ዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ውስጥ አዋቂ ምንጮቿን ጠቅሳ አቡነ ማቲያስን አቡነ ጳውሎስን ለመተካት መንግስት ካዘጋጃቸው 3 ጳጳሳት መካከል አንዱ መሆናቸውን ኦክቶበር 11 ቀን 2012 ዘግባ ነበር። ዛሬ የሆነውም ይኸው ነው። ምንጮቻችንን በዚህ አጋጣሚ እናመሰግናለን።
ዘገባው በከፊል እንዲህ የሚል ነበር – ለትውስታ፦
ዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች እንደሚሉት መንግስት በተለይም በሕወሓቱ አባይ ጸሃዬ የሚመራው ቡድን 3 ጳጳሳትን እንዲሾሙ አጭቶ አቅርቧል። የነዚህ አባቶች ዝርዝርም ለዘ-ሐበሻ ምስጢሩ ከአዲስ አበባ ሾልኮ ገብቷል።
1ኛ እጩ፦ አቡነ ማቲያስ
የመጡት፡ ከትግራይ
መንግስት በፓትርያርክነት እንዲቀምጡ ከሚፈልጋቸው አባቶች መካከል አንዱ አቡነ ማቲያስ ናቸው። አቡነ ማቲያስ ዛሬ ቤተክርስቲያን ለ3 እንድትከፈል ምክንያት ከሆኑት መካከክ አንዱ ናቸው እየተባሉ ይተቻሉ። በተለይም ሃገር ቤት ካለው ሲኖዶስ፣ ውጭ ካለው ሲኖዶስ ውጭ የሆነ ገለልተኛ ቤተክርስቲያን በውጭ ሃገር በማቋቋም የመጀመሪያው ናቸው። በአቡነ ተክለሃይማኖት የፕትርክና ዘመን ተወግዘው የነበሩት እኚሁ አባት “አቡነ ማቲያስ” የሚለውን ስማቸውን ሁሉ ተነጥቀው ነበር። በዚህም ወቅት ገለልተኛ ቤተክስቲያን አቋቁመው ቤተክርሲያንን ለመከፋፈል ሞክረዋል ተብለው ይተቻሉ። እንደ ዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ዘገባ ከሆነ አቡነ ማቲያስ በቤተክርስቲያን ተወግዘው ከነበሩባቸው ምክንያቶች መካከል በወቅቱ መንበራቸውን ጥለው በመውጣት የኢዲዩ አባል ከመሆናቸውም በላይ ሌሎች ምክንያቶችም ይጠቀሳሉ።
በአሁኑ ወቅት በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ሆነው በማገልገል ላይ ያገለገሉት አቡነ ማቲያስ በሕወሓት ሰዎች ለቤተክርስቲያን ፓትርያርክነት እንዲመረጡ ከታጩት መካከል አንደኛው ናቸው።
የኦክቶበር 11ዱን ዘገባ ይመልከቱት-
– See more at: http://amharic.zehabesha.com/archives/11230#sthash.0Tjwkkfx.dpuf