Health: የጨጓራ ህመሜ ወደ ካንሰርነት ተቀይሮ ይሆን? መፍትሄውን ጠቁሙኝ እባካችሁ

February 9, 2014

ዕድሜዬ 43፣ ፆታዬ ወንድ፣ ስራዬ ደግሞ በግል ስራ የምትዳደር፣ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነኝ፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ የተጠናወተኝ ጨጓራ እስካሁን ያሰቃየኛል፡፡ አንቲ አሲድ ሽሮፕና የጨጓራ ክኒኖች ቀለቦቼ ናቸው፡፡ በሳምንት ውስጥ ውስጤ ሳይቃጠል በሰላም የማሳልፋቸው ቀናት ሁለት አይሞሉም፡፡ የጭንቀቴ መንስኤ ግን ይህ የጨጓራ ህመም ብቻ እንዳይመስላችሁ፡፡ እንደ እኔው በኃይለኛ ጨጓራ ሲቸገር የነበረው አባቴም በመጨረሻ ችግሩ የጨጓራ ካንሰር ሆኖ ተገኘ፡፡ ሐኪሞቹም በኦፕሬሽን ሊሞከር ከሚቻለው በላይ ተስፋፍቷልና ጨረር ይሞከርለት ተብሎ ነበር፡፡ እሱም ብዙም ሳይረዳው ካረፈ ዓመት ሞላው፡፡ እናም እኔም ጨጓራዬ በለበለበኝ፣ ቃር በበዛብን ቁጥር ውስጤን ከሚሰማኝ የማቃጠል ፀባይ ይበልጥ የሚረብሸኝ ወደ ካንሰርነት ተቀይሮ ይሆን? ወይ የሚለው ስጋቴ ነው፡፡ ይሄን ስጋቴን በምን ላጥፋው? ወደ ካንሰርነት ተቀይሮ ከሆነስ የኦፕሬሽ ጥቅም እምን ድረስ ነው?
ተድላ ነኝ

የዶ/ር ዓብይ ምላሽ፦ ውድ ተድላ ጥያቄህን ከአክብሮት ጋር በሚከተለው መንገድ አስተናግደነዋል፡፡ በተለምዶ ጨጓራ እያልን የምንጠራው ህመም ለጨጓራ ብቻ የተወሰነ ህመም ሳይሆን ትንሹን አንጀት ጨምሮ በተናጠል ወይንም በጋራ የውስጥ ግድግዳቸው ተልጦ ሲቆስል የሚኖር የማቃጠል የህመም ስሜት ነው፡፡ ቃር፣ ደረት እና ከእምብርት በላይ ማቃጠል፣ ጀርባ እና ውስጥ እጅ መንደድ፣ ማግሳት፣ ማቅለሽለሽና ማስመለስ ሁሉ ከጨጓራ ህመም ምልክቶች ሊመደቡ ይችላሉ፡፡ የጨጓራ ካንሰርም ተመሳሳይ ምልክቶች ሊኖሩት ሲችሉ ጨጓራ ካንሰር ቁስሉ የሚገኘው ግን እዛው ጨጓራ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ የካንሰርነት ባህሪይ ያላቸው ሴሎች ግን ከጨጓራም አልፈው አካባቢውን ሊያዳርሱት ወይንም በደም እና ሊምፍ አማካኝነት ወደ ሩቅ ቦታ ሊዛመቱ ይችላሉ፡፡

ውድ ዓለሙ አባትህን በጨጓራ ካንሰር ማጣትህ ጭንቀትህን ቢያንረው አያስገርምም፡፡ አስፈላጊውን ምርመራዎች በማድረግ ግን ይህን ጭንቀትህን ማስወገድ ትችል እንደነበር ስንነግርህ አሁንም አልረፈደምና ምርመራዎችን ልታደርጋቸው እንደምትችል ልናሳስብህ እንወዳለን፡፡

በመጀመሪያ የጨጓራ ካንሰር ጠቋሚ ምልክቶችን ለማብራራት ያህል የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ በል፡፡ የጨጓራ ካንሰር ዕድሜ ሲገፋ ይበልጥ የሚስተዋል ህመም እንደመሆኑ
ከአርባ ዓመት ዕድሜ በኋላ ድንገት የሚጀምር የጨጓራ ህመምን በቸልታ ማለፍ አያስፈልግም፡፡ አዲስ የተነሳ የጨጓራ ህመም ብቻም ሳይሆን ድንገት ከአርባዎቹ ዕድሜ በኋላ ተባብሶ እረፍት የሚነሳ የጨጓራ ህመምንም ሐኪም ጋር ቀርቦ የጨጓራ ካንሰር አለመሆኑን ማየት ያስፈልጋል፡፡

ክብደት መቀነስ፣ ሆድ ላይ የሚስተዋል እብጠት ወይንም ምግብ መዋጥ አለመቻልም እንዲሁ ከጨጓራ ህመም ምልክቶች ጋር በህብረት ከታዩ የጨጓራ ካንሰር ተከስቶ ሊሆን ይችላልና መዘግየት አያስፈልግም፡፡

ከሁሉ ይበልጥ ግን የጨጓራ ክኒኖችን እየዋጥክ የማቃጠል ስሜቱን ለማሸነፍ ከመጣር ይልቅ በደንብ ልትመረመር እና ልትታከም ይገባል፡፡ በቀላሉ አልታገስ ያለ የጨጓራ ህመም ሔሊኮባክተር ፓይሎሪ በሚባለው ባክቴሪያ አማካኝነት የተነሳ የጨጓራ ህመም ሊሆን ይችላልና በቀላል የደም ምርመራ ማወቅ ይቻላል፡፡ ህክምናውም እጅግ ቀላል ሲሆን ሶስት አይነት መድሃኒቶችን (ሁለት አይነት አንቲ ባዮቲክስ እና አንድ የአሲድ ምርት የሚቀንስ ታብሌት) ለሁለት ሳምንት ብቻ በመውሰድ ለዓመታት የጨጓራ ህመም እንዳይመለስ ያደርጋል፡፡

ባክቴሪያው በደም ምርመራ እንደሌለ ከተረጋገጠና ሐኪምህ የጨጓራህን ቁስል ባህሪይ ለማወቅ ከፈለገ (የካንሰርነት ባህሪይ ይኑረው፣ አይኑረው) የራጅ ምርመራ ያደርግልሃል፡፡

ይሄኛው የራጅ ምርመራ ግን ከተለመደው የተለየ ነው የሚሆነው፡፡ ምክንያቱም የጨጓራህን ውስጣዊ ግድግዳ ያለበትን ሁኔታ በራጁ እንዲታይ አስቀድመህ የምትጠጣው ኬሚካል ይኖራል፡፡ ወይንም ደግሞ ሐኪምህ በኢንዶስኮፒ የጨጓራህን ውስጣዊ ግድግዳ ሊመለከትና ከተጠራጠረም ከቁስሉ አካባ ናሙናዎችን ወስዶ በፓቶሎጂ ምርመራ የካንሰርነት ባህሪይ እንዳለውና እንደሌለው ማረጋገጥ ይችላል፡፡

ገና በ43 ዓመት ዕድሜህ ህመምህ የጨጓራ ካንሰር የመሆን ዕድሉ እጅግ አናሳ ቢሆንም ጥያቄህን ለመመለስ ያህል ለጨጓራ ካንሰር የሚደረገው ህክምና በዋነኝነት በኦፕሬሽን ቆርጦ ማውጣት መሆኑን ልንጠቁምህ እንወዳለን፡፡ በሽታው ሳይሰራጭ ከተደረሰበት ከካንሰሩ ሙሉ ለሙሉ የመፈወስ እድል ሲኖር ብዙው ጊዜ ግን ይህ አያጋጥምህም፡፡ በተጨማሪም ከቦታው አልፎ ለተስፋፋ የጨጓራ ካንሰር ከኦፕሬሽ ጎን ለጎን የጨረር ህክምና መስጠትም ይቻላል እያልን ወድ ተድላ ሳትዘገይ ሐኪም ዘንድ ቀርበህ ትታይ ዘንድ በድጋሚ እንመክርሃለን፡፡

3 Comments

  1. ይድረስ ለአቶ ተድላ የደረስብህ ችግር አንተና የደረስበት ስው ብቻ ነው ሊገነዘበው የሚችለው።በተለምዶ የጨጔራ መላጥ ሲባል እንስማለን ግን አብዛኛውን ባለሞያዎች እንኴን በትክክል የተረዱት በጣም ትንሽ ናቸው። አጠር ላድርግና የዚህ በሽታ መንሻው ይሄሎውቫይርስ የተባለው ቫይረስ ነው። ለዚህም ቫይረስ ትክክለኛውን መድሀኒት ተገኝቶለታል።አብዛኛውን ግዚ ባለሞያዎች ባለማውቅም ይሁን በማውቅ ትክክለኛን መድሀኒት አይስጥም። ይህም የእኔ የአለፈ ተሞክሮየ ነው። ውድ ወንድሜ በሚቀጥለው ዕትም የመድሀኒቱን ስምና ውጤቱን በስፊው አስረዳለሁ።

  2. Bemejemeria Egziabher yimarh elalehu. Wondme hoy, Zare ye Ethiopia Orthodox Tewahdo betekrstian be Tsebelwa ena Tsegaw betadelachew Abatochi eji Ye Egziabhern madan aminew lemihedubat yesew lijochi hulu fitsum fewsn tfewsalech!!! Benetsa. Haymanot ena zer tsota ena kelem atiteykm, Ye Amlakachin madan Le Adam lijoch hulu newna. Filagotu kaleh bezih gebteh eyew. (memhirgirma.wordpress.com) Melkam Edil Emegnlhalehu.

  3. አቶ ካሳዬ ዮሴፍ ለአቶ ተድላ ባለሙያዎችን ሁሉ በመሽምጠጥ ስለ ጨጉዋራ በሽታ ለዘባረቁት መልሱ እነሆ፤ በመጀመሪያ ደረጃ እርግጠኛ ሳይሆኑ ባለሙያን መዘርጠጥ ከአገሪቱ መሪዎች የተገኝ ትምህርት በመሆኑ ልናስወግደው የሚገባ ባህርይ ነው፤ ወደ ዋናው ነጥብ ስመለስ ሄሊኮባክተር (Helicobacter) ባክቴሪያ እንጂ ባይረስ አይደለም፤ ይህ ባክቴሪያ ከ25 አመት ግድም በፊት በሁለት የአውስትራሊያ ተመራማሪዎች የተገኝ ሲሆን ለጨጉዋራ በሽታም ምክንያት እንደሚሆን ተደርሶበት በአሁኑ ወቅት ሁሉም ሆስፒታሎች የሚመረምሩትና ሕክምናውም ፀረ ባክቴሪያ መድሃኖቶች እንደሆነ ከታወቀ ሰንብትዋል፦
    amoxicilline, Claritromycine በመባል የሚታወቁት ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶች ከ pantoprazol ከሚባል የጨጉዋራ መድሃኒት ጋር ለአንድ ሳምንት ከወሰዱት ባክቴሪያው ከጨጉዋራዎ ይወገዳል፤

    ዶ/ር ካሳሁን በጋሻው

Comments are closed.

Previous Story

ሕወሓት ከመለስ ጋር አብሮ ተቀብሯል – ክፍል 2

haile larebo
Next Story

ምኒልክን ብትወቅሱ ማንነታችሁን ትረሱ (በኃይሌ ላሬቦ)

Latest from Blog

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡ ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ሳሙኤል አወቀ እንደ ቅድመ አያቶቹ ዝቅዝቅ መታየትን ያልተቀበለና በጥናት የታገለ ከመጀመሪያዎቹ ፋኖ ሰማእታት አንዱ ነው፡፡  ሰማእታትን መዘንጋት አድራን መብላት ነው፡፡ አደራን መብላትም እርምን መብላት ነው፡፡ እርምን መብላትም መረገም ነው፡፡እርማችንን

በትሮይ ፈረስነት የመከራና የውርደት አገዛዝን ማራዘም ይብቃን!!!   

June 16, 2024 ጠገናው ጎሹ በሥልጣነ መንበር ላይ የሚፈራረቁ ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መከረኛውን ህዝብ ከአስከፊ ድንቁርና እና ከሁለንተናዊ የመከራና የውርደት ዶፍ ጋር እንዲለማመድ  ከሚያደርጉባቸው እጅግ በጭካኔ  የተሞሉ ዘዴዎቻቸው መካከል ኮሚቲ፣

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ

ሲሳይ ሳህሉ / ቀን: June 16, 2024 የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት
Go toTop