July 17, 2019
8 mins read

አፍ ያለው ጤፍ ይቆላል ወይንስ ካልተናገሩ ደጃዝማችነት ይቀራል – በፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው  

ለመሆኑ የህዝባችንን መብት ያፈነውን ወያኔን በምርጫ የረታው የግንቦቱ 1997  የህዝባዊ ትግል ዋና መሪ ቅንጅትን በእኔነት ሽኩቻ ካፈረሱት በላይ የጎዳ በወያኔ ከኬንያ  ተመልምሎ የተላከው ህዝቡ ክህደቱ ወይም ተንሸራታች ያለው ልደቱ አያሌው መሆኑን የ CRDA ምርጫ ታዛቢ ፓስተር ከበደ ደጉ የሰጠውን ተአማኒ ምስክርነት ያልሰማ ከዩቱብ ላይ ፈግሎ ይስማው:: ልደቱ በዚያ የጎደፈ ታሪኩ ሳይወሰን የመለመላቸው ተከታዮች  ሃገር ቤት ሳለ ጸሃፊው ያገኛቸው  የኮሌጅ  ባልደረቦቹ የሚገኙበት በዚያ የትግል ዘመን የወጣቱን ትግል የወያኔ ፓርላማ ሲያጣጣል ታጥቂው ሲያስር በዘግናኝ ሁኔታ ሲገርፍ ሲገድል ከድሃ ህዝብ የተሰበሰበውን ደሞዝ ከመቀበል ውጭ ምን ያህል የህዝቡን ትግል ደግፈው ነበር? ይልቁንስ ከፋፋይ የትግሉ ተሳታፊዎችን በልዩ ልዩ መለያያይ ወያኔ ከከፋፈለበት በተጨማሪ በእድሜ ከ50 በላይና በታች ብለው የአዛውንቶቹን የዳበረ ልምድ ያጣጣሉ ነበሩ::  በመጨረሻም ጡረታ ሲወጡ ስንት የህዝብ ብሶት ማቅረብ የሚገባቸው  አንዱ በሚኖርበት በለገጣፎ አካባቢ የጅብ ጩሀት ረበሸን ብሎ በሚዲያ የተናገር ሲሆን የሚረብሸው የሚዘገንነው የእናት በወያኔ ታጣቂ የተገደለ ልጇ አስክሬን ላይ  ስታለቅስ በወያኔ ኢሰባአዊ ታጣቂ ስትገፈተር ያሰማቸውን የሰቆቅቃ ጩህት እንዳሰሙ ግን የወያኔ አበልና የውጭ ሃገር ጉብኝት ክባካቤ አደንቁሯቸው ነበር:: በዚህ ሁኔታ የከረሙት ጉዶች ጭራሽ ህወአት ብሎ ራሱ ወያኔ በፈጠረው ስም አልጠራውም ብሎ መቀሌ በመሸጉት የወያኔ ግፈኛ ባለስልጣኖች ፊት ተደፍቶ ሲሞግትላቸው የቆየ ሰው ስለኢትዮጲያ ወቅታዊ ጉዳይ ውይይት ትንታኔ ያቅርብ የሚል ሚዲያ  በጣም የወረደ ሆኖብኛል::

በተመሳሳይ መልኩ  የድሮ የወጣቱን ትግል በጀብደኝነት በከተማ የትጥቅ ትግል ብዙዎችን ያስጨርሰው ኢህ አፓ ኣመራሮች የራሳቸውን ትግል ኣጋር መምህር ጌታቸው ማሩን ለስብሰባ ጠርተው ገድለው ክቡር ኣስከሬኑን በአሲድ ያቃጠሉት ኣመራሮች  ክፍሉ ታደሰ ድምጹን ሲያጠፋ ያሬድ ጥበቡ ደመቀ መኮንን ላይ የሰጠው ትንታኔ ስ ህተት መሆኑን  ሲያስተባብል ዛሬም ሌላ የግዝት መግለጫ ውን የሚያስተናግዱ ጉዶችን ሚዲያ ማለት ይከብደኛል :: የወያኔ የዘር ጥላቻ ዋና አራማጅ ሆኖ በሃረር በአርሲ አማሮች ከገደል ይጣሉ ዘንድ ቀስቃሽ የነበረ ታምራት ላይኔ” የእምነት ሰው” መሆኑ  በጎ ሲሆን ዛሬም በእውነተኛ ልብ ያኔ የፈጸመውን ሳይናዘዝ የትግል አጋሩ ቆራጡ አንዳርጋቸው እንደታምራት መስረቅ  እችል ነበር ያለውን ለመለስ ዜናዊ ፓርላማ ስኳር በላሁ ያለው ሰውና መሰሎቹ በመደመሩ መቀላቀል በነፍስም በስጋም መብታቸው ሲሆን ዛሬም ፖለቲካውን ሊዘውሩ መድረክ ሊሰጣቸው አይገባም::

የኦሮሞ ወገናችን  በክፉ ቃል እየተጠራ ለም መሬቱ በባላባቶች መያዙን  የሁሉም ብሄር ዘር በተለይ የአማራ ልጆች የተዋደቁለትን ትግል በመካድ አማራን ጠላት በማደረግ ኢትዮጲያዊነትን የካደው የኦነግ መስራች ሌንጮ ለታ በትግሉ መጀምሪያ ወቅት ከወያኔ ጋር የቀመሩት ህገመንግስት ተብዬ ሃገር አጥፊ መሆኑን ባልደረባው ነጋሲ ጊዳዳ ከማለፋቸው በፊት ሲናዘዙበት ዛሬም ድረስ የሚሟገትለተ ሰው ከትንሿ ኦሮሚያ  ፕሬዚዳንትነት የትልቋ ኢትዮጲያ ሚንስትርነት ይሻለኛል የአሮፓ ብርድ ከሚጠብሰኝ ወደሞቃቷ ኢትዮጲያ መመለስ ይበጀኛል በሚል የህዝቡን ትግል ከግል ጥቅሙ ጋር የሚያነጻጽር ማፈሪያ ሰው እንዴት በዋቢነት በኢትዮጲያን ጉዳይ በበጎ ሊመክር ይጠበቃል?

በሃገራችን በወጣቶቹና በተቀረው ማህበረሰባችን ብርቱ ትግል በፈጣሪ የተገኘውን  በጎ ለውጥ የሚመሩት ዶ/ር አብይና ባልደረቦቻቻቸው  ከሰሞኑ  በጽንፈኞች ጫና ወደእልክ ከገቡበት ይመለሱ ዘንድ በጸሎትም በምክርም  መታገል ሲገባ  ያኔ የወያኔ የማደንዘኛ ፕሮግራሞችን  ማስታወቂያዎችን ይሰሩ የነበሩ ልማታዊ አርቲስት ተብዬዎች ጋዜጠኛ ተብዬዎች እነቴዎድሮስ ጸጋዬ የርእዮቱና መሰሎቹ ዛሬ የለውጡን መሪዎች በተገኘው ቀዳዳ ሲወርፉ ዝም ልበልን?

የራሱን ትዳር ሁለቴ ያፈረሰው የስነመለከት አስተማሪዎቹን ባላ አሻሮ ያለና የወያኔን ህጐወጥ የአስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ በይፋ ይቀጥል ያለ ዶክተር ተብዬው ወዳጄነህ የሃገርና የፖለቲካ ተንታኝ በሆነበት ሃገር እንደ ኣቤ ጉበኛ ኣልወለድም ያሰኛል::

ውድ የሚዲያ  ማህበረሰብ ሆይ ሚዛናዊ እንሁን ሰከን እንበል:: ወዳጄነህ ያለው በአሮጌው የጎሰኝነት አቁማዳ የኢትዮጲያ በጎ አንደነት ወይን ጠጅ አይቀመጥም:: በዚሁም መልክ አሮጌና የተበላሸ ወይን ጠጅ ያላቸው  ክፉ ሰዎች በሙሉ ይቅርታ ንስሃ ሳይስተካክለሉ መድረክ ላይ ሊሰብኩን አይገባም:: ቢያንስ አሳዳጅ የነበረው የመጽሃፍ ቅዱሱ ሳውል ጳውሎስ የወሰደውን  ያህል ወይም የበለጠ የፖለቲክና የመድረክ እረፍት VACATION  ይውሰዱልን በቁስላችን ላይ እንጨት ኣይስደዱብን::

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop