January 7, 2020
11 mins read

የግብጽ ባርነት ይሻለናል? – ኤፍሬም አሰፋ ክአዋሳ

ከአራት መቶ አመታት ያለነሰ ዘመን  በግበጽ ሀገር በግዞት የኖሩ ህዝበ እስራኤል በሙሴ መሪነት ባህረ ኤርትራን ተሻግረው  ወደ ሚወርሷት ርስት  በተጉዙባት ረጂም  ጉዞ ወቅት    በአመጻና ባለመታዘዝ  ስራቸው ምክንያት መከራ ቢበዛባቸው ‹ከግብጽ ያወጣሀን በበረሀ ልታጠፋን ነውን?› ብለው በመሪያቸው በሙሴ ላይ ተቆጡ፣ የፈርኦንን አገዛዝ ናፈቁ ከሚወርሷት መልካም ሀገር ይልቅ የባእድ ሀገር  ባርያ  ሆኖ መኖርን መረጡ ፡፡ ግብጽ ግን ለነሱ የተመቸች ሆና አልነበረም ብዙ ስቃይና መከራን አስተናግደውባታልና፡፡

የእናታችን ኢትዮጵያ  ማዕዷ ለሁላችንም በቂ ሆኖ ሳለ  ፈርጣማ ጡንቻ ያላቸው ወንድሞቻችን ግን  እናታችን የሰጠችንን ልግስና በመንፈግ   የበይ ተመልካች ሆነን በቀቢጸ ተስፋ ለአመታት  እንድንቆይ አድርገውን ነበር፡፡

ለፈጣሪ ምስጋና ይሁንና በዲሞክራሲ ሃይሎችና በህዝብ በተከፈለ ዋጋም የእናት ኢትዮጵያ ልጆች በሙሴዎቻችን መሪነት  ለሁሉም ወደምትበቃ የላቀችና የበለጸገች እናት ሃገርን ለመውረስ የለውጥ ጉዞ ከጀመርን እነሆ ሁለት አመታት አስቆጥረናል፤

ሆኖም ግን የበለጸገችና የታፈረች ታላቅ   ሀገር ኢትዮጵያን  እንዳናይ  ከለውጡ ዋዜማ ጀምሮ  ለራሳቸው ምቾትና ድሎት በመሻት ፍትህና ዲሞክራሲ አልባ የሆነውን የሞተና የተቀበረ  አስተዳደር ከተቀበረበት በማውጣት፣ እነደጣኦት እንዲመለክ ያልቆፈሩት ጉድጓድ አልነበረም፡፡

የተከበሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በለውጡ ማግስት፡ በኢሳት ቲቪ  ከጋዜጠኛ ሲሳይ አገና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ  በለውጡ ሂድት ሊከሰቱ የሚችሉ ሶስት ሁኔታዎችን (Scenarios) እነደሚከተለው አመላክተው ነበር፤- 1ኛ/ የተገኘው ለውጥ ስር-ነቀል ነው ወይንስ ጥገናዊ  ነው ከነዚህ ከሁለቱ አንዱ ቢሆን  ምን  ሊከሰት ይችላል ሌላው   2ኛ/ ‹ካልበላሁት ልበትነው› የሚልና ለአመታት የሃገሪቱን ሀበት ሲቀራመቱ የኖሩ ሰዎች  የሚፈጥሩት ሁኔታ ሲሆን፣የመጀመርያው ሁኔታ ማለተም ስርነቀል ለውጥ የሚደረግ ከሆነ እውነተኛ የማህበረሰብ ስርአት የሚዘረጋበት፣ ዲሞክራሲዊ ጠቋማት የሚፈጠሩበት፣ ፍታዊ የዳኝነት ስርኣት ያለበትና  ዜጎች ሰልፍ ቢያደርጉ የማይገደሉበት ወዘተ ስርአት ይሆናል፡፡ በዚህን ወቅት ከለውጡ ተቃራኒ የቆሙት ሃይሎች በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ነውጥ ሊያስነሱ ይችላሉ ነገር ግን ሁላችንም ከመንግስት ጎን ሆነን ከተሰከፍን ነገሮች በዚያ ሁኔታ አይቀጥሉም ብለው ነበር፡፡

ፕሮፌሰሩ መጻኢውን አስቀድመው የተመለከቱት ይመስላል፡፡ በለውጡ ሂደት ወቅት ‹ካልበበላው ልበትነው› ብሎ የተነሳው ሃይል በሃገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ስትናወጥ አሳልፋለች፤በተጨማሪም ለውጡን ሲደግፉና ሲሳተፉ የነበሩ የተወሰኑ ክፍሎች በፈተናዎች መብዛትና ከለውጡ ተቃራኒ በቆሙ ሃይሎች ተጽእኖ ምክንያት ማፈግፈግ፣ ማጉረምረም ብሎም ለውጡ ያመጣው ፋይዳ የለም የበፊቱ  ይሻለናል በማለት ከለውጡ ተቃራኒ ሆነው እንደተነሱም  የሚታወስ ነው፡፡

ሁኔታው አንዳንዴ የተወሰንን ኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ አደጋገፈን ይመስለኛል፤ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድናችን ሲጫወት ለመደገፍ ወደ ስቴድዮም እንገባለን፣ ጨዋታው ሳይጀመር ስቴድዮም ይቀወጣል፤ ከአፍታም በኋላ ቡድናችን ግብ ያስቆጥራል፤ይበልጡኑ ድጋፉ በከፍተኛ  የግለት ስሜት  ይቀጥላል፡፡ ቀጥሎም ተቃራኒ ቡድን ጎል ያስቆጥራል፣ ስቴድየሙ በድንገት ጸጥ ይላል ፤አፍታም ሳይቆይ ማጉረምረም ይጀመራል ፤  ነገሮች በዚህ መልኩ ተቃራኒ ቡድን ማጥቃቱን ቀጥሎ ግቦች ሲቆጠሩ ቀስ በቀስ  ስቴድየሙን ለቆ  መውጣት የብዙ ስፖርት ደጋፊዎች መገለጫዎች ከሆኑ ቆይቷል ፡፡ አንዳንዴም ብሄራዊ ቡድናችን ጨዋታውን መቆጣጠር  ሲጀምርና ከተቃራኒው ቡድን መሪነቱን ሲረከብ ስቴድዮሙን የለቀቁት  ደጋፊዎች   ተመልሰው ወደ ደጋፊነት ሲመለሱ የተመለከትንበት አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው ፡፡

ወረተኝነት ጎልቶብናል ፤‹በሞቀበት ማደር›ን የመሳሰሉ ወጥ ያልሆኑ  ስብዕናዎች መገለጫዎቻችን ከሆኑ  ጊዜያት ተቆጥረዋል ፡፡ በሀገራችን  ከመጣው የለውጥ  ሂደት አንጻርም እኚን ከላይ የተዘረዘሩትን አይነት  በጀመሩበት  አለመጽናት፣  ጎል ሲገባና ድል ሲገኝ ብቻ የምናመሰግን፣ ችግርና ድካም ሲገጥም ግን የምንሳደብ፡  መልካም የለውጥ ፍሬዎች ሲገኙ የምናመሰግን፣ አለመረጋጋቶችና ነውጦች ሲገጥሙን የምንራገም፤ በጎው ነገር ብቻ የራስ ክፉው ነገር ግን የሌላ  አርጎ የመውሰድ እስስታዊ ባህሪ ያስተዛዝባል ፣ ጥቂት የማይባሉ አቋም የለሽነትና ወኔ ቢስነት የኛ ገሃድ የወጡ መገለጫዎች ናቸው፡፡  በመልካም ጊዜ ብቻ በስሜት የምንጓዝ በፈተና ጊዜ ግን ከሃዲዎች ሆነናል፡፡

በሁለት አመታት ውሰጥ በርካታ ሀገር አፍራሽና ዘግናኝ የሆኑ ግጭቶችን በማድረግ ህዝብን ከህዝብ ሃይማኖትን ከሃይማኖት በማጋጨት ሓገርን ለመበታተን የተደረጉ ሴራዎችን ተመልክተናል፡፡ወገኖቼ!  በጥፋት ሃይሎች ድርጊት ሳንሸበር ትእግሰትን ሰንቀንና ከመንግስት ጎን ተሰልፈን በጽናት ድጋፍ ከሰጠን ሁኔታዎች መልካም ይሆናሉ ፡፡ በለውጡ ግስጋሴ  ወቅት በጋራ መጓዝ ከጀመርን በኋላ በጊዚያዊ አለመረጋጋቶችና ፈተናዎች ሳንረበሽ በመተጋገዝና በመረዳዳት ለውጡን ማስቀጠል ይገባናል፡፡

የቀደመውን   ፍታዊ ያልሆነ አስተዳደር መናፈቅ ግን ባርነትን እንደመውደድ የስቆጥርብናል፡፡ ሃያ ሰባት አመት ሙሉ የተሰራበት የመለያየት   አስተሳሰብና ኢ-ፍታዊ  የሀብት አጠይቃቀምን ፍታዊ ወደሆነው ፖለቲካና ኢኮኖሚ ለመድረስ  ሁለት  አመት በቂ  ነው  ማለት ትክክል አይመስልም፤ ምክንያቱም  በዲሞክራሲ ዳዴ ለምንል ለኛ ቀርቶ በተረጋጋ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ውስጥ ሆነው የዲሞክረሲ ከፍታውን ይዘዋል የተባሉት  ሃገራት መሪዎች በምርጫ ወቅተ እንተገብራለን ብለው የተነሱባቸውን  ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሀሳቦች ጥሩ ወይንም መጥፎ ናቸው ተብለው በህዝባቸው የሚገመገሙት  ከአራት ወይንም አምስት አመታትን   የመሪነት ጊዜያቸው በኋላ ነው፡፡ ለውጥ ያለጊዜ የማይካሔድና ሊለካ የማይችል የተፈጥሮ ህግ ነውና፡፡

በመጨረሻም ለኢትጵያውያን ወገኖቼ  በእርግጠኝነት የምንናገረው ነገር፡- ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ የሁሉም ልጆቿ  ነጻ  አስተሳሰብ የሚያሸንፍበት፣የባህልና የቋንቋዎች እኩልነት የሚረጋገጥበት  ለሁሉም የምትበቃ ሁላችንንም የምታቅፍ የፍቅር ሃገር እንደምትሆን ነው፡፡

ስለዚህም ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ!  በምንም የማንንትና የሃይማኖት አጀንዳዎች ሳንከፋፈል በአንድነትና በፍቅርና ሀገራችን ወደ ተሸለ የብልጽግናና  የዲሞክራሲ ማማ እናድርሳት መልእክቴ ነው፡፡

ፈጣሪ ኢትዮጵያን   ለዘላለም ይባርክ፡፡

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop