July 21, 2019
30 mins read

የሕወሃት ሰይጣናዊ እጆች – በገ/ክርስቶስ ዓባይ

በገ/ክርስቶስ ዓባይ
ሐምሌ 14 ቀን 2011 ዓ/ም

ከሃያ ሰባት ዓመታት የችግር፤ የሰቆቃና የመከራ ቸነፈር በኋላ በኢትዮጵያ የተስፋ አየር እየነፈስባት ነበር። ወላጆች የልጆቻቸውን በሰላም ወጥቶ በሰላም መመለስ በስጋት እየተንቆራጠጡ ይጠብቁበት የነበረው ሁኔታ አልፎ ‘እፎይ!’ በማለት፤ የወጣቱን ጠቅላይ ሚንስትር ዓቢይ አህመድን ዕድሜና ጤና እንዲሰጥላቸው ፈጣሪያቸውን  እየተማጸኑ ቆይተዋል። ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ኤርትራን ጨምሮ ያለፈውን እረስተን ለመጭው ጊዜያችን በፍቅርና በይቅርታ ተደምረናል በማለት አንድነታቸውን አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ከሰይጣን ጋር ቃልኪዳን የተጋባው ሕወሃት ግን  ፍቅር፤ ሰላምና አንድነት የሚባሉት የሕዝብ እሴቶች ሊዋጥለት አልቻለም።

ሕወሃት ወገኑን እርስ በእርስ እያጋጨና ደም እያፋሰሰ ለተጠናወተው የአጋንንት መንጋ የሰው ሕይወት እየገበረ መቀጠሉን እንደ አማራጭ በመውሰድ እስከአሁን ድረስ ዓይኑ እንደቀላ ነው። ሕወሃት በሰላም  ተደመር! ቢባል እምቢ አልደመርም በማለት እያንገራገረ መሆኑን በየጊዜው በተቀነባበረ መልኩ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በቅጥረኞቹ እያስወሰደ ያለውን ግድያና ረብሻ መረዳት ብቻ ይበቃል።

ሕወሃት ለዚህ ሁሉ ትዕቢትና ንቀት እንዴት የልብ ልብ አገኘ? ብለን መጠየቅ ብልህነት ብቻ ሳይሆን መሠረታዊ መረጃም መጥቀስ አስፈላጊ ይሆናል። በእርግጥ ሕወሃት ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያን አንጡራ ሀብት ሲዘርፍ መቆየቱ የአደባባይ ምስጢር ነው። ግንቦት 20 ቀን 19873 ዓ/ም የሕወሃት ጭምብል የሆነው ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር ሕወሃቶች በቅድሚያ ያደረጉት የኮንስትራክሽን ሚኒስቴርን በማፍረስ እጅግ በጣም በውድ ዋጋ የተገዙ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን በምርኮ መልክ ወደ ትግራይ ማጓጓዙን ተያያዘዙት።

በቀጣይም በመላው አገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ይገኝ የነበረውን የአገር ውስጥ ማከፋፈያ ድርጅት ሀብት የነበረውን በቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወረሱት። በሦስተኛ ደረጃ እንዲሁ በመላው አገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች የነበረውን ብዙ ሚሊዮን ኩንታል የእህል ዘር የተከማቸባቸውን የእርሻ ሰብል መጋዝኖች ከነሙሉ ንብረቱ ወረሱ። በአራተኛ ደረጃ ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ ጀምሮ ለአገሪቱ የድንገትኛ አደጋ መጠባባቂያ የተከማቸውን ወርቅ ወረሱ።

ቀጥሎም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የነበረውን የአገሪቱን ጥሬ ገንዘብ በሞላ እንዲሁ በምርኮ መልክ ወረሱ። በተጨማሪም በተለያዩ ከተሞች የነበሩትን የኤሌክትሪክ ጀኔሬተሮች ቀን ቀን ሲፈቱ እየዋሉ ማታ ማታ ይጭኑ እንደነበር ይታወቃል። በዚህ መንገድ በጎንደር ከተማ ይገኝ የነበረውን ጄኔረተር መውሰዳቸው አይዘነጋም።

ከደብረ ማርቆስ ወጣ ብሎ ወደ ሁለት መቶ ሰው ይተዳደርበት የነበረውን ንብረትነቱ የአውራ ጐዳና ባልሥልጣን የሆነ የድንጋይ መፍጫ ፋብሪካ እንዲሁ ቀን ቀን ሲፈቱ በመዋል በምሽት እየጫኑ አግዘውታል። የአልሜዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ከተቋቋመ በኋላም ከባህር ዳር፤ ከኮምበልቻ፤ከድሬ ዳዋ እና ከአዋሳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች የተለያዩ ማሽኖችን እየነቀሉ በግልጽ መውሰዳቸውም አይረሳም። የዓለም ማያን የግብርና ዩኒቨርስቱ ቤተ መጻሕፍትም በመዝረፍ ለመቀሌ ዩኒቨርስቲ ማቋቋሚያ ማዋላቸው የአደባባይ ምስጢር ነው።

ሕወሃቶች በዚህ ብቻም አላበቁም፤ በደርግ ዘመን የተወረሱ የመንግሥት ቤቶችን በተለይ በጉራጌ የንግድ ማኅበረሰብ የተያዙትን ቁልፍ ቁልፍ የንግድ ድርጅቶችን በኪራይ መጨመር ሰበብ እያስለቀቁ በራሳቸው ሰዎች እንዲያዙ አደረጉ። በማስከተልም አንዳንድ አትራፊ የመንግሥት ድርጅቶችን ወደ ግል እናዛውራለን በሚል ሰበብ የልውውጥ ሠነድ በማዘጋጀት ብቻ አየር ባየር ስም እያዛወሩ አብዮታዊ ኢንቬስተር የሚሉትን የዘረፋ ክንፍ በመፍጠር በእራሳቸው ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ አደረጉ።

ይሁን እንጂ ‘ያዳቆነ ሠይጣን ሳያቀሥ አይለቅም’ እንዲሉ ይህን ሁሉ አድርገው ሊረኩ ስላልቻሉ የአዲስ አበባን የግል እርስትና በማዘጋጅ ቤት ሥር ያሉ በየቀበሌው የነበሩ የልጆች መጨዋቻ ተብለው የተተውትን ክፍት ቦታዎችን ሳይቀር እየሸነሸኑ ግማሹን ሸጡ ግማሹንም በራሳቸው ቁጥጥር ሥር እንዲሆኑ አደረጉ። ይህንን ሁሉ ግፍና በደል ሲፈጽሙ ሊገዳደራቸው ቀርቶ በይፋ ደፍሮ ሊቃወም የቻለ ኢትዮጵያዊ አልተገኘም።

በክልል ስምም በመጠቀም ለዘመናት የኖረውን ሕዝብ በመግደልና በማፈናቀል፤ ከጎንደር ወልቃይትን፤ ጠገዴን፤ እና ጠለምትን  ከወሎ ራያን እና አፋርን እንደ ድፎ ዳቦ በመቁረስ ወደ ትግራይ እንዲጠቃለሉ በማድረግ የመሬት ዘረፋ አከናውነዋል። ይህንን እኩይ ዓላማቸውን እውን ለማድረግ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጽሙ መቆየታቸው ከሕዝብ የተሰወረ አይደለም። በመሆኑም ከግድያ ያመለጡ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ሕይወታቸውን ለማትረፍ፤ ለስደተኝነት ተዳርገው በዓለም ዙሪያ ተበትነዋል።

ሕወሃቶች ከኢትዮጵያ አልፈው በምሥራቅ አፍሪቃ ሰላም እንዳይኖር እጅግ በጣም የረቀቀ ሴራ ሲያሴሩ ኖረዋል። በመጀመሪያ የሶማሊያን ቀጥሎም የደቡብ ሱዳንን ሁኔታ ማየቱ ብቻ በቂ ነው። የደቡብ ሱዳንን እንዲያደራድር የተመደበው ሥዩም መስፍን እንኳን ሊያስታርቅ እንዲያውም የሕወሃትን አጀንዳ እውን ለማድረግ ሪክ ማቻርን እንደሚደግፍ መስሎ በመቅረብና የጦር መሣሪያ በማስታጠቅ ከእርቅ ይልቅ ወደ የማይታረቅ ግጭት እንዲያመራ ከፍተኛ ደባ መሥራቱም አይዘነጋም።

ከዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ ሠራዊት በሰላም ማስከበሩ እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል። ግን እርምጃው ፍትሐዊ እንዳልነበረ ሐቀኛ የፖለቲካ ጠበብት ኢትዮጵያውያን ያገናዘቡታል የሚል ከፍተኛ እምነት አለ። እዚህ ላይ ማየት ያለብን የዓለም የጸጥታው ምክር ቤት አንድም እንዴት ባለ ሙስና የተጨማለቀ መሆኑን፤ ወይንም ሆነ ተብሎ ኢትዮጵያን ቀጣይነት ወደ አለው ወደ የማያልቅ የጦርነት ማጥ አዙሪት እንድትገባ የታቀደ ደባ እየፈጸመ ምሆኑን ማጤን ተገቢ ይሆናል።

የሶማሊያም ጉዳይ ከዚህ የተለየ አይደለም። ምክንያቱም የጎረቤት አገሮች በሰላም ማስከበሩ ሂደት እንዲሳተፉ የሚፈቀድ ከሆነ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የዘረፋ ወንጀል እንዲፈጸም በር ይከፍታል። ሌላው ቀርቶ መኪናዎች እንኳ ሳይቀር በቀላሉ ሊዘረፉ ይችላሉ። የገንዘብና በቀላሉ ሊጓጓዙ የሚችሉ ውድ ንብረቶችን በስውር ድንበር በማሻገር ሕገወጥ ቅሚያ ሊካሔድ ይችላል። ለእንዲህ ያለ ወንጀል የተጋለጡና የዓይን እማኝ የሆኑ ሰዎችም ምስክር እንዳይሆኑ በግፍ እንዲገደሉ ይጋብዛል። ድርጊቱ ግን ይዋል ይደር እንጂ በአፈ ታሪክ መልክ ለልጅ ልጅ ስለሚተላለፍ ለቀጠናው ሰላም በየጊዜው የሚያመረቅዝ የዘለቄታ ጠንቅ መሆኑ ግልጽ ነው።

ስለሆነም የዓለም የጸጥታው ምክር ቤት፤ የጎረቤት ሀገሮችን እንዲህ ባለው የሰላም ማስከበር ሁኔታ እንዲሳተፉ የሚፈቅድ ከሆነ ሆን ተብሎ ደም እንዲቃቡና ለትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ፤ ጊዜ እየጠበቀ የሚፈነዳ ቦምብ እንደመቅበር ይቆጠራል።

በተለይ ደግሞ ሕወሃት ለዚህ የሚያበቃ ዲስፕሊንና ተአማኒነት የሌለው ድርጅት መሆኑ በግልጽ ይታወቃል። ደርጅቱ ከአመሠራረቱ ጀምሮ በስርቆት፤በመዝረፍና በመግደል የተካነ መሆኑን ተሪኩ ይመሰክራልና። እጅግ በጣም የሚዘገንና ኅሊናን የሚሞግት ኃላፊነትን በአግባቡ ካለመወጣት የተወሰደ እርምጃ ለመሆኑ እንኳን ለተማረና ፊደል ለቆጠረ ይቅርና ማንም ተራ ሰው የሚረዳው ሐቅ ነው።

ቀጠናው ሰላም ከሆነ ሕወሃት በሥልጣን ለይ ሊቆይ ስለማይችል፤ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ እንደ ሰላም አስከባሪ በመምሰል የበግ ለምድ እንደለበሰች ተኩላ ሆኖ፤ጊዜ ለመግዛት የሚያስችለው አንዱ መንገድ ይህ ብቻ ስለነበር የግድ የአካባቢው ሰላም እንዲደፈርስ እረጅም የሆኑ ሰያጣናዊ እጆቹን በማስገባት ሰላምን ለማናጋት ሲያማስል ቆይቷል። የዚህ ሁሉ ግፍና መከራ ዳራው የአገራችንን ስምና ዝና የሚያረክስና የሚያሳንስ እንደሚሆን ለብልኆች የተሰወረ አይሆንም።  `

አልሸባብ በተዘዋዋሪ መንገድ ትጥቅ እንዲያገኝ በማድረግ እንዲጠናከርና ምሥራቅ አፍሪካ የባሰውን እንዲረበሽና ሶማሊያ ሰላም እንዳታገኝ ተንኰል ሲሠራ መቆየቱ የሚያከራክር አይደለም በእርግጥ ይህ ሁሉ ሀቅ፤ በወቅቱ የነበረውን የዴሞክራሲ ጭላንጭል በመጠቀም ይታተሙ በነበሩት ልዩ ልዩ ጋዜጠኞችና መጽሔቶች ሲዘገብ መቆየቱ አይካድም። ይሁን እንጂ እንደዚህ ያለውን የአገር ከባድ ምስጢር እያነፈነፉ ለሕዝብ ያጋልጡ የነበሩት የአገሪቱ የቁርጥ ቀን ጋዜጠኞች እየታደኑ በመታፈን ደብዛቸው እንዲጠፋ፤ ለጅብ እራት ተሰጥተዋል። አንዳንዶችም ታስረው ሥቃይና ሰቆቃ ሲፈጽምባቸው፤ በፍርድ ቤት ሲንገላቱ የመርፌ ቀዳዳ የምታህል ዕድል ያጋጠማቸው ደግሞ አገራቸውን እየጣሉ ተሰደዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የአገሪቱ መከላከያ ንብረት የነበሩትን አየር ኃይሉን፤ ልዩ ልዩ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን፤ ሚሳይሎችን ጨምሮ በምርኮ ስም ወደ ትግራይ አግዘዋል። ከአንድ ዓመት በፊትም የአገሪቱን የቴሌኮሙኒኬሽን የኢንተርኔት መረጃ ቋት የሆነውን ዘመናዊ መሣሪያ ወደ ትግራይ መውሰዳቸው የሚዘነጋ አይደለም።

አዲስ አበባ ውስጥ ቦሌ፤ ካዛንቸስ፤ አዋሬና አሥመራ መንገድ በአብዛኛው በሕወሃት ዓባላት የተያዘ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። በአሁኑ ወቅት ሕወሃቶች ዶላርና የብር ኖቶችን በጆንያ ጠቅጥቀው በየቤታቸው አጭቀዋል።

ሕወሃት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመቆጣጠር እንዲያመቸው ጤፍና ሌሎች የየዕለት ፍጆታ የሆኑትን እህሎች  በአውስትራሊያ ኩባንያ  እንደተገነባ በሚነገርለት ከተራራ ሥር በተሠራ ዋሻ  ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል የድንገተኛ ጊዜ መጠባባቂያ እህል በትግራይ ውስጥ መከዘኑም ይነገራል። እንግዲህ ይህንን ሁሉ በቁጥጥራቸው ሥር ስላደረጉ የልብ ልብ ተሰምቷቸዋል ማለት ይቻላል።

እጅግ  በጣም የሚደንቀው ግን የትግራይ ምሁራን ቀድሞ በፍርሃት ተሸማቀው ሊያደርጉት ባይችሉም፤ አሁን እየታየ ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ስሜት በመጋራት ሕወሃት እንደ ጫካ በመቁጠር፤ የመሸገበትን የዋሁን የትግራይ ሕዝብ ሊታደጉት ሲገባ ዝምታን መርጠዋል። በአሁኑ ሰዓት እነዚህ የትግራይ ልሂቃን ከህወሃት ጋር በመወገን የተጀመረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የለውጥ ትግል ለመቀልበስ ያለ የሌላቸውን ኃይልና ዕውቀት እየተጠቀሙ ይገኛሉ። እነዚህ ከርሳሞች ለወገናቸው አንድነትና ሰላም በማብሰር ከሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን እንዲሠለፍ ማስተማር ሲገባቸው ኅሊናቸውን በገንዘብ ሸጠው የትግራይን ሕዝብ ወደ ገደል ለመጨመር እየገፈተሩት ናቸው።

እነዚህ እንደ አሉላ ሰሎሞን ያሉ ሆድ አምላኩ የሚያስቡት በአእምሮአቸው ሳይሆን በሆዳቸው በመሆኑ በትግራይ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የክህደት ወንጀል እየፈጸሙ ይገኛሉ። እስከ አሁንም ቢሆን በኢትዮጵያ ሕዝብ አርቆ አስተዋይነት እንጂ እንደ እነርሱ ሴራና ተንኰል ቢሆን ኖሮ የሩዋንዳውን ዓይነት የዘር ፍጅት ለማስጀመር በብዙ የኢትዮጵያ ቦታዎች ለመለኮስ ጥረት አድርገዋል።

ያም ሆነ ይህ ግን ከእንግዲህ ወዲህ የቱንም ያህል የተንኰል ሤራ ቢሠራ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓይኑን ከፍቷል። በየትኛውም መንገድ ቢሆን ሕወሃት ከእንግዲህ እንደ እባብ አፈር ልሶ ሊነሳና እንዳለፈው ጊዜ አገሪቱን እየዘረፈና ሕዝቡን ያለአግባብ እየገረፈ ሊያስተዳድር እንደማይችል የተገነዘቡ አይደሉም። ሐቁ ይህ መሆኑን እያወቁ፤ ነገር ግን አምነው ሊቀበሉ አልፈለጉም፤ ኃሊናቸውን ለለውጥ አላዘጋጁምና። ሌላው ቀርቶ አናሳ (minority) መሆናቸውን እንኳ ዘንግተዋል።

የፈለገው ተዓምር ቢፈጠር በየትኛውም መለኪያ ችግር ላይ የሚወድቁት በመጀመሪያ የትግራይ ልሂቃን መሆናቸውን ማጤን ተገቢ ይሆናል። ነገሮችን እና ሁኔታዎችን እያወቁና እየተረዱ፤ በግዴለሽነት ሕዝብን ለመሠሪና ሠይጣናዊ ተልዕኮ ለማዘጋጀት መጣር ከቀጠሉ፤ የመጀመሪያው ሰላባዎች የሚሆኑት የትግራይ ልሂቃን ናቸው።

ከእነዚህ መካካል አንዱና ዋነኛው አብርሃ ደስታ ተጠቃሽ ነው። አብርሃ ደስታ የትግራይን ሕዝብ ለመታደግ ከተደራጀው ‘የአረና’ የአመራር ዓባል በመሆኑ በታሠረበት ወቅት እሱን ለማስፈታት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጮሆለታል። ነገር ግን ሁኔታዎች ፈር እየያዙ ሲሔዱ የቆመለትን ድርጅትና ሕዝብ በመካድ ከሕወሃት ጋር መቆሙን አረጋግጧል። በተለይም ከኤርትራ ጋር እየተደረገ ያለውን ስምምነትና መቀራረብ ሲያይ እንደ እሬት እንደጎመዘዘው በግልጽ መናገር ብቻ ሳይሆን የዋሁን የትግራይ ሕዝብ ለተቃውሞ እንዲወጣም ቀስቅሷል።

አሁንም ቢሆን ሕወሃት ከአገር ውስጥ ያለውን የአገሪቱን አንጡራ ሀብት ሙልጭ አድርጎ ወስዶ፤ ከውጭም ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና ከተለያዩ አገሮች በተራድኦና በብድር፤ በኢትዮጵያ ስም የተገኘውን ገንዘብ በሙሉ ጥርግርግ አድርገው ከወሰዱ በኋላ አገር የመመሥረት ሕልማቸውን እውን የማድረግ ዕቅድ በምኞት ደረጃ መገንጠላቸውን አረጋግጠዋል።

ነገር ግን ከተለየያዩ የዓለም አቀፉ ድርጅቶችና የሲቪክ ድርጅቶች ዘንድ ዕውቅናን ለማግኘት እንዲህ በቀላሉ የሚቻል አይደለም። በእርግጥ በ1983 ዓ/ም የኤርትራን መገንጠል እውን እንዳደረጉት ዓይነት ቀላል አይሆንም። በዚያን ጊዜ የታሪክ አጋጣሚ ሆነና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የነበሩት ቡጥሮስ ቡጥሮስ ጋሊ  ነበሩ ። እርሳቸው ደግሞ ግብጻዊ በመሆናቸው የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉ ስለነበሩ በለስ ሲቀናቸው ቶሎ ብለው ሥልጣናቸውን በመጠቀም የኤርትራን መገንጠል ተግባራዊ እንዲሆን አድርገዋል።

በአሁኑ ወቅት ግን እንዲህ ያለው ዕድል በቀላሉ ስለማይገኝ እየተኬደበት ያለው አቅጣጫ የተለዬ እየሆነ ነው።   በዚህም፡

በአንደኛ ደረጃ ሕገ መንግሥቱ ምንም ዓይነት መሻሻል እንዳይደረግበት መከላከል እንደዋነኛ ተግባር አድርገው በንቃት እየሠሩ ናቸው።

በሁለተኛ ደረጃ የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 39 አስመልክቶ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የኦነግን የመገንጠል ፖሊሲ በመርዳት፤ የኦሮሞ መንግሥት እንዲመሠረትና እንዲጠናከር ውስጥ ውስጡን እየሥሩ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል።

በሦስተኛ፤ ደረጃም የሶማሌን የመገንጠል እንቅስቃሴ ውስጥ ውስጡን እየረዱ መሆናቸውን ዲጂታል ወያኔ በማለት በአደራጁዋቸው የሜዲያ ሠራዊት ጥያቄያቸው ፍትሐዊ መሆኑን እየገለጹ ይገኛሉ።

አራተኛ፤ አቶ ጃዋር ሲራጅ መሐመድና አቶ አሉላ ሰሎሞን ለጋርዮሽ ግብ የሲዳማን ክልል የመሆን ጥያቄ እየደገፉ መሆናቸው የትሕነግን ዓላማ ለማሳካት ይረዳል በሚል የደቡብን ሕዝብ በማተራመስ ላይ ናቸው።

አምስተኛ፤ ኦዴፓም የኦነግን የመገንጠል እሳቤ ተግባራዊ ለማድረግ አዲስ አበባን ወደ ኦሮሞ ለማጠቃለል በትጋት እየሠራ ነው።

ስድስተኛ ኦነግ ከመገንጠሉ በፊት የአማራ ክልልን በመጋፋት እየወሰደ ያለውን የግዛት ማስፋፋት እርምጃዎችን ትህነግ (ወያኔ) እየደገፈ መገኘቱን እያየን ነው።

ሰባተኛ፤ በዶ/ር ደብረ ጽዮንና በዶ/ር ዓቢይ መካከል የፖሊሲ አንድነት እንጂ ልዩነት እንደሌለ ሊታወቅ ይገባል። ዶ/ር ዓቢይ የትግራይን የመገንጠል ፍላጎት ደጋፊ እንጂ ተቃዋሚ አለመሆኑን በብዙ መንገድ ማረጋገጥ ይቻላል።

ይኸውም፤እስከ አፍንጫው የታጠቀ የመከላከያ ሠራዊት ከትግራይ እንዳይወጣ በወያኔ ሲታገድ የተወሰደ እርምጃ የለም። ከላይ እንደተገለጸው የአገር ሀብት ተዘርፎ እያለ ለማስመለስ የተደረገ ጥረት የለም። ሥልጣናቸውን መከታ በማድረግ የአገር ሀብት የመዘበሩና በንጹሐን ዜጎች ላይ እጅግ የሚዘገንን ወንጀል ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ የነበሩ ከፍተኛ ወንጀለኞች በትግራይ መሽገው እንደልባቸው ሲፏልሉ ዶ/ር ዓቢይ ምንም ያደረገው ነገር የለም። ይህም የሚያሳየው ዶ/ር ዓቢይ የወያኔ ወንጀለኞችን ስውር ከለላና ጥበቃ እያደረገ መሆኑን ያመለክታል።

እዚህ ላይ የሁለቱን ስምምነት ባለመረዳት እናት አገራቸውን በማስቀደም በቅንነት በማገልገል ላይ የነበሩት ጄኔራል ሰዓረ መኮንን በሁለቱ ምስጢራዊ ስምምነት መስዋዕት እንደሆኑ መገመት አይከብድም። በተጨማሪም ለወገናቸውና ለአገራቸው በታማኝነትና በጽናት ለመሥራት በቆረጡ ጄኔራል አሳምነው ጽጌን ጨምሮ በአምስት የአማራ ክልል ከፍተኛ የአመራር አባላት ላይ የተወሰደው የጅምላ ግድያ ላይ የሁለቱም አካላት ሴራ እንዳለበት ግልጽ ነው።

ሕዝብ ለሕዝብ ምንም ችግር የለበትም ነገር ግን የሕወሃ ሰይጣናዊ እጆች በመላው ኢትዮጵያ ላይ መርዝ እየረጩና የዕልቂት እሣት እየለኮሱ መሆኑን ማወቅና ማሳወቅ የወቅቱ አንገብጋቢ ሁኔታ ነው።

ከዚህ እኩይ ተግባር በኋላም የሕዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየርና ለሁለቱም ወገን ከፍተኛ ሥጋት እየሆነ የመጣውን የአማራን መነቃቃት ለማዳከምና ሕዝቡንም ከትግል እንቅስቃሴው ለመግታት በማሰብ በብዙ መቶ የሚሆኑ ታዋቂ የአማራ ምሁራን እየታደኑ ለእስር እየተዳረጉ ናቸው። ከእነዚህም ከጉዳዩ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው የባልደራስና የአብን ዓባላት ይገኙበታል።

በተጨማሪም ‘ወናፉ’ ጠ/ሚንስትር ዶ/ር ዓቢይ ከሕወሃት በሚያገኘው ይሁንታ የአገሪቱንን ከፍተኛ የሥልጣን እርከኖች ሁሉ በኦዴፓ ዓባላት ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ማድረጉ እየታወቀ፤ በቅርቡ በፓርላማ ባደረገው ንግግር ግን “ኦዴፓ የማይገባውን የሥልጣን ቦታ ይዟል የሚባል ከሆነ ሥልጣኔን አሁኑኑ እለቃለሁ!” በማለት ሽምጥጥ አድርጎ ክዷል። ይህን ሁሉ ውሸት እየሰሙ የትሕነግ ጡረትኞች በመደመም ሣቃቸው እንዳይወጣ በአንድ እጃቸው አፋቸውን ይዘው በሌላው እጃቸው ደግሞ ልክ ነህ ቀጥል የሚሉ ይመስላሉ።

-//-

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop