(ኤርሚያስ ቶኩማ)
ብዙዎቻችን ቴዲ አፍሮን ከሙዚቃ ሥራውና ከሐገር ወዳድነቱ ባሻገር እምብዛም የግል ሕይወቱን እና ምን አይነት ሰው እንደሆነ አናውቀውም እርሱም ቢሆን ስለራሱ ማውራት ስለማይወድ እና ይህንን ፈፀምኩኝ ብሎ ስለማያወራ የቴዲን ማንነት በግልጽ ልናውቀው አልቻልንም ሆኖም ቴዲ አፍሮ እንደዚህም አይነት ሌላ ገፅታ አለው።
★ ሐምሌ 30,1998 ዓመተ ምሕረት በድሬዳዋ ደርሶ በነበረው የጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ30 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ
ለወገን ደራሽነቱን አሳየን።
★ ጥቅምት 1,2002 Elshaday relief and development ባዘጋጀውና ከ50 ሺህ በላይ በተገኘበት የአዲስ አበባ ስታዲየሙ
ኮንሰርት ከ 1 ሚሊየን ብር በላይ አሰባስቦ ለእርዳታ ድርጅቱ ያስረከበ ሲሆን በእለቱ ለአበበች ጎበና ሕፃናት ማሳደጊያ 100
ሺህ ብር ለይልማ ገ/አብ የወርቅ ብእር ሸልሟል።
★ ጥቅምት 23,2002 በህመም ላይ ትገኝ ለነበረችው ማንአልሞሽ ዲቦ መታከሚያ ይሆን ዘንድ 20 ሺህ ብር አበረከተ
★ ጥቅምት 17,2004 የወጣት አስመሮም ሃይለስላሴን ነፍስ ለማዳን ለሶማሊያ ሽማግሌዎች 700 ሺህ ብር ከፈሎ የወገኑን
ህይወት አተረፈ።
★ ጥቅምት 17,2004 ለኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ማህበር የ200 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጎ ለማህበሩ ያለውን አጋርነት አሳየ። ማህበሩም የምስጋና ምስክር ወረቀት ሰጥቶታል።
★ የአራት ኪሎ ወጣቶች ከአልባሌ ሥፍራ ይርቁ ዘንድ በአባቱ ስም ተቋቁሞ ለነበረው የእግር ኳስ ቡድን ለአራት አመታት በየአመቱ ግማሽ ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
★ በራሱ አነሳሽነት ለአበበ መለሰ ኮንሰርት በማዘጋጀት የአርቲስቱን ህይወት ከህልፈት ታደገ።
★ ጥቅምት 2005 ቀድሞ ይማርበት ለነበረው ቤቲልሄም ት/ቤት የኮምፒውተር እና የሙዚቃ መሣሪያ ድጋፍ አደረገ።
ይሄ ነው ሌላኛው የቴዲ አፍሮ ገፅታ
በተለያየ ግዜያት በተዘጋጁ ዝግጅቶች ላይ እንደዚሁም እዛው ድረስ በመሄድ ለወይዘሮ አበበች ጎበና እፃናት ማሳደግያ ከመቶ ሺ ብር በላይ የገንዘብ እርዳታ።
ባለቤቱ አምለሰት ባስመረቀችው አረንጋዴ መሬት ዶክመንተሪ ፊልም ምርቃት ላይ በእንጨት ለቀማ ይተዳደሩ ለነበሩ እናት የ 20ሺብር ቼክ ሰታቸዋል።
እንደዚሁም ለተለያዩ ድምፃዊያን ግጥም እና ዜማ በነፃ የሰጣቸውም አሉ:: ይህ ህዝቡ የሚያውቀው ነው ቴዲና ድጋፍ ያደረገላቸው ብቻ የሚያውቁት ብዙ አለ።
ማሳሰቢያ ይህንን ፅሁፍ በድጋሚ የለጠፍኩት አንድ በምርቃና የድሮ መጽሔት ጽሁፎችን እየገለበጠ መፅሀፍ ካሳተመ በዃላ እራሱን እንደደራሲ ቆጥሮ ለመተቸት የሞከረ በጫት የደነዘዘ ወጠጤ በማየቴ ነው።
ትክክለኛውን ቴዲ አፍሮን ምን ያህሎቻችን እናውቀዋለን?
Latest from Blog
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤ 15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን
ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር
የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!” አቶ ቡልቻ ደመቅሳ
ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ቴዲ አፍሮና ጃዋር መሐመድ፤ ”ንጉሥ አንጋሹ ፖለቲከኛ” የዘመኑ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ የሆነው ጃዋር መሐመድ ‘አልፀፀትም’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን መጽሐፍ 🔴What separates Jawar and Abiy is their measure of how much non-Oromos
ቴዲ አፍሮና ጃዋር መሐመድ፤ ”ንጉሥ አንጋሹ ፖለቲከኛ”
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ
ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )
“ገብርዬ ነበረ የካሳ ሞገሱ…..” በጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ አብይን የሚያንዘፈዝፉት የእንስቷ ንግግሮች አድምጡት
“ገብርዬ ነበረ የካሳ ሞገሱ…..” በጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ
ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ
ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)
ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ