April 9, 2019
15 mins read

ለ‹ፋታ› ንፉግ የሆነው ፖለቲካችን  (አብርሃም አየለ)

የ1966 ዓ.ም. ለውጥን ተከትሎ አገሪቱን በጠቅላይ ሚንስትርነት ይመሩ የነበሩት ክቡር ፀሐፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃ/ወልድ ስልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ በልጅ እንዳላካቸው መኰንን መተካተቸው ከአርባ አራት ዓመት በፊት የነበረው ትውስታ ነው፡፡ የተተኩት አዲሱ ጠቅላይ ሚ/ር ስልጣናቸውን እንደያዙና በቅጡም ሳይደላደሉ – ከግራ፣ ከቀኝ፣ ከኋላና ከፊት የተከተለው ተቃውሞና ሰላማዊ ሰልፍ አገሪቱን አረጋግተው አስተዳደራዊ አሰራራቸውን ለመዘርጋት ሁኔታዎች አልተመቻቹላቸውም ነበር፡፡ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ለመወጣት፤ እንዲሁም ሕዝቡም ሆነ አገሪቱ የሚፈልጉትን ለውጥ ለማምጣት ‹ፋታ› እንዲሰጣቸው ተቃዋሚዎቻቸውን አበክረው ይጠይቃሉ፡፡ ከጊዜም በኋላ ‹ፋታ› የሚለው ቃል የፖለቲካ ስላቅ ከመሆን አላለፈም እንጂ፡፡

 

እንዳልካቸውን የሚሰማቸው አላገኙም፡፡ የተቃውሞው አድማስ እየሰፋ በተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ቀጠለ፡፡ ለዚህም ተቃውሞ ኢሐአፓ፣ መኢሶንና ሌሎችም የተቃዋሚ ቡድኖች በተቀጣጠለው ተቃውሞ ላይ ቤንዜን በመጨመር አጋጋሉት፡፡ ነገሩ ያላማረውና አመጣጡም ሆነ አመላካች ግቡ መልካም ሆኖ ያላታየው እውቁ ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ዋና አዘጋጅ በሆነበት አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ‹ማንም እየተነሳ ቱግ ማለቱን ትቶ አርፎ ስራውን ይስራ› የሚል አስተያየት ሰነዘረ፡፡ ከዚህ ሀሳብ በተፃራሪ የቆሙት የወቅቱ ‹ተራማጆች› ጋዜጠኛው የሰጠውን ምክር አዘል አስተያየት በማጣጣል ‹እርስዎንና መሰሎችዎን ያስደንግጥ እንጂ ..›በሚል ሀተታ የተያዘው የለውጥ ሂደት የዘመናት የትግል ውጤት እንደመሆኑ እየተጋጋለ እንደሚቀጥል በተለመደው በራሪ ወረቀት ይገልጻሉ፡፡ ፋታ የጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስተር ጥያቄያቸው ሰሚ  ባለማግኘቱ ‹የዘመናት  የትግል ውጤት› የሆነው መንፈስ አሸንፎ እሳቸውም እስር ቤት ይገባሉ፡፡ ከዚያም የሆነውና የምናውቀው ሆነ፡፡

 

ነገሩን ለማሳጠር የዚሁ እንቅስቃሴ ድምር ‹ደርግ› የሚባለወን ዲያቢሎሳዊ ስብስብ ለስልጣን አበቃ፡፡ በዚሁ ስብስብ የተገደሉትን የሁለቱን ሊቀ መናብርት ማለትም የሌ/ጀነራል አማንና የብ/ጀነራል ተፈሪ ባንቲን የስልጣን ዘመን በመቀነስ ቀሪውን የደርገ ቆይታ ሌ/ኰሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማሪያም ደርግ ወደ መቃብር እስከተሸኘበት ድረስ ፈነጩበት፡፡ ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታ የማታውቀውን የእርስ በርስ እልቂት በመሪ ተዋናይነትም አስተናገዱ፡፡ ጨካኙ መንግሥቱ በጭፍጨፋቸው የቀራቸው የህብረተሰብ አካል አልነበረም፡፡ ሕፃኑ፣ ወጣቱ፣ ጎለምሳው፣ ተማሪው፣ ወታደሩ ሰራተኛው ፆታና እድሜ ሳይለዩ ፈጁት፡፡ ለስልጣናቸው ማብቃትና ለሳቸውም አገር ጥሎ መፈርጠጥ ዋናውና አንኳር ምክንያት ይሄው ገደብ የለሽ ግድያቸው እንደሆነ ምንም አያጠራጥርም፡፡

 

‹ፋታ› ወደተነፈጉት ጠቅላይ  ሚ/ር እንዳልካቸው  መኰንን እንመለስ፡፡ በወቅቱ እኝህ ሰው በነበራቸው የትምህርትና የሥራ ተሞክሮ ሁኔታዎች ተመቻችቶላቸው ስራቸውን ቀጥለው ቢሆን ኖሮ – የነጭና ቀይ ሽብር ተብሎ ስም የወጣለት እልቂት ይካሄድ ነበር? ከኤርትራ ጋር የተካሄደውና ለብዙ ወገኖች (ኢትዮጵያም ኤርትራም) እለቂትና ለአገራቱም መድህን ሊሆን ይችል የነበረው የኤኮኖሚ ውድመት ይፈፀም ነበር? ለዚች ደሃ አገር በተለያየ መልኩ ቤዜ ሊሆኑ ይችሉ የነበሩት የጦርና የሲቪል ባለስልጣናት እንዲሁም ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ይገደሉ ነበር? በአጠቃላይ ለማስቀመጥ በሌ/ኰሎኔል መንግሥቱ ዘመነ መንግሥት የተካሄዱት ሌሎች ሰባአዊና ቁሳዊ ውድመቶች ተግባራዊ የማይሆኑበት እድል የሰፋ እንደነበር መገመት ይቻላል፡፡

 

አገራችን ወደአለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ስንመለስ፤ ወጣቱና አንደበተ ርትዕ ጠቅላይ ሚኒስትር ጅማሯቸው መልካም ነው፡፡ በሂደት ሊያሻሽሎቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንዳሉ ይታመናል፡፡ ሆኖም፤ በአጭሩ የስልጣን ዘመናቸው ብዙ አመርቂና አስደናቂ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡ ይህንኑ በአጭር ለመግለጽ፤ በሕይወት እናገኛቸዋለን ብለን ያላሰብነውን የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ በጦርነት ፍጥጫ የነበሩትን ኤርትራንና ኢትዮጵያን ሰላም እንዲያሰፍኑ፣ በተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ሰባዐዊ መብታቸው ተጠሶ በአሰቃቂ ሁኔታ ይገኙ የነበሩ ወገኖቻችንን ከራሳቸው ጋር ይዞ በመምጣትና ከዚያም ህጋዊ በሆነ መልኩ መብታቸው እንዲጠበቅ ማድረግ፣ ሎሌች ሌሎችንም አድርገዋል፡፡ እኝህን መሪ ከማደንቅበት እንዱ ምናልባትም ዋናው ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን የሰጡትን ክብር ነው፡፡ ባለፉት አርባ ያህል ዓመታት የኖርንበት ድባብ፤ ቀይ ሽብር፣ ነጻ እርምጃ፣ እጅ ይቆረጣል፣ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል፣ ወዘተ እየተባልን የኖርን ዜጎች ዛሬ አገራችንና  ሕዝቧን ከፍ ከፍ የሚያደርግ መሪ ስናገኝ የፈጣሪ ፀጋ ነው ከማለት ውጭ ሌላ ምን ማለት ይቻላል?  አገራችን ሰላም የሰፈነባት ሆና ለዘመናት በማኅበራዊ ኑሯችን፣ በኤኮኖሚና በፖለቲካውም ምህዳር የተረጋጋች እንድትሆን ይህንን እድል በአግባቡና በሰከነ ሁኔታ ልንከባከበው ይገባል፡፡ ይህንንም ስናደርግ አግባብ በሆነና በሰለጠነ መንገድ አስተያየት በመስጠት መሆን እንዳለበት በማመን ነው፡፡

 

ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን ሲመጡ የተረከቧት አገር፤ በሚያሳዝን ሙስና የተዘረፈች፣ በሚያሰቅቅ ሁኔታ የሕዝቡ ሰባዓዊ መብት የተጣሰበት፣ ስልታዊ በሆነ መንገድ ሕዝቡ  በዘርና በጎሳ እንዲከፋፈል የተደረገበት፣ የውጭ ምንዛሪም ሆነ የአገሪቱ የፋይናንስ አቋም የተመናመነበት ምናልባትም የተሟጠጠበት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በሜቴክ፣ በሕዳሴው ግድብ፣ በልማት ባንክ፣ ባልተገለፀው ኤፈርትና በሌሎችም የደረሰውን ዝርፊያ ስንመለከት አገሪቱ አገር ሆና መቀጠሏም የሚገርም ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ይህን በመሰለ አቋም የምትገኝን አገር እንኳን በአንድ ዓመት ከዚህ በኋላ በሚገኙ ብዙ ጊዜያትም አንኳን ማስተካከል ከተቻለ የሚደነቅ ይሆናል፡፡

 

በተለያዩ  የአገራችን አካባቢዎች የመፈናቀልና የጦርነት ችግሮች አሉ፡፡ ይህም ለሃያ ሰባት ዓመታት የተዘራው የተንኮል አዝመራ ውጤት ለመሆኑ አማኝ መቁጠር አስፈላጊ አይሆንም፡፡ ይህን ከመሰለው እኩይ ሰቆቃ ለመታደግ የምንወስዳቸው ርምጃዎችና የምንሰጣቸው አስተያየቶች እንዲሁም ምክር የሰከነና በጥበብ የታጀበ መሆን ይኖርበታል፡፡

 

የሶሻል ሚዲያውን ለጊዜው ወደ ጎን በማለት (በዚህ መድረክ ላይ የሚሳተፉት በአብዛኛው የአገራችንን ሰላም የማይፈልጉ ምንደኞች በመሆናቸው) አንዳንድ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችና የግል ጋዜጦች/መጽሔቶች ላይ ወቅታዊ ሁኔታችን ባላገናዘበ መልኩ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በአስተዳደራቸው ላይ የሚሰነዝሩት አንዳንድ አስተያየትቶች ከመስመር የወጡ ሆነው አግኝቼቻዋለሁ፡፡ የኢሳት የተወሰኑ ጋዜጠኞች የሚወረውሯቸው ቃላትና አስተያየቶች – ምን ነካቸው? ያሰኛል፡፡ አሁን አሁንማ ብዙ የኢሳት ወዳጆች የነበሩ ወዳጆቼ ‹አይ ኢሳት በቃኝ› ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ የጣቢያው አስተዳደርም በዚህ ጉዳይ ላይ ለህልውናው  መቀጠል ሊያስብበት ይገባል፡፡ አቶ ኤርምያስ ለገሰ ጠቅላይ ሚንስትሩ የኢንሳ ባልደረባ በነበሩበት ወቅት ይህን አደረጉ፣ ይህን ፈጸሙ እያለ ብዙ ለመናገረ ያደረገው ሙከራ አግራሞት ጭሮብኛል፡፡ የግለሰቡ አነጋገርና የሰውነት እንቅስቃሴ ሀሳብ የሚሰነዝር ብቻ ሳይሆን የተለየ ተልእኮ ያለው ያስመስላል፡፡ እንዲያው ነገርን ነገር  ያነሳዋልና ያገለገለወን ኢሕአዴግን ከመክዳቱ በፊት ራሱ በጻፈው ‹የመለስ ትሩፋት› ገጽ I ላይ ‹በኢሐዴግ የፖለቲካ ጎዳና በአባልነት፣ በመካከለኛና ከፍተኛ ካድሬነት ከ12 ዓመታት በላይ አገልግሏል› በሚል ተገልጾል፡፡ እንግዲህ ኢሕአዴግን ስናውቀው ካድሬ ማለትም ምን ማለት እንደሆና የአርባ ዓመታት ተሞክሯችን እንደሚነግረን አቶ ኤርምያስ በእነዚህ ጊዜያት ለኢትዮጵያ  ሕዝብ እርጥብ ቄጤማ እንዳላነጠፈለት የምንገነዘብ ይመስለኛል፡፡ ‹በሌላው ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ …..› እንዲል መጽሐፉ መጀመሪያ ራስንም መመርመር ጠቃሚ ይሆናል፤፤

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉበት ሁኔታ፤ የገናውን ዳቦ ያስታውሰኛል፡፡ የታወቁት ጠላቶቻቸው የማይሸርቡት ተንኮልና ሴራ የለም፡፡ ሊደግፎቸው የሚገቡት ደግሞ እንዲሁ የሆነውንም ያልሆነውንም እያነሱ ችግር አብቃዮች ሆነዋል፡፡ ለእኝህ ሰው በተቻለ መጠን ድጋፋችንን ሳናቋርጥ፤  አስፈላጊና ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አስተያየት/ምክር እየሰጠን ወደቀናው መንገድ በጋራ ብንጓዝ አገራችንንም ወገናችንንም እንጠቅማለን፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ስልጣን በተረከቡበት እለት ከአደረጉት ንግግር የሚከተለውን በመጥቀስ ልሰናበት፤

 

‹በታሪካችን በተለያዩ አጋጣሚዎች አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ የመጀመር እድሎችን አግኝተን ብዙዎቹን በወጉ ሳንጠቀምባቸው አምልጠውናል፡፡ አሁንም፣ ይህ የስልጣን ሽግግር አዲስ ምዕራፍ የምንጀምርበት ሌላ ታሪካዊ እድል ነው፡፡ በመሆኑም በከፍተኛ ስሜት ልንጠቀምበት ይገባል‹

[email protected]

 

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop