በሰባ ደረጃ
ከመኮንን ድልድይ ከእንጨት ፎቁ በላይ
ሲመሽ እንገናኝ
መጣሁ አንቺን ብዬ ሳይከብደኝ እርምጃዉ
በሰባ ደረጃዉ
አዝማች፡
በሳሪያን ኮት ላይ ያንን ቀጭን ኩታ ጣል አድርጌ
በመኮንን ድልድይ ልምጣ በደረጃዉ በፒያሳ አድርጌ
በፍቅር ማነቂያዉ ዶሮ እንዳይል በከንቱ እረ አንቺን ወዶ ..(ዶሮ ማነቂያ፣ ዕሪ በከንቱ)
ክራሩን ስትሰሚ ብቅ በይ ቆሞያለሁ ከበርሽ ማዶ
ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ
ማታ ማታ
ማታ ማታ
አምጣት ከጎኔ ትቀመጥ
እንጀራ አይቀርብም ካለወጥ
አቅፎ ገላዋን አልጠግብ ያለዉ
ማነዉ ካላችሁ ማነዉ ማነዉ?
ልቤ ልቤነዉ ልቤ እራብተኛዉ
እሏን ወዶ ሌት የማይተኛዉ
ይዉጣ ይዉጣ እግሬ ይዛል በእርምጃዉ
ከሏ አይብስም ሰባ ደረጃዉ
ዘበናይ ዘበናይ….
ሲመሽ ወደ ማታ ሁሉ ዘግቶ በሩን
ታም ታራም ሳረገዉ ብቅ በይ ክራሩን
ታም-ታራራም-ታራራም…..
ፀጉራን ተተኩሳዉ እንደ አርምዴ ሜሪ
ዘበናይ ናት ፍቅሯን በክራር ነጋሪ.
ታም-ታራራም-ታራራም…..
ሄዶ ከኮሪያ ዘማች ሲመለስ
ያወሳል ናፍቆቱን በክራሩ ድምጵ
ፍቅርሽ አስጨንቆ መላወስ አቃተኝ
ተደናበርኩልሽ ጥይት እንደሳተኝ
ሳተና ነበርኩኝ ተካሽ በመዉ ዘሬ
ለዘበናይ ብቻ እጄን ሰጠሁ ዛሬ
አዝማች
በሳሪያን ኮት ላይ ያንን ቀጭን ኩታ ጣል አድርጌ
በመኮንን ድልድይ ልምጣ በደረጃዉ በፒያሳ አድርጌ
እንደ አውራ ዶሮ ክንፍ ኮቴን እየሳብኩት መሬት ለመሬት
በዞርኩት ገላሽን ሳትወጣብኝ ፀሀይ ሳይነጋብኝ ሌት
ሲመሽ ወደማታ ማታ ማታ
አቤት ያንቺ ፍቅር ሲበረታ
ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ
ብቅ በይ ሲገረፍ ክራር ሲመታ
ማታ ማታ
ማታ ማታ
ሞልቶ በአራዳ የአርመን ዳቦ
ሳሳ አካላቴ ሰዉ ተርቦ
አቅፎ ገላዉን አልጠገብ ያለዉ
ማነዉ ካላችሁ ማነዉ ማነዉ?
ልቤ ልቤነዉ ልቤ እራብተኛዉ
እሏን ወዶ ሌት የማይተኛዉ
ይዉጣ ይዉጣ እግሬ ይዛል በእርምጃዉ
ከሏ አይብስም ሰባ ደረጃዉ
ዘበናይ ዘበናይ….
አይወጣም ደረጃ ቢፈጥን ሴሼንቶ
እንደኔ ካሌደ በፍቅር ተገፍቶ
ታም-ታራራም-ታራራም…..
መድፈሪያሽ ወርቅ ነዉ ብርም አይገዛሽ
ልብ የሌለዉ ሀብል ግድም አይሰጥሽ
ታም-ታራራም-ታራራም…..
ከአንገትሽ ላይ አርጊኝ እንደማርትሬዛ
ወደወዲያ እንዳልል አደብ እንድገዛ
ተከለከለ አሉ የንጉስ አዳራሽ
የክት ያለበሰ አይገባም በጭራሽ
መጣሁ ከኮሪያ ይዤልሽ ሰዓት
በፓሪ ሞድሽ ላይ አምርሽ ታዪበት
ዘበናይ ዘበናይ….
ግጥምና ዜማ፡ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
ሙዚቃ ቅንብር፣ ሚክሲንግ፣ ኪቦርድ እና ቤዝ ጊታር፡ ዳግማዊ ዓሊ
ናሙና ዝግጅት፡ አብርሃም ዘዉዴ
ክራር፡ ታመነ መኮንን
ድምጵ ቀረጳ፡ ክብረት ዘ/ኪዮስ
ፕሮዲዩስድ፡ በቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)