ከቦጋለ አበበ
ኮትዲቯራዊው ኮከብ ዲዲየር ድሮግባ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ ተሰልፎ መጫወቱ አግባብ መሆኑን የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ማረጋገጡን ቢቢሲ ዘገበ።
ድሮግባ በሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ጋላታሳራይ ከጀርመኑ ሻልክ ዜሮ አራት ጋር ሲጫወት ተሰልፎ አንድ ግብ ከመረብ አሳርፏል።ይሁን እንጂ የጀርመኑ ክለብ ድሮግባ ለጋላታሳራይ ተሰልፎ የተጫወተው ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ነው ሲል ለአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ይግባኝ ጠይቋል።
የሰላሳ አራት ዓመቱ ድሮግባ ሁለቱ ክለቦች አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት በተለያዩበት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ለቱርኩ ክለብ ለመጫወት አልተመዘገበም በሚል ሻልክ ያቀረበው ጥያቄ በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ሲጣራ ቆይቶ ተጫዋቹ ለጋላታሳራይ የተጫወተበት መንገድ አግባብ እንደሆነ ተረጋግጧል።
ድሮግባ ባለፈው የፈረንጆች የካቲት ሃያ ቀን ሁለቱ ክለቦች ባደረጉት ጨዋታ ከቻይናው ክለብ ሻንጋይ ሽኑዋ በውሰት መጥቶ ሳይመዘገብ መጫወት የማይችል ቢሆንም ተጫዋቹ ከሃያ ቀን ቀደም ብሎ ለጋላታሳራይ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ለመሰለፍ መመዝገቡ ተረጋግጧል።
ጋላታሳራይ ድሮግባን በሻምፒዮንስ ሊግ አሰልፎ ማጫወቱ አግባብ ሆኖ ባይገኝ በጨዋታው ያገኘውን ነጥብ የመነጠቅ አደጋ ያጋጥመው ነበር።ይሁን እንጂ ክለቡ ጥፋተኛ ሆኖ ባለመገኘቱ በደርሶ መልስ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ከሻልክ ጋር በእኩል ነጥብ ይጫወታል።
በደቡብ አፍሪካ ዋንጫ ኮትዲቯርን የዋንጫ ባለቤት የማድረግ እድሉ የከሸፈበት ድሮግባ አሁንም በአውሮፓ ክለቦች ተፅዕኖ ፈጣሪነቱን እያስጠበቀ ይገኛል።በእንግሊዙ ቼልሲ ክለብ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ባነሳ ማግስት እንግሊዝን ለቆ ዳጎስ ያለ ደመወዝ ወደሚከፍለው የቻይናው ክለብ ሻንጋይ ሽኑዋ አምርቷል።ከስድስት ወር ቆይታ በኋላም ከቻይናው ክለብ በውሰት ወደ ቱርኩ ጋላታሳራይ በማምራት ዳግመኛ የሻምፒዮንስ ሊግ ድምቀት ሆኗል።
ለሻንጋይ ሽኑዋ ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር ያህል ለመጫወት ተፈራርሞ የነበረው የኮትዲቯር የቁርጥ ቀን ልጅ ድሮግባ ወደ ኢስታንቡሉ ክለብ ጋላታሳራይ የመጣው ባለፈው ጥር ለአሥራ ስምንት ወር ያህል ለመጫወት ነው።
እ.ኤ.አ በ1978 መጋቢት ላይ የተወለደው ድሮግባ 2003 ላይ ለማርሴል ክለብ በሦስት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ዩሮ በመፈራረም በውድድር ዓመቱ አስራ ሰባት ግቦችን ከመረብ አሳርፏል።ክለቡን ለታላላቅ የአውሮፓ ጨዋታዎች በማብቃትም በእግር ኳስ ስሙን ማግነን ችሏል።
ድሮግባ 2004 ላይ ቼልሲን በሃያ አራት ሚሊዮን ዩሮ በመቀላቀል የፕሪሚየር ሊግ፤ሻምፒዮንስ ሊግ፤ሦስት ኤፍ ኤ ካፕና ሁለት የሊግ ካፕ ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል።ድሮግባ በእንግሊዝ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተጫዋች በሆነበት ወቅት ሁለት ጊዜ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች በመሆን ተመርጧል።
ከቼልሲ ክለብ ጋር በርካታ ድሎችን በማጣጣም በዓለም ካሉ ታላላቅ የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል አንዱ መሆን የቻለው ድሮግባ ቼልሲን ከተሰናበተ በኋላም በቻይና ተወዳጅ ተጫዋች ሆኖ ሰንብቷል።አሁን ደግሞ በቱርኩ ታላቅ ክለብ በመሰለፍ እያሳየው ያለው ድንቅ ችሎታ የስፖርት ቤተሰቡ መነጋገሪያ ሆኗል።
የአውሮፓ ፉትቦል ፌዴሬሽን ድሮግባ ሕጋዊ ተጫዋች ነው አለ
Latest from Blog
ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት
80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?
በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና
ሰው ሆይ!
“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።” መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን
ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች
\በጎንደር እና ወታደራዊ ውጥረት / ፋኖ በላሊበላ ኤርፖርት ዉጊያ/ ባለሃብቱ በአዲስ አበባ ታሰሩ የቀድሞው መከላከያ አመራር ፋኖን ሸለመ || ሻ/ቃ ዝናቡ ስላወቅሁ ደስ ብሎኛል || ጥር 7 አዲስ ቪዲዮ
በጎንደር እና ወታደራዊ ውጥረት / ፋኖ በላሊበላ ኤርፖርት ዉጊያ/ ባለሃብቱ በአዲስ አበባ ታሰሩ
አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ
አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም
ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ
የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ
ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ አንድ አባውራ ምንነቱ ያልታወቀ እህል ከገበያ ገዝቶ ለሚስቱ አምጥቶ ሰጣት አሉ፡፡ ከሰጣትም በኋላ ሚስቱ ያንን እህል ፈጭታ ቂጣ ላርግህ ብትለው፣ እንጀራ ላርግህ ብትለው፣ ገንፎ ላርግህ ብትለው … ምን አለፋህ
ወሰንየለሽ ኦሮሙማዊ ዕብደት!!
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን
የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ