May 13, 2019
16 mins read

” ፍርደ ገምድሉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ !!” – በአቻምየለህ ታምሩ

“የኦሮሞ ብሔርተኞች የሚታገሉት የኦሮሞ አባ ገዳዎች ባለርቱን እያፈለሱና ማንነቱን በኃይል እየቀየሩ እንደ ዋርካ ተስፋፍተው በያዙት ለምለሙ የጋራ አገራች እምብርት ላይ ያበቀሉትን ኦሮምያ የሚባል እባጭ የኦሮሞ አገር ብቻ ለማድረግ ነው። አማራ ደግሞ የሚታግለው መላው የኢትዮጵያ ክፍል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማንነቱ ተከብሮ በእኩልነት የሚኖርበት የጋራ አገር እንዲሆን ነው። ” የሚል መደምደሚያ አንብቤ አልመስልህ ስላለኝ ከሌሎች ጋር ልወያይበት አሰብኩኝ።

በመጀመሪያ ከበጎው የጋራ መነሻ ሃሳብ እንነሳ።

“አማራ የሚታገለው መላው የኢትዮጵያ ክፍል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማንነቱ ተከብሮ በእኩልነት የሚኖርበት የጋራ አገር እንዲሆን ነው።”

ይህ ከባድ ሃቅ ነው። አማራው ሕብረተሰባችን በመላዋ ኢትዮጵያ በየአከባቢው ካሉ ማህበረሰቦች ጋር እንዴት በፍቅር ተከባብሮ መኖር እንዳለበት አውቆ በሰላም ተጋብቶና ተዋልዶ በመኖር ላይ ይገኛል። አቻም የገለጸውን ሃሳብ አማራ በሚለው ቦታ አብን የሚባለውን ፓርቲ ስናስገባበት ትርጉሙ ሙሉ በሙሉ ይቀየራል። እውነትነቱንም ያጣል።

አማራው ኢትዮጵያን የጋራ ሃገር ለማድረግ ሲታገል አንድ ከጉራጌ ማህበረሰብ የተወለደ ኢትዮጵያዊ የፖለትካ መሪ ከባህር ዳር ነዋሪዎች ጋር እንዴት አድርገን ኢትዮጵያችንን የጋራ አገር እንድትሆን እንታገል የሚል ውይይት ለማድረግ ቢመጣ ኢትዮጵያዊነትን ለእኛ መስበክ አቅም የለህም ተብሎ ሊገፋ ወይስ የተወሰኑ የአካሄድ ልዩነቶች ቢኖሩብንም ትልቁ ግባችን “የጋራ አገር” የሚለውን አተልቀን በመያዝ እንኳን ደህና መጣችሁ ተብሎ እንደ ዓላማ ጓድ ልንቀበለው ይገባ ነበር? ከዝህና ከበርካታ ሌሎች ነጥቦች ጋር አያይዘን አብን የተባለው ክልላዊ የፖለትካ ቡድንን የአማራው ነጸ ብራቅ አድርገን ካየነው አማራ የሚታገለው ለጋራ አገር ነው የሚለውን ያበላሽብናል።

ኢትዮጵያን የጋራ አገር የማድረግ ፍላጎቱ ያላቸው 84ቱም ብሄሮች ናቸው እንጂ አማራው ብቻ አይደለም። አቻም በተለይ በአጻጻፍህ ላይ የኦሮሞን ማህበረሰብ በሙሉ በአንድ ቅርጫት ውስጥ ከተህ ከዝህ ከጋራ አገር ከሚለው እሳቤ ያወጣህበት አካሄድ ያለውን እውነት አይገልጽም። ለምን መሰለህ? በኢትዮጵያዊነት ትግል ውስጥ እንኳን ኦሮሞ የሆኑ ወገኖቻችን በቆራጥነት ለጋራ ሃገር የሚታገሉ የኦሮሞ ልጆች አውቃለሁኝ። ዛሬ እነ ዶ/ር አብይ በልባቸው ውስጥ ስላለው ድብቅ ዓላማ ብለህ ልትከራከረኝ ብትችልም በዓለም አደባባይ ላለፉት 27 ዓመታት አንዴም ኢትዮጵያ የምትባል ቃል በኩራት ሳይገለጽባት የዘለቀችውን ሃገራችንን በ 30 ደቂቃ ንግግር ውስጥ 40 ጊዜ ስሟን የሚገልጹ መሪዎችን ከኦሮሞ ማህበረሰብ እያየን ነው።

በረዥሙ ሃተታዬ ውስጥ በፍጹም እንዳይዘነጋብኝ የምፈልገውና አብዛኞቻችን የምንስማማበት የጋራ ሃሳብ ‘ኢትዮጵያን የጋራ አገር” የማድረጉ ሃሳብ ነው። ይህ የአቻም ሃሳብ የእኔም ሃሳብ የብዙዎቻችን እንደሆነ ካልዘነጋን ከዝህ ቀደም በነበረን የታሪክ ዕይታ ወይም የታክቲክ መለያየት ተነስተን ሜዳውን የንትርክ እንድናደርገው አልመኝም። ይልቁንስ ትልቁ ራዕይ ላይ ኣተኩረን የጋራ አገር ለመመስረት ሃላፊነቱን በሙሉ ለአማራው ሕዝብ ልንተወው መታሰብ የለበትም በሚለው ብንመክር?

ለምን የጋራ አገር በአማራው ብቻ ሊገነባ አስፈለገው? አማአኣው ኢትዮጵያ የጋራ አገር መሆን አለባት ሲል ከኦሮሞ ከምባታ አፋር ጉራጌ ወዘተ ጋር ተጣምሮ ኢትዮጵያ ብሎ ቢነሳ ለምን ስህተት ይሆንበታል?

አቻም ኢዜማ ምስረታ ላይ አማሮች ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ኢትዮጵያን የጋራ አገራችን እናድርጋት ብለው መነሳታቸውን በሚገባ ተቃውመህ ጽፈሃል።

ከአማራው ውጪ ያለነው ኢትዮጵያዊያን እንዴት እጃችንን ኣጣምረን ተቀምጠን አመራው ሌሎቻችንን ኣግልሎ የመታገያ ድርጅቱንም በአማራ ስም ብቻ ሰይሞ መላዋን ኢትዮጵያ የጋራ አገር እንዲያደርግልን ተማምነን እንቀመጣለን? በዝህ መልኩ የጋራ አገር ናትና ተቀበሏት የምንባለውን ሃፈራችንን በምን ሂሳብ የጋራ አገር ናት ብለው ሊረከቡን ይችላሉ ተብሎስ ታሰበ?

ወንድሜ አቻም የጋራ አገር የምንገነባው በጋራ መክረን እንጂ በምን ዕዳው አማራው ለብቻው ተደራጅቶ በደሙ የጋራ አገር ሊሰጠን ይችላል? ድሮም አልሆነም ዘንድሮም ሊሆን ኣይችልም።

መላው ኢትዮጵያዊያን በጋራ በመደራጀት የጋራ አገራችንን በእኩልነት ተጠቅመንባት ተከብረንባት አክብረንባት የምንኖርባትን ድሞክራሲያዊት አገር እንገንባ።

Achamyeleh Tamiru ያስነበበን ሙሉ መልዕክት የሚከተለው ነው።

ፍርደ ገምድሉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ

ተንታኝ ነኝ የሚል ሁሉ በያገኘው መድረክ እየወጣ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የአማራና የኦሮሞ ልሂቃን ጫፍና ጫፍ ይዘው እየጎተቱ ዋልታ ረገጥ ያደረጉት አስመስሎ ሲያቀርበው ይውላል። ይገርማ! የኦሮሞ ብሔርተኞች የሚታገሉት የኦሮሞ አባ ገዳዎች ባለርቱን እያፈለሱና ማንነቱን በኃይል እየቀየሩ እንደ ዋርካ ተስፋፍተው በያዙት ለምለሙ የጋራ አገራች እምብርት ላይ ያበቀሉትን ኦሮምያ የሚባል እባጭ የኦሮሞ አገር ብቻ ለማድረግ ነው። አማራ ደግሞ የሚታግለው መላው የኢትዮጵያ ክፍል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማንነቱ ተከብሮ በእኩልነት የሚኖርበት የጋራ አገር እንዲሆን ነው።

በኦሮሞ ብሔርተኞችና በአማራ ልሂቃን መካከል ያለው ልዩነት ምድሩንም ሰማዩንም የኦሮሞ ብቻ ነው በሚሉ አግላዮችና መላው ኢትዮጵያ የጋራችን ነው በሚሉ አካታቾች መካከል ያለ ልዩነት ነው። የኢትዮጵያን ፖለቲካ እንተነትናለን የሚሉ አፍ ነጠቆች ግን መላው ኢትዮጵያ የጋራ አገራችን ነው የሚሉትን አካታች የአማራ ልሂቃንና ሰማዩንም ምድሩንም የኛ ብቻ ነው የሚሉ አግላይ የኦሮሞ ብሔርተኞችን ጠርዝና ጠርዝ ላይ የቆሙ፤ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በመወጠር ወደ ግጭት እንዲያመራ እያደረጉ ያሉ እኩል አጥፊ ኃይሎች አድርገው ይከሷቸዋል። ይህ ግፉዓንንና ግፈኞችን እኩል የማውገዝ ፍርደ ገምድል ብያኔ የጭካኔ አስተሳሰብ ከማለት በስተቀር በሌላ ቃል ሊገልጸው አይችልም።

ለአቅመ ማሰብ የደረሰ ማንም ሰው የአባቶቻችን አገር ኢትዮጵያን በጋራና በእኩልነት የምንኖርባ የሁላችን ርስት ለማድረግ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ተሸክመው የሚታገሉንና ባለርስቱን ከቤቱና ካገሩ እያፈለሉ፤ ሀብትና ንብረቱን እየወረሱ ምድሩንም ሰማዩንም «የኦሮሞ ብቻ» ለማድረግ አገር ለመመስረት የፈጠሩትን አርማና ቆራጣ ካርታ አንጠልጥለው ሲዞሩ የሚውሉ ናዚዎችን በእኩል ሚዛን ሊያስቀምጥና እኩል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግሮች አድርጎ ሊያቀርባቸው አይችልም።

የኢትዮጵያ ብቸኛው ችግር የኦሮሞ ብሔርተኞች ናዚያዊና የትግራይ ብሔርተኞች ፋሽስታዊ ፖለቲካ ነው። አካፋውን አካፋ፤ ዶማውን ዶማ ለማለት የማይደፍሩ ተንታኝ ነን ባዮቻችን ግን ሰውን ከርስቱ እያፈለሱ ሰማዩንም ምድሩንም የኦሮሞ ብቻ ለማድረግ ቆራጣ ካርታ ይዘው የሚዞሩን ናዚዎች ፖለቲካ ሕጋዊ ለማድረግ [legtimacy ለመስጠት] ምናባዊ የአማራ ጽንፍ ፈጥረውላቸው false equivalce ሲሰሩ ይውላሉ።

ኢትዮጵያ የጋራ አገራችን ናት፤ ውስጣቸው የሌለችዋን ኢትዮጵያ እንመራለን የሚሉ የመንደር ብሔርተኞች ለኢትዮጵያ መንበረ መንግሥት አይመጥኑም፤ ዜጎች በአገራቸው እየኖሩ አገርህ ሂድ ተብለው መፈናቀላቸው ይቁም፤ አፓርታይድን ተቋማዊ ያደረጉት የጎሳ ክልሎች ይፍረሱ፣ ሕገ መንግሥት ተብዮው የቅሚያና የዘረፋ ደንብ ይሻር፣ ወዘተ የሚሉት ሰብዓዊና ፍትሐዊ ጥያቄዎች እንደ ግፍ ካልተቆጠሩ በስተቀር የአማራ ልሒቃን የሚያራምዱት አካታች ፖለቲካ የአግላዩ የኦሮሞ ብሔርተኞች ሌላ ጽንፍ ሊሆን አይችልም።

ስለሆነም ከፍርደ ገምድሉ የኢትዮጵያ ተንታኞች እይታ በስተቀር ኢትዮጵያ ምድር ላይ የአማራና የኦሮሞ የሚባል ፖለቲካ የለም! ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፖለቲካ ምድሩንም ሰማዩንም ኬኛ የሚሉ ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኞች የሚያራምዱት ናዚያዊ ፖለቲካና አማራውና ሌላው ኢትዮጵያዊ የተካተተበት ሁሉንም የኢትዮጵያ የማኅበረሰብ ክፍል የመላው ኢትዮጵያ ባለበት ለማድረግ የሚካሄድ ትግል ብቻ ነው። የኦሮሞ ብሔርተኞችን የወንጀል ፖለቲካ ቅቡል ለማድረግ በምናብ የተፈጠረው አይነት ሌላ ጽንፍ ላይ የቆመው አግላይ የአማራ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ውውጥ የለም። የአማራ ልሂቃን የሚታገሉ ኢትዮጵያ የሁሉም የፍትሕ አገር እንድትሆን እንጂ እንደ ኦሮሞ ብሔርተኞች አንዱ ብቻ ተለይቶ ባለቤት የሚሆንባት የግፍ ምድር እንድትሆን አይደለም።

«ኢትዮጵያ የጋራችን» የሚሉትን የአማራ ልሒቃንና ምድሩንም ሰማዩንም «ኬኛ» የሚሉት የኦሮሞ ብሔርተኞች ሁሉት ተቃራኒ ጫፎች አድርገው የሚያስቀምጡ ተንታኞች ግን እነሱ ኢትዮጵያውያን ማዕከል ያደረገ ብለው የሚያስቡት ፖለቲካ ምን አይነት ይሆን? ኢትዮጵያን የጋራ አገራችን ናት ብሎ ማሰብስ እንዴት ሆኖ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ማተባቸውን ከበጠሱ የኦሮሞ ብሔርተኞች እኩል ጽንፈኛት ይሆናል? ለጋራ አብሮነት የሚተጉት የአማራ ልሒቃን ለልዩነት የማይወዳጁት የኢትዮጵያ ጠላት ከሌላቸው የኦሮሞ ብሔርተኞች እኩል እኩል ስጋቶች ሊሆኑ ይችላሉ? ኢትዮጵያዊ ሆኖ ለመኖር የቆረጠስ አካታቹ የአማራ ልሒቃን ፖለቲካ ከአግላዩ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እኩል እንዴት ስጋት ሊሆንበት ይችላል?

እንደ እውነቱ ከሆነ ምድሩንም ሰማዩንም «የኦሮሞ ብቻ ነው» የሚለውን ናዚያዊ እሳቤ ማዕከል ያደረገውን የኦሮሞ ብሕርተኞች ፖለቲካ «ኢትዮጵያ የጋራ አገራችን ናት» የሚለውን የአማራ ሊሒቃን አካታች ፖለቲካ ሌላ ጽንፍ አድርጎ ለማቅረብ መሞከር ለእኩልነትና ለጋራ አብሮነት እየታገሉ ያሉትን ሁሉ በማሸማቀቅ ሰማዩንም ምድሩንም ኬኛ የሚሉ ወሮበሎችን ከማፈርጠሙና አቻ አግኝተናል ብለው ናዚያዊ ፖለቲካቸውን የበለጠ እንዲገፉበት ከማድረግ የዘለለ ፋይዳ የለውም!

https://youtu.be/1Skp2UtnFjs

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop