April 19, 2018
20 mins read

ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

በደርግ ዘመን በአብዛኛው ለታይታና በተግባር ለማይገለጥ ማስመሰያነትም ቢሆን “ሁሉም ነገር ለሕጻናት!” የሚል መፈክር ይሁን መመርያ በየቦታው በተለይም የሕጻናት ኮሚሽን የሚባለው መሥሪያ ቤት በነበረበት አራት ኪሎ አካባቢ ተለጥፎ ይታይ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በመፈክር ደረጃ በግልጥ ተለጥፎ አይታይ እንጂ “ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ!” እና “ሁሉም ምርጥ ምርጥ ነገር ለትግራዋይ” የሚል መፈክር በሕዝቡ ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ነው፡፡ ዐይን ዐይን የአዲስ አበባ የመኖሪያና የንግድ ቦታዎች የሚሰጡት ለትግሬ ነው- ትግሬ ከጠፋ ነው ለሌላ በተለይም ለኢ-አማራ የሚሰጠው፡፡ ባይገርማችሁ ስማቸውን ወደ ግደይና ወደ ዘበርጋ እንዲሁም ወደ ፈይሣና ቶቆ የለወጡ አምበርብሮችና ሸዋንግዛዎች (አማሮች ለማለት ነው!) ብዙ ናቸው፡፡ ይህም የሆነው መንግሥታዊ መዋቅሩ ፀረ-አማራ በመሆኑ አማሮች ሊቀጠሩ የሚሄዱባቸው በትግሬዎች የሚተዳደሩ መ/ቤቶችና ባለሥልጣኖች እነዚህን አማሮች በአማራነታቸው ምክንያት እየተጠየፏቸው “ምን ታመጣላችሁ? አንቀጥራችሁም” ስለሚሏቸው ነው፡፡ ብዙ የምናውቀውና በታሪክ መዘግብ የተቀመጠ ጉድ አለ፡፡ … ይህች ዘመን በጭንቅላቱ ማሰብ ላቆመ ሆድ-አምላኩ ትግሬ በሚሊዮኖች ዓመታት አንዴ የምትታይ የደስታና የፈንጠዝያ ዘመን ናት – የተጋሩ ሃሊዮኮሜት፡፡  የታሪክ ወልጋዳ አልጋ ላይ ተኝታ በምታጣጥረው ኢትዮጵያ ላይ ምድረ ባንዳ የባንዳ ውላጅ ከነ(የ)ውስጥና ውጪ ተባባሪዎቹ ነፍሷ ገና ያልተለየው በድኗ ላይ በመስፈር ሀገሪቱን ስሊዋን አንቆ እየቦጠቦጣት ይገኛል፡፡ የዚህ የጅብ መንጋ ዋና መሪና ዕቅድ ነዳፊ ወያኔ ትግሬ ነው፡፡ ይህ መራር እውነት እስከ ዓለም ፍጻሜና ከዚያም በኋላ የማይዘነጋ መሆኑ ለመልካም ትግሬዎች መጥፎ ዜና ቢሆንም ምሕረት-የለሹ ታሪክ እንዲህ አደረገንና ኢትዮጵውያንን ጉድ ሠራን፤ “ተለያየን!” አለች ያቺ ልጇን ደራሽ ጎርፍ የወሰደባት የኩታበር ሴት፡፡ በዚህ እየታዘብነው በምንገኘው  አንዱ ሌላውን ያላንዳች ርህራሄ ቀርጥፎ የመብላት አስቀያሚ ሂደት ሳቢያ መተማመን ጠፍቶ ልጆቻችንና የልጅ ልጆቻችን በዚህ ዘግናኝ የታሪካችን ጠባሳ ምክንያት ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ አሁን ላይ ሆነው ሲያስቡት ቶሎ መሞትን ያስመኛል፡፡ እውነቴን ነው፡፡ የቆዬ ያየዋል – “ሦርያና ሶማሊያ ከኛ ይሻላሉ” የሚባልበት አስቀያሚ የታሪክ አንጓ በኢትዮጵያ ይከሰታል፡፡ ይህን ለማወቅ ደግሞ የጥጋበኛ ወያኔ ትግሬዎችን የዘረፋና የግፍ ድርጊት መመልከት ብቻ በቂ ነው – ነቢይነትን አይሻም፡፡

ወያኔ ትግሬዎች እንዴቱን ያህል ወራዳዎችና ይሉኝታቢሶች እንደሆኑ ሳስበው እንደሰው መፈጠሬን በተለይም እንደዚህ ዘመን ኢትዮጵዊ ሆኜ በአፍሪካ ቀንድ መገኘቴን አፍርበታለሁ፡፡ ሥራቸው ሁሉ ሰው ሆኖ መፈጠርን ያስጠላል፡፡

ይህችን አጭር ማስታወሻ ልጽፍ የተነሳሁት አሁን ከምሣ መልስ ወልቃይት ድረገጽን ከፍቼ ሳነብ ባገኘሁት ትኩስ ዜና በጣም ስለተናደድኩ ነው፡፡ ዜናው አስገራሚ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በዘረፋና በስርቆት እንደቆረቡ ፀሐያቻው ማዘቅዘቋ ያስደንቃል፡፡ መቼ ይሆን የሚማሩት? መቼ ይሆን ወደኅሊናቸው ተመልሰው ሰው ሰው የሚሸቱት? ኧረ መቼ ነው ልብ የሚገዙት? ዋናውን ብሩንዶና ፍሪምባ ይዘውት ሳለ ለድሆች መድረስ ያለበትን ቅንጥብጣቢና ምላስ ሰምበር ከመስረቅ የሚቆጠቡትና ኩራት ቢጤ የሚጎበኛቸው መቼ ይሆን? ለመሆኑ እንዲህ እምብርት ያጡት ምን ሆነው ነው?

ጎጃም ውስጥ መርጦ ለማርያም በሚባል ሥፍራ አካባቢ አንድ ድልድይ ታድሷል አሉ፡፡ ከዚያ ድልድይ የወጣ ብረታ ብረት በሦስት መኪና ከነሪሞርኬው ተጭኖ ወደትግራይ ሊጓጓዝ ሲል ሕዝቡ ያዘው አሉ፡፡ በዚህ ዜና የማይገረም ኢትዮጵዊ ቢኖር የማይሞቀው የማይበርደው ድንጋይ ነው ወይም በዘረፋ የሰከረ ቀንደኛ ወያኔ አሊያም ደጋፊ ነው፡፡

አሁንም በዚያ ተጨፈኑ ላሞኛችሁ የጥንት መንገድ መጓዝ ያምራቸዋል፡፡ ምን ዓይነት ስም-የለሽ ደደብነት ነው?

እንዴ! አንድ ድርጅት ከ27 ዓመት ሀገራዊ ሥልጣን በኋላም በሽፍትነት ለመቀጠል ይህን ያህል ይዘቅጣል?

ለነገሩ እነሱ እውነታቸውን ነው፡፡ “የማያድሩበት ቤት አያመሹበትም” ይባላል፤ “ድመት መንኩሳ ዐመሏን አትረሳ”፣ “መጥፎ ጠባይ ሳያስቀብር አይለቅ” ወዘተ. እንላለን፡፡ ወያኔን በድርበቡ ለመግለጽ እኚህን መሰል አንዳንድ አባባሎች ሳይጠቅሙን አይቀሩም፡፡ ሀገሪቱን እንደሀገራቸው፣ ሕዝቡንም እንደሕዝባቸውና ፖለቲካውን እንደፖለቲካቸው የማይቆጥሩ ወፍዘራሽ ወያኔዎች የሚናገሩትን ብቻ ሣይሆን የሚያደርጉትን ሁሉ ስናይ ተፈጥሯቸውን መቀየር የሚያስችላቸው ቀመር እስካሁን ሊገኝ አለመቻሉን ነው፡፡ ስህተተኛው ከነሱ መልካም ነገርን የሚጠብቅ እንጂ እነሱ ምንጊዜም ተሳስተው አያውቁም ብቻ ሳይሆን ለመሳሳትም ቅንጣት በር አይከፍቱም፤ አለመሳሳታቸው የሚረጋገጠው ደግሞ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ያለመገኘት ቁርጠኝነታቸው ሲታይ ነው፡፡ በደምብ የሚያውቁት የነሱ እውነት – ኢትዮጵያዊ ሆኖ አለመገኘት ነው፡፡ ያኔ ይሞታሉ፡፡ ወያኔ የሚሞተው ኢትዮጵያዊ ሲሆንና የኢትዮጵያን ጥቅምና ፍላጎት ለማክበር ሲወስን ነው፡፡ ይህን ዓይነቱን ስስ ብልት ፈረንጆቹ Achilles’ heel ይሉታል፡፡ የወያኔ ስስ ብልት ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ የወያኔ ስስ ብልት ኢትዮጵያን በታሪካዊነቷ ከነሕዝቧና የግዛት አንድነቷ መቀበል ነው፡፡ ይህን መቀበል ማለት ከእስልምና ወደ ክርስትና ወይም ከቡድሂዝም ወደ ሽንቶይዝም ሃይማኖትን የመለወጥ ያህል ነው፡፡ አንድን የማንነት መገለጫ ትተህ ወደሌላው ስትቀየር መስዋዕትነት አለው – አሁን አሁንማ አንገትን በሰላ ካራ እስከማስበጠስ ጭምር፡፡ የምትቀበለው እንዳለ ሁሉ የምትተወውም አለና ሂደቱ ቀላል አይደለም – የሚዲያ ቅብብሎሹን የወሬ ጋጋታና ማኅበራዊ የቡና ማጣጫነቱን ትተን ማለት ነው፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያን ከነታሪኳ ለማጥፋት በጠላቶቻችን የተተከለ አህመድ-ግራኛዊ የመርገምት ድንጋይ እንደመሆኑ ከዚህ የአባቶቹና የጌቶቹ ዓላማ ፈቀቅ ቢል የሚደርስበትን ያውቃል፤ በዚያ ላይ ወደፖለቲካው መድረክ ከወጡ ጀምሮ የሠሩት ሥራ ከማንም ጋር የሚያቀባብር ባለመሆኑ የገዛ ጥላቸውን ሳይቀር እየፈሩ በሥጋት የሚኖሩ ናቸው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ፈረስ በመለወጥ የሚስተካከላቸው የሌላቸው የወያኔ ጌቶች የትሮይን ፈረስ ለማበጀት ሰከንድ አይፈጅባቸውም፡፡ ዐቢይ ፈረስ በአንድ ቀን አዳር ሊሠሩ ይችላሉ፡፡

በመሠረቱ በኛ ስንፍናና ፍርሀት እንጂ እንደነሱ ጭካኔና ክህደት ቢሆንማ ኖሮ እንኳንስ 30 እና 40 ዓመታት ለሦስት ወርም በቤተ መንግሥታችን ውስጥ ተቀምጠው አይጨመላለቁብንም ነበር – ጥሬ ብስናታቸውን እየጋቱን እንዲህ እኛም የሚያበሰናን የምናወራርደው የኃጢኣት ይሁን የወንጀል ቁልል ገመና ስላለብን ሊሆን ይችላል፤ እንጂ ቅምቡርስ  ዘንዶን አትውጥም፤ ድኩላና ሚዳቋም በአንበሣ ሰውነት አይሰለጥኑም፡፡ ሰባቶች ሚሊዮኖችን አያንበረክኩም፡፡ ቀን ሲዘምና ሲጥል ግን ጉንዳን ሱሪ ታስወልቃለች፤ ላምም በሬን አሸንፋ ገደል እስኪገባ ታሳድደዋለች – እናም መሆን ያለበት ሁሉ በጊዜው ይሆናልና ጨቋኝም ተጨቋኝም አይግረማቸው፡፡ “ፍርጃ ነው!” የምንለውም ወደን አይደለም – ትዛዙ ከላይም ነውና፡፡

እኛን ግን ይበለን፡፡ እንዲያውም ሲያንሰን ነው፡፡ ታሪካችን በሙሉ የሚያወራው እርስ በርስ እየተጠላለፍን ስንፋጅ እንጂ በተረት ተረቱ እንደምንሰማው በሀገር ፍቅር ነድደን እርስ በርስ ስንፋቀርና ሀገርን ስንገነባ አይደለም፡፡ የፍስሐ ያዜን መጻሕፍት እናንብብ፤ የአለቃ ተ/የሱስን መጽሐፍ እናንብብ፡፡ መላውን የታሪክ መዛግብትና መጻሕፍት እናገላብጥ፡፡ ምንድን ነው ያለን ውብ ታሪክ? ጦርነትን ማሸነፍ ብቻውንና በራሱ ታሪክ አይደለም፤ ጦርነትን መሥራትም ታሪክ አይሆንም፡፡ ልጅ የአባትን፣ አባትም የልጅን ዙፋን ለመቀማት በዱር በገደል እያሳደዱ መግደልና አካልን መቆራረጥ ጥሩ ታሪክ ከተባለ ጥሩነቱን በዚያ ረገድ ለመጃጃል ፈቃደኛ ለሆነ ሰው መተው ነው የሚበጀው፡፡ የአሁን ቅርጻችን ከየት መጣ? እስኪ የሀርጌሣዋን የትናንትና ሰሜን ሶማሊያን እንኳን እንመልከት – እርሷ እንኳን ባቅሟ ከብዙ ተዛማጅ ጥቅማ-ጥቅሞች ጋር በ600 ዶላር መምህር ቀጥራ ከኛ አልወሰደችም? የየትኛው ሀገር ዜጋ ነው የባህርና የየብስ ዐውሬ ቀለብ ሆኖ የሚቀረው? እኛን የማይበልጥ ሀገር እስኪ አንድ ጥሩልኝ…. እንደሚባልልን ብንሆን ኖሮ ፈጣሪም እነዚህን መዥገሮችና የቀን ጅቦች አይልክብንም እኛም ቢያንስ እንደኒዠር ሕዝብ በነፃነት አደባባይ እየተንጎማለልን “ያልፍልን” ነበር፡፡ በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂት በስተቀሮች በስተቀር አሁን ብቻ ሣይሆን ከጥንትም የሚላኩብን ጅቦች በልተው የማይጠግቡ፣ ዘርፈው የማይረኩ፣ ዕድሜ ልካቸውን የሰው ማጀትና የሰው ሣሎን እንደመዘበሩ አንድም ሳይጠረቁ ዕለተ ሞታቸውን የሚጠብቁ ጭራቆች ናቸው፡፡ እነዚህኞቹ ጉዶች ደግሞ ከሁሉም የባሱና የከፉ ሆኑና ባልጠፋ የሚዘረፍ ነገር የድልድይ ስብርባሪ ሳይቀር ይዘርፋሉ፡፡ ምን ዓይነት ተፈጥሮ ይሆን? መጥኔ ለቀጣይ ትውልዳቸው፡፡ ሱቅ ውስጥ እንደገባ ሕጻን ሁሉም ነገር እንዳማራቸውና እንደተቀራመቱት አረጁ፡፡

በቡሃቃ ሌባ ሀገር ስትመራ ሦስት አሠርት ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ በሊጥና በዳቦ መጋገሪያ ማሽን ሌቦች አንድ ታላቅ የሚባል ሕዝብ ሲተዳደር ሦስት ውድ አሠርት ዓመታት አለፉ፡፡ መንግሥት ሆነውም ባንክና የመንግሥት ግምጃ ቤት በሚሰርቁ ሌቦች ሰንመራ የማይተኩ 30 ዓመታት ነጎዱ፡፡ ገና ለገና ትግራይና ዋሻዎቿ በጋራ የኢትዮጵያ ሀብትና ንብረት ሞልተው አላበቁምና ብለው ብለው የጣሊያን አርማታ ብረት በድልድይ ዕድሳት ስም በቻይና ገለባ ብረት እየተኩ  ከየሥፍራው በመነቃቀል መውሰዳቸውን እንደዱሮው ቀጠሉበት – በዚህ ጠባያቸው ከእንግሊዝ ጋር ይመሳሰላሉ፤ እንግሊዝ እንኳን ባዕድ ናት፡፡ እነሱ ግን ነገን የማያስቡ ድፍን ቅል “ኢትዮጵውያን” ናቸው – ቢያንስ በስም፡፡ ማፈር ከምድር ቢጠፋ፣ ይሉኝታ ከናካቴው ባይፈጠር በዚህን ያህል ደረጃ ወርደው ይህን የመሰለ አስጸያፊ ስርቆት ይፈጽማሉ ብሎ መገመት ይከብዳል፡፡ “ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል” እንደሚባለው ነው፡፡ ኤፈርትን የመሰለ ቢሊዮኔር ድርጅት ይዘው፣ ሞሶበን የመሰለ ቢሊዮኔር ድርጅት ይዘው፣ ከሁሉም ከሁሉም እንዳሻው የሚፈነጥዙበትን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክንና ንግድ ባንክን የመሰለ፣ ቴሌን የመሰለ፣ አየር መንገድን የመሰለ፣ ጉናን የመሰለ፣ በጥቅሉ ኢትዮጵያን የመሰለች የማትነጥፍ ጥገት ይዘው ወደዚህ ልክስክስ የቁርጥራጭ ብረት ስርቆት ሲገቡ ስናይ የኛ ኃጢኣት ግዝፈት ነው በግልጽ ሊከሰትልን የሚገባው፡፡ ለእንደነዚህ ዓይነት ሌቦች ልንጋለጥ የቻልንበትን ታሪካዊ ስህተትና ሃይማኖታዊ ህፀፅ መርምሮ እውነቱን የሚያስረዳን የምሁራን ኮሚቴ አሁኑኑ ይቋቋም እባካችሁን፡፡ እኔ እጅግ አፈርኩ፡፡ እኔ እነሱን ብሆን ወደዚህ ዝቃጭ የስርቆት ተግባር አልወርድም ነበር፡፡

በስማም ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ! ምን ጣለብን ግን?

አንድም እንቅልፍና ዕረፍት ሳያምራቸው ለዚህን ሁሉ ዘመን ሲሰርቁ ከርመው አሁን እንኳን ትንሽ ጋብ አይሉም? ከየጠቅላይ ግዛቱ ወደ ትግራይ ያጋዙት ያ ሁሉ ዕቃና ማሽነሪ ሳያንስ አሁን ደግሞ መንግሥታዊ ቁራሌ ተቋቁሞ ንብረታችን በጠራራ ፀሐይ እንደዚህ ይዘረፍ? እግዚኦ መሓረነ ክርስቶስ!   ነገ ምን ብለን ይሆን ይህን ቅሌት ለመጪዎቹ ትውልዶቻችን የምናወራው? አሣፋሪ እኮ ነው በውነቱ፡፡ እስኪ ጤናማ ነን የምትሉ ትግሬዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋገሩና አንድ መግለጫ ቢጤ አውጡበት፡፡ ይህን ዘመን ያላዩና ስለዚህ ዘመን የወያኔ ትግሬ ጉድ ያልሰሙ ብፁዓን ናቸው፡፡

ለገምቢ አስተያየት – [email protected]

 

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop