July 17, 2019
16 mins read

ይቅርታ የማስጠየቅ ሱስ – ይሄይስ አእምሮ

ይሄይስ አእምሮ

እንደብሂሉ እውነትም አንዳንድ መጥፎ ጠባይ ሳያስቀብር አይለቅም፡፡ ሕወሓትን የያዘው ግፍ የሠራባቸውን ዜጎች ሣይቀር  ይቅርታ የማስጠየቅ አባዜ ከመነሻው እስከመጨረሻው ሊለቀው አለመቻሉን ስገነዘብ እጅግ ድንቅ ይለኛል፡፡ ያንን መላው የሀገራችን ሕዝብ የሚያውቅለትን የተጨፈኑ ላሞኛችሁ የይቅርታ ማስባል ጅል ዐመሉን አሁንም የሙጥኝ እንዳለ ነው፡፡ “ሞኝ እንዴት ብሎ ይረታል?” ቢሉ “እምቢ ብሎ” ይባላል፡፡ ወያኔም ከዚህም የባሰ ነው፡፡

ሰሞኑን ባሕር ዳርና አዲስ አበባ ላይ ተካሄደ በተባለው እንደኔ ግንዛቤ ፖለቲካዊ ግድያ፣ እንደነሱው እንደ መንግሥቶቹ ደግሞ  “መፈንቅለ መንግሥት” ተብሎ በተለፈፈው ዕልቂት (massacre) ሰበብ አዴፓ ይቅርታ እንዲጠይቅ ወያኔ ምንም ሣታፍር ጠይቃለች፡፡ ለነገሩ ገድላ ስታበቃ ገዳዩን አፋልጉኝ ከምትል ወያኔን ከመሰለች ዐውሬ ድርጅት ደግ ነገር መጠበቅ በተለመደው አገላለጽ ከእባብ ዕንቁላል የርግብ ጫጩት እንደመጠበቅ ያለ የዋህነት ነው፡፡

እጅግ የሚገርመው ደግሞ ወያኔ ይቅርታ ማስጠየቅን እንደፋሽን ትያዘው እንጅ እርሷ ራሷ ግን የይቅርታን ምንነት በፍጹም የማታውቅ መሆኗ ነው፡፡ ወያኔና ይቅርታ ዐይንና ናጫ ናቸው፡፡ ማንንም ይቅርታ ብላ አታውቅም፡፡ “ይቅርታ” የሚባል ቃል በወያኔ መዝገበ ቃላት ከነጭርሱ የለም፡፡ የገዛ ጓዶቿን ሳይቀር አብልታና አጠጥታ በተኙበት የምታርድ ከሣጥናኤልም ዕጥፍ ድርብ ጨካኝ ናት –  ሕወሓትም በሏት ተሓሕት ወይም ትህነግ፡፡ ይህን የመሰለ አስገራሚ  ጠባይ ያላት እስፍኒክስ ፍጡር ናት እንግዲህ ትናንትና ወዲያ ማታ አዴፓን “አመራሮችህ ስለሞቱ፣ ጥቂት አመራሮች ደግሞ ስላልሞታችሁ – ሞታችሁን በጉጉት ስንጠብቅ – ባለመሞታችሁ ምክንያት የተረፋችሁት ትምክህተኛ ኃይሎች ይቅርታ ጠይቁ” ዓይነት አስቂኝ የአቋም መግለጫ ያወጣችው፡፡ ትዝብትንና ምን ይሉኝን መፍራት በወያኔዎች ዘንድ አይታወቅም፡፡ አሥረው የገረፉትን ሰው፣ አሥረው ኢ-ሰብኣዊ ድርጊቶችን የፈጸሙበትን ሰው “የግፍ ግፍ በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ ይቅርታ እንዲጠይቅ ሲያስገድዱት ብዙ ጊዜ ታዝበናል፤ በአሽሙርና በለበጣም ስቀናል፡፡ ያው ሲፈጠሩ ጀምሮ የተጠናወታቸው ባሕርይ ነው ብለን ግን ትተናቸው ነበር፡፡ አሁን በዚህ ሰዓትም አለቦታውና አለሁኔታው ያን የሰለቸና እጅ እጅ ያለ ዐመል ሲደግሙት ግን እነዚህ ሰዎች በርግጥም የተያዙበት በሽታ ለየት ያለ መሆኑን እንረዳለን፡፡ እናዝንላቸዋለንም፡፡ ለታመመ ማዘን ኢትዮጵያዊ በጎ ዕሤት ነውና፡፡ የሚደንቀው ነገር መቀሌ ውስጥ ተሸጉጠውም ይህን ጠባይ አልተውም፡፡ ማንንና ለምን ይቅርታ እንደሚያስጠይቁም አላወቁም፡፡ ከዚህ በላይ ዕብደት ደግሞ የለም፡፡

ሀዘን ላይ ያለን ሰው ከጎኑ ተቀምጠው ሲቻል የዕዝን ይዘው በመምጣት ያስተዛዝኑታል እንጂ “ወንድሞችህን በሞት በመነጠቅህ የኢትዮጵያን ‹ሕዝቦች› ይቅርታ ጠይቅ” ብሎ ማላገጥ  ከአእምሮ ህክምና ጠቢብም ሆነ ከጠበል የመፈወስ አቅም በላይ የሄደ ትልቅ ደዌ ነው፤ በወንድሞቻቸው ላይ ማሾፍ ነውር መሆኑን ሊያውቁ በተገባቸው ነበር፡፡ ግን የማወቂያ ተፈጥሯዊ አካላቸው በዘረኝነትና በጥቅም ምች ተመትቶ ከሥራ ውጪ ሆኗልና ለዚህ አልታደሉም፡፡ እኔ ከምር አፍሬያለሁ፡፡ ጤነኛ ነኝ የሚል ዜጋ ሁሉ  በነዚህ ጉዶች እንደሚያፍር እርግጠኛ ነኝ፡፡ ሀፍረተቢስነታቸው ቅጣ አጣ፤ ይሉኝታቢስነታቸው ለከት አጣ፡፡ ምን እንደሚሻላቸው አላውቅም፡፡ የትግራይ ሕዝብ ከነዚህ ነቀዞች እንዴት ነጻ መውጣት እንደሚችልም አላውቅም፡፡

እንግዲያውስ እንደውነቱ ከሆነ ይቅርታን ቢያውቁ ኖሮ እነሱ ነበሩ በአሁኑ ሰዓት በይቅርታ ፀበል ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ታርቀው የሠሩትን ሁሉ በመናዘዝና በመጸጸት ያፈረሷትን ታላቅ ሀገር በጋራ መገንባት የነበረባቸው፡፡

Who sodomized my fellow citizens because of their ethnic group? Who committed extra judiciary killings for the last 44 years all over Ethiopia? Who mutilated, maimed, mistreated, roasted with oil, toasted with fire, whipped, hanged, defamed, etc. the Amharas because they are Amharas? Who is responsible for the death of millions of Amharas for the simple reason that they were Amhara? Who has designed a political program which states that “chauvinist Amharas” should be eliminated because they are “enemies” of Tigrians? Who sterilized the Amharas with the budget of the so called federal government? Who dismantled Ethiopia with ethnic politics which targeted especially the Amharas? Who looted the nation in general? Who destroyed the history of Ethiopia? …  እንግዲህ ይቅርታ መጠየቅና ከሕዝብ ጋር መታረቅ ያለባቸው እነሱ ወያኔዎቹ መሆን ነበረባቸው፤ እርግጥ ነው ከአማራውም ሆነ ከሌላው ወገን የተባበራቸው በጥቅምና በሆድ የተገዛ ብዙ ዜጋ አልነበረም ማለት አይደለም – አሁን ድረስ አለ፡፡ ለማንኛውም እነዚህ ማፈሪያዎች የሰውን ጩኸት መቀማት ሥራቸው ነውና የማይባል ነገር በማይባልበት ጊዜና ሁኔታ እያሉ ማሳቃቸውን ቀጥለዋል – ቀሽም ድራማ እየተወኑ በሣቅ ሲያስገለፍጡን ዕድሜያቸውን አገባደዱ፡፡ “መጥኔ ለወለደሽ ያገባስ ይፈታሻል” አሉ እመት ተጓዳ፡፡ እውነታቸውን ነው፡፡ ሀፍረትን ባወጣ መቸብቸብ እንደወያኔ ነው፡፡ ከዚያ መሳቀቅና አንገትን በሀፍረት መድፋት ብሎ ነገር አይኖርም፡፡

የነሱን ጨረስኩ፡፡ በዚህች አጋጣሚ ለአርቲስቶቻችን ትንሽ ማሳሰቢያ መስጠት አሰኘኝ፡፡ ወዳጅና ዘመድ አርቲስት ካላችሁ ንገሯቸው፡፡

ከትናንትና ወዲያ ኢቢኤስን ስመለከት አንድ ድራማ ላይ የአርትን መሞት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አንድ ነገር ታዘብኩ፡፡

ልብ አድርጉልኝ፡፡ አንድ ተውኔት ሲጻፍ የራሱ የሆነ የአጻጻፍ ሥልት አለው፡፡ የገጸ ባሕርያት አሳሳል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ መቼት፣ ወዘተ. ትኩረት የሚሰጣቸው ናቸው፡፡ እንደሀገራችን ድራማ ማንም እየተነሣ የሚጫወትበት አይደለም – ኪነ ጥበብ፡፡ በሀገራችን ልክ እንደፖለቲካው ሁሉ ማንም ወለፈንዴ እየገባ ኪነ ጥበቡንም ያጨማልቀዋል፡፡ ዝም ሲባሉ ደግሞ አይዟችሁ የተባሉ ያህል ይባሱኑ ያግማሙታል፡፡ ለነገሩ ተመልካች ካለ ምን በወጣቸው ሥራቸውን ለማሻሻል ጥረት ያድርጉ! ተገልጋይና ተጠቃሚ ካለ ደግሞ ንግዱም ሆነ ሌላው በተለመደው ሸፋፋ ሚዛን እየተለካ መቀጠሉ አይቀርም፡፡ ሀገርን ማጥፋት ለካንስ እንዲህ ቀላል ነው!

በዚያ ባየሁት ድራማ የገጠር ሴቶች በገጠርኛ ቅላጼ ያወራሉ፡፡ አንዷ አሮጊት እንዲህ አለችና ጸሐፌ ተውኔቱን አቀለለችው፡፡ “እኔማ ተፈረሱ አፍ ታልሰማሁ አላምንም!”

ይህ ድራማ በመላዋ ኢትዮጵያ እየተደመጠ ነው ብለን እናስብ፡፡ እንዲያ ከሆነ የኔ አክስቶችና አጎቶች ገጠር ሆነው ይህን የአሮጊቶቹን ወግ እየኮመኮሙ ነው፡፡ የሴቶቹን “የፈረስ አፍ” ከእንግሊዝኛ ፈሊጥ ወዳማርኛ በቀጥታ – ምንም እንኳን ሳይዋዛ – ሲያደምጡ ምን እንደሚገባቸው አስቡ እንግዲህ፡፡ የኢትዮጵያ አርት(ሥነ ጥበብ) ሆይ ወዴት እየሄድሽ ነው!

“From the horse’s mouth…” ሲባል ተሰምቶልኛል፡፡ አጅሬ በቀጥታ ተረጎመና “ከፈረሱ አፍ “ብሎት ቁጭ፡፡ ዱሮስ የወያኔ ግርፍ ትውልድ ጥራዝ ነጠቅ እንጂ ምን የጠለቀ ዕውቀት ሊኖረው! በዚህ ዓይነት “ከመሬት ተነስቶ ነገር ይፈልገኛል” የሚለውን በእንግሊዝኛ ውጣው ቢሉት ያ “አርቲስት” – “Standing from the ground he finds me a thing.”ሊል መሆኑ ነው፡፡ አቤት ሀገር፣ አቤት ትምህርት፣ አቤት አርት፣ አቤት ከያኒ፣ አቤት ድምጻዊ፣ አቤት መምህር፣ አቤት መሃንዲስ፣ አቤት የህክምና ዶክተር፣ አቤት ነርስ፣ አቤት ዳኛ፣ አቤት ፖለቲከኛ….. ተያይዞ ገደል የሆነበት የመጨረሻ ዘመን፡፡ Sorry for my pessimistic view…. Forget not the fact that I am also part of the national madness.

እኔም እንዳቅሚቲ ልተረጉም ነው፡፡ ማን ከማን ያንሳል፡፡ Who minus who?

By our children, please sit down – በልጆቻችን እባክህ ቁጭ በል፡፡(ሰው በአክብሮት ሲነሳልህ)

This sold slave has passed him.  ይህ መሸጦ ባርያ አለፈለት፡፡

By the crucified! በተሰቀለው! (አግራሞትን ለመግለጽ)

Let plant religion destroy you. ተክለ ሃይማኖት ድራሽህን ያጥፉት! (እርግማን)

He doesn’t go; he doesn’t come, he cuts his father. አይሄድ አይመጣ ቁርጥ አባቱን!

Let my mouth be slit for you my lion.  አፌ ቁርጥ ይበልልህ የኔ አንበሣ!

Education is not by one day. Enough for now. ትምህርት በአንድ ቀን አይደለም፤ ለአሁን ይበቃል፡፡

እንዳዘናችሁም እንደተዝናናችሁም በመገመት የዛሬውን ትዝብቴን በዚህ ላይ ልቋጭ፡፡

 

በነገራችን ላይ ይህ ከዚህ በላይ ያቀረብኩት ትርጉም ለቀልድ የቀረበ እንጂ የምር የሚመስለው እንዳይኖር ማሳሰብ እፈልጋለሁ – ጊዜው እኮ አላስተማምን አለ፡፡ ቀለድኩ ስትል ሰው የምርህ እንደሆነ ግንዛቤ ወስዶ የሚበላሽበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነው ያለ – በኢሕአዲግኛ አገላለጽ፡፡ ለዚህ ግን እንደ አቅጣጫ – እንደ ኢሕአዲግ መጠን – ግልጸኝነት ባለው ሁኔታ ሕዝበኝነትን ለማጠንከር እንደ አካሄድ ዴሞክራሲያዊ የትግል መስመርን … ሆ! ከነሱው የባስኩ ኢሕአዲግ ሆኜ አረፍኩት አይደል?

ልዩ ማሳሰቢያ፡- ከተወሰኑ ወራት ወዲህ አማራን ማሳደድ ሆነ ብሎ የተያያዘ ኃይል ያለ ይመስላል፡፡ አማራ እንደዳይኖሰር ራሱን ከምድረ ገጽ ከመጥፋት ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት እንደ ሥጋት የቆጠሩ ኃይሎች የአማራውን ቅስም ለመስበር በተያያዙት ዕኩይ ተግባር የአማራውን ተስፋዎች ከያሉበት መምታትና ማስመታት እንደዋና ሥራ ይዘውታል፡፡ በብዙ ቦታዎች አማራን በገፍ ማሰር እንደጀብድ የሚቆጠር የባለጊዜዎች የቀን ከቀን ተግባር መሆኑን እያስተዋልን ነው፡፡ ይህ አካሄድ ለማንም አያዋጣም፡፡ በመቱት ቁጥር የሚያቆጠቁጥ ባሕር ዛፍ ነው፡፡ አማራም ባሕር ዛፍ ነውና ነገ በምሬት ሊከሰት ለሚችለው የአጸፋ መልስ ንጹሓንን ለጉዳት እንዳትዳርጉ በኢትዮጵያ አምላክ እንማጸናችኋለን፡፡ ይህን አዲስ ዘመቻ በአማራ ላይ የከፈታችሁ ወገኖች ሠይፋችሁን ወደ ሰገባው መልሱ፡፡ ጥፋተኛን በህግ መጠየቅ፣ የወንጀል ተጠርጣሪን ካላንዳች የዘር መድሎ በማስረጃ መክሰስ ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን ለአማራ በመቆማቸው ምክንያት ብቻ እያሳደዱና ምክንያት እየፈጠሩ መግደል የዞረ ድምር አለው፡፡ ያን የዞረ ድምር ደግሞ እውነቴን ነው አትችሉትም፡፡ የማትችሉትን ጦርነት ቆስቁሳችሁ ሕዝብን እርስ በርስ አታባሉ፡፡

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop