ዛሬ በአየሁት ጉዳይ ዶ/ር አብይ አሳዝኖኛል፡፡ ለማንኛውም ጊዜ እንስጠው ላላችሁ ጊዜ መስጠቱን አጥተንበት ሳይሆን በጊዜው ወሳኝ ነገሮችን መሥራት ስለሚጠበቅ ነው፡፡ ለነገሩ እኔ ብሆን ምን አደርግ ነበር በሚለው እሳቤ ማሰቡ ሳይቀለኝ አይቀርም፡፡ ምክነያቱም እንዲደረግልኝ የምፈልገውን ከሆነ እኔ ራሴም ብሆን ማድረግ እችል ነበር ወይ የሚለውን ሳስብ ነው እስኪ እኔ ማድረግ ይቻላል ብዬ የሚከተሉትን ነጥቦች አብይ ማስተላለፍ የፈለኩት፡፡
- በመጀመሪያ ቀን አብይ የተናገረው የራሱ እምነትና አላማ ከሆነ እሱኑ መከተል ብችል ጥሩ ነው፡፡ በዚህ ሀሳቡ ብዙዎች ተስማምተው አወድሰውት እንደነበር አይተናል፡፡ እኔም ጥሩ ነው ከሚሉት ነኝ፡፡
- ሕዝብን መጎብኘቱ መልካም፣ ከቻለ ሁሉንም በቋንቋው ማናገር ቢችል መልካም ግን አላስፈላጊ ነገሮችን ከመናገር ብት ቢቆጠብ፡፡ በተጓዘባቸው ቦታዎች ሁሉን የሚያስደስት ነገርን ባይናገርም፣ የመቀሌው ጉዞውን ተከትሎ ግን ብዙዎችን ያስቀየመ መሰለኝ፡፡ መቀሌ ለምን ሄደ አደለም፡፡ በትግርኛ ለምን ተናገረ ብለውም የከፋቸው አሉ፡፡ በእኔ አተያይ ይሄ ያው ዘረኝነት የፈጠረብን ልክፍት እንጂ ቢችልስ ሁሉንም በቋንቋው ቢያናገር ጥሩ ነበር፡፡ ጂግጂጋ ሄዶ ሰላምታ በሶማሊኛ መስጠቱ በራሱ ትልቅ ሊያስመሰግነው የሚገባ ነው፡፡ የፌደራል ቋንቋ መጠቀም አለበት ብለውም ሕጋዊ ሊያስመስሉት የሞከሩ አሉ፡፡ ሊውም ሕገ መንግስት የተባለውን የመለስን ድርሰት ጠቅሰው፡፡ የዚህ ሕገ-መንግስት ተብዬ የጥንቆላ ሰነድ ጉዳይ ብዙ ሴራዎችን እንደ ሰነደ ብዙ ጊዜ ተናግሬያለሁ፡፡ የሆነ ሆኖ ግን አብይን በቋንቋ ችሎታው ከማድነቄም በላይ ሕዝቦቹን (የሚመራቸውን) በየቋንቋቸው በቻለው ያህል ማናገር መሞከሩ እጅግ የሚያስከብረውና የሚያስወድደው ነው ከዘረኞች በቀር፡፡ የመቀሌው ጉዙዎ ችግሩ መነሻው ሁለት ይመሰልኛል አንድኛው ትግራይ የወያኔ መንፈስ የሰፈነበር በመሆኑ፣ ታዳሚዎቹም ተመርጠው በሚመስል መልኩ ካድሬ የሚመስሉ በመሆናቸው አጠቃላይ የውይይቱን ሂደትና ገጽታ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን በተለየ የትግራይ ሕዝብ ሌላ ፍላጎት እንዳለው አስመስሏል፡፡ በዛ ውይይት ከተሰበሰቡት ይነሱ የነበሩ ጉዳዮች በሌሎች ቦታዎች በአሁኑ ወቅት ከሚነሳው አንጻር ቅንጦት አስመስሏል፡፡ ለምሳሌ ተሰብሳቢዎቹ ከአነሷቸው አንዱ ሌሎች ቦታ ችግር ላይ ናቸው ያሏቸውን ትግሬዎች ነው፡፡ በመላ አገሪቱ ግን ችግር ፈጣሪዎች ለወያኔ በስለላና በተለያዩ እቅድ አስፈጻመነጽ የተሰማሩ ትግሬዎች እንሆኑ ነው ሕዝብ እያየም እየተገነዘበም ያለው፡፡ ይህ ትግራይ ላለው ሙሉ በሙሉ አይገባውም ማለት አይቻልም፡፡ ያም ሆኖ ስንት ኦሮሞ፣ ስንት አማራ ሌላውም ምን ያህል በእስር፣ በስደት፣ አልፎም እንደሚገደል ያውቃሉ፡፡ ቢያንስ ከእስር የሚፈታውን ሕዝብ ብዛት በዜና ይሰማሉ፡፡ ኦሮሚያ በዚህ አመት ብቻ በ10ሺዎች ነው ከእስር የተለቀቁት፡፡ ገና ብዙ በተለያዩ ቦታዎች እንዳሉም ይነገራል፡፡ በሌሎችም ቦታ እንደዛው ነው፡፡ ይሄ ሁሉ የሆነው በትግሬ ወያኔዎች ነው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በፊት ጀምሮ በኦሮሚያ አንዳንድ በገሀድ በሕዝብ ላይ ትልልቅ እልቂትን ለማድረግ የተሰማሩ ትግሬዎችን የኦሮሚያ መንግስት ፖሊስ መያዙና ማሰሩን ትግሬዎች እንዴት ተደፈርን አይነት ጩኸት ያሰማሉ፡፡ ዛሬ ሌላው ሕዝብ ትግሬን በእርግጠም እያየ ያለው በጥሩ አይን አደለም፡፡ ይህ ግን የሌሎቹ ሕዝቦች ችግር ሳይሆን የትግሬዎቹ የእኛ ብለው ከአመኑበት አረመኔና ወንበዴ ከሆነው ወያኔ ቡድን ጋር በአጋርነት በመስራት ለሕዝብ ጠላት መሆናቸው ነው፡፡ ትግሬ ከጥንትም ጀምሮ ከሌላው ሕዝብ ጋር ይኖራል፡፡ በወያኔ ዘመን ግን ሁሉንም አጥፍተን እኛ ብቻ እንኑር ስላሉ ነው፡፡ ይሄን ያለአንዳች ይሉኝታ ሲያደርጉት ኖረዋል ዛሬም አይን አውጥተው የሚናገሩት ይሄንኑ ነው፡፡ ትግራይ የሚኖረው ትግሬ የዚህን ያህል እንደሆነ ላይረዳ ይችል ይሆናል፡፡ ካድሬዎቹ ግን አሳምረው ያውቁታል፡፡ እንግዲህ በዚህ ልክ ወንጀል በየቦታው የሚሰሩ ትግሬዎች በበዙባት አገር ኦሮሚያ በተባለው ሰፊ ክልል 11 ብቻ ሲታሰሩ አሮሞ ግን አሁንም በአስር ምን አልባትም በመቶ ሺዎች በአሳቃቂ ሁኔታ በእስር ቤት ይማቅቃል፡፡ ሌላውም እንደዛው ነው፡፡ ይህን አብይ ለማስታምም ከመሞከር ሁኔታዎን በግልጽ መናገር አለመቻሉ ለብዙዎች አስከፍቷል፡፡
- ሌላው ወንበዴው ወያኔ ሰማዕቶቼ የሚላቸውን የኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ቀንደኛ ጠላቶች ሆነው ሳለ ጭራሽ ሁሉም በሰማዕትነታቸው እንዲቀበል 27 ዓመት አስገድዷል፡፡ ይሄው ሁኔታ የሰማዕታት በሚል በተገነባው ሀውልት አበባ ጉንጉን ከማስቀመጥ ጀምሮ፣ በውይይት ወቅት በመቶ ሺዎች ገብረናል ስለዚህ እኛ ልንከበር ይገባል ከሚሉ ተሰብሳቢዎች እስከ በመጨረሻ ለዶ/ር አብይ የተበረከተለት ስጦታ ብዙዎችን የሚያናድድ ነው፡፡ አበባ ጉንጉን ማስቀመጡንና ስጦታን መቀበሉን ዶ/ር አብይ እምቢ ማለት በሚችልበት ሁኔታ አደለም፡፡ እንግዳም፣ መሪም ነኝ ብሎ ሄዷልና፡፡ በውይይቱ ወቅት ግን በመቶ ሺዎች ገብረን ያመጣንውን ነጻነት ብለው ለፎከሩት የአብይ መልስ ሙሉውን አልሰማሁም፡፡ ከዚህ ንግግር ጋር ግን እነደ መልስ የመሰለው ጭራሽ የወልቀይቱ ጉዳይ መስሎ ነው የታየኝ፡፡ ሰውዬው(ፎካሪው) ሲያነሳ ከነበረው አንዱ የወልቀይት ጉዳይ ነበርና፡፡ እዚህ ጋር አብይ ሰውዬውን በንግግሩ ከመገሰጽ ጀምሮ ቀጥሎ በሚያደርጉት አግባብ በአለው መልስ የትግራይንም ሕዝብ ሌላውንም የሚያስደስት ነገርን መናገር ይችላልና፡፡ አበባ ጉንጉኑንም ቢያስቀምጡ፣ ስጦታውንም ቢቀበሉ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ እነዛ ሞቱ የተባሉ ወያኔ ሰማዕት የምትላቸውን ወንበዴዎች የሚያያቸው እንደጠላት ሊያውም አገርንና ሕዝብን ያፈረሱ እንጂ እንደ ሰማዕት አደለም፡፡ ከእነዛ የተረፉት ይሄው 27 ዓመት እኮ አየናቸው በተግባር የተሰማሩበትን ውንብድናና አረመኔነት፡፡ ዶ/ር አብይም ይህን ያውቀል፡፡ ከልቡ ለዚህ እውቅና እየሰጠ ከሆነ ከኢትዮጵያ ጠላት ጋር እንደተባበረ ይቆጠራልና፡፡ እንደ ስልት ግን ማድረጉን የሚያረጋግጥልን ከሆነ መልካም ነው፡፡
አብይ በጎንደሩ ጉዞው ለሕዝብ በአደረገው ንግግሩ ፊቱ ላይ የሚነበበው ጥሩ ያልሆነ ሥሜት ነበር፡፡ ጎንደሬዎቹ እንደተቀየሙት ገብቶታል፡፡ ይሄንኑም ተናግሮታል፡፡ ወድጄለታለሁ፡፡ ጃኖ የለበሰውም ለእነሱ ሲል ይመስላል፡፡ የሆነ ሆኖ ግን በተወሰንም ቢሆን ከወልቃይቶች ጋር እንዲህ መነጋገሩ ጥሩ ይመስላል፡፡ የወልቃይት ሕዝብ ጉዳይ ማንም ሰው ከሚጠይቀው መብት በላይ ነው፡፡ የገዛ አገራቸውን በግድ ተነጥቀው እየደረሰባቸው ያለው በደል እጅግ የከፋ ነው፡፡ ትግሬ ወያኔ ከተፈጠረ ጀምሮ ግፍ ሲያደርስበት የነበረ ሕዝብ ነው፡፡ በእርግጥም በመቀሌው የአብይ ንግግር አዝነው ነበር፡፡
አብይ ከወያኔ ይልቅ ከሕዝብ ጋር ቢሆን ሚሊዮኖች ናቸው የሚደግፉት፡፡ አሁን ላይ በተግባር ምን እየሰራ እንደሆነ ግልጽ አልሆነልንም፡፡ መሠረታዊ የሚባሉ እርምጃዎችን በአስቸኳይ መሥራት ይጠበቅበታል፡፡ ሳስበው አሁን እሱን በሆነው ባልሆነው ጃስ ማለቱ ሳይሆን እንደተባለውም ትንሽ ጉልበት ሆኖ የሚሰራውን ጥቂት ጊዜ ሰጥቶ ማየት እንሞክር፡፡ ግን ቢያንስ የሚከተሉትን አድርጎ ማየት እንፈልጋለን
- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአስቸኳይ እንዲሽር
- ሁሉን አቀፍ ጉባኤ ጠርቶ ማወያየት(ተቃዋሚዎች፣ ከውጭ ያሉትን ጨምሮ፣ የሕብረተሰብ ተወካዮች የአሀይማኖትና አገር ሽማግላች)፡፡ አንድ ጉባዔ ለመጀመር ያስፈልጋል
- አላግባብ የታሰሩ ዜጎች ሁሉም እንዲለቅ
- ቀጥሎ ሕገ መንግስቱን ጨምሮ ሌሎች በርካት የሽብር ሕጎችን እንዲሽር
- ለሚቀጥለው ምርጫ ነጻ እንዲያደርግ(እንዲያረጋግጥ)
ለእነዚህ እርምጃዎች ግን ማሰብ ያለበት እንደ ኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴርነት እንጂ እንደ ወያኔው ኢህዴግ ሊቀመንበርነት መሆን የለበትም፡፡ የወያኔን ኢህአዴግ መንግስት ነው ብሎ እያሰበ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴር ሊሆን አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢሕዴግ ጠላቱ ነውና፡፡ ኢትዮጵያን ያለመንግስት ለ27 ዓመት በወሮበልነት የፈነጨ ቡድን ነውና፡፡ መንግስትና ፓርቲ እንኳን ሳይለዩ የድርጅታችን አቋም በሚል የወሮበላ ሕግ እያወጡ እስከዛሬ አሉ፡፡ ኢትዮጵያ በመንግስት ያስፈልጋታል፡፡ ፓርቲ በአንድ አገር አሸነፈ ማለት ካቢኔ አቋቁሞ መንግስታዊ ሥልጣንን በአደራ ይረከባል እንጂ መንግስት አደለም፡፡ ፓርቲ አገር እየመራ ስለድርጅቱ ማውራት ወንጀልም ነው፡፡ የመንግስትን ሥልጣን ተጠቅሞ ያሩሱን ድርጅት እያጎለበተ ነውና፡፡ ይሄ ለአብይም ሆን ለብዙዎቹ የወያኔ ኢህዴግ ሰዎች ግልጽ የሆነላቸው አይመስልም፡፡ ተቃዋሚዎቹም አስተሳሰባቸው ተመሳሳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከዚህ የአስተሳሰብ አረንቋ መውጣት አለባት፡፡ አሁን የተሰየመው ካቢኔም የዚሁ አስተሳሰብ ውጤት እንጂ ሥራ ለመስራት የሚያስችል አይመስልም፡፡
አሁን ከማየው ሁኔታው አብይ በግሉ መልካም ሊሆን ይፈልግ ይሆናል ግን ለሁሉ መልካም መሆን አይጠበቅበትም፡፡ መሠረታዊና ግልጽ የሆኑ የህዝብ ጥያቄዎችን መፍታት ቀዳሚ ተግባሩ ያድርግ፡፡ ለዛም ራሱ ሁሉን ማድረግ አይጠበቅበትም፡፡ ፍላጎቱን በግልጽ ከተራዳ ብዙ ሊረዳው የሚችል ኃይል ከጎኑ ነው፡፡ ችግሩም ብቻውን ሊፈታው አይችልም፡፡ አቋሙ ብቻ ጥርት ይበልልን እንጂ ሁላችንም በየአለንበት ሆነን የምንረዳው ብዙ አለ፡፡ አሁን በራሴ ከደረስኩበት አንጻር የተወሰነ ጥረት እያደረገ እንደሆነ የማያቸው አሉ፡፡ እነዚህን እዚህ ላይ መናገር አልፈልግም፡፡ እኔ ዜና ነገሪም አደለሁም እና፡፡ ሚዲያዎች የሚያወሩት መስማት የሌለብንን መጥፎውን ብቻ እያጎሉ ከሚነግሩን ምን እየተሰራ እንደሆነም መረጃ ማግኘት ቢችሉ፡፡ ነገሮች እዚህ የደረሱት በብዙ መሰዋዕትነት ነው፡፡ አብይም ቢሆን ከሕዝብ ፍላጎት ውጭ ባይሆን ይበጀዋል፡፡ አሁን ላይ ብዙዎች ከሕዝብ ጎን ናቸው፡፡ ወያኔን አልጨረስንውም እንጂ ጥለንዋል፡፡ ግን በግርግር እንደገና ሊያንሰራራ ይችላልና አሁን አብይን ነገሮችን በትኩረት እያየ ወደፊት በቃሉ መሠረት እንዲቀጥል ነው፡፡ አሁንም ትግሬ ወያኔዎች በየቦታው በሴራ እያደቡ ነው፡፡ ያጠፋውንም ቢያጠፋ ግን ከትግሬ ወያኔ ጋር አብይን ደምሬ የእነሱ ጉልበት መሆን አልፈልግም፡፡ ለነገሩ ብዙ ስለጠበቅን ይሆናል እንጂ አይሳሳትምም ብሎ ማሰብ በራሱ ስህተት ነው፡፡ እኔም በባለፉት ሁለት ጽሁፎቼ አላስፈላጊ ስሜት ውስጥ ግብቼ በአብይ መናደዴን ለመግለጽ ለወያኔ ወንበዴዎች ግብዓት የሚመስል መልዕክት መጻፌ ትክክል እንዳልሆንኩ በዚሁ አጋጣሚ አንባቢዎቼን በይፋ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ አብይን ወደፊትም ቢያጠፋ ልናገር እችላለሁ ግን በምንም መልኩ ለወንበዴው ወያኔ ቡድን ግብዓት እንዲሆን አልፈልግም፡፡
ሁላችሁም ኢትዮጵያውያን ልነግራችሁ የምፈልገው በአሁኑ ወቅት ትግሬ ወያኔዎች በአብይ ላይ ብዙ ግድፈት እንዲታይ አሰፍስፈው እየሰሩ ነው፡፡ ስለዚህ እንንቃ፡፡ ወደድንም ጠላንም በትግሬ ወያኔዎች ፈቃድ አደለም አብይ ጠ/ሚኒስቴር የሆነው፡፡ ከወንበዴው ቡድን እንዲላቀቅ ተጽኖ እናደርጋለን እንጂ እንደስልት የሚጠቀምባቸውን አካሂዶቹን ሁሉም በመጥፎ መተርጎም የለብንም፡፡ እኔ የፖለቲካ ተንታኝ አደለሁም፡፡ የነገሮችን አካሄድ ግን ሥራዬ ብዬ ከተከታተልኩ ብዙ እረዳለሁ፡፡ አሁን አብይ የአቅሙን እየታገለ እንደሆነ የማያቸው አንዳንድ ፊንጮች አግኝቻለሁ፡፡ ይልቁንም ተቃዋሚ ምናምን ነን የሚሉ ሚዲያ ላይ ከሚያወሩ ጠጋ ብለው በጠረጴዛ ዙሪያ ያነጋግሩት፡፡ እራት ተጋብዘው ከመብላት ባለፈ አላማቸውን ለመወያየት የሚያስችል ግንዛቤ ይኑራቸው፡፡ በእራት ግብዣ ወቅት ስለ ኢሕአዴግና ተቃዋሚዎች ከሚያወሩ ስለመንግስትና ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበረሰብ የመሳሰሉት ትክክለኛ የፖለቲካ ስነምህዳር የሚሰፋበትን ማንሳት ነበረባቸው፡፡ አብይ ጠ/ሚኒስቴር ሆኖ እንደ ኢህአዴግ ሲያወራ በጠ/ሚኒስቴር ቦታ ሆነህ ይህን ስለኢህዴግ ማውራት አትችልም ማለት ይጠበቅባቸዋል፡፡የጠ/ሚኒስቴርነቱን ስልጣን ተጠቅሞ ማለቴ ነው፡፡ ስለድርጅቱ ማውራት የሚችለው እንደ ኢህአዴግ ሊቀመንበርነት ኢሕአዴግን ወክሎ በሚቀርብበት ጊዜ ነው፡፡ የጠ/ሚኒስቴሩ ቦታ የኢህአዴግ ሳይሆን የመንግስት ሥልጣን ቦታ ነው፡፡ ነገ ሌላ ተቃዋሚ ሊቀመጥበት ይችላልና፡፡ በዚህ አሳቤ ወደፊት ግን በፍጥነት አንቀጥል፡፡ የበዓዴንና ኦህዴድ አመራሮች ከክልል ራሳችሁን አጠናክሩ፡፡ ለማ አዲስ ካቢኔ የሰየመ ይመስላል፡፡ እንማስበው ለውጤት ነው ብዬ እገምታለሁ፡፡ በአዴንም ተመሳሳይ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡ በተለይ የወያኔ ትግሬዎችን ከበአዴን ጉያ ነቅሶ ሊያወጣ ይገባዋል፡፡ ሌሎች ክልልሎችንም ጉልበት እየሆናችሁ አነቃቁ፡፡ ደቡብ ቢያንስ በዞንና በወረዳ ደረጃ ከኦሮሚያና አማራ ክልል ያልተናነሰ ትንቅንቅ ውስጥ ያሉ እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ኮንሶን እንደምሳሌ እንውሰድ፣ ጉራጌም እንደዛው ነው፡፡ የኦሮሚያ መንግስት በአዋሳኝ ቦታዎች የሚነሱ ግጭቶችን በአስቸኳይ ሊያስቆም ይገባል፡፡ አሁን ላይ በጉጂና ጌዶ ማህበረሰብ ግጭት አለ፡፡ ግጭቱ ሚዲያ ላይ እንደሚራገበው ጉጂ ገዳይ ጌዲዎ ሟች ሳይሆን ከሁለቱም ወገን ነው፡፡ በዛ አካባቢ ደግሞ ከድሮም ጀምሮ ነው ችግሩ፡፡ የሆነ ሆኖ የኦሮሚያ መንግስት የተናጥል እርምጃም ቢሆን ወስዶ ግጭቱን ሊያስቆም የሚችልበትን ዘዴ መቀየስ ያስፈልጋል፡፡ አሁን ላይ የጌዲኦ መጨፍጨፍን እያገዘፉ የሚያወሩት አብይ ኦሮሞ ጠ/ሚኒስቴር ስለሆነ ጉጂዎች በጌዲኦ ላይ ተነሱ ለማለት ነው፡፡ እንዲህ ያሉ ክፍተቶችን በመዝጋት ነው ወያኔን መቀበር የምንችለው፡፡
በመጨረሻ አብይ በባህርዳር መሪ የሚያስብለውን ንግግሩን አደንቅለታለሁ፡፡ አሁንም ግን እኛ ኢህአዴጎች ማለቱን እንዲያቆም አጥብቄ እነግረዋለሁ፡፡ ጠ/ሚኒስቴር አብይ እንጂ የኢህአዴግ ሊቀመንበር አብይ የባህርዳርንም ሆን ሌላ ሕዝብ በአገር መሪ ቦታ ሆኖ መናገር አይችልም፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=PkI4jFp-BdM
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! አሜን!
ሰርፀ ደስታ