October 3, 2014
21 mins read

Health: የወሲብ አፈፃፀም ለጡንቻ፣ ለወገብና ለጀርባ ህመም ይዳርጋል እንዴ?

ጥያቄ፡-1
እግሬን በጣም ይሸመቅቀኛል፡፡ ብዙዎች ሲናገሩ እንደምሰማው የቁም ወሲብ ለዚህ እንደሚያጋልጥ ነው፡፡ እኔ ደግሞ ይህንን ድርጊት በተደጋጋሚ ፈፅሜያለሁ፡፡ ታዲያ ችግሬ ከዚህ የመጣ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ምክንያቱም ሌላ የጤንነት ችግር የለብኝም፡፡ እውን የእግሬ መሸማቀቅ ከቁም ወሲብ የመጣ ነው? መፍትሄውስ ምንድነው?
ተዘራ

ጥያቄ፡-2
ለተከበራችሁ ለጤና አምድ አዘጋጆች፤ ከባለቤቴ ጋር ወሲብ በምንፈፅምበት ሰዓት ወገቤንና ጀርባዬን ያመኛል፡፡ በተለይም ባለቤቴ ከኋላ ሆኖ የሚፈፅመውን የወሲብ (ፖዚሽን) ጀርባዬን ያሳምመኛል፡፡ ምን ባደርግ ይሻለኛል? ህመሙ አስቸግሮኛል፤ ባለቤቴንም ማስቀየም አልፈልግም፡፡ እስቲ አንድ በሉኝ፡፡
የዘወትር አንባቢያችሁ ነኝ

መልስ፡-ውድ ጠያቂዎቻችን የሁለታችሁም ጥያቄዎች ጭብጥ ተመሳሳይ በመሆኑ በአንድ ላይ አስተናግደናቸዋል፡፡ መልካም ንባብ፡፡
ውድ ተዘራ፡- ከተለመደው ባህላችን ውጪ ምንም ሳትፈራ እንደ ወሲብ ባሉ ‹‹አይነኬ›› ጉዳይ ላይ በግልፅ መጠየቅህ የሚበረታታ ነው፡፡ ለችግሮቻችን ተገቢውን መፍትሄ ለማግኘት በግልፅ መጠየቅ፣ መወያየት፣ መነጋገር… ልናዳብረው የሚገባ ባህል ነውና፡፡
ይህን እንደመግቢያ ካልኩ በቀጥታ ጥያቄህን ወደ መመለሱ ላምራ፡፡ በደብዳቤህ የገለፅክልን ዋነኛ የጤና ችግር የእግር መሸማቀቅ ነው፡፡ በተለይም በተደጋጋሚ ፈፅሜዋለሁ ላልከው ከቁም ወሲብ ጋር የተያያዘ መሆን አለመሆኑን ነው የጠየከን፡፡ ጥያቄህ ጠቅለል ባለ መልኩ ስለቀረበ አንዳንድ ዝርዝር ሁኔታዎችን ለማወቅ ይከብዳል፡፡ በተለይም የእግር መሸማቀቁ ይበልጥ ብታብራራው ኖሮ ጥሩ ነበር፡፡ ማለትም መቼ እንደ ጀመረህ፣ እንዴት እንደሚነሳብህ፣ ምን ያህል እንደሚቆይ፣ የሚያባብስብህ፣ የሚያስታግሱልህ ሁኔታዎች ምን ምንድናቸው? ወሲቡን እንደፈፀምክ ወዲያው ነው የሚጀምርህ፣ ወይስ ዘግይቶ፣ የመሸማቀቁ ሁኔታስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ ሄዷል ወይስ እየቀነሰ… የሚሉትንና ሌሎች ተዛማጅ ሁኔታዎችን ብታብራራልን ኖሮ የችግሩን ምንነትና መንስኤውን ለማወቅ ይበልጥ ይረዳን ነበር፡፡
ይሁንና አንተ ከፃፍክልን መረጃ ተነስተን በወሲብ እንቅስቃሴና በእግር መሸማቀቅ/በጡንቻ ህመም መሀል ያለውን ተዛምዶ ለማየት እንሞክር፡፡ እንደመነሻ ወሲብና እንቅስቃሴዎቹ ለጤና ያላቸውን ፋይዳ በመግለፅ እንጀምር፡፡

ወሲብና የጤና ፋይዳዎቹ
ወሲብ ከፈጣሪ ለሰው ልጆች ከተሰጡ ፀጋዎች አንዱ ነው፡፡ ከአዳምና ሄዋን መፈጠር ጀምሮ ያለና ለህይወት ቀጣይነት እጅጉን አስፈላጊ ከሆነ ጠቃሚ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ወሲብ በአግባቡ ከተፈፀመ ዘርን ከመተካት ባለፈም አብሮነትንና የፍቅር ህይወትን በማጣፈጥ ትዳርንና ኑሮን የሚያጎለብት የህይወት ቅመም ነው፡፡
ጤናማ ወሲብ
– ራስ ምታትን ያስወግዳል፣
– ከጭንቀትና ከድብርት ይገላግላል፣
– ውፍረትን በመቀነስና ትርፍ ስብን በማቃጠል በአላስፈላጊ ውፍረት ሳቢያ የሚመጡ የጤና እክሎችን ይከላከላል፣
– ለቆዳ ውበትና ለፀጉር ዕድገት ይረዳል፣
– የዳበረ ጡንቻና ጥሩ ቅርፅ እንዲኖረን ያደርጋል፣
– አዕምሮን በማረጋጋት ሰላም እንዲሰፍን ያደርጋል፣
– ሌላም ሌላም
በእነዚህና በሌሎች ፋይዳዎቹ አዕምሯዊም ሆነ አካላዊ ጤናችንን የተሟላና የተጠበቀ ያደርጋል፡፡
ይሁንና ጥንቃቄ የጎደለውና ጤናማ ያልሆነ ወሲባዊ ተራክቦ (unsafe sex) ብዙ የጤናማ ማህበራዊ ችግሮችን ሊያስከትል እንደሚችል ግልፅና ግልፅ ነው፡፡ ስለሆነም ጠያቂያችንም ሆነ ሌሎች አንባቢዎቻችን ከወሲብ ጋር በተያያዘ ሁሉም ይህን ማስታወስ እንደሚገባው ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡
ስለወሲብም ሆነ የጤና ተጽዕኖዎቹ ይህን ያህል ካልኩ በቀጥታ ጥያቄዎቹን ወደ መመለስ ላምራ፡፡ ሁለቱም ጥያቄዎች በወሲብ ተራክቦ ወቅት የሚደረጉ አካላዊ እንቅስቃሴዎች ሊያስከትሉት በሚችሉት የአካል ጉዳት በመሆናቸው አያይዘን እንመልሳቸዋለን፡፡

የወሲብ እንቅስቃሴና የጡንቻ መሸማቀቅ
በወሲብ ተራክቦ ወቅት መላው የሰውነታችን ጡንቻዎች ከባድ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡ በተለይም የዳሌ፣ የወገብ፣ የታችኛው ጀርባ ክፍል፣ የሆድ፣ የብልት፣ የእጅና የእግር ጡንቻዎች ትልቁን ድርሻ በመውሰድ ወሲባዊ እርካታን ከመፍጠርም ባሻገር ከላይ ለተገለፁት የጤና ፋይዳዎች ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡ ይሁንና ማንኛውም ፋዳ ያለውና እርካታን የሚሰጥ ነገር አንፃራዊ ጉዳይ ሊኖረውም ይችላልና የእነዚህ ጡንቻዎች መድከም ወይም መዛልም አልፎ አልፎ ድካምን፣ የህመም ስሜትን ብሎም ከበድ ያለ የጡንቻ መሸማቀቅን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ይህም እንደየሰውና እንደየአፈፃፀሙ ይለያያል፡፡ ማለትም በተለያዩ የስፖርትም ሆነ የስራ እንቅስቃሴዎች የፈረጠሙና ጠንካራ ጤንቻዎችና ሰውነት ያለው ሰው ከመጠነኛ ጊዜያዊ ድካም ባለፈ ምንም ችግር ላይከሰትበት ይችላል፡፡ እንዲሁም የወሲቡ አፈፃፀም ሁኔታም የራሱ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ማለትም ተራክቦው ለምን ያህል ጊዜ መቆየቱ፣ ፍቅር ሰሪዎቹ የሚጠቀሙት የተራክቦ አቅጣጫ (position)፣ የድግግሞሹ ብዛት፣ የሚያደርጉበት ቦታ፣ ሌሎች የጤና ችግሮች መኖር አለመኖራቸው ወዘተ… ለተጠቀሱት ህመሞች የሚኖራቸው አስተዋፅኦም ይለያያል፡፡ በጡንቻዎች ላይ ከፍተኛ ሚናን ሊፈጥሩ የሚችሉ የተራክቦ አይነቶች በተደጋጋሚና ለረዥም ሰዓት የሚፈፅም ሰው የጡንቻ መሸማቀቅ፣ የወገብ ህመም፣ የጀርባ ህመምና አጠቃላይ ድካም ይበልጥ ሊሰማው ይችላል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የመጀመሪያው ጠያቂያችን የጠቀስከው አይነት ችግር ነው፡፡ በተደጋጋሚ የቁም ወሲባዊ ተራክቦን መፈፀምህንና እግርህን እንደሚያሸማቅቅህ በመግለፅ የሁለቱን ተዛምዶና የመፍትሄ ሀሳብ ጠይቀኸናል፡፡ ጠያቂያችን የጠቀስከው የተራክቦ አቅጣጫና አፈፃፀም ከፍተኛ የሆነ የጡንቻ ጥንካሬን የሚጠይቅና አድካሚ በመሆኑ ያለውን አይነት መሸማቀቅና ህመም ሊያስከትል ይችላል፡፡ በተለይ የፍቅር አጋርህን የመደገፍና የመሸከም ጫና ከታከለበት ተጨማሪ ኃይልና ጥንካሬን ሊጠይቅ ይችላል፡፡ በተለይም በዚህ አይነቱ የአፈፃፀም ሁኔታ ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት የታፋና የዳሌ ጡንቻዎች የመዛል፣ የመሸማቀቅና (Muscle spasm) ‹‹ስትራፖ›› የሚባለውን አይነት የመጠዝጠዝ ህመሞች ይከሰትባቸዋል፡፡ እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ሁሌና በሁሉም ሰው ላይ ሳይሆን እንደየሰዉና ሁኔታው ይለያያል፡፡
የጠያቂያችንም ህመም በቀጥታ ከወሲባዊ ተራክቦው ጋር የተያያዘ ነው ለማለት በቂ መረጃ ስላልሰጠኸን አስቸጋሪ ነው፡፡ ለምሳሌ ሁሉም በተራክቦው ወቅትና ያንን ተከትሎ የህመም ስሜቱ የሚከሰት ከሆነና ካለ ወሲባዊ እንቅስቃሴው የማይከሰት ከሆነ በእርግጥም መንስኤው እሱ ነው ሊባል ይችላል፡፡ ሌላው ከወሲባዊ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውና ሁለተኛዋ ጠያቂያችን ያነሳችው የወገብና የጀርባ ህመም ጥቂት ልበልና ወደ ጋራ የመፍትሄ ሀሳብ እመለሳለሁ፡፡

ወሲብና የጀርባ ህመም
ይህም በአንዳንድ ሰዎች ላይ በተለይም በሴቶች ላይ በወሲባዊ እንቅስቃሴ ሳቢያ ሊከሰቱ ከሚችሉ አንፃራዊ የወሲብ ጉዳቶች አንዱ ነው፡፡ በተለይም የሰባን የጎን፣ የወገብና የማህፀን አካባቢ ጡንቻዎችን (pelvic muscle) ይበልጥ የሚንቀሳቀሱበትን የወሲብ አቅጣጫና አፈፃጸም ለጀርባ ህመምና ለወገብ ህመም የመጋለጡን ዕድል ይጨምረዋል፡፡ በተለይም የሴቷ ለሩካቤ ስጋው ያላት ተነሳሽነትና ፍላጎት እንዲሁም አፍቃሪዎች ያንን ተገንዝበው ዘና ብለው ለጋራ እርካታ ስሜት ለስሜት ተግባብተው አብረው ወደ ፍትወተ ፈንጠዝያ (orgasm) የሚደርሱበትን ወሲባዊ መጣጣም መፍጠር መቻል አለመቻላቸው ለህመሞቹ መከሰት አለመከሰት ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ ያ ሳይሆን ቀርቶ ፍላጎቱና ምቾቱ ሳይኖራት በማትፈልገው አቅጣጫና ሁኔታ የምታደርገው ተራክቦ ጡንቻዎቹ ይበልጥ በማኮማተር እንዲሸማቀቁና ህመም እንዲያስከትል ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ በመጣጣም፣ በሙሉ ፍላጎትና ዘና ባለ ሁኔታ ከሆነ ግን የጡንቻዎች መላላትና ዘና የሚያደርጉ ወሲባዊ ንጥረ ኬሚካሎች መመንጨት ስለሚኖሩ ምንም የህመም ስሜት አይኖርም፡፡ መጠነኛ ህመም ቢኖር እንኳ በደስታውና በእርካታው ይሸፈናል- አስደሳች ህመም ይሆናል ማለት ነው፡፡
የእነዚህ አለመመቸትና የህመም ስሜቶች ከላይ እንደተብራራው ከሴት ሴትና ከሁኔታ ሁኔታ ይለያያል፡፡ ለዚህ አስተዋፅኦ ከሚያደርጉት አንዱ የተራክቦው አቅጣጫ (position) ሲሆን ጠያቂያችን እንደጠቀስሺው አይነት ወንዱ ከኋላ ሆኖ የሚፈፅመው ተራክቦ ለጀርባና ለጎን ህመም የመዳረግ ዕድሉ ይጨምራል፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ቅድመ ሁኔታ ካልተሟላ ደግሞ ህመሙ የከፋ ሊሆን ይችላል፡፡ ጠያቂያችን እነዚህን ሁኔታዎች በዝርዝር ስላልገለፅሽልን ያንቺም የጀርባ ህመም እንደመጀመሪያው ጠያቂያችን መንስኤው ወሲባዊ ነው ለማለት ቢከብድም ከዚያ ጋር የተያያዘ ሊሆንም ይችላል፡፡ ከዚህ ማብራሪያ ተነስተሽ ነው ወይስ አይደለም ለማለት ህመሙ የሚከሰትበትን የሚብስበትን ወቅትና ሁኔታ፣ የሚያባብሱና የሚያረግቡ ሁኔታዎች ምን ምን እንደሆኑ፣ በየጊዜው እየባሰ ነው ወይስ እየቀነሰ የሚሄደው፣ ወዘተ… የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ይኖርብኛል፡፡
ይህን ያልኩበት ምክንያት የጀርባ ህመም ከቀላል እስከ ከባድ የተለያዩ መንስኤዎች ስላሉት ተቻኩሎ በወሲቡ ሳቢያ ነው ማለት ሊያናጋም ይችላልና ነው፡፡ አብዛኞቹ የጀርባ ህመም መንስኤዎች ቀላልና የሚያሳስቡ ቢሆንም አንዳንድ ለከፋ የጤና ችግር ሊዳርጉ የሚችሉ መንስኤዎችም ስላሉ እንደነዚህ አይነቶቹ ላለመኖራቸው በደንብ እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ጥርጣሬው ካለም ወደ ተገቢው የህክምና ባለሙያ ዘንድ ሄዶ ማረጋገጥ ብልህነት ነው፡፡
በተለይም የጀርባ ህመም ከበድ ያለና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና ስራ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ከሆነ እንዲሁም የሌሎች የፀና ህመም ጠቋሚ ምልክት ከሆነ ቶሎ ህክምና ሊያስፈልገው ይችላል፡፡ ለምሳሌ የህመሙ ሁኔታ ከጊዜው ወደ ጊዜ እየጨመረ ከሄደ፣ ከአከርካሪ ህመምና እብጠት ጋር የተያያዘ ከሆነ፣ ወደ ታፋና እግር የሚሰራጭ የመደንዘዝ ወይም የመጠዝጠዝ አይነት የነርቭ መጎዳት ምልክቶች አብረው ከተከሰቱ፣ እንደ ትኩሳት፣ ሳል፣ መክሳት የመሳሰሉ የበሽታ ምልክቶች ካሉ… ፈጥኖ ወደ ሐኪም መሄድ ያስፈልጋል፡፡

ወሲብን ተከትሎ ለሚከሰት የጡንቻ ህመም መፍትሄዎች
ህመሙ ወዲያው የማይጠፋና አሳሳቢ ከሆነ መፍትሄ ያሻዋል፡፡ ያለበለዚያ ከወሲቡ የሚገኘውን ሐሴት ሊያጠፋው ይችላል፡፡ እንደሚታወቀው ወሲብን ጣፋጭ ሊያደርጉ የሚችሉ የተለያዩ የወሲብ አፈፃፀም አቅጣጫዎች ስላሉ ከእነዚህ ውስጥ የትኛው ይሻለናል፣ ይበልጥ ምቾት የሚሰጠንስ የቱ ነው? ለህመምና ለምቾት ማጣት የሚዳርገኝ የትኛው ነው? በማለት መጠየቅና የተሻለውን መምረጥ ያስፈልጋል፡፡ ምናልባትም ይህን ለይቶ ለማወቅ የተለያዩ አቅጣጫዎችን ደጋግሞ መሞከር ያስፈልግ ይሆናል፡፡ በዚህ ሂደትም ሆነ ተራክቦው ህመም በሚያስከትልበት ጊዜ የወሲብ ተጣማሪን/የፍቅረኛ አጋርነትና ሁኔታውን ተረድቶ ማመቻቸት ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡ እናም ስለ ሁኔታው በግልጽ ተነጋግሮ ምቾት ያለውን ተራክቦ አቅጣጫና ሁኔታን በጋራ መምረጥ ችግሩን ያቃልለዋል፡፡
ይህ ሁሉ ተሞክሮ አሁንም የጡንቻ መሸማቀቁና የጀርባ/የወገብ ህመሙ አልታገስ ካለ አንዳንድ ቀድሞ የመከላከል እርምጃዎችን ከተራክቦው በፊትና በኋላም መውሰድ ችግሩን ሊያቃልል ይችላል፡፡ ቀለል ያሉ የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች፣ በሙቅ ውሃ መታጠብ፣ የጡንቻ መኮማተር ካለም በበረዶ ማላላት፣ ህመም ባለበት ቦታ ለስለስ ባለ ሁኔታ መታሸት (massage)፣ የተራክቦን ቦታ ምቹና የማይቆረቁር ማድረግ፣ እና ጡንቻዎችንና ስሜትን በጥሩ ማነሳሻ (warming up) መጀመር ችግሩን ከሚቀንሱ የመፍትሄ እርምጃዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ከዚህ ባለፈ ሁለቱ ተጣማሪዎች እስከተመቻቸው ድረስ የፈለጉትን አይነት የወሲብ አቅጣጫ በፈለጉበት ሁኔታ በመጠቀም ምቾታቸውንና ጤናቸውን ማጎልበት ይችላሉ፡፡ ታዲያ መሰረታዊ በሽታን የመከላከል ጥንቃቄዎች ሳይዘነጉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ጤናማ ወሲባዊ እንቅስቃሴ የሚሰጠው የጤና ጥቅም በጂምናዚየም ውስጥ ከሚደረጉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ባልተናነሰ ለጤናማ ሰውነት እንደሚጠቅም በመስኩ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
ወድ ጠያቂዎቻችን ከሰጠኋችሁ ማብራሪያ ግንዛቤን እንዳገኛችሁ በመተማመን መልካም የፍቅር ህይወትን እየተመኘሁ ልሰናበት፡፡ ሰላም!!

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop