March 18, 2013
6 mins read

የትእምት ካፒታል ስንት ነው? [ጥብቅ ምስጢር]

አብርሃ ደስታ ከመቐለ

ዛሬ እሁድ መጋቢት 8 የኢህኣዴግ ኣባል ድርጅቶ ች ጉባኤያቸው እንደጀመሩ ኢቲቪ እየነገረን ነው።

በመቐለ ከተማ ‘ቀውጢ’ የተባለ የድጋፍ ሰልፍ ተጠርቶ እየተከናወነ ይገኛል። ሃይለኛ ዝግጅት ነው። በህወሓት ታሪክ ለድርጅታዊ ጉባኤ ስብሰባ ድጋፍ ለማሰባሰብ ህዝባዊ ሰልፍ ሲጠራ የኣሁኑ ለመጀመርያ ግዜ ነው። ደርግም ለሞት ሲቃረብ ሰልፍ መጥራት ኣብዝቶ ነበር ኣሉ።

ለፕሮግራሙ የወጣ ወጪ ስንት መሆኑ ለማወቅ ያደረኩት ጥረት ኣልተሳካም። ግን በጣም ብዙ መሆኑና ከትግራይ መንግስት ካዝና እንደሆነ ግን ኣውቄያለሁ። ፓርቲና መንግስት ኣንድ የሆነበት ሀገር፤ የግብር ከፋዮች ገንዘብ ለፓርቲ ሰልፍ ዝግጅት ሲውል ኣይገርምም!!!?

ከሰልፉ በላ ይ ይበልጥ ቀልቤን የሳበው ግን የትእምት (ትካል እግሪ ምትካል ትግራይ) ወይ EFFORT (Endowment Fund For the Rehabilitation of Tigray) ተሽከርካሪዎች በመቐለ ከተማ ያደረጉት ትእይንት (ሰልፍ) ነው። በጣም ገርሞኛል። ብዛታቸው፣ ዓይነታቸው፣ ሁለመናቸው።

ትእምት በጣም ሃብታም መሆኑ ገባኝ። ‘ታድያ ይሄን ይዘን ለምን ኣላደግንም?’ የሚል ጥያቄ ጫረብኝ። የሚገርም ነው።

ገርሞኝ ዝም ኣላልኩም። ኣንድ የትእምት ሰራተኛ የትእምት ኩባኒያዎች ካፒታል ስንት እንደሆነ ጠይቄው የሚከተለውን መረጃ ሰጥቶኛል። (ፅሑፉ የራሱ ነው)።

“የሌለው ኢፌርት የሚባል ንግድና የኢንዱስትሪ ካንፓኒ ትርፍ ሳይጫምር ከ 50ቢሊዮን በላይ የቀዋሚ ሃብት ባለቤት የሆነ ነው፡፡

የኢፈርት ንግድና ኢንዱስቱሪ ዝርዝር ስማቸውና ካፒታላቸው በመጠኑም ቢሆን ልጠቁም
ካፒታላቸው የሚታወቁ ድርጅቶች
1. መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ቁ1 ቀዋሚ ንብረት 3.467 ቢሊዮን
2. መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ቁ2 ቀዋሚ ንብረት 4.395 ቢሊዮን
3. ሱር ኮንስትራክሽን ቀዋሚ ሃብት 4.179 ቢሊዮን
4. ትራንስ ኢትዮፕያ 650መኪኖች ሌላ ቀዋሚ ሃብት 2.934 ”
5. መስፍን ኢንጅነሪንግ መቀሌ ቀዋሚ ሃብት 2.500 ”
6. መስፍን ኢንጅነሪንግ ቃሊቲና ዱከም 2.643 ”
7. ጉና ኮርፖሬሽን በመላው ኢትዮፕያ 23 ቅርንጫፍ 5.412 ”
8. ሜጋ ኣሳታሚ ሜጋ ኮርፖሬሽን ሜጋ ህትመት ቀዋሚ ሃብት 1.200 ”
9. ውቅሮ ሳባ ቆዳ ፋብሪካ ቀዋሚ ሃብት 600 ሚሊየን
10. ዓዲግራት መድሃኒት ፋብሪካ 700 ሚሊየን”
11. ኢዛና ወርቅ ማኣድን ቁፋሮና ጥናት 910 ሚሊየን
12. ብሩህ ተስፋ ላስቲክ ፋብሪካ 480 ሚሊየን
13. ማይጨው ቹፑድ ፋብሪካ 746 ሚሊየን
14. ሂወት እርሻ መካናይዜሽን ሕሞራ 820 ሚሊየን
15. ተከዜ ጥልቅ ጉድጋድ ቁፋሮ 467 ሚሊየን
16. ዓድዋ እምነበረድ ፋብሪካ 790 ሚሊየን
17. ዓድዋ ጋርሜንት ጨርቅ ስፌት ፋብሪካ 315 ሚሊየን
18. ዓድዋ ጨርቅ ፋብሪካ ቁ1 1.757 ቢሊየን
19. ዓድዋ ጨርቅ ፋብሪካ ቁ1 1.917 ቢሊየን
20. መስፍን ኢንጅነሪንግ ትንሽ መኪና መገጣጠምያ 350 ሚሊየን
21. እስታር መድሃኒት ኣስመጪና ኣከፋፋይ 150 ሚሊየን
22. ደደቢት ብድርና ቁጠባ ድርጅት 6.250 ቢሊየን
23. ፔርሊ የተሽከርካሪ ጎማ ኣከፋፋይ 560 ሚሊየን
24. ጥጥ መድመጫ ሑመራ ዳንሻ 200 ሚሊየን
ድምር የኢፈርት ቀዋሚ ካፒታሉ የሚታወቅ ብቻ 39.314ቢሊዮን

ካፒታላቸው የማይታወቅ የኢፈርት ሃብቶች
1. ኤክስ ፕሬስ ትራንዚት ኣ.ኣበባ መቀሌ ዱከም ደቺኦቶ ጁቡቲ የሚገኘው
2. ድምፅ ወያኔ ትግራይ በመቀሌ
3. ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል
4. ሬድዮ ፋና
5. ወጋገን ባንክ 32ቅርንጫፍ 51ፐርሰንት የህውሓት ሼር
6. ኣፍሪካ ኢንሹራንስ 18 ቅንጫፍ 20 ፐርሰንት የህውሓት ሼር
7. በለንደን ዱባይ ኣሜሪካ ሳዑዲኣረብያ ያሉ ቤቶች ኪራያቸው
8. የትግራይ እርዳታ ማህበር ሬስት በተክለወይኒ ኣሰፋ የሚመራ በስመ እርዳታ ማህበር
9. የትግራይ ልማት ማህበር ማልት በተወልደ ዓጋመ የሚመራ
10. የትግራይ የጦር ኣካል ጉዳተኞች ከ 1 ቢሊዮን በላይ ካፒታል
11. ህውሓት የነበሩ ታጋዮች መረጃጃ ማህበር በተክለወይኒ ኣሰፋ የሚመራ
12. ኣበርገለ የፍየል በግ ከብተ ማደለብያ
13. የቻይና እና ኢፈርት ወርቅ ቆፍሮ በሽሬ መደባይ ታብር
14. የኢፈርት ወርቅ ቁፋሮ በሽሬ ፅንብላ መይሊ
ከላይ የተዘረዘሩት ካፒታላቸው የማይታወቅ የንግድና ኢንዱስትሪ ድርጅቶች ከጥናት የተመሰረተ ካፒታል ኣይታወቅም እንጂ ካፒታላቸው ከ 39.314 ቢሊዮን ይበልጣል”

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop