ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
[email protected]
ግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም.
መግቢያ
ይህችን ክታብ በዚህ ርእስ እንዳዘጋጅ ያነሳሳችኝ “ልማታዊ መንግስት-እንደ ቻይና፤ ነገሩስ ባልከፋ” በሚል ርእስ ዶ/ር ደስታው አንዳርጌ ግንቦት ፲ ቀን ፪ሺ፮ ዓ.ም ያቀረቡልን ክታብ ናት። ከ’ሀ’ እስከ ‘ሠ’ ተዘርዝራ የቀረበችውን ይህችን ክታብ ሳነብ፤ እንደኔ ያለውን እንቅልፋም ተማሪ ቀስቃሽ ምሁር፤ በክታባቸው አማካይነት ጣቴን ይዘው ወደ ጠቀሷቸው አገሮች ወደ እስያ፤ ቻይና፤ ታይዋንና ጃፓን በመንፈስ ወሰዱኝ።
ተመልከት! ልማታዊ መንግስት ይሉሀል:: ሰላም በምድራቸው፤ በጎ ፈቃድ በዜጎቻቸው አዕምሮ እና ስነ ልቡና ላይ ልማትን የመሰረቱ እነዚህ የቻይና የጃፓንና የታይዋን መንግስታት ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት የዘረጋው የልማት ግን፤ በጅብና በአህያ፤ በተኩላና በበግ፤ በጃርትና በዱባ መካከል የተዘረጋ የልማት ተቃራኒ ጥፋት ነው።” እያሉ በማነጻጸር ያስጎበኙኝ መሰለኝ።
ቀጥለውም፤ “የኢትዮጵያን ግማሽ ህዝብ ያቀፈችውን ኢትዮጵያዊቷን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን እመራለሁ ብለው ፓትርያርክ ነኝ የሚሉት “ካዲስ አበባ ወጥቼ በየገጠሩ ስዘዋወር ዓለም ያደነቀው ልማት ሲጣደፍ አየሁ” እያሉ ሲናገሩ ሰምተሀል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በዘረጉት ያብነት ጉባዔ ተሳትፌያለሁ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ትክክለኛ ቄስ ነኝ የምትል ከሆነ፤ ያስጎበኘሁህን አይተህ፤ የነገርኩህን ሰምተህና ተረድተህ፤ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መምህራን ካስተማሩህ የልማት ዘይቤ ጋራ አነጻጽረህ፡ በክህነታዊ ሀለፊነትህ የምትለው ለማለት አትፍራ” ያሉኝም መሰለኝ።
በዚህ ስሜት ላይ ሆኘ ክታቧን ለመጨረስ ቀጥየ ሳነብ፤ በተራ ዝርዝር ሐ ላይ “የአገር ፍቅርና የሃላፊነት ስሜት” በምትለው አንቀጽ ስር፤ እኛ ኢትዮጵያውያን የተሰለፍንበት መስክ የሚጠይቀንን ሀላፊነት መውሰድ የማንችል ደካሞች መሆናችንን ለማሳየት፡ እኒሁ የተከበሩ መምህራችን ብዙ ምሳሌዎችን ከጠቀሱ በኋል፤ “ለበጎውም ለክፉውም ተጠያቂው ሁልጊዜ ሌላ ነው። . . . . . . . ራስን መጠየቅ፤ እውነትን መጋፈጥ መንፈሳዊ ወኔ ይጠይቃላ።” ካሏት እንደ ጦር ፍላጽ ከምትናደፈው ቃለ አጋኖ ላይ ደረስኩ።
[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]