May 21, 2019
21 mins read

    “የጥላች ንግግር ህግ ”  – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

” ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ በህግ የምትመራ እና የህግ የበላይነት በሁሉም ዜጋ ላይ የሚተገበርባት ሀገር ከሆነች ፣’ የጥላቻ ንግግርን ‘ የሚከለክል ህግ ያስፈልጋታል፡፡ “
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
“የጥላቻ ንግግር” ማለት ምን ማለት ነው? “ለጥላቻ ንግግር”  የተለያየ ሆኖም ተቀራራቢ ፍቺ ሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት የሰጡታል።
አንዱን የጥላቻ ንግግር ትርጉም እንውሰድ።
‘ የጥላቻ ንግገር ’ “ ሁሉንም ዓይነት በጥላቻ የተሞሉ ማነሳሳቶችን ወይም ሆን ተብለው የሚራገቡ የግጭት ቅስቀሳዎችን ጠቅልሎ የያዘ ሃሰብ ቢሆንም ፣ በጥላቻ ንግግር ተጠቃሎ የጠገለጸ ሰፊ ተርጉም በውስጡ አካቶ የያዘ ነው፡፡
  “የጥላቻ ንግግር“ አሳሳችና አደናጋሪ እውነት የሚመስሉ ሃሳቦችን በውስጡ የያዘ ነው፡፡አንድ የተደራጀና የታወቀ ቡድን ፣ ጎሣ ፣ ዘር ፣ ኃይማኖት በስሜት ግሎ ፣በኃይል ፍንቅሎ ፤ ለጥፋት እንዲነሳ የማድረግ ጉልበት አለው፡፡  እውነት በሚመስል የፈጠራ ሃሰብና ምስልም የተቀነባበረ ነው፡፡ጠብ አጫሪ የሆኑ ፣በጎሳ፣በዘር፣በኃይማኖት፣ወዘተ ላይ ያተኮሩ ለጠብ የሚያበቁ በመርዝ የተለወሱ ሃሰቦች ለቅስቀሳ ይጠቀማል፡፡ የጠበበ ሀገረኝነትን (ብሔርተኝነትን) በማነፀባረቅም “ፊትአውራሪዎቹ እኛ  ነን ፡፡ እናንተ መጤ ናችሁ፡፡“ በማለት ፣ባአናሳዎቹ ላይ ብዙሃኑ ለጥቃት እነዲነሱ ይገፋፋል፡፡ ተጨባጭ ባልሆኑ የፈጠራ ሃሰቦች ሀገሬው የውጪ ሀገር ዜጎችን  እና ሥደተኞችን እንዲጠላ የማደረግ ተግባርንም ያካትታል፡፡ ከረዢም ዓመት በፊት በአካባቢው የሚኖሩ ነገር ግን በቋንቋ ና በባህል የሚለዩ ዜጎችን ፣በቁጥር የሚበልጠው ዜጋ እንዲጠላና እንዲያጠቃቸው የሚስችል የሃሰት ቅሰቀሰም ፣’በጥላቻ ንግግር’ ውስጥ ይጠቃለላል፡፡“ ይለናል፣
  የአውሮፓ የሰብአዊ መብት ፍርድ ቤት ።
’Hate speech‘ as “ all forms of expression which spread ,incite ,promote or justify racial hatred, xenophobia ,antisemitism or other forms of hatred based on intolerance, including intolerance expressed byaggressive nationalism and ethnocentrism,discrimination and hostility towards minorities, migrants and people  of immigrant origin.“
              (The European court of human rights
 የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ፣በ2016 እአአ ፣ዩቲዩብ ፣ፌስ ቡክ፣፣ቲዊተር፣ ከተባበሩት መንግስታት ጋር ፣የጋራ መግባብያ ሰነድ ፈርመዋል፡፡የጥላቻ ንግግርን በገፃቸው ላለማስተናገድ፡፡ የጥላቻ ንግግሮች  (Hate speech) ግን ዛሬም  በነዚህ የማህረሰብ ድረ ገፆች በምስልም ሆነ በድምጽ መስተናገዳቸው አላባራም፡፡(ወድያው ቢያጠፉትም) በተለይም በአፍሪካ፡፡
ከደሃዋ አፍሪካችን ይልቅ፣  አሜሪካም ሆነች የበለፀጉት ምዕራብውያኑ ፣ቻይና ና ሩሲያን ጨምሮ ፣የመቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂው በጃቸው በመሆኑ እና ከድረ ገጾቹ ባለቤቶች ጋር የመደራደር አቅሙ ስላላቸው ፣በእነሱ ሜዳ ላይ እነዚህ የጥላቻ ንግግር ተዋንያኖች እንደልባቸው መፈንጨት እንዳይችሉ አድርገዋል፡፡ የጥላቻ ንግግርን መከልከያ ግልጽ የሆነ ህግም ካወጡ ሰንብተዋል፡፡
   ለምሳሌ አውሮፓውያኑ ከናዚ ጀርመን ሽንፈት በኋላ የህንን ህግ ተግባር ላይ አውለውታል፡፡ይህንን ህግ ለማውጣት ያስገደዳቸውም ፣በዘራቸው ምክንያት ብቻ በአይሁዳዊያን ላይ የደረሰው እጅግ ዘግናኝ የሆነ ጭፍጨፋና ግፍ ነበር፡፡
  የጥላቻ ንግገርን በማንኛውም መልኩ ፣ለመስማትም ሆነ ተፅፎ ለማየት  እንደማይፈልጉና ይህንን በህግ የተከለከለ ተግባርም ፈጽሞ የተገኘም ፣በህግ እነደሚጠየቅና በህጉ የተቀመጠውን ቅጣት እንደሚያገኝ ፣ በዛን ዘመን የጥላቻ ንግግርን ህግ ያወጡ፣ ጀርመን፣ፖላንድ፣ሃነጋሪ፣እና አውስትራሊያ በየህጎቻቸው ደንግገዋል፡፡ (ህጉ ላይ በየጊዜው የተሻሻሉ ሃሰቦች እንደሚጨመረበት ግን መዘንጋት የለበትም፡፡)
   በአህጉረ አፍሪካ ፤የጥላቻ ንግግርን የሚገታ ህግ በግንባር ቀደምትነት  ያወጡት ፣ኬኒያና ደቡብ አፍሪካ ናቸው፡፡
  ዛሬ፣ዛሬ በተለይም በኢትዮጵያ ፣በማህበራዊ ድረ ገፆች በሙሉ ፣በተለይም በፌስ ቡክ ፣አንድ ግለሰብ በተለያዩ የሐሰት ሥሞች በመጠቀም “የሸር ገፁን ከፍቶ” ያሻውን ፣አናዳጅና አገንፋይ ንግግሮችን፤ጽሑፎችን ፣ምስሎችን ወዘተ ።ቢለቅ ፣ማንም ሃይ የሚለው የለም፡፡
   “ የዜግነት ግዴታዬ ነው፡፡ያገባኛል፡፡“ በሚል ሥሜትም ተጀቡኖ (አክቲቪስት ተብሎ) አንዳችም ገንቢ ሃሳብ የማያቀርብ ፣ሁሌም በገፁ ከፋፋይና ጠብ አጫሪ ጹሑፎችን በማውጣት ፣”በለው!ልኩን አሳየው፣” የሚል ሆኖ ቢገኝም ፣እሰከዛሬ “ በቃ! “ ያለው የለም፡፡ በለውጡ ማግስት እጅግ የተለጠጠውና ህግ አለባ የሆነው ተጠያቂነትን የዘነጋ ዴሞክራሲያችንም ፣ በራሰቸው ራሰቸውን ያነገሱ አክቲቪስቶችን ፈጥሮልናል፡፡
   ዴሞክራሲ ማለት እንደሰካራምና እንደ እብድ ፣ጤነኛ የሆኑ ሰዎች ያሻቸውን ፣በየትም ቦታ ና ሥፍራ ይዘባርቁ ፣ይሳደቡ፣ይለፋደዱ፣ማለት ሆኖ ተግኝቷል።ይህ ብቻም አይደለም ፣ “በእኛ ሀገር ዴሞክራሲ  ፣ ጤነኛ የሆኑ ሰዎች እየጨሁ ና  “ቡከን ጦር አውርድ!“ እያሉ፣ በአደባባይ ዱላና ብረት ይዘው ፣ ሰላማዊውን ዜጋ ማስፈራረት የሚችሉበት አውድ ፈጥሮላቸዋል።” ብለን  ፣እስክናምን ድረስ ፣በኢትዮጵያ  አያሌ ድራማዊ የሆነ አሳፋሪ ና አሥፈሪ ተግባር ተፈፅሟል፡፡በሻሸመኔ ፣በጎጃም ፣በቡራዩ ፣በአዲስ አበባ፡፡ወዘተ፡፡ …
   ዛሬም የጥላቻ ንግግሮች በቴሌቪዢን መስኮቶች ከዚህ ና ከዚያ ይወረወራሉ፡፡አንድ ግለሰብ ተነስቶ “በመላ ኢትየጵያ ሰላም የለም ፡፡ “ይላል፡፡ ሌሎችም ይደግሙታል፡፡ይባስ ብሎ ሌላው “በመኪና የትም ክፍለ ሀገር አትንቀሳቀሱም፡፡እኔ ራሴ በአውሮፐላን ነው የመጣሀት፡፡“ ይለናል፡፡ እኛ እኮ ዛላንበሰ ፣ፐዌ፣ጂጂጋ፣ደሎ መና፣አርሲ ሮቤ፣ ሐረር፣ደንቢደሎ፣ቦንጋ፣ጋምቤላ ፣ ጎጃም ና ጎነደር ፡፡ወዘተ፡፡ከክፍለ ሀገር አውቶበስ ተራ ተሳፍረን በዛን ዕለት ተጉዘናል፡፡“ አዲስ አበባ ብቻ ነው ሰላም ያለው፡፡“ እያለ በድፍረት ሲናገር ና በዴሞክራሲ ሥም እጅግ የተለሳለሰውን   የፌደራል መንግሥት ሲያወግዝ ማንም “ተው እንጂ! ምን ታከብዳለህ?“ ያለው የለም፡፡ እንዲህ አይነቱን ጨለምተኛ አስተሳሰብ ማራገብ በራሱ፣ ለዚች ሀገር ሰላም ና ብልፅግና ከቶም  የሚበጅ አይደለም፡፡
   ጨለምተኛ አስተሳሰቦችን የሚንፀባርቁ ንግግሮች ከመናገር ነፃነት አንጻር የሚታዩ ቢሆኑም፣ ለሚሰማቸው የዋህ ሰው የማበጃ ምክንያት ይሆናሉ፡፡ ይህንን በውል የሚገነዘቡት፣ አንድ አንድ የበለፀጉ ሀገራት  ምሁራን ፣ እነሱ ንቃተ ህሊናው በተመነደገ ህብረተሰብ ውስጥ ስለሚኖሩ፣ “የጥላቻ ንግግር አራሱ ጥላቻም ቢሆን ንግግር እስከሆነ ድረስ ህግ ሊወጣለት አይገባም፡፡የሰውን አፍ በህግ መዝጋት ተገቢና ፍትሃዊም አይደለም፡፡” ይሉናል፡፡ይሁን እንጂ ይህ አምክንዮ ለእኛ ሀገር ቀርቶ ለነሱም ሀገር እንደማይሰራ ልቦናቸው አሳምሮ ያውቀዋል፡፡
 አንድን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት ያለውን ግለሰብ ወይም ቡድን ወይም ኃይማኖት ወይም ጎሣ ና ዘር ወይም ሉአላዊ ሀገር ና ህዝብ ለይቶ ፣ በሐሰት ሥሙን ማጥፋትና ፣  በጎሣውና በዘሩ ልዩነት  ብቻ ከሌላው ወገኑ እንዲገለል ና ገፍ እነዲፈጸምበት መቀስቀስ፣ ኃይማኖቱንም ማጠልሸት እንዲሁም ሀገራዊ ስሜቱን ማንቋሸሽ ፣መዘዙ እጅግ አስቀያሚና እንደሶርያና ሱማሊያ ዓይነት ውድመትን የሚያስከትል እነደሆነም አላጡትም ፡፡
   የጥላቻ ንግግር “ደፈይና“ ግልፅና የማያሻማ ነው፡፡ “የጥላቻ ንግግር በጎሳ፣በዘር፣በኃይማኖት፣በፆታዊ ጉዳዮች  ላይ አነጣጥሮ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን ያጠቃል፡፡“
   “ Hate speech attacks a person or group on the basis of race,religion,gender or sexual orientations…“
     ይህ በድርጊት ትላንት በኡጋነዳ በቱትሲ ና ሁቱዎች ተከስቷል፡፡የዘር ግጭቱን ማን በጥላቻ ንግግር እንዳረገበው የታወቀ ነው፡፡በ1994 እኤአ 800,000 (ስምንት መቶ ሺ ) ሰዎች በግፍ እና ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት መገደላቸው ከቶም አይዘነጋም፡፡፡
   በ2007 እኤአ በኬንያ ፐሬዝደንታዊ ምረጫ ወቅት ፣ሃገሪቱ ባሏት ሦሥት ትልልቅ ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት 1100 (አንድ ሺ አንድ መቶ) የዋህ ኬኒያዊን ያለቁት በአንድ የሬድዮ ጣቢያ “የጥላቻ ንግግር “ አባባሽነት ነበር፡፡
   ይህን መሰሉ የየኋች  ድንገተኛ እልቂት ዳግም እንዳይከሰት ነው ፣ኬኒያ የጥላቻ ንግግርን የሚከለክል ህግ ያወጣቸው፡፡
    ሀገራችንም በየቀኑ እየባሰበት የሚሄደውን “የጥላቻ ንግግር ” ለመግታት እና የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የጥላቻ ንግግር መከላከያ ህግ ያስፈልጋታል፡፡
“የጥላቻ ንግግር መከላከያ ና መቆጣጠሪያ ህግ“ ማውጣት ተገቢ ቢሆንም፣ ይህንን ሳይወለጋገድ  በመልካም ቁመና  ተግባራዊ ለማድረግ የሚችሉ ተቋማት ግን በመላ ሀገሪቱ የሉንም፡፡
  በአንዳንድ ክልሎች ያሉ እና በመዲናችንም በአዲስ አበባ ያሉ የቴሌቪዢን ጣቢያዎች ይህንኑ ያሳብቃሉ። በዴሞክራሲ ሥም ፣የዋሁን ህዝብ ወደተሳሰተ አመለካከትና አስተሳሰብ እንዲያዘነብል በዘወትር ፕሮፖጋንዳቸው እየተጫኑት ነው፡፡ጠመንጃ ና የእሥር ቤቱ ቁልፍ ዛሬ በእነሱ እጅ ቢሆንም ነገ በሌላ እጅ መግባቱ አይቀርም። “ጥይት ባይገላቸው ባዮሎጂ አይምራቸውም።”
    በነገራችን ላይ ጥይት ባይገለኝ ከባዮሎጂ አላመልጥም ያሉት የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ መለሥ ዜናዊ ነበሩ።ይህንን ተፈጥሯ እውነት ብቻ ሳይሆን   ኢሕአዴግ የሚባለው ፓርቲ  መበሥበሱን ነፍሳቸውን ይማረውና የፓርቲው ዋና እሰትራቴጂስት   በጥሩ ቋንቋ ገልፀውልን ነበር፡፡ “ቦናፓርቲዝምበፓርቲው ውሥጥ  ተሥፋፍቶል።”በማለት።  ። በወቅቱ የአንድ ቤተሰብን የሀብት ማጋበስ ብቻ አልነበረም ለመጠቆም የሞከሩት ፡ እሳቸውም የተሳተፉበት፣መሰል የቡድን ብዝበዛዎች ፣እና በምዝበራ መበልፀግ መኖራቸውን ነው ፣ለመጠቆም የፈለጉት፡፡
  ዛሬም፣ የቀድመው የፓርቲው መሪና ጠ/ሚ ከተናገሩት የበለጠ ፣ ህዝብ ምን ይልናል ተብሎ የማይታፈርባቸው ቀልዶች እየተቀለዱ ፊልምና ትያትሮች እየተሰሩ ፣ በየቴሌቪዢኑ መስኮት በየቀኑ እየተለቀቀልን ነው፡፡
  ይህ አገር እንደ ማክስ ኦፍ ዞሮ ዓይነት አንድ ቁንፅል ትዕይነት ወይም ፊልም እየተሰራ በሚዲያ ሲቀርብ ዝም የሚባልባት ሀገር ሆኗል፡፡
  ነገሩ እነዲገባችሁ የፊልሙን ታሪክ ልቀንጭብላችሁ፡፡…በማከስ ኦፍ ዞሮ ፊልም ላይ ዋናው ገፀ ባህሪ ዞሮ( አንቶኒዮ ባንድራስ ነው ዞሮን ሆኖ የሚያከትረው) እስርቤት ገብቶ ነበር፡፡ ጠላቱ ደግሞ ይህንን በህዝብ ተወዳጅ የሆነ ጀብደኛ ባለው ከፍተኛ የመንግስት ሥልጣን ተጠቅሞ እሥርቤት ውስጥ እንዳለ  ሊያስገድለው ወደ እስረቤት መጣ፡፡በየክፍሉም እየገባ እሥረኞችን እየቀሰቀሰ ከእናንተ መካከል ዞሮ የሚባል እስረኛ አለ ወይ ብሎ ሲጠይቅ እስረኛው በሙሉ አነድ በአነድ እኔ ዞሮ ነኝ (I am zoro) በማለት ፖሊሶቹን ግራ ሲያጋባ ፖሊሶቹ እሱ ክፍል  ከመምጣታቸው በፊት በሞቱት አንድ ሽማግሌ አሥከሬን ተመስሎ በቃሬዛ ተሸክመዉት  ከአስርቤት ውጪ ወደሚገኝ መቃብር ስፍራ ወስደው እነደነገሩ ጫር፣ጫር አድረገው ቀበረውት ተመለሱ፡፡ ዞሮም እነሱ ከነ ጠባቂቸው ሲመለሱ ከመቃብሩ ፈነቅሎ በመውጣት በቂ ሥልጠና በማድረግ ራሱን እና ህዝቡን ነፃ አወጣ፡፡…
  ሥለጉዳዩ ከዚህ በላይ ማብራራት አየስፈልገኝም፡፡ይሁን እንጂ ማንም በወንጅል የሚጠረጠር ሰው በፍርድቤት እስከልተረጋገጠበት ጊዜ ድረስ “ወንጀለኛ ነው፡፡“ ብዬም ፣ሥሙን ጠርቼ መናገርም በራሱ ወንጅል እንደሆነም እገነዘባለሁ፡፡ግን፣ግን ማንም በመንግስት የሚፈለግ ተጠርጣሪ ፍርድቤት ቀርቦ ራሱን ነፃ ሊያወጣ ይገባዋል፡፡ከዚህ  ባለፈ ፣ “ሁላችንም የኢሕአዴግ አባላት በጥቂትም ሆነ በብዙ ወንጀል ሰርተናል እኛ በልፅገን ብዘሃኑን አደኸይተነዋል…“ የሚል መንፈስ ነገሩ ካለው  አምክንዮው በራሱ ብዙ ያከራክራል፡፡
  ከዚህ ሁሉ ከህግ በላይ የመሆን ግልፅ ተግባር ተነስተን ፣ “የጥላቻን ንግግር በተመለከተ ህግ ማውጣት ፋይዳው ምንድነው? ብለን ለመጠየቅ ግን እንገደዳለን፡፡
  የሆኖ ሆኖ የጥላቻ ህጉ የሚወጣ ከሆነ ፣የጥላቻ ንግግር አድራጊው በፌደራል ደረጃ መጠየቅ ይኖርበታል፡፡ይህም “የዐይነህ ቀለም ደብሮኝ ነው ያሰርኩህ“ ከመባል የድነናል፡፡ምክንያቱም በሃያና ሠላሣ አንቀፅ የተከፋፈለውን ንግግራችንን እና ጽሁፎቻችንን ሁለት አነቀጽ ብቻ አንብበው ና አዳምጠው ፣ ምንም ዓይነት የጥላቻ ንግግርን የማያንፀባርቀውን ፅሑፋችንን እና ንግግራችንን ፣የጥላቻ ንግግር ተናግሯል ወይም ፅፎል ወዘተ፡፡በማለት ሊያጉሏሉን ፣ሊያሰቃዩን አና  እስከወዲያኛው ወደዘብጥያ ሊወረውሩን ይችላሉና!…
 “ የጥላቻ ንግግርን የሚከለክለው ህግ ከወጣ  “፣በሀገርና በህዝብ ላይ ያልተሰበ፣ግልፅና ቅፅበታዊ የሆነ  ውድመት ሊያመጣ የሚችልን ፣ሴጣናዊ ሃሰብ በውስጡ የያዘ ፣ ማንኛውንም ንግግር ና ጽሑፍ ፣ የተቀነባበረ ድምጽ እነዲሁም ድምጽ ና ምስል፣ምልክት፣ የኪነ ጥበብ ውጤት ፣ወዘተ በማንኛው መንገድ ማሰራጨትን የተመለከተ ብቻ  መሆን ይኖርበታል።
  “The restriction is necessary to prevent a clear and present danger of some very serious evil.“

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop