለዉ ስደት፣ዉርደት፣ድህነት፣ሞት…… ምንጭ የሆኑ አስተሳሰቦች እና ድርጊቶችን ከመሰረት ማምከን እየተቻለ በሰሞንኛ  ጉዳዮች ላይ መጠመድ የሚያሰገኘዉ ዕዳ እንጃ ፋይዳ የለም ፡፡

ኢትዮጵ ትናነትና ዛሬ በሚል አስተያየት ለመስጠት መነሻየ  “በበቢሲ” የዓማርኛ የፅሁፍ ዜና እ.ኤ.አ. ህዳር 4 ፣2022 በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ቁልፍ ጉዳይ  “ምዕራብ ትግራይ/ ወልቃይት ” የሚለዉ ነዉ ፡፡

በአንድ አገር ላይ የህዝቦች ወይም ዜጎች  ሉዓላዊ መብት የሚጠበቀዉም ሆነ የሚከበረዉ በዚህች አገር በሚኖሩ ህዝቦች ብቻ እንደሆነ ይታወቃል ፡፡

ሆኖም ከሞኝ ደጂ ዛፍ….እንዲሉ  ስለራሱም  ሆነ ስለ አገሩ ግድ በማይል እና ዕረኛ እንደሌለዉ የበግ መንጋ በሚባዝን ማህበረሰብ ለምን ፤ከልካይ የለብንም በሚል ስሁት አስተሳሰብ በታሪክ እና በመልካ ምድር ከኦሪት አስከ ትናንት (1983 ዓም) የጎንደር ክ/ሀገር የግዛት አካል የነበረዉን የኢትዮጵያ ክፍል -ሰሜን ጎንደር /ዳባት አዉራጃ  በቁርጥ ቀን የህዝብ ልጆች የህይወት እና የአካል ዋጋ መሰዋዕት ኢትዮጵያን ዳግም ዳር ድንበሯን ከመቆረስ  “ወልቃይት እና  ተከዜ መለስ ” ወደ ኢትዮጵያ የአስተዳደር ቋት በማስቀረት እንዲሁም  ትህነግ ለሁለተኛ ጊዜ ትግራይ ክ/ሀገር የኢትዮጵያ የግዛት አካል ሆና እንድትቀጥል ሳይፈልግ በግድ እንዲስማማ  ሆኗል፡፡

ሆኖም  ሆድ ያበዉን ጌሾ እንዲሉ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የሰሜን ምዕራብ እና ዐማራ ህዝብ ለደረሰበትን የዘመናት ስደት ፣ዕልቂት እና ሞት  ዕንብርት የሆነዉን ጎንደር / ሰሜን ጎንደር …ሁመራ…..ወልቃይት ወይም በቀደመዉ ስያሜ ዳባት አዉራጃ ከታሪክ ፣ህግ እና ከኢትዮጵያ መልካ ምድራዊ መገለጫዎች ዉጭ ዛሬም ምዕራብ ትግራይ ማለት ከሙያ ስነምግባር ዉጭ ኢትዮጵያዊ ጥያቄን የሚያስነሳ እና ሀቅን የካደ ስለሚሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ ሊለዉ ይገባል፡፡

አበዉ ነገርን ከስሩ ፤ዉሃን ከምንጩ ይላሉ እና በቁስል ላይ እንጨት ሳይሆን መድኃኒት ነዉና  ኢትዮጵያ ዉስጥ ጠያቂም ተጠያቂም የለም ብሎ እንደወረደ በአገር ጉዳይ ላይ ታሪክን  እና ዕዉነታን መግሰስ  ሲነጋ ያስተዛዝባል ፡፡

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

 

Allen Amber

የዜና መፅሄቱ ይዘት በዕጭሩ ይህን ይመስላል ፡-

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ውስጥ ቁልፍ ጉዳይ የሆነው ስፍራ

“ምዕራብ ትግራይ/ወልቃይት ወሳኝ ቦታ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው?”,

4 ህዳር 2022

ከጥቅምት 2013 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሲሞቱ ሚሊዮኖች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

ባለፈው መጋቢት ወር የተደረሰው የተኩስ ማቆም ስምምነት የተስፋ ጭላንጭል ቢፈጥርም፣ ነሐሴ ላይ ጦርነቱ ዳግም አገርሽቷል።

ጦርነቱ ብዙ ምስቅልቅሎችን አምጥቷል። የምዕራብ ትግራይ/ወልቃይት ጉዳይ ደግሞ አንዱ ነው። ለመሆኑ የወልቃይት ጉዳይ ዋነኛ ነጥብ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop