March 29, 2018
7 mins read

ከሆነማ መልካም? – ከገዙ በቀለ (ዶ/ር)

ነገሩ አንዳንዴ ቢሆንም፣ ከሐዘን ወደ ደስታ የሚወስድ ነገር መቼም አይታጣም። በዚህ አኳያ ዶ/ር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ምድር ላይ ካላው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ሲተያይ ደስታዬን ከፍ አድርጎታል። ቀጥሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ የሚለው ግምቴም ትልቅ ነው። ገና ምኑ ታይቶ ሊባል ይቻላል፤ ተገቢ ነው።አላያማ ያመኑት… የተባለው ብሂል መከተሉ ነው። የታሰበው  ካልሆነ የተለመደውን ብዕሬን ማሾሌ አይቀሬ ነው። ብቻ ለጊዜው ፍቀዱልኝና ደግ ደጉን ልበል!  የለማ መገርሳ ቡድን አይበገሬውን ኃይል ተዳፍረዋልና ሊበረታታ ይገባዋል ባይ ነኝ። የለማ መገርሳ ቡድን ይህን ጥንካሬ ያገኘው ሕዝቡን በመስማቱና ከሕዝቡ ጋር በመወገኑ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሉታዊ ጥርጣሬም አብሮኝ አንዳለ ልደብቅ አልችልም። በወደፊት ጉዞችን  ላይ አንዳችም ጋሬጣ አይኖርም ከሚሉት ወገን አይደለሁም። ሁሉም ተሳካ፤ ሁሉም ሰመረ፤ ድል በድል ሆንን ብዬ ሽንጤን ገትሬ፣ አፌን ሞልቼ የምናገርበት ጊዜ ላይ አልደረስኩም። ለጊዜው ግን ለሕዝባችንና ለዶ/ር አብይ አህመድ በጎውን ተመኝቻለሁ።

ዶ/ር አብይ የተረከቡት ሃላፊነት አገራችን በከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ በገባችበት ሰዓት ላይ ነው። በአንዳንዶች አባባል አገራችን መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች። የፖለቲካ፣ የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚ፣   ቀውስ ሰፍኖባታል። የግዛት አንድነቷ ሳይቀር አደጋ ተደቅኖበታል። ዶ/ር አብይ የጥንቱን ኮሮጆ ዳበሰው፣ የድሮውን መዝገብ አገላብጠው ልምራ፣ ችግሩንም ልቅረፍ ካሉ፣ሁሉም ነገር ታጥቦ ጭቃ መሆኑ ነው። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በዚህ ዓይነት ወጥመድ ተተብትበው ነበርና!  በመሆኑም የፈየዱት አንዳችም ነገር የለም። ዶ/ር አብይ እራሳቸውን የሕዝብ ተመራጭና ተወካይ አድርገው ካልወሰዱ፣ ችግሩ የባሰ ሊሆን ይችላል።ኢትዮጵያን የሚያክል አገር፣ የአንድ ፓርቲ ብቻ ጥቅም አስጠባቂ ሆኖ መመራት ከቶም አያዋጣም። ይህንን ለማድረግ አሻፈረኝ ካሉ፣ኢህአዴግን ብቻ የሙጥኝ ካሉ፣ የሕዝቡን አመኔታና ድጋፍ በፍጥነት ሊያጡ ይችላሉ።ይልቁኑ ታሪክ የጣለባቸውን አደራ  በሚገባ ቢወጡ፣ አገራችን እንድ እምርታ ወደፊት ትሄዳለች።

 

ማንኛውም የአገራችን ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ወገኖች የተፈጠረውን በጎ ጅምር ለመጠቀም፣ በሰላማዊ መንገድ ዓላማቸውንና ፕሮግራማቸውን ለሕዝቡ ለማስተዋወቅ ከአሁኑ ማቀድ  ይኖርባቸዋል። ዘወትር ጥላቻን ብቻ መንዛቱ ጠቃሚ አይሆንም። ሕዝቡን መሰማት፣ ከሕዝቡ ጋርም መመካከር ተገቢ ነውና። በጥላቻ ተመስርቶ የሕዝቡን አብሮ የመኖር ባሕል መሸርሸር ግን ለማንም አይጠቅምም።በተለያየ ምክንያቶች ጠመንጃ ያነገቡ ኃይሎች በሰላማዊው መንገድ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምኞቴ ነው። በዚህ አጋጣሚ የአገራችንን መከፋፈል የሚመኙ፣ የሚቋምጡ፣ አጋጣሚውንም የሚናፍቁ ካሉ እርባና ቢስና ቅዥት አራማጆች ናቸው።

ከዶ/ር አብይ አህመድና ከካቢኒያቸው በአስቸኳይ ምን ይጠበቃል?

  1. በሕዝባችን መካከል መቀራረብ እንዲዳብር ማድረግ፣የነበረውም እንዲቀጥል ማበረታት፣
  2. በአገር ውስጥ ሆነ በውጭ ያሉትን የሲቪክ ማህብራትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ፣ ምሁራን፣ የሕዝብ ተወካዮችን …ወዘተ በአገራችን ጉዳይ ላይ በሰላማዊ መንገድ እንዲሳተፋና እንዲመክሩ ማስቻል፣
  3. አስችኳይ አዋጁን ማንሳት፣
  4. ጦሩ በድንበር ጥበቃ ላይ እንዲሰማራ፣ በአመራር ደረጃም ለውጥ ማድረግ። በደህንነት መሥሪያ ቤቱም ላይ የአመራር ለውጥና አገራዊ ጥቅም ባለው መልክ እንዲዋቀር ማድረግ፣
  5. የታሰሩ የፓለቲካ እስረኞችን ያለ አንዳች ቅደመ ሁኔታ መፍታት፣
  6. ፍርድ ቤቶች፣ ምርጫ ቦርድ፣ የፀጥታ ኃይሎች የአንድ ፓርቲ አገልጋይ እንዳይሆኑ ማስወሰን፣
  7. የመሰብሰብ፣ የመናገር፣ የመጻፍ፣ በጠቅላላው ዲሞክራሲያዊ መብት እንዲጠበቅ ማድረግ፣
  8. ብሔራዊ እርቅ የሚሰፍንበትን መንገድ ማመቻቸት፣
  9. በአጭር ጊዜ ውስጥ ዲሞክራሳዊ ምርጫ የሚካሄድበትን መንገድ ማሳናዳት፣
  10. የኢኮኖሚ ልማት እንዲካሄድ መጣር፣ ሁሉም ሕዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን መሞከር፣
  11. ሃያ ሰባት ዓመት ሙሉ የነበሩ  መርሐ ግብሮችንና ፖሊሲዎችን  በድጋሚ መርመር፣ ጠቃሚ ያልሆኑትን ማስወገድ፣
  12. በጠላትነት ከተፈረጁት ጎረቤት አገሮች ጋር ግንኙነቱ የሚሻሻልበትን መንገድ ማጤን የሚሉትን ያጠቃልላል።

ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም ተጓዳኝ ሃሳቦች በሥራ ላይ ከዋሉ እሰየው ከሚሉት ወገን ነኝ። በድጋሜ ለለማ መገርሳ ቡድን፣ ለቄሮ፣ ለፋኖ፣ ለዘርማ ብሎም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተጋድሎ አድናቆቴን እገልጻለሁ።

ቸር ቸሩን ያሰማን !!

 

 

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop