March 16, 2013
14 mins read

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ምላሽ ሰጠ

ዘ-ሐበሻ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ፍሬ-አልባ ጩኸት በሚል ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ስለዲ/ን ክብረት የሰጡትን አስተያየት አስነበበናችሁ ነበር። አሁን ደግሞ ዲ/ን ዳን ኤል ክብረት ሃገር ቤት ለሚታተመው ላይፍ መጽሔት በሰጠው ቃለምልልስ ለፕሮፌሰሩ ጽሁፍ ምላሽ አቅርቧል። ቃለምልልሱን እንደወረደ እንካችሁ።

ላይፍ፡- በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲ በብሔራዊ ቲያትር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ባዘጋጁት ‹‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ›› በተሰኝ መጽሀፍ ዙሪያ ውይይት ተደርጎ ነበር፡፡ በውይይቱ ግምገማቸውን ከሚያቀርቡ ሰዎች አንተ አንዱ ስለመሆንህ ተነግሮ ነበር፡፡ ነገር ግን በእለቱ በስፍራው አልተገኝህም፡፡ ምክንያትህ ምንድነው ነበር ?

ዲ/ን ዳንኤል፡- ይህንን ነገር ካነሳህው እናውራው፡፡ መቼም አንድ ፕሮግራም መጋበዝህ ለሦስተኛ ወገን ከመነገሩ በፊት የአንተ ፈቃደኝነት ይጠየቃል፡፡ ፕሮግራምህ እንዴት ነው? በዚያ ወቅት ነጻ ነህ ወይ ? አገር ውስጥ ትኖራለህ? ተብሎ ይጠየቃል፡፡ እነዚህ ነገሮች ግን ለእኔ አልተደረጉም፡፡ ስለ ፕሮግራሙ መጀመሪያ ደውሎ የነገረኝ ብርሀኑ ደቦጭ ነበር፡፡ እሱም ያለኝ “በፕሮፌሰሩ መጽሀፍ ዙሪያ ውይይት ተዘጋጅቷል ከቻልክ ሄደን የሚደረገው ነገር እንመለከታለን” ነው ያለን፡፡ ከዚህ ውጪ የተነገረኝ ነገር አልነበረም፡፡ ቀኑ እየተቃረበ ሲመጣ አርብ እለት አንድ ሰው ከአሜሪካ ደውሎ “በውይይቱ ላይ የምታቀርበውን የመጽሐፍ ግምገማ ቀድተህ ላክልኝ” አለኝ፡፡ እኔ እኮ አልተጋበዝኩም አልኩት ፤ “ኧረ ተው መጋበዝህን ከፌስ ቡክ ላይ አይቼ ነው የደወልኩልህ” አለኝ ፤ እኔም “እስኪ ላከውና እኔም ልየው” አልኩት፡፡ እኔም በፕሮግራሙ ጥናት አቅራቢ መሆኔን ከፌስ ቡክ ላይ ተመለከትኩኝ፡፡ ቅዳሜ ቀን አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ስሜ ወጥቶ አየሁትኝ፡፡ የዚያን እለት የፕሮግራም አዘጋጅ ነኝ ያለ ሰው ስልክ ደውሎ ‹‹ነገ ጽሁፍ ታቀርባለህ›› አለኝ፡፡ እኔም “እንዴት ያለ እኔ ፍቃድ ስሜን በጋዜጣ በማውጣት ፈቃደኝነቴን ዝግጁነቴን ባልተጠየኩበት ሁኔታ ፕሮግራም ትይዛላችሁ?” ስለው ብርሀኑ ደቦጭ አልነገረህም እንዴ አለኝ፡፡ ብርሀኑ ከእኔ ውጪ ከሶስተኛ ወገን ከመስማቱ ውጪ መጽሀፉን በመገምገም እንደምናቀርብ የሚያውቀው ነገር እንዳልነበረ መጀመሪያ በደወለልኝ ቀን ከነገረኝ ነገር በመነሳት ከማወቄ ውጪ ብርሀኑ ከዚህ ወዲህ አልደወለልኝም፡፡ ሰማያዊ የሚባል ፓርቲ የዝግጅቱ አዘጋጅ መሆኑን ያወኩት ከዚያ በኋላ ነው፡፡ መቼም አንድ ፓርቲ ሰውን ሲጋብዝ በይፋ የፓርቲው ማህተብ በማስፈር እንዴት ደብዳቤ እንዲደርስ አያደርግም? ለአንድ ሰው መብት መከበር እታገላለሁ የሚል ፓርቲስ ያልጋበዘውን ሰው እንዴት እከሌ በፕሮግራሙ ላይ የጥናት ወረቀት ያቀርባል በማለት በጋዜጣ ያስነግራል? ለእኔ ነገሩ በጣም አስገራሚ ሆኖ አልፏል፡፡

ላይፍ፡- ‹‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ›› በተሰኝው መጽሀፍ ዙሪያ በመጦመሪያ ብሎግህ ላይ የራስህን ግምገማ ካወጣህ በኋላ ፕሮፌሰሩን ጨምሮ የተለያዩ ምላሾች ተሰንዝሮብሀል፡፡ ነገር ግን እንዴት ጠጠር ከወረወርክ በኋላ በዝምታ መዋጥህ ብዙዎች ከመጀመሪያው አስተያየቱ ስህተት እንደሆነ በማወቁ ነው ይሉሀል?

ዲ/ን ዳንኤል፡- በተሰጡት ምላሾች ዙሪያ ብዙ ነገር የምለው ነበረኝ፡፡ እሳቸው እንዳሉት ሳይሆን መጽሀፉን በደንብ አድርጌ አንብቤዋለሁ፡፡ እንኳን አነስተኛ የገጽ ብዛት ያለው መጽሀፍ ይቅርና ብዙ ሺህ ገጾች ያላቸው መጻሕፍት አነባለሁ፡፡ ከመጽሀፉ ያወጣኋቸው ሁለት ነገሮች ነበር፡፡ አንደኛ ታሪክ አይከሽፍም፡፡ ምን ማለት ነው? ለምሳሌ እኔ ይህን ቢሮ ለመስራት እቅድ ነበረኝ ፤ ነገር ግን አልሰራሁትም ከሸፈ፡፡ ይህ የቢሮ ክሽፈት ተብሎ ሊነገር አይችልም፡፡ ክሽፈቱ የዳንኤል ቢሮ ሊባል ግን ይችላል፡፡ ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ታሪክ ከሸፈ ሊባል አይቻልም ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ እኮ የተጻፈው ብቻ አይደለም ፤ ያልተጻፈ ብዙ ታሪክ አለ ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ የክሽፈት ምሳሌ ሊሆን አይችልም፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እኮ የአክሱም ስልጣኔ ፤ የላልይበላ የመሳሰሉት ይገኛሉ፡፡

ሌሎቹ ፕሮፌሰሩ የጠቀሷቸው የታሪክ መጻሕፍት ናቸው፡፡ የታሪክ ጸሀፍቱ መጻህፍቱን ከጻፏቸው 41 ዓመታት ያህል ተቆጥረዋል፡፡ ፕሮፌሰር መርዕድ ሲሞቱ ፤ ፕሮፌሰር ታደሰ አልጋ ላይ ሲውሉ ጠብቆ የእነሱ ስራ ላይ ሂስ ማቅረብ ተገቢ ነው? ከእነዚህ ሰዎች ጋር ለዓመታት አብረው የነበሩ ሰው ጊዜ ጠብቀው ይህን ማድረጋቸው በእኔ አስተያየት ትክክል አይደለም፡፡ ፕሮፌሰሩ መጽሀፍቱን በደርግ ዘመን ነው ያዘጋጀሁት በማለት በብሔራዊ ቴአትር መናገራቸውን ሰምቻለሁ፡፡ ነገር ግን ይህ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡መጽሐፉን ለማሳተም ሳንሱር ቢያስቸግራቸው እንኳን የጥናት ወረቀቶቹን በተለያዩ መድረኮች በማቅረብ እነ ታደሰን መሞገት ይችሉ ነበር፡፡ ደርግ እኮ ከወደቀ 21 ዓመታት ተቆጥሯል፡፡ ታዲያ ለምን ከደርግ ውድቀት በኋላ መጽሀፉን ሳያሳትሙት ቆዩ? መስፍን በቁጣ ስሜት ለኔ መልስ በማለት የጻፉት ጽሁፍ ምላሽ ያልሰጠሁት አንደኛ ለእሳቸው አክብሮት ስላለኝ ነው፡፡ ወደድንም ጠላንም በዚች ሀገር ታሪክ ውስጥ የራሳቸውን አሻራ አኑረዋል፡፡ በዚህ ላይ በአደባባይ ከሚናገሩ ጥቂት ምሁራን አንዱ መሆናቸውን ከግምት በመክተት ነገሩን በዝምታ ማለፍ መርጫለሁ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለፕሮፌሰሩ ምንም ምላሽ አትስጥ በማለት ምክራቸውን ለግሰውኛል፡፡

ላይፍ፡- ፕሮፌሰሩ በዋናነት “ቤተ መንግሥቱን” አየሁት በማለት በሰጠህው ምስክርነት ተበሳጭተዋል፡፡ የማላውቀውን ዶክተር በመጥቀስ ነገሩን ሌላ ትርጉም እንዲይዝ አድርጓል ብለዋል፡፡

ዲ/ን ዳንኤል፡- የጠቀስኩትን ታሪክ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያውቁት ስድስት ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ከስድስቱ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በህይወት የሚገኙት ፕሮፌሰሩና መንግስቱ ኃ/ማርያም ብቻ ናቸው፡፡ የዶክተሩን ስም መጥቀስ ያልፈለኩት ዶክተሩ በህይወት ስለሌሉ ነው፡፡ ይህንን መናገር ድብትርና የሚል ትርጓሜ አያሰጥም፡፡ እኔ ለድብትርና አልበቃሁም፡፡ ዮፍታሄ ንጉሴ የጻፈውን ካነበባችሁ ድብትርና ትልቅ ማዕረግ መሆኑን ትገነዘባላችሁ፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ይህን ሹመት የሚሰጡ በሆኑና በተቀበልኳቸው ደስታውን አልችለውም፡፡

ላይፍ፡- ፕሮፌሰሩ የኢትዮጵያ “ታሪክ ከሽፏል” ካሉባቸው ነጥቦች አንዱ የአገሪቱ የስኬት ታሪክ መቀጠል ባለመቻሉ ነው፡፡ ለምሳሌ የአክሱም ሃውልትና የላበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት የሰራ ህዝብ እንዴት በደሳሳ ጎጆ ይኖራል ? ይላሉ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ ሕዝቤን አላወግዝም በማለት ራሳቸውን ለጥይት የሰጡላት አገር እንዴት ጠዋት የሚናገሩትን ለማታ መድገም የማይችሉ አባቶችን ታፈራለች ? በማለት ክሽፈቱ በሁሉም የታሪክ አውድ መኖሩን በመጥቀስ ይሟገታሉ፡፡

ዲ/ን ዳንኤል፡- የኢትዮጵያ ታሪክ በአንድ ሰው እድሜ በሚደረግ ጥናት የሚደረስበትና ከሽፏል የምንለው አይደለም፡፡ የአክሱም ሀውልት ወይም የአቡነ ጴጥሮስን አይነት የሞራል አርአያ ማጣታችን የታሪካችን ቁንጽል አካል ነው፡፡ ይህንን በማንሳት ብቻ ታሪካችንን ከሽፏል ማለት ተገቢ አይደለም፡፡

ላይፍ፡- ፕሮፌሰር መስፍን እኮ አንድ ያልከሸፈ የኢትዮጵያ ታሪክ ለማግኝት አልቻልኩም ነው ያሉት?

ዲ/ን ዳንኤል፡- አልፈለጉም፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ በአንድ ሰው እድሜ እንደማትጨርሰው ተነጋግረናል፡፡ ምናልባት የምናውቀው የመካከለኛውንና የሰሜን ኢትዮጵያን ጉዳይ ነው፡፡ ብዙ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ያልተዳሰሱ ጉዳዮች ደግሞ አሉ፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ በምልአት ዛሬ ልትናገር አትችልም፡፡ በነገራችን ላይ እንደ ባለሙያ ሁሌም መጠንቀቅ ያለብን ስለ አንድ ነገር በምልአት ልታውቅም ልትደርስበትም አትችልም፡፡ ስለዚህ ይመስለኛል ፤ ሊሆን ይችላል ፤ እገምታለሁ ትላለህ እንጂ እርግጠኛ ልትለው የምትችለው ነገር በጭራሽ የለም፡፡ ያውም እንደ ኢትዮጵያዊነት ውስብስብ በጣም ብዙ ባህሎች ያሉት ህዝብን በዛ ደረጃ ማስቀመጥ ትክክል አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተረድቼዋለሁ የማትለው ልዩ ሕዝብ ነው፡፡ አንድን ጉዳይ በቃ ጨርሷል ስትል ብድግ የሚል ፤ ተኝቷል ስትለው የሚነሳ ፤ ከ1997 ዓ.ም በፊት የነበረውን 97 ላይ ለምንድነው ብድግ ያለው? ለሚለው እንኳን ተንትኖ የሚነግርህ የለም::

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop