እ.አ.አ. በ2ዐ14 በአለም ታዋቂ የሆኑ የቡና ቆይዎች እና ባለሙያዎች በሰጡት ምስክርነት ለኢትዮጵያ ቡና 25 ነጥብ በመስጠት ከአለም የ1ኛ ደረጃ ሲያጐናንፅፉት የኬንያ በእጥፍ አንሶ ከ12 ነጥቦች 2ኛ፣ ኮሎምቢያ በ1ዐ ነጥብ 3ኛ ደረጃ አጐናፅፋዋታል፡፡ እ.አ.አ. ለ2ዐ18 ለአሜሪካ የጥሩ ምግብ ሽልማት ከታጩት 27 ተወዳዳሪዎች መካከል 26 በኢትዮጵያ ቡና የሚወዳደሩ ነበሩ፡፡ (Daily coffee new, 2017). ለነገሩማ ገና ከጠዋቱ ነው አሜሪካኖች በኢትዮጵያ ቡና ፍቅር የወደቁት፤ የአሜሪካ መስራች እና ሶስተኛው ኘሬዜዳንት የሆኑት ቶማስ ጀፈርሰን እ.ኤ.አ. በ1824 ቡና የስለጠነው አለም መጠጥ ነው ብለዋል፡፡ ሥልጣኔ ብዙውን ጊዜ ከባህል ምንነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ስለዚህ በአለም ላይ ካሉት ጥቂት ሥልጣኔዎች አንዱ የኢትዮጵያ መሆኑን በናችን አረጋግጧል ማለት ነው፡፡ በዚህም ነው ኢትዮጵያ ለአለም ካበረከተችው አስተዋፅአ አንፃር ቡና ከፍተኛውንና ልዩ ቦታ ይይዛል፡፡ ምክንያቶቹ ደግሞ ቡና ለአለም መጠጥ ብቻ ሣይሆን ምክንያታዊ አስተሣሠብ እና ዲሞክራሲያዊ ባህል እንዲዳብር የቡና መጠጫ ቤቶች / / coffee house/ አይነተኛ አስተዋፅኦአድርገዋል ይላል ጀርገን ሐቨርማስ ፣ ለቨርማስ እንደሚለው ከሆነ በቡና መጠጫ ቤቶች ሰዎች ተሰብስበው ከአልኮል ይልቅ ቡና እየጠጡ ያለምንም ገደብ የሀሣብ ክርክር እና ፍጭት በማድረግ በምክንያታውነት ተቀባይነት ባለው ሀሣብ መግባባት ይደረሡ ነበር ይላል፡፡ መንግሥታትም እምነት እና ቅቡልነት ከህዝቡ ለማግኘት በ coffee house ስምንነት የተደረሰባቸውን ሃሣቦች ይተገበሩ ነበር ይላል፡፡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚሉት ከሆነ ቡና ከመምጣቱ በፊት አውሮፐውያን አልኮል በመጠጣት የሚፈጥሩት ጫጨታ ቡና በመተካት ስካራቸውን አስቀርቶላቸዋል ይላሉ፡፡ በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሣዩት ደግሞ በቀን 2 እና ከዚያ በላይ ሰኒ ቡና መጠጣት የእድሜ ጣሪያን በ15 አመታት እንደምጨምር ተረጋግጧል፡፡ የእድሜ ጣሪያ ደግሞ ከፍትሃዊ የሃብት መገለጨዎች አንዱ ነው፡፡ አዘወትሮ ቡና መጠጣት የልብ ድካምን እንደሚቀንስ በጥናት ተረጋግጧል፡፡
ይህንን ያህል ጠቀሜታዎች እየሠጠው ያለ ቡናችን በብዙ ተስፋዎች አና ተግዳረቶች እየተሞላ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 23ዐ 764.41 ቶን ቡና በመላክ ከ76ዐ ሚሊዮን ዶለር በላይ ገቢ አግኝታለች፡፡ የመጠን አፈፃፀሙ በሀገሪቱ ታሪክ 2ኛው ሪከርድ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአለም ቡና ገበያ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የአለም የቡና ገበያ መሸጫ ዋጋ ከ13 አመታት ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ መጠን በቀነሰበት ሁኔታ ነው፡፡ በአጠቃላይ የቡና እንቆቅልሽ / coffee paradox/ ፍንትው ብሎ በወጣበት ጊዜ መሆኑ ነው፡፡ በአለም ላይ የቡና ፍጆታ እየደገ ነው፡፡ በዚህ አመት እንኳን 2 በመቶ በላይ አድጓል፡፡ የቡና አቅርቦት ቢጨምርም ፤ የጥሬ ቡና ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ቢቀንስም ለጠጪዎች የቡና ዋጋ አልቀነሰም፡፡ የጥቂት ድንበር ተሸጋሪ ኩባንያወች እና ቡና ቆይወች ትርፍ በከፍተኛ ሀኔታ እያደገ ነው፡፡ በሌላ በኩል ቡና አብቃይ አርሶ አደሮች እና ሃገሮች ገቢያቸው በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል፡፡ በተለይም ቡና አብቃይ አርሶ አደሮች የምርት ወጪያቸውን እንኳን ለመሸፈን እንኳን አልቻሉም፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ኢትዮጵያ በመጠን 2ኛ ሪካርድ የሆነ ቡና ወደ ውጭ የላካቸው ይህ አበረታች ክንውን ነው፡፡ በተጨማሪም በበጀት አመቱ አለም አቀፍ የቡና ቀን በደማቅ ሁኔታ መከበሩ፣ በኬንያ ከሌሎች ሀገራት እና ከአለም አቀፍ የቡና ድርጅት ጋር በመሆን አሁን ያለወን የአለም የቡና ንግድ ስርዓት ሀገራችን አውግዛ መፍትሔ እንደሚሻው መግለጽ መቻሉ፣ የሀገሪቱን ቡና በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስተዋውቅ የ2ዐ2ዐ የቡና ጠዕም ውድድር ሀገራችን እንደሚሄድ እድል መገኘቱ ፤ በተጠናቀቀው በጀት አመት በተሠሩት የኘሮሞሸን ሥራዎች ባለፈው ዓመት አራተኛ የነበረችው አሜሪካ 1ኛ የኢትዮጵያ ቡና ገዥ ሀገር መሆኗ፣ (አሜሪካ ከአለም 75 በመቶ ቡና ወደ ሀገሯ በማስገባት የመጀመሪያውን ደረጃ የምትይዝ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ትርጉሙ ከፍተኛ ነው፡፡)
የአፍሪቃን የቡና ፍጆታ እንዴት አናሳድገው የሚል ጉባኤ በአ/አ መካሄዱ እንደሁም 49,239ሄ/ር (83.2%) ጉንደላ ተካሂዷል፡፡ እንዲሁም በነቅሎ ተከላ ለማደስ 35,373 ሄ/ር ዕቅድ ተይዞ 25,731.5 ሄ/ር (72.7%) ነቀላ የተካሄደ ሚሊዮን በሔክታር ጉንደላ እና ነቅሎ ተከላ መካሄዱ ከአበራታች ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸዉ፡፡
ይሁንና በበጀት አመቱ የተለያዩ ተግዳረቶችም አጋጥመው ነበር፡፡ ከእነዚህ ውሰጥ ቡና ቅሸባ እና ስርቆት ናቸው፡፡ በሀገራችን ላይ በቡና ላይ የሚደረግ ስርቆት ሀገርን እንደመሸጠ ይቆጠራል፡፡ ምክንያቱም ቡና የኢትዮጵያን ህዝብን እንደሙጫ የሚያጣብቅ ማህበራዊ ካፒታል ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብራንድ ነው ፡፡ ጀርመን በኢንጂነሪንግ፣ ፈረንሣይ ሽቶ፣ ህንድ ቅመማቅመም፣ ስውዘርለንድ በሰዓት፣ ብራዚል ሲባል አግር ኳስ እንደሚባለው ሁሉ ኢትዮጵያ ሲባል ቡና ማለት ነው፡፡ ብራንድ ደግሞ በምንም መልኩ ሊሰረቅ ወይም ሙስና ሊፈፀምበት አይገባም፡፡
ለምሳሌ ከነኰሪያ እና ታይዋን የምንማረው በፍጥነት በማደግ ላይ በነበሩበት ጊዜ ሌባ እንኳን ለክቶ የሚሠርቅበት ብሔራዊ መግባቢት ፈጥረዉ ነበር፡፡ ለምሳሌ ት/ቤት በ1ዐዐሺህ ይገነቡ ከነበረ መሐንዲሱ 1ዐ በመቶ የራሱን ድርሻ ይጨምርበት እና ጥራቱን ጊዜው መጠኑ ላይ አይደራደርም ነበር፡፡ የኤክስፖርት ምርትማ ምንም ዓይነት ሙስና እንዳይፈፀምበት ስምምነት ደርሰውበት ነበር፡፡ የኤክስፖርት ጉዳይ የህልውና ጉዳይ መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ እኛም በቡና ላይ የሚፈፀም ቅሸባ እና ስርቆት የሀገሪቱን ብራንድ እንደመስረቅ የሚቁጠር በመሆኑ ሁላችንም ልንዋጋው ይገባል፡፡ በቡና ላይ የሚፈጠር ስርቆት የሀገሪቱን ገፅታ በማበላሸት የሀገሪቱን መለያ የሚያሳጣ እና ሀገሪቱን በከፍተኛ ሁኔታ የሚጐዳ በመሆኑ ሁላችንም ይህንን አስነዋሪ ድርጊት መዋጋት የሀገሪቱን ልዩ ብራንድ የማስቀጠል እና የሀገሪቱን አንፃራዊ ብልጫ በማሣደግ ተወዳዳሪነቷን ከፍ በማድረግ የሀገሪቱን እድገትና ልማት በማስቀጠል የሁላችንም ኢትዮጵያ የመገንባት ጉዳይ ሊሆን ይገባል፡፡