ከኢሳያስ ከበደ
(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 53 ላይ ታትሞ የወጣ)
የወሲብ ስሜት የሞራል ደንቦችን ሲፈታተን ከዘመን ዘልቋል፡፡ አሁን ያለንበት ዘመን በልቅ የወሲብ ድርጊቶች ምክንያት ሰዎች ለማህበረሰብ ደንቦች ተገዢ እንዳይሆኑ ጋሬጣ የሚሆኑ አማራጮች በሰፊው የሚዳረስበት ጊዜ ነው፡፡ ልቅ የወሲብ ድርጊት አሁን አሁን ስርጭቱ በዓለም ዙርያ ይናኝ እንጂ ከጥንት አንስቶ እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ሰዎች የወሲብ ስሜታቸውን በተለያዩ የጥበብ ስራዎች እንደገለፁ ታሪክም በመዝገቡ አስፍሯል፡፡ ልቅ የወሲብ ድርጊት (ፖርን) ዛሬ ላይ እንደ ኢንዱሰትሪ ከመንሰራፋቱ በፊት የጥንት ዘመን ሰዎች የወሲብ ስሜታቸውን በግብራቸው ሳይሆን በቅርፃ ቅርፅ፣ በስዕል እንዲሁም በስነፅሁፍ ለቀጣይ ትውልድ አስተላልፈዋል፡፡ ለዚህ አይነቱ ድርጊት እማኝ ለመሆን የታሪክ መዘውር ጥንታዊቷ የሮም ግዛት ወደነበረችው ፖምፔይ ይጠቁማል፡፡ ፖምፔይ ከአቅራቢያ ካለው ተራራ በፈነዳ እሳተ ጎመራ መርዛማ አመድ ተውጣ የወደመች ከተማ ናት፡፡ ውድመቱ ካለፈ ከዘመናት በኋላ አርኪዮሎጂስቶች በከተማዋ ፍቅር የሚሰሩ ቅርፃ ቅርፆች እንዲሁም የወሲብ ስሜት ቀስቃሽ ስዕሎች ለማግኘት ችለዋል፡፡ እነዚህ ግኝቶች ለ200 ዓመታት ከሰፊው ህዝብ እይታ ተከልክለው የቆዩ ሲሆን አሁን ላይ በካሊፎርንያ በሚገኝ ሙዝየም ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡
አዳም ሄዋንን ካወቃት ዘፍጥረት አንሰቶ እስከ አሁን ሰው በማህበረሰብ የከለከለውን ልቅ የወሲብ ስሜት በተለያዩ ስራዎች አስፍሯል፡፡ ይህም አካሄድ ካለንበት ጊዜ አንስቴ እስከ ምፅአት ቀን እንደሚቀጥል እርግጠኛ የሚያደርገን ደግሞ ኢንተርኔት ዓለምን የመቆጣጠሩ እውነታ ነው፡፡ የኢንተርኔት ግኝት የፓርን ኢንዱስትሪው ትርፋማ እንዲሆን አስችሎትል፡፡ ከልቅ የወሲብ ድርጊት ሽያጭ የሚገኝ ገቢ እንደ ስፖርት ካሉ መዝናኛዎች ከሚገኝ ገቢ በመጠን ይስተካከላል፡፡ እ.ኤ.አ በግንቦት 2001 ዓ.ም የታተመው የኒውዮርክ ታይም መፅሔት ከልቅ የወሲብ ድርጊት ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ ‹‹ ወደር የሌለው›› በማለት ገልፆታል፡፡ ፖርን በዓለም ዙሪያ ወደ 54 ቢሊዮን የሚጠጋ ዓመታዊ ትርፍ እንደሚያስገኝ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማል፡፡ ምንም አይነት ማህበረሰባዊ ቁጥጥርን አሻፈረኝ ካለው ፖርኖግራፊ ጋር የእይታ ትውውቅ የሚደረግበት አማካኝ ዕድሜ 11 ዓመት ነው፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢንተርኔት ባለበት ሁሉ ልቅ የወሲብ ድርጊቶችን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል፡፡ ኢንተርኔት ለፖርን ኢንዲስትሪው አስተዋፅኦ ቢያደርግም የድርጊቱ ውጥን ሀሳብ ጥንትም ቢሆን በሰዎች ልቦና ተቀብሮ ነበር፡፡ በጥንታዊቷ ፖምፔይ የተገኙት የወሲብ አነቃቂ ቅርፃ ቅርፆች እና ስዕሎች ሁሉንም የማወቅ ጉጉት ያለው የሰው ፍጥረት ልቅ የሆነ የወሲብ ፍላጎት ድሮም ቢሆን አሁን በውስጡ እንዳለ አመላካቾች ናቸውና፡፡
የልቅ ወሲባዊ ድርጊት ታሪካዊ ጉዞ
ከ16ኛው እስከ 18ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በወቅቱ ይከለከል የነበረውን የወሲብ ገደብ በመጋፈጥ ሰዎች የወሲብ ስሜታቸውን በስነፅሁፍ ይገልፁ ነበር፡፡ ለዚህም ጥንታዊት ሮም እና ፈረንሳይ ግንባር ቀደም ሀገራት ናቸው፡፡ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ፖርኖግራፊ አቀንቃኝ ወደሆነችው አሜሪካም ወሲብን የሚያነቃቁ ድርሰቶች መግባት የጀመሩት እ.ኤ.አ በ1780 ዓ.ም ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1789 ዓ.ም የፈረንሳይ አብዮት ፖለቲካዊ ፖርኖግራፊን ይዞ ብቅ አለ፡፡ አብዮቱ ከመቀስቀሱ በፊት የፈረንሳይ ፖለቲከኞች እና ሹማምንቶች የፖርኖግራፊ ተጠቃሞዎች ስለበሩ በወቅቱ የነበረውን የሉዊ 14ኛ ንጉሳዊ አገዛዝ ለማስወገድ የፈረንሳይ ተቃዋሚዎች ንግስት ማርያ አንቶኔት አፀያፊ ወሲብ ስትፈፅም የሚያሳይ በራሪ ወረቀቶችን ያሰራጩ ነበር፡፡ የፈረንሳይ አብዮተኞች ፖርኖግራፊን የንግሥቲቱን ስም ለማጥፋት ተጠቅመውበት እንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡፡ ይህንን ተክትሎ በፖርኖግራፊ ታሪክ ትልቅ አስትዋፅኦ ያደረገው ፈረንሳዊ ማርከስ ዴሳዴ የፖርኖግራፊን ገፅታ ከፖለቲካው መድረክ በማውረድ ልቅ ወሲብን ሁሉንም አይነት የሞራል መሰረት መዋጊያ መሳሪያ አደረገው፡፡ ሳዴ በፃፋቸው መፅሐፍቶችም ሰው በተገኘው አጋጣሚ እርካታን በአካሉ መሻት እና ማግኘት እንዳለበት ገልጧል፡፡ የሳዴ እርካታን የመሻት ሂደትም አካላዊ እንግልት እንዲሁም ሰዎችን በማሰቃየት የሚገኝ ደስትን ያካትታል፡፡ ከሳዴ ስምም በመነሳት በ1780 በኋላ የወሲብን እርካታ በአካላዊ እንግልት እንዲሁም በስቃይ ማግኘት የሚፈልገው ሰው ሳዲስት (saddest) በመባል ይጠራ ጀመር፡፡ ሳዴ ይሰብካቸው የነበሩት የወሲብ ሀሳቦች ለዛሬዎቹ የፖርን ፊልሞች ጭብጥ መሰረቶች ናቸው፡፡ ሳደም ፓርኖግራፊን መሰረታዊ የሞራል ደንቦች በገሀድ ለመፃረር የተጠቀመ የመጀመሪያው ሰው ነው፡፡ በማህበረሰብ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ተፅዕኖ ከቁጥር በማስገባት ከ18ኛ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የሳዴ ስራዎች ከብዙሀኑ ተሸሽገው ኖረዋል፡፡
የወረቀት መመረትን ተከትሎ ፖርኖግራፊ የህትመት ስራዎች መሰራጨት ጀመረ፡፡ እኤአ በ1970 ዓ.ም ፖርኖግራፊ የዶክመንተሪ ይዘት ባለው ፊልም ተዘጋጅቶ ከሀገረ ዴንማርክ ብቅ አለ፡፡ የአሜሪካውያንን የሞራል ገደብ በመጣስ ‹‹የወሲብ ነፃነት በዴንማርክ›› የሚለው ፊልም በሀገረ አሜሪካ ለእይታ በቃ፡፡ ዴንማርክም ለፖርኖግራፊ እውቅና የሰጠኝ ግንባር ቀደም ሀገር ሆነች፡፡ ቀጥሎ ወጥ ታሪክ ባላቸው የሆሊውድ ፊልሞች ውስጥ ወሲብን ልቅ በሆነ መልኩ ፊልም ውሰጥ ማካተት አስደንጋጭነቱ እየቀነሰ መጣ፡፡ ከ1980 አንስቶ እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን ባለው ጊዜ ፓርኖግራፊ አስገራሚ እድገትን አስመዘገበ፡፡ እኤአ በ1985 ‹‹የእርቃን›› እና የልቅ ወሲብ ገበያው በዓለም አቀፍ ደረጃ 75 ሚሊየን ዶላር ሲያስገባ እኤአ በ2009 ገቢው ወደ 4.9 ቢሊየን ዶላር አሻቀበ፡፡ ፓርኖግራፊም እንደ ፓሜላ አንደረስን ያሉ አሜሪካዊ እንስቶችን በወሲብ ልቅነታቸው በዓለም ዙርያ ዝነኛና ከበርቴ አደረገ፡፡ በኢንተርኔት ዘመን ከሙዚቃ፣ ከመፃህፍት፣ እንዲሁም ከአገልግሎት ሰጪ ድረገፆች ይልቅ የፖርን ድረገፆች በእጥፍ ይጎበኛሉ፡፡
ባለፉት 500 ዓመታት ማህበረሰብ ለፖርን ያለው አመለካከት መቀየሩ፣ የቴክሎጂ እድገትን ተከትሎ ድርጊቱ መስፋፋቱን እንዲሁም የሞራል መሰረቶች ፖርኖግራፊን ለመቆጣጠር እንደተሳናቸው ታሪክ ያስረዳል፡፡ የወሲብ ልቅነት አስደንጋጨ ዕድገት ታሪክ ምን ቢያወሳ እና የሚያስገባውን አህዛዊ ትርፍ መረጃዎች ቢጠቁሙም፣ ፖርኖግራፊ ልንክደው የማንችል አሉታዊ ገፅታ በማህበረሰብ ላይ ያሳድራል፡፡
የልቅ ወሲባዊ ድርጊት አሉታዊ ገፅታዎች የሀሳብ፣ የድርጊት እንዲሁም የምርጫ ነፃነት የካፒታሊዝም መገለጫዎች ናቸው፡፡ የነፃነት ሀሳብ በወሲብ ስሜት ሲገለፅ ያለ ከልካይ ስሜትን በሚያስተናግደው ፓርኖግራፊ ጣሪያውን ይነካል፡፡ በኢንተርኔት ፖርን ብለው ፍለጋ ቢያደርጉ ከ2ሚሊየን በላይ ድረገፅችን ያገኛሉ፡፡ በሀገራችን እነዚህ ድረገፆች ለሰዎች ተደራሽ እንዳይሆኑ የሚደረግ ቁጥጥር ባለመኖሩ ህፃን፣ ወጣት፣ አዋቂ፣ ጎልማሳ፣ እንዲሁም ጤናማ ማህበረሰብ ከመፍጠር አኳያ የሚያበረክተውን አሉታዊ ተፅእኖ ከቁጥር በማስገባት ፓርኖግራፊን ማውገዝ የእያንዳንዳችን ፋንታ ነው፡፡ ካፒታሊዝም የምርጫ ነፃነትን ይሰጣልና፡፡ S
Health: ፖርኖግራፊ – (ወሲባዊ ምስሎችንና ፊልሞችን የማየት ሱስ)
Latest from Blog
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤ 15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን
ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር
የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!” አቶ ቡልቻ ደመቅሳ
ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ቴዲ አፍሮና ጃዋር መሐመድ፤ ”ንጉሥ አንጋሹ ፖለቲከኛ” የዘመኑ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ የሆነው ጃዋር መሐመድ ‘አልፀፀትም’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን መጽሐፍ 🔴What separates Jawar and Abiy is their measure of how much non-Oromos
ቴዲ አፍሮና ጃዋር መሐመድ፤ ”ንጉሥ አንጋሹ ፖለቲከኛ”
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ
ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )
“ገብርዬ ነበረ የካሳ ሞገሱ…..” በጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ አብይን የሚያንዘፈዝፉት የእንስቷ ንግግሮች አድምጡት
“ገብርዬ ነበረ የካሳ ሞገሱ…..” በጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ
ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ
ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)
ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ