June 30, 2014
15 mins read

Health: ዲ.ኤን.ኤ – DNA ለምን ጉዳይ? እንዴት? መቼ?

 

ዲ.ኤን.ኤ (Deoxy Ribonucleic Acid) /DNA/ በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ሌሎች በሙሉ የያዟቸው የሞለኪውል ቅንጣቶች ሲሆኑ፤ ገና አንድ ጽንስ ተፅንሶ የተሟላ አካል ባለቤት እንዲሆንና የህይወትን አካላዊ ተግባር እንዲያከናውን የሚረዳ ነው፡፡

የዲ.ኤን.ኤ ቅንጅታዊ ስርዓት (DNA sequence) በዚህች ምድር ላይ ያሉ ሰዎችን በሙሉ ልክ እንደ አሻራ መለየትና የማጣመር ብቃት አለው፡፡ በዚህም ሰዎችን በተለያዩ ነገሮች እንዲለዩ ማድረግ ያስችላል፡፡

የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ ምንነትና የህጋዊነት ክርክሮች

የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ የሚከናወነው እጅግ ግላዊ ለሆኑ ጉዳዮች ለምሳሌ ለበሽታዎች ስለሚኖር ተጋላጭነት ሲሆን፤ በተለያየ ሁኔታ ለንግድ የተቋቋሙ ኩባንያዎች የሰዎችን የጤና ምስጢር ለመግለፅ ሳይሆን የዲ.ኤን.ኤ ቅደም ተከተል መለያና ከሰው ሰው የሚለየው ሾርት ታንደም ሪፖርትን /Short Tandem reports/ በመመርመር ሁለት ሰዎች የሚገናኙት ወይም የሚለያዩ መሆኑን ነው የሚያጣሩት፡፡ የፖሊስ ሳይንቲስቶች ኢስ.ቲ አርስ የተባለውን ምርመራ ይጠቀማሉ፡፡ በትዳር ላይ መማገጥንና ማታ አንሶላ ከተጋሩዋትና በራስ ዲኤንኤ መካከል ያለውን መጣጣም ለማወቅም ይቻላል፡፡ እንደ ባለሙያዎች አገላለፅ ሰዎች የዲኤንኤ መመርመሪያን በቀላሉ ሊገዙት ስለሚችሉ ወደ ምርመራ ቢዝነሱ ይሮጣሉ እንጂ ስለ ህግ ጉዳየችም ሆነ የሌሎችን ግለሰባዊ መብት ስለመጋፋታቸው ለማሰብ ጊዜ አይኖራቸውም፡፡

በበርካታ ሀገራት የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ ከሚያስከትለው ጉዳት በተጨማሪ ከፍተኛ የህግ ፈተና ገጥሞቷል፡፡ በብዙ ሳይንቲስቶች ጥናታዊ ምርመራ በዓለም የጄኔቲክ ምርመራ እጅግ ትልቁ ገበያ ያላት ሀገር አሜሪካ በእያንዳንዱ ግዛት ስለግለሰቦች መብትና ስለሚከለከሉ ህጎች ምንም መረጃ የለም፡፡ በርካታ ግዛቶች በትዳር ላይ ስለሚኖር መማገጥም ሆነ አባትነትን ለመለየት ዲ.ኤን.ኤ የሚሰበስቡና ቢዝነስን የሚያከናውኑ ድርጅቶች ያሉ ቢሆኑም በየትኛው ህግ እንደሚዳኙ ምንም ማስረጃ ለማግኘት አልተቻለም፡፡ ለምሳሌ እ.ኤ.አ 1996 ድረስ ማንኛውም የኒዮርክ ግዛት ነዋሪ የሆነን ሰው ጄኔቲክ ምርመራ ወይም ያለፍላጎቱ ውጤቱን መግለጽ ህገ ወጥ ነበር፡፡ ያለ ግለሰቡ ፍቃድ የሚደረግ የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ ብዙዎችን ለስጋት ሲዳርግ፤ የህክምና ማህበረሰቡን የህግና የስነ ምግባር አጣብቂኝ ውስጥ ከቷል፡፡

ኢንተርኔት አዘውትሮ የመጠቀም ዕድል ያለውና የጤና ድህረ ገጾች የሚጎበኝ ሰው የሚወሰልት የትዳር ተጓዳኝን ለማወቅ፣ የልጅዎ አባት መሆን አለመሆንዎና መሰል ጥርጣሬዎችን ለማረጋገጥ ከፈለጉ ‹‹እኛ ዘንድ ይምጡ!›› የሚሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የንግድ ማስታወቂዎችን የማንበብ አጋጣሚ ይኖረዋል፡፡ ሆኖም የምርመራውን ትክክለኛነት፣ ስለ ህጋዊ ተቀባይነትና ስለሚያስከትለው የስነ-ልቦና ቀውስ ማንም ያስተዋለ ባይኖርም ተግባሩ አለመወገዙን ነው የተለያዩ ሚዲያዎች የሚዘግቡት፡፡ በእንግሊዝም ተግባሩ ህገ ወጥ ነበር፡፡ ነገር ግን ቀስ በቀስ የምርመራው ጥቅም እየጎላና እያደገ በመምጣቱ ታላቅ ይፋዊ ተግባር በመሆን ላይ ነው፡፡

 

ዲ.ኤን.ኤ ምርመራ – ለአርኬዎሎጂ

የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ በአርኪዎሎጂ ምርምር ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው፡፡ ይህም የተለያየ የጀኔቲክ ኮዶችንና ቅደም ተከተሎችን (Genetic Codes and Sequences) በመጠቀም ከብዙ ዓመታት በፊት በምድር ላይ ህይወት ምን እንደሚመስልና ተያያዥ የቀደምት የአኗኗር ሁኔታን ለመጠቆም የሚያስችል ነው፡፡ ይህ ደግሞ በተለያየ ወቅት የምድራችንን የስነ ህይወት ገፅታዎችን ከማንፀባረቅም በተጨማሪ ተያያዥ የሆኑ ምርምሮች የበለጠ እንዲደረጉ አስተማማኝ መረጃን ለመስጠት ያስችላል፡፡

 

የወላጅነት ማረጋገጫ – በዲ.ኤን.ኤ ምርመራ

የተለያየ አጋጣሚ የልጆቻቸውን ማንነት መለየት ላቃታቸው የአብራካቸውን ክፋይ በምርመራው ማረጋገጥ የሚያስችል ሲሆን፤ ሌላው ደግሞ ድብቅ በሆነ የወሲብ ውስልትና ውስጥ የሚፈጠሩ የመደፈር፣ የማርገዝና የተወለደ ልጅን የእኔ አይደለም ብሎ ላለመቀበል መደፋፈርና ከህግ ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታትም የተሻለና አማራጭ የሌለው ሆኗል፡፡

 

የወንጀል ነክ ጉዳዮችን ለማሳወቅ

ወንጀለኞች ወንጀል ሰርተው በሚጠፉበት ጊዜ ከአካላቸው ጋር ከተነካኩ ነገሮች በሙሉ በሚወሰዱ ናሙናዎች የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ በማድረግ ከማንነታቸው ጋር የማዛመድ ስራ በመስራት ተጠርጣሪዎችን ለማግኘት ያስችላል፡፡ በየጊዜው እየተሻሻሉ በሚመጡ የዲ.ኤን.ኤ የምርመራ ቴክኖሎጂ ከምርምሩ ጥበብ መሻሻል ጋርም እጅግ የረቀቁ አካሄዶችን በማድረግ በዙሪያው የሚጠረጠሩ ሰዎችን ለማግኘት ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይህ ታዲያ ከአሸባሪነት ጋር በተያያዘም ራሱን የቻለ አስተዋፅኦ ሊያደርግም ይችላል፡፡

 

የጠፋ የቤተሰብ አባልን ለማግኘትና የዘር ሐረግን ለመፈለግ

የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ በተለይም በትውልድ ሐረግ ውስጥ የማይቀየረውን ዋይ ክሮሞዞም (Y chromosome) መሰረት ባደረገ መልኩ የቤተሰብ የዘር ሐረግ ተለይቶ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡ ይህም የተረሱ የዘር ሐረግንም ሆነ በአንድ አካባቢ ተለይተው የሚገኙ ሰዎችንም ከሌሎቹ ለመለየት ያስችላል፡፡ በዚህም ለምሳሌ ልክ ለረዥም ጊዜ እንደተለያዩት የደቡብና የሰሜን ኮሪያ ዜጎች ከረዥም ዘመናት በኋላ የቤተሰብ ማንነታቸው ተለይቶ እንዲገናኙም ይረዳል፡፡ በሳይንሳዊው ምርምር ለሚጠቀምበት ብቻ ማለት ነው፡፡

 

የተሻለ ጤንነት ያለው ልጅ እንዲወለድ

ከወሊድ በፊት በእናት ሆድ ውስጥ ያለውን የልጆች የጤንነት ደረጃ በማወቅ በጊዜው በቂ የሆነ ለውጥ የሚያመጣበትን እንክብካቤና ምርመራ ለማድረግ የዲኤንኤ ምርመራ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ በተለይም ህፃናት የማይድኑ አስቸጋሪ ህመሞችን ይዘው እንዳይወለዱ ችግራቸው በጊዜ ታውቆ ቁጥጥር እንዲደረግበት ለማድረግ የዲኤንኤ ምርመራ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

 

በዘር የሚተላለፉ በሽታዎችን ለማወቅ

ከላይ ከተጠቀሰው የጤና እንከን በተጨማሪም የዲኤንኤ ምርመራ በዘር የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመታደግ በተለይም ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዳይተላለፉና አንድ ትውልድ ላይ እንዲገታ ትልቅ እርዳታ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም እንደ ካንሰር ያሉ ህመሞች የሚበዙበት የሴሎች ደረጃና ሁኔታም ሆነ ምክንያቱን ቫይረስም ይሁን ሌላ ነገር ለመለየት ያስችላል፡፡ ታዲያ ይህ ከተለያዩ ህዋሳት በሚገኙ የዲ.ኤን.ኤ ምርመራዎች የተዛማጅ ስራዎች በማነፃፀርም የሚከናወን ነው፡፡

 

የአዲስ ስነ ፍጥረት ግኝትን ለመጠቆም

የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ የተለያዩ አዳዲስ ስነ ህይወታዊ ግኝቶችን የብቃት ሁኔታና በህይወት የመቆየት እድላቸውንም ለመመርመርና ለመጠቆም የሚረዳ ነው፡፡ ይህም የአንድን ዝርያ አመጣጥ ለማሳወቅ ወይም ከሌሎች ነባራዊ የስነ ፍጥረት አካላት ጋር ያላቸው ተዛማጅነትንም ለማጥናት የሚረዳ ነው፡፡

 

የሙታንን አካላት ለመለየት

በተለያየ አጋጣሚ የሚዋደዱ ሰዎች አንዳቸው ተለይተው መጥፋትና ሞተው አስክሬናቸውንም ለመለየት መቸገርን የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ የሚፈታው ይሆናል፡፡  በተለያዩ ምክንያቶች ለምሳሌ በአውሮፕላን መከስከስ በሚደርስ ችግር ባህር ውስጥ ሰጥመው የሚገኙ አስከሬኖችን ለመለየት የሚጠቅመው የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ ነው፡፡ ይህ የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ በውሃ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ኬሚካሎችንና ውሃውም ራሱ በሚፈጥረው ተፅዕኖ የሰዎች አካላት ሊጎዳ ስለሚችል ማንነታቸውን ለመለየት ያስቸግረናል፡፡ ስለዚህም ከአስከሬኑ በሚወሰድ ናሙናና ከመሰል የሌላ ሰው ናሙና ጋር በማመሳከር በአስከሬኑ ዙሪያ በቂ መረጃ እንድናገኝ ያስችላል፡፡ የአስክሬኑ የዝርያ ምንጭ፣ ሀገሩንና የህዝቦቹን ማንነት የመግለፅ አጋጣሚም እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

 

የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ በታዋቂ ሰዎች ላይ የደቀነው ስጋት

በቀዳሚነቱ የሚነገርለት የእንግሊዝ የዲ.ኤን.ኤ ስርቆሽ ህግ የታዋቂ ሰዎች ጄኔቲክ መለያቸው በአንዳንድ ፕሬስ ላይ ሊቀርብ ይችላል የሚለውን ስጋት ለማስወገድ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2002 የንጉስ ሀረይ ፀጉርን በመውሰድ የቀድሞ ልዕልት ዲያና አፍቃሪ የነበረው ጀምስ ሔዊት ልጅ መሆኑን ለማረጋገጥ መስረቁን ዘገባዎች አቀረቡ፡፡ ይህን የዩኬ የሰው ልጅ ጄኔቲክ ኮሚሽን የሰዎችን ጄኔቲክ መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ ህጉ ጠበቅ እንዲል ጥሪ አቅርቧል፡፡ እ.ኤ.አ በ2006 በእንግሊዝ ያለግለሰቡ ፈቃድ የሰውን ዲ.ኤን.ኤ መመርመር ወንጀል እንዲሆን ተደረገ፡፡ ያም ፀጉርን፤ ምራቅንና ማንኛውንም የሰው ህዋስን ያለፍቃድ መውሰድ ህገ ወጥ ተግባር እንደሆነ ያጠቃልላል፡፡ ማንም ተይዞ የተቀጣ ባይኖርም ድርጊቱን መፈፀም በገንዘብና በሶስት ዓመት እስራት ያስቀጣል፡፡

እንግዲህ ከላይ በዝርዝሩ እንደተገለፀው የዲኤንኤ ምርመራ ለበጎ ተግባር /ለህክምና/ መሆኑ ቀርቶ ለማህበራዊ ጉዳዮች በማዋል ሰፊ የቢዝነስ መስክ እየሆነ መምጣቱ የግለሰብ መብት መጋፋቱ የህግ ጥያቄን አስከትሏል፡፡ በርካታ የዓለም አገራት ቴክኖሎጂው ያላቸው በስፋት እየተከራከሩበት እንደሆነ ቢታወቅም ሌሎች ያልተዳሰሱት ሀገራት ጉዳዩን ህጋዊ እልባት ይሰጡት ይሆን ብሎ ከጠየቀ በኋላ ያ እስከሚሆን መጠበቅ የለብንም ሲል ያስጠነቅቃል፡፡ ይህም ማለት የዘር ህዋስ መታወቂያ ካርዶችን በየዞርንባቸው ስፍራዎች ጥለናቸው ስለምንነሳ የግለሰብ ነፃነትና መብት ለብዙ የማናውቃቸው ሰዎች ምርመራ የተጋለጠ ነው፡፡

 

 

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop