March 28, 2013
16 mins read

መልካም መሪ ማግኘት ምንኛ መታደል ነው?! – በታምሩ ገዳ (ጋዜጠኛ)

(በታምሩ ገዳ)

በየትኛውም የእድገት  ደረጃ  ይሁን የፖለቲካ  አመለካከት ወይም የሃይማኖት  ስርአት  ውስጥ ለሚገኝ ማህበረሰብ ሁነኛ መሪ ማግኘት ከእድሎች ሁሉ ትልቁ እድል ነው  ቢባል ማጋነን አያስብልም፡፡

ለዚህ ይመስላል የሮማ  ካቶሊክ ቤ\ክርስቲያን   በቀርቡ 266ኛዋን  መሪ(ፓፓ ) ለመምረጥ የሃይማኖቱ አባቶች  በቫቲካን ከተማ  በተሰባሰቡበት  ወቅት በ 150,000ዎች  የሚቆጠሩ ምእመናን ቀጣዩ የሃይማኖታችን አባት  ማን ይሆኑ? በማለት  የምርጫው ውጤቱን ለማወቅ  በታላቁ  የቅዱስ  ጴጥሮስ  አደባባይ ተሰባስበው የነበረው፡፡ በዚህ የምንፈስ  ቅዱስ መሪነት  በተካሄደው  የመጪው  የቤተክርስቲያኒቱ  መንፈሳዊ አባት መረጣ    ላይ  የብዙዎቹ ምርጫ ሆነው  የቀረቡት  ከ120 ሚሊዮን  በላይ የእምነቱ ተከታዮች  ያሏት አገር  ብራዚል  ከሳኦ ፖሎ ከተማ  የመጡት  አርክቢሾፕ ኦዲሎ ሺረር ነበሩ፡፡ ለምን? ቢባል አርክ ቢሾፕ ኦዲሎ  በቫቲካን ውስጥ  በሚገኙ  ታላላቅ መነኮሳት  ዘንድ ቀረቤታ ያላቸው አባት በመሆናቸው ነበር ፡፡ይሁንና የምርጫው ስነስርአት ሲጠናቀቅ  አባ ጆርጁ ቤርጎባሌዮ የ1.2 ቢሊዮን ህዝብ(በአለማችን ላይ ያለው የካቶሊክ አማኞች ቁጥር  መሆኑ ነው) አባት ናቸው  የሚለው  ዜና  ሲሰራጭ በዙዎች  አባ ጆርጁ  ቤርጎባሌዮ ወይም አባ ፍራንሲስ ማናቸው?  የሚለው ጥያቄን መጠየቅ ጀመሩ፡፡ የብጹነታችውን ማንነት ጠንቅቀው የሚያውቁት  በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ አዲስ አባት  አገኘን (we have a Pope!)ሲሉ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ለወትሮው ፓፓው  ለህዝቡ የሚጸልዩት ወይም  ህዝቡን የሚባርኩት እርሳቸው ሲሆኑ በአሁኑ ግን እርሳችው ለተስብሳቢው ህዝብ  !እባካችሁ  ጸልዩልኝ!” ሲሉተማጽነዋል፡፡

ላለፉት ስምንት አመታት  በፓፓነት ማእረጋቸው ሲያገለግሉ ቆይተው በህመም  ምክንያት  በቅርቡ ስልጣናቸውን በፍቃደኝነት  የለቀቁት  አቡነ ቤኔዲክት  16ኛውን በመተካት  ሰልጣኑን የተረከቡት  አቡነ ፍራንሲስ አባታቸው ጣሊያናዊ የባቡር  ላይ ሰራተኛ   ሲሆኑ የፋሺስቱን  አገዛዝ  በመሸሽ በእርጀንቲና  ቦነስ አይረስ  ከተማ  ፍሎረነስ  በተባለች  አንስተኛ አካባቤ  መኖር ጀመሩ ፡፡ ልጃቸው  አቡነ ፍራንሲስ በ1936 እኤአ  እዚያው አርጀንቲና ውስጥ ተወለዱ፡፡  ለደሆች እና ለተፈጥሮ ሃብት ተቆርቋሪ ከነበሩት  ከቅዱስ ፍራንሲስ  (ከሃብታም  ቤተሰብ ተወልደው ስለደሃዎች እና ጭቁኖች መብት መከበር ሲሉ በሮም  ጎስቋላ ስፍርዎች  ከመጻጉዎች እና ከደሃዎች ጋር ይኖሩት ከነበሩት የኦሲሱ  ቅዱስ ፍራንሲስ ናቸው ) መጠሪያ ሰያሜ ያገኙት አዲሱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን  አባት  የሆኑት ብጹነታቸው ለደሃዎች   ደህንነት እና  እኩልነት  የሚሟገቱ ታላቅ  አባት እንደሆኑ ብዙዎች ይመስክሩላቸዋል፡፡አባ ፍራንሲስ  በብዙ መልኩ ከቅንጦት እና ምቾት ካለው  አለማዊ  ኑሮ  ይልቅ ዝቅተኛ የሆነ (ሎው ፕሮፋይል) የሚመርጡ ሲሆኑ እነዚህ ምልካም ተግባሮቻቸው  መካከል  በቅዳሴ ጊዜ  በአለማዊ ሰዎች  ዘንድ  ከተዋረዱት  በእግዚአብሄር  ፊት ግን  እኩል ከሆኑት  በቦይነስ አይረስ  ከተማ  ከሚገኙ የቀድሞ ሴትኛ አዳሪዎች  ጋር አብረው  በመጸለይ የሃይማኖታዊ   አባትነታቸውን  እና አርያነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ከዚያም አልፎ ለስልጣነ ክህነታቸው  ሲባል ለግላቸው የተመደበላቸውን ዘመናዊ ሌሞዚን  መኪና  ከእነ ሹፌሩ  እርግፍ አድርገው በመተው (ሹፌሩን በማሰናበት)  እራሳቸው  በህዝብ የማመላለሻ አውቶቡስ  በመገልገል  የደሃው ህዝብ አካል መሆናቸውን   አስመስክረዋል፡፡

                      

(ወደእኔ ይመጡ ዘንድ ህጻናትን አትከልክሏቸው፡-አባ ፈራንሲዮስ ህጻን  ልጅ ታቅፈው)

በአጠቃላይ አኗኗሯቸው  ቀለል ያለ ኑሮን የሚመርጡት ብጹነታቸው የላቲን አሜሪካ  ካፈራቻቸው  የመጀመሪያው  የሮማ  ካቶሊክ ፓፓ ሲሆኑ እርሳችው መመረጥም  በቤተክርስቲያኒቱ  ውስጥ  ላላፉት 1300 አመታት ከአንድ አካባቢ (ከአውሮፓ ብቻ ) ይመጣ የነበረው የፓፓነት  ስርአትን   በመለወጥ  ፋኖ ወጊ ሆነዋል፡፡ ለዚህ ይመስላል በአሜሪካ:  በአፍሪካ  በደቡብ አሜሪካ እና በእሲያ  የሚገኙ  በቢሊዮኖች  የሚቆጠሩ የካቶሊክ እምነት ተከታዩች   እንዲሁም በርካታ የአገር መሪዎች  የብጹነታቸው ምመረጥን (viva il papa !!) በማለት  እንደ ታላቅ ድል የቆጠሩት ፡፡ብዙዎችም ፓፓው ድህነትን በማስወገድ  ዘመቻ እንዲሳተፉ ተማጽነዋቸዋል፡፡ ምንም እንኳን በጹነታቸው  በግላቸው ለምእመናኑ እና  ለደሃው ህዝብ ቅርብ የሆኑ  መንፈሳዊ አባት  ቢሆኑም  የትውልድ አገራቸው  አረጀንቲና በ1970ዎቹ  እኤአ  በነበረው ወታደራዊ  ጁንታ ሳቢያ  አገዛዙን  በመቃወማቸው ብቻ ህይወታቸውን  ላጡ ከ30,000 በላይ  ሰላማዊ

ዜጎች  ቤተክርስቲያኒቱ ተቃውሞዋን አላሰማችም  የሚል ብርቱ  ወቅሳ ቀርቦባታል፡፡ይህንንም ወቀሳ በተመለከተ አቡነ ፍራንሲስ  በ2010 እኤአ በአርጀንቲና ውስጥ ለሚታተም አንድ ጋዜጣ በሰጡት ሰፊ አስተያየት  አርሳቸው ሰዎች እንዳይታሰሩ  ሙያቸውን  በመቀየር እንዲደበቁ ወይም አገራቸውን ጥለው  እንዲሄዱ በማደረግ የታሰሩትም እንዲፈቱ በመሟገት የበኩላቸውን ጥረት ማድረጋቸውን በመግለጽ ውንጅላውን አስተባብለዋል፡፡

ቀደም ባሉት ጊዜያት   በአንዳንዳንድ ምግባረ በልሹ ካህናት  የተነሳ ከሙስና  እንስቶ ጨቅላ ህጻናትን  የመድፈር  እና መሰል  ክሶች የቀረቡባት  የሮማ ካቶሊክ  ቤተክርስቲያን  በቤቷ  ውስጥ የተጋረጡት  ችግሮችን  ለመቅረፍ የአቡነ ፍራንሲስ  ወደ ቤተክርስቲያኒቱ በአባትነት  መምጣት  መልካም አጋጣሚ ቢሆንም  አባጣ ጎባጣ የሆኑ መንገዶችን ለምጥረግ  በርቱ  ፈተናዎች ከፊታቸው  የጠብቋቸውል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የብጹነታቸው  የግል ታሪክ ጸሃፊ የሆኑት  ሴርጆ ሩቤን  ሰለአዲሱ ፓፓ  ባህሪ ሲገልጹ  “በእሁኑ ወቅት  በለውጥ ጎዳና ላይ ያለን ይመስለኛል ፡፡ይህ ሁኔታ  ግን ቀላል  አይደለም፡፡ብጹነታቸው ቤተክርስቲያኔቱ  ወደ አደባባዮች(ጎዳናዎች) መውጣት  ስትችል  ብቻ ነው የህዝቡን ችግር መረዳት የምትችልው ብለው ያምናሉ( poor Church for the poor )፡፡” ሲሉ ተናግርዋል፡፡ በደግነታቸው  እና በእውነተኛ ርህራሄያቸው  በበርካታ የካቶሊክ  ማህበረሰብ ዝንድ  እውቅና ያገኙት አቡነ ፍራንሲስ  የፓፓነቱን ስልጣን ከያዙ  በሁዋላ እንኳን  ያ ደግነት የተላበሰ ባህሪያቸውን ባለመለወጥ ሰሞኑን ከእርሳቸው ጋር ለሚኖሩ  ካህናት  እራሳቸው  ምግብ  አብስለው በማዘጋጀት እራት እንዲቋደሱ አድርገዋል፡፡ አርፈውበት በነበረ አንድ ሆቴል ውስጥም ለተስተናገዱበት ወጪ  ከገዛ ኪሳቸው ገንዘብ በማውጣት  ከዚህ ቀደም የነበረውን የቀይ ምንጣፍ እና ልዩ መስተንግዶ ባህልን  ወደጎን አድርገውታል፡፡

ብጹነታቸው  ባለፈው አርብ ጠዋት ላይ  በቫቲካን ከተማ  ከሚገኙ  የዝቅተኛው  ማህበረሰብ ክፍል ከሆኑት  (ብሉ  ኮላርስ )  እየተባሉ ከሚጠሩት  የቤተመንግስታቸው  አትክልተኞች እና  የጽዳት  ሰራተኞች  ጋር  በጋራ  በመሆን  የህብረት ጸሎት ያደረሱ  ሲሆን በስተመጨረሻም አያንዳንዱን ሰራተኛ  በግል አነጋግረዋል፡፡ለወትሮው  ለጳጳስ  ወደ ተዘጋጀው  የክብር መቀመጫ ከመሄድ  ከምእምናን  በስተሁዋላ  በመቀምጥ  እንደተራው ምእመናን  ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ  የጋራ ጸሎት  አድርገዋል፡፡ ሰሞኑን ምእራባዊያኖች ባከበሩት የ40 ቀናት እና 40 ሌሊት  ጾም(የሁዳዴ ጾም)  ክፍል አንዱ የሆነው ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ከሃዋራቱ ጋር የመጨረሻውን እራት(Lord’s Supper) የበላበት እና  የሃዋሪያቶቹን እግር በማጠብ  እነርሱም የእርሱን እርያነት እንዲከተሉ ትህትናውን ዝቅ ብሎ  ያሳየበትን  ምእራፍ በማሰታውስ  ብጹነታቸው ካሳል ዴል ማርሞ (Casal del Marmo) በተባለ የወጣት አጥፊዎች እስር ቤት በመሄድ ከህግ ታራሚዎቹ ጋር  አብረው እንደሚያሳልፉ  ከቫቲካን የወጣው መግለጫ  ያመለክታል፡፡

የቤተመንግስት  ነገር ከተነሳ  ከላይ እንደተገለጸው  ቀላላ ኑሮን ዘወትር የሚመርጡት  ብጹነታቸው አሁንም ወደ ቫቲካን  ተዛውረው  “በቤሊዮን የሚቆጠረው  ምእመናን አባት በመሆኖት ለክብሮት ሲባል የቀድሞው የአቡነ ቤኔዲክት 16ኝውን  ሆነ የቀደምት አባቶች ቤተመንግስትን ይረከቡ” ቢባሉም አሻፈረኝ በማለት  በፓፓው ምርጫ ሰሞን እዚያው ቫቲካን ውስጥ አርፈውበት በነበረው ባለ ሁለት ክፍል ሆቴል ውስጥ  ለጊዜው መቀመጥን  መምረጣቸው ተነግሯል፡፡ይህ ማለት ቤተመንግስቱን ሙሉ በሙሉ አይጠቀሙሙበትም ማለት ሳይሆን  ከመደበኛ ስራዎቻቸው መካከል አንዱ የሆኑት እንግዶችን ለምቀበል ስብስባዎችን ለማካሄድ  ወደ ጽፈት ቤታቸው ጎራ ማለታቸው አልቀረም፡፡  አብዛኞቹ ባለስላጣናት ስልጣን በያዙ ማግስት ዘመድ አዝማዶቻችውን  ለመጥቀም ሲሯሯጡ  ወይም ቀደም ሲል አስቀይመዋቸው የነበሩ ወገኖችን ለማባረር አሌያም ከእነአካቴው ለማጥፋት ላይ ታች በሚሉበት   አሁን ባለንበት በ21ኛው  ክ\ዘመን  በየትኛውም ጎራ ይሁኑ በየትኛውም ስፍራ አንደ አቡን ፍራንሲስ  የመሰለ መንፈሳዊ አባት ማግኘት  ለሃይማኖቱ ተከታዩች ብቻ ሳይሆን እምነት ለሌላቸውም(አለማዊያን) ቢሆን  ጥሩ አርእያ መሆኑ የሚቀር አይመስልም፡፡  (tamgeda@gmail.com)

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop