ህዝበ ክርስቲያንን ያሳዘነ ሥልጣን በእግዚአብሔር ቤት መቅሰፍት ነዉ! ከዉርደትና ዉድቀት ሌላ የሚያመጣዉ ተስፋ የለም!
በአጥቃዉ ቦጋለ
በቅድስት አገራችን ኢትዮጵያ የሃይማኖት ነጻነት ከአደጋ ላይ ወድቋል። ታሪካዊትና ቀደምት ቤተክርስቲያናችን ዉስጥ በሃይል ገብቶ የመሸገዉ የገዥዉ ቡድን ለዘመናት በኖሩ የሃይማኖት እምነቶች ላይ የሃይል ዘመቻ ከፍቷል፤ የአማኙን ህዝበ ሰላም ነስቷል። የእርቀ ፤ የሰላምና አንድነት መድረክ ተዘግቶ ከምዕመናን ፍላጎት ዉጭ የታካሄደዉ የካድሬዎች የሃይማኖት መሪ ሹመት እጅግ አሳሳቢ ሁኗል። መንግስት በጥንታዊታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ እጁን አስገብቶ እየፈጸመ ያለዉን ህገ ወጥ ድርጊት በጥብቅ እንቃወማለን።
በሃይማኖት አባቶች አማካይነት የሰላምና አንድነት ጉባኤ ለሶስት ተከታታይ አመታት ፓትርያሪክ በህይዎት እያለ ቀኖና ተጥሶ በመንግስት ጣልጋ ገብነትና አስገዳጅነት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስን አዉርዶ የተካሄደዉን ህገወጥ ሹመት በእርቅ መፍትሄ ለመፈለግ የተጀመረዉን የሽምግልና ሂደት የወያኔዉ ቡድን አሰናክሎ እንደተለመደዉ በዘር ያዘጋጃቸዉን የካድሬ አባት ሹሟል። ይህንን ከንቱ የጥፋት ሹመት ህዝበ ክርስቲያን ከአሁን በፊትም በአባትነት አልተቀበለም አሁንም አይቀበለዉም። በምክክር ለመፍታት የተጀመረዉን ጥረት አክሽፎ የኔ ዘር ብቻ ስልጣን ላይ መቆናጠጥ አለበት በሚለዉ የወያኔ ጎጠኛ አባዜና ጣልቃ ገብነት በሩ ተዘግቶ የሰላምና አንድነት ሂደቱ በሃል ተገፍትሮ በአጣዳፊ አሁንም እንደገና የተካሄደዉን ህገወጥ የፓትርያሪክ የዉምብድና ምርጫ በጽኑ እናወግዛለን።
እኛ ምዕመናን በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፓትርያሪክ ዘኢትዮጵያ የሚመራዉን ህጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣዉን መግለጫና መመሪያ በሙሉ ድጋፍ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችን እንገልጻለን። በዘር ተደራጅቶ የእናት በተክርስቲያንችን ታሪካዊ ጥንካሬ የሚሸረሽር ቀኖናን የሻረ ሴራ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም ከመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሁነነን የሃይማኖትና የህዝቦች መብት የሚያስከብር ስርዓት እስከ እስኪረጋገጥ ድረስ ከህጋዊ ቅዱስ ሲ ሰኖዶስ ጎን ተሰልፈን ድጋፋችን እየሰጠን እስከ መጨረሻዉ የሰላም ምዕራፍ እንደምንቀጥል ቃል እንገባለን።
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በተክርስቲያን ምዕመናን/ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ
በእግዚአብሔር ቤት አባቶችን ማሳደድ፤ በምዕመናንን የዕምነት ነጻነት ጣልቃ መግባት፤ ለእርቀ ሰላም የቆሙ በህዝብ የተወከሉ አባቶችን አሸባሪ ናቸዉ ይታሰሩ፤ ይገረፉ፤ ይሰቀሉ የሚል ቡድን በምንኮራባት አገራችን የጥፋት ዘመቻ ሲከፍት በቸልታ ማየትና የገለልተኛ ኑሮን ማመማቸት ፍጹም ሃይማኖታችን አይፈቅድም። አበዉ አባቶቻችንም በችግር ጊዜ አንድ እንድንሆን መክረዋል፤ ለዘመናት በሃይማኖትና በአገር ነጻነት ተጋድሏቸዉ አስመስክረዋል፤ በችግር ጊዜ ጠላት ጥቃት ሲዘነዝርብን ያለምን ቅድመ ሁኔታ ይቅር ተባብለን በአንድ ላይ እንድንቆም እና በአሸናፊነት እንድንወጣ ህያዉ የሆነ ትምህርት አስተምረዉ አልፈዋል፤ ይህን ከትዉልድ ወደ ትዉልድ የተላለፈ እንደ አገርና እንደ ህዝብ አጽንቶ ያኖረንን የአበዉ ቃል ማክበርና ማስከበር ብሎም የእግዚአብሄርን ቤት በዕምነት ጸንቶ መጠበቅ ህያዉ ሥራ ነዉ።
ዉድ ምዕመናን !
ለሃይማኖታችን ነጻንት ከምን ጊዜዉም በበለጠ አንድነታችን አጠናክረን በግፍ ከተሰደዱት የሃይማኖት አባታችን ከብጹዕ ወቅዱ አቡነ መርቆሪዮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፓትርያሪክ ዘኢትዮጵያን ቡራኬ እየተቀበልን ጸሎታችን ለማሰማት ወደ ቸሩ አንድ አምላክ የምንጮህበት ዘመን አሁን ነዉ። ብጹዕ አባቶች በገዳማትና በአድባራት ተማዕጽኖ በጾም በጾለት ተለምነዉ ተመርጠዉ በሚሾሙበት የየተቀደሰ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ መንበር በዘር አድሎ ሹመት በቅድስት አገር ኢትዮጵያ እዮተፈጸመ ያለዉን ድርጊት አጥብቀን ማዉገዝ አለብን። መላዉ ምዕመናን ተባብረን በመታገል በቤተ ክርስቲያናችን የሚካሄደዉን ህገ ወጥ ሴራ ለማስቆም በዕዉነት እንነሣ። በመጨረሻም የህዝብ መብትና የሃይማኖት ነጻነት በእናት አገራችን እንዲከበር ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ እጅና ጓንት ሁኖ ድምጽ እንዲያሰማ መልክቴን አስተላልፋለሁ።
በመጨረሻም የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን/ካቴድራል መላዉ ምዕመናን በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ ርሰ ሊቃነ ጳጳሳ ፓትርያሪክ ዘኢትዮጵያ በሚመራዉ ሲኖዶስ በህዝብ ድምጽ ወስኖ መቀላቀሉ ለኦርቶዶክስ አማኝ ሁሉ ታላቅ ደስታ ነዉ። እንኳን ደስ ያላችሁ እላለለሁ። ይህ ትልቁ የአንድነታችን ወሳኙ አካል ነዉ። ብዙዎች ገለልተኛ በሚል ዘይቤ ታፍነዉ የኖሩ ምዕመናን በድምጽ ዉሳኔ ወደ አንድነቱ ጎራ እንደሚቀላቀል እርግጠኛ ነኝ። በተለይም የዋሽንግተን ዲሲ ቅድስት ማሪያም እና የሚኖሶታ ደብረ ሰላም ቅዱስ መድሃኒያለም ምዕመናን ድምጻቸዉ የሚያሰሙበት ጊዜ ደርሷልና አሁኑኑ ሳይዘገይ ይወስኑ። የኦርቶዶክስ አንድነት ሙሉ በሙሉ ከዳላስ መቀላቀል በኋላ ተረጋግጧል።
ቅድስት አገር ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቅ!!!
ወስብሃተ ለእግዚአብሔር።S