June 28, 2013
9 mins read

Health: እባካችሁ ንጥሻ ገደለኝ፣ አስም እንዳይሆንብኝ ፈርቻለሁ

አሁን ዕድሜዬ 37 ሲሆን ባለትዳርና የ2 ልጆች አባት ነኝ፡፡ ሀሳብ የሆነብኝ ነገር ሁሌ ጠዋት ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ተከታታይና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ማስነጠስ ልቤን ውልቅ ሊያደርጋት ይደርሳል፡፡ ሲያስነጥሰኝ ታዲያ ሰውነቴ በሙሉ በላብ ይዘፈቅና መላ ሰውነቴን ያሳክከኛል፡፡ ብዙም ሳይቆይ ደግሞ ቀጭን ፈሳሽ ከአፍንጫዬ ይወጣል፡፡ አባቴ የአስም በሽተኛ ነበርና ይህ ነገርም ታዲያ በዘር የወረስኩት አስም እንዳይሆን እጅግ ፈርቻለሁና መፍትሄ ብትለግሱኝ እላለሁ፡፡
አበራ ነኝ

ውድ ጠያቂያችን አበራ ካለማቋረጥ እንደሚያስነጥስህ፣ ከዚህ ጋርም ተያይዞ ፊትህን እንደሚያሳክክህ፣ ከአፍንጫህም ቀጭን ፈሳሽ እንደሚወጣ እና አባትህም የአስም ህመም ተጠቂ መሆናቸውን ገልፀሀል፡፡ ካቀረብካቸው የህመም ምልክቶች ተነስተን ስንመለከተው ችግርህ ከአፍንጫ መቆጣት ጋር ተያያዥ ሆኖ ይታያል፡፡ ይህ መሰል ክስተትም ለብዙ ጊዜ እንደሚደጋገምብህ ገልፀሀል፡፡ ይህም መሆኑ የአፍንጫ መቆጣት ችግር ከአንዳች መንስኤ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ያሳያል፡፡ እንዲህ መሰሉ በየወቅቱ ከአንዳች መንስኤ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ችግር ከአለርጂ ህመም አንፃር የሚታይ ይሆናል፡፡ በዋናነት ደግሞ የጠቀስካቸው ምልክቶች ለአፍንጫ አለርጂ አይነተኛ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህን የመሰለ ህመም በህክምና መጠሪያው ‹‹የአፍንጫ አስም›› ወይም ‹‹አለርጂክ ሳይንሳይስቲስት›› ብለን ልንጠራው እንችላለን፡፡
የአፍንጫ አስም (አለርጂ) ልክ እንደሳንባ አለርጂ ትንፋሽ የማሳጠር፣ ሳል የማሳልና ሲተነፍሱ ‹‹ሲር ሲር›› የሚል ድምፅ የማያሰማ ይሁን እንጂ ዋና መንስኤው ከአለርጂ ጋር በመያያዙ ይመሳሰላሉ፡፡ እንዲሁም ህመሞቹ በየጊዜው እያሰለሱ የመምጣታቸውም ጉዳይ እንዲሁ ይመሳሰላል፡፡ የሚደረግላቸውም ህክምና ፀረ አለርጂ መድሃኒቶች በመሆናቸው ተያያዥ መሆናቸውን ያመለክታል፡፡ አንዳንዴ የአፍንጫ አለርጂ (አስም) ለሳንባ አስም (አለርጂ) ክስተት ጠቋሚ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ማለት ግን የአፍንጫ አስም ያለበት ሁሉ ወደ ፊት የሳንባ አስም ይከሰትበታል ማለት አይደለም፡፡ ከደብዳቤህ እንደተረዳነው አባትህ የአስም ህመም ያለባቸው እንደመሆናቸው መጠን አንተም የአፍንጫ አለርጂ ቢኖርብህ ብዙም አያስገርምም፡፡ ምክንያቱም አለርጂ በባህሪው በዘር የመተላለፍ ባህሪ ያለው በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ወደ ፊት ልክ እንደ አባትህ የሳንባ አስም ተጠቂ ትሆናለህ እያልን አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ በአፍንጫ አለርጂ መልክ ግን መከሰቱ አልቀረም፡፡
ውድ አበራ አለርጂ ማለት ሰውነታችን ለአንድ ለሚያስቆጣው ነገር ሲጋለጥ የሚከሰት ችግር ነው፡፡ እንዲህ አይነት ባህሪው የሚኖራቸው ደግሞ አንዳንድ ሰዎች በተፈጥሯቸው አለርጂውን ለሚቀሰቅሰው ነገር ቁጠኛ ሲሆኑ ነው፡፡ ሰውነታችንም እንዲህ መሰሉን ቁጠኝነት የሚገልፀው በሰውነታችን የበሽታ መከላከያ ሃይል በኩል ሲሆን እነዚህም ሃይላት በሚያመርቷቸው ኬሚካሎች (በተለይ ‹‹ሂስታሚን›› የተባለው ኬሚካል) ቆዳን የማሳከክ፣ አፍንጫን የመለብለብ፣ ንፍጥ የማዝረክረክና ማስነጠስ መሰል ምልክቶችን እንዲያሳይ ያደርጋል፡፡ የተለያዩ ሰዎች ለተለያዩ ነገሮች ሰውነታቸው ተቆጭ ሊሆን ይችላል፡፡
በተለያዩ አበቦች ውስጥ የሚገኘው ፓለን፣ አንዳንድ ምግቦች፣ የተወሰኑ የመድሃኒት አይነቶች፣ የአቧራ ብናኞች፣ የእንስሳት ፀጉር (በተለይም ድመት)፣ የፋብሪካ ጭሶች (ወይም የሲጋራ ጭስ)፣ እንዲሁም መርዘኛ ነፍሳቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ የአለርጂ መነሻ ምክንያቶች ያሏቸው በመሆኑም ማን ሰውነቱ ለየትኛው የአለርጂ መነሻ ሊቆጣ እንደሚችል በውል ለይቶ ማወቅ ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ የድመት ፀጉር ሲሸታቸው አለርጂው የሚነሳባቸው ሰዎች ችግሩ እንዳይቀሰቀስባቸው መንስኤ የሆነችውን ድመት ማራቅ ይኖርባቸዋል፡፡ በመሆኑም አንተም ብትሆን አለርጂው በምን እንደሚነሳብህ ለይተህ በማወቅ እንዳይደጋገምብህ ከሚያስነሳብህ መንስኤ መራቅ አንዱ የመከላከያና የህክምና አማራጭ ነው ማለት ነው፡፡
ውድ ወንድማችን ከዚህ ውጭ ከላይ የጠቀስካቸው ምልክቶች ሲከሰቱብህ የሚከተሉትን መድሃኒቶች በማስታገሻነት መውሰድም ይመከራል፡፡ ባለ 4 ሚግ አንድ ኪኒን ክሎርፌኒራሚን (Chlorpheniramine) በቀን (Cetrizine) በየቀኑ ልትወስድ የምትችል ሲሆን ምልክቶቹም እንዳቆሙልህ መድሃኒቶችን መውሰድ ታቆማለህ፡፡ ወደ ፊትም ሲነሳብህ በዚህ መልኩ መቀጠል ይኖርብሃል፡፡ የአፍንጫን አለርጂ ከላይ ባለው መልኩ ለመከላከል እና ለማስታገስ መሞከር እንጂ ማዳን አይቻልም፡፡
ከዚህ በተጨማሪ አንዳንዴ ይህ የአፍንጫ አለርጂ ወደ ‹‹ሳይነሳይቲስ› ሊቀየር የሚችልበት እድሉ ስላለም ልታጤነው ይገባል፡፡ በተለይ የአፍንጫህ ፈሳሽ ወፍራምና ወደ ቢጫነት እየተቀየረ ከመጣ ስትናገር የአፍንጫህን መዘጋት በመነፋነፍ መልኩ ከታዘብክ እንደትኩሳትና ራስ ምታት አብረው ከታዩ በተጨማሪ ህክምናነት የአንቲባዮክ ህክምና ሊያስፈልግህ ይችላል፡፡ (ለምሳሌ ባለ 250 ሚሊ ግራም አንድ ክኒን አሞክሳስሊን በቀን ለሶስት ጊዜ ለ7 ቀናት ልትወስድ ትችላለህ) ይህ ህክምና የሚያስፈልገው ‹‹ሳይነሳይቲስ›› የተባለው የአፍንጫ መመርቀዝ ህመም በባክቴሪያዎች ሊመጣ ስለሚችል ነው፡፡ ውድ አበራ ከረጅሙ በአጭሩ ለጥያቄህ ያለው ምላሽ ይህን ይመስላል፤ መልካም ጤንነት፡፡

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop