July 25, 2014
12 mins read

Health: በእንቅልፍ ልቤ ከብልቴ የሚወጣውን ፈሳሽ እንዴት መቆጣጠር እችላለሁ?

(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 51 ላይ ታትሞ የወጣ)
ጂቲ እባላለሁ፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ፡፡ ዋነኛ ችግሬ ምን መሰላችሁ? በእንቅልፍ ልቤ በተደጋጋሚ የዘር ፍሬዬ እየፈሰሰ ተቸግሬያለሁ፡፡ ይህ ችግር በተደጋጋሚ መከሰት ከጀመረ አንድ ዓመት ይሆነኛል፡፡ በሳምንት ቢያንስ ሶስት ቀን ይህ ችግር ይከሰትብኛል፡፡ ሁሌም ከእንቅልፌ ስነቃ በተደጋጋሚ የሌሊት ልብሴ፣ የውስጥ ሱሪዬ እና አንሶላዬ ረጥቦ እና አልጋዬ ባልተለመደ ጠረን ታውዶ አገኘዋለሁ፡፡ ይህ ነገር ደግሞ ለሀፍረት ስሜት ያጋልጠኛል፡፡ ለራስ ምታት ህመምም ይዳርገኛል፡፡ ገና ተማሪ ስሆንኩ እስካሁን የሴት ጓደኛ የለኝም፡፡ ወሲብም ፈፅሜ አላውቅም፡፡ አልፎ አልፎ ግን ማስተርቤት አደርጋለሁ፡፡ ስለዚህ ውድ የዘ-ሃበሻ አዘጋጅ ይሄ ነገር የሚከሰትብኝ ለምንድን ነው? ወሲብ ብጀምርስ ይህ ነገር ይጠፋል? ከዚህ ነገር መላቀቅ የምችለው እንዴት ነው? እባክህ ለችግሬ መልስ ፈልግልኝ፡፡ ጂቲ ነኝ

የዶ/ር ዓብይ ዓይናለም ምላሽ፡- በተፈጠረብህ ነገር ብዙ አትደናገጥ፡፡ ምክንያቱም ይህ ችግር ያንተ ብቻ ሳይሆን የብዙ ወንድ እና ሴት ወጣቶች እንዲሁም ጎልማሶች ችግር ነው፡፡ እንደ የተለየ ጤና ችግር በመቁጠርም አትረበሽ፡፡

በእንግሊዝኛ ኖክቱርናል ኢሚሽን (Nocturnal Emission) በመባል የሚታወቀው በሌሊት የሚከሰት የዘር ፍሬ በዘፈቀደ መፍሰስ በአብዛኛው በወጣትነት ዕድሜ ላይ በሰውነት ውስጥ የሚከሰት ባይኮሎጂካል እና የሆርሞን ለውጦችን ተከትሎ በስፋት የሚከሰት ጤናማ የጉርምስና ምልክት ነው፡፡ በተደጋጋሚ የሚከሰት ከሆነ ግን ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ እንገደዳለን፡፡ ነገር ግን ይህ ችግር በአነስተኛ መጠንም ቢሆን በጎልማሶች እና በአረጋዊያን ላይም ሊከሰት ይችላል፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በእንቅልፍ ልብ የዘር ፍሬ የሚፈሰው በሁለት መልኩ ነው፡፡ የመጀመሪያው እና በአብዛኛው የሚከሰተው በእንቅልፍ ልብ የብልት መወጠርን (መቆምን) ተከትሎ ነው፡፡ ይህ ነገር በአብዛኛው ወሲባዊ ህልሞችን በመመልከት እና በወሲባዊ ሀሳብ መወጠርን ተከትሎ የሚከሰት ነው፡፡ በአንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ ብልት ሳይወጠርም የዘር ፍሬ ሊፈስ ይችላል፡፡ ይህ ነገር ደግሞ ከወሲባዊ ሀሳቦች ጋር የተገናኘ አይደለም፡፡ ስለዚህ የአንተ ችግር ከሁለቱ በየትኛው ውስጥ እንደሚወድቅ ለራስህ መልስ ስጥ፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ወንዶች 84 በመቶ የሚሆኑት ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ይህ ችግር ይከሰትባቸዋል፡፡ በተደጋጋሚ የማስተርቤሽን ተግባር የሚፈፅሙ ወጣቶች በእንቅልፍ ልብ የዘር ፈሳሽ ለመፍሰስ ችግር የተጋለጡ ናቸው፡፡ በመንስኤው ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚገልፁት በእንቅልፍ ልብ የሚከሰተው የዘር ፍሬ መፍሰስ ወሲብ ካለመፈፀም ጋር እንደማይገናኝ ይጠቁማሉ፡፡ በእንቅልፍ ልብ ዘር ፍሬ የመፍሰስ አጋጣሚ የሚፈጠረው በተለያዩ ምክንያቶች ነው፡፡ በሰውነታችን ውስጥ በሚከሰት የሆርሞኖች ለውጥ የመጀመሪያው ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የዘር ፍሬ ክምችት በሰውነታችን ውስጥ መኖር ደግሞ በሁለተኛነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች በተጨማሪ ወሲብ እና ተያያዥ ጉዳዮችን ሲፈፅሙ ህልም ማየት እና ስለወሲብ ደጋግሞ ማሰብ እንዲሁም ከመኝታ በፊት ወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞችን መመልከት እንዲሁም መጽሐፍትን ማንበብ በእንቅልፍ ወቅት ዘር ፍሬ የመፍሰስ ችግርን እንደሚያስከትል ይጠቁማሉ፡፡

ወድ ጠያቂያችን ጂቲ በወር አንድ ጊዜ እና ሁለት ጊዜ በእንቅልፍ ልብ የዘር ፍሬ የመፍሰስ ችግር ጤናማ እንዲሁም ተፈጥሯዊ እና ምንም አይነት ችግር የሌለው ነው፡፡ ነገር ግን በየቀኑ እና እንደ አንተ በሳምንት ሁለት ሶስቴ የሚከሰት ከሆነ እና እሱን ተከትሎ መደበርን፣ ራስ ምታትን፣ አቅም እንዲሁም እንቅልፍ ማጣትን የሚያስከትል ከሆነ ግን ጤናማ ስላልሆነ በፍጥነት ባለሞያን ማማከር ያስፈልግሃል፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር በሰውነታችን ወስጥ የሚኖረውን የቴስቴስትሮን መጠን በማሳነስ ለተለያዩ ሆርሞን ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የዘር ፍሬ በብዛት መፍሰስ በሰውነታችን ውስጥ ጤናማ ያልሆነ የዘር ፍሬ ፈሳሸ ምርት ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ጤናማ ያልሆነ የዘር ፍሬ ምርት ደግሞ በተለይ ወንዶችን ለመሀንነት ችግር ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ የዘር ፍሬ ብዛት በመመረቱ የተነሳ የዘር ፍሬ በብዛት የሚፈስ ከሆነ የሚፈሰው የዘር ፍሬ በአብዛኛው ትክክለኛ ቅርጽ እና መጠን ያለው ስለማይሆን ከሴት እንቁላል ጋር ተገናኝቶ ጽንስ የመፍጠር አቅሙ እጅግ አነስተኛ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ይህ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ያለው የዘር ፍሬ ክምችት አነሰተኛ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ በአንድ ጊዜ በሚፈስ የዘር ፍሬ ውስጥ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሴሎች ይገኛሉ፡፡ በአንድ ሚሊ ሊትር የዘር ፈሳሽ ውስጥ የሴሎች ብዛት ከ20 ሚሊዮን በታች ከሆነ ጽንሰ የመፍጠር አቅም አይኖረውም፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በእንቅልፍ ልብ የዘር ፍሬን መፍሰሰ በወሲብ ወቅት ከሴቷ በፊት ቀድሞ የመርካት ችግርን እና ሌሎች ስንፈተ ወሲብ ችግሮችን ያስከትላል፡፡ የሰውነት ክብደት መቀነስን እና በራስ የመተማመን መንፈስንም ያሳጣል፡፡ ለራሳችን የምንሰጠውን ግምት በመሸርሸርም የፀፀት እና የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡

ወደ መፍትሄው ስንመጣ የመጀመሪያው በጀርባ አለመተኛት ነው፡፡ ወደ መኝታ ከመሄድ በፊት ወተት አለመጠጣት እና ብዙ ምግብ አለመመገብም ይመከራል፡፡ በተለይ ደግሞ እራት ወደ መኝታ ከመሄዳችን ቢያንስ ከ3 ሰዓት በፊት መመገብ እና እራት ላይ ብዙ ቅመም የበዛበት ምግብን፣ ከመጠን በላይ ወይን ከመጠጣት፣ እንቁላል፣ ስጋ እና ሌሎች አነቃቂ ነገሮች የበዛባቸው ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ ቢቻል እራት ላይ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን ማዘውተር ጠቃሚ ነው፡፡ ሌላው መፍትሄ ደግሞ ምግብን በደምብ አድቅቆ መመገብ እንዲሁም የፈሳሽ አወሳሰዳችንን ማስተካከል ነው፡፡ በተለይ ከእራት በኋላ ብዙ ፈሳሽ አለመውሰድ፣ ቀን ላይ ብዙ ውሃ መጠጣት፣ ከመኝታ በፊት ሽንትን መሽናት ጠቃሚ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የዘር ፍሬ የሚፈሰው ሊነጋጋ ሲል ስለሆነ በጠዋት የመነሳት ልማድን ማዳበርም ይመከራል፡፡

ውድ ጂቲ ፈረስ መጋለብን እና ሳይክል መንዳትን የመሳሰሉ ችግሮችንም ለዚህ ችግር ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ መሰል ተግባራትን መቀነስም ጠቃሚ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የእግር ጉዞ ማድረግ፣ ከመኝታ በፊት ወሲብ ቀስቃሸ ፊልሞችንም ሆነ ጽሁፎችን ከመመልከት እና ከማንበብ መቆጠብ፣ እለታዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማዘውተር እንዲሁም ብልት እና አካባቢውን በየቀኑ በአግባቡ ማጽዳት እና የተመጣጠነ የአመጋገብ ስርዓትን ማዳበር ጠቃሚ ነው፡፡

በእንቅልፍ ልብ ካለፍቃድ እና ካለፍላጎት የዘር ፍሬ የመፍሰስ ችግርን ከላይ በመፍትሄነት የተዘረዘሩትን ነገሮች በአግባቡ እና ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ በማድረግ ካለብህ ችግር መላቀቅ ትችላለህ፡፡ በእነዚህ መንገዶች የምትፈልገውን ለውጥ ማምጣት ካልቻልክ ግን በአፋጣኝ ባለሞያዎችን ማማከር ይገባሃል፡፡

(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 51 ላይ ታትሞ የወጣ)

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop