ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌ ሌና
ወያኔ /ኢህአዲግ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ትልቁ የፖለቲካ አጀንዳ አድርጎ የተነሳው ሕዝብን ከሕዝብ ጎሳን ከጎሳ ሀይማኖትን ከሀይማኖት የፖለቲካ ድርጅትን ከፖለቲካ ድርጅት በማጋጨትና በማጣላት ላይ ሲሆን ህሕዋት እያራመደ ባለው የዘርና የጎሳ ፖለቲካ የተነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ ከመቸውም ጊዜ በላቀ እና ታይቶ በመይታወቅ ሁኔታ የወያኔ መንግስት አሁን የኢትዮጵያን ህዝብ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልልና አካባቢ ሕዝቡ ኢትዮጵያዊነቱን እንዳያይ በዘር እየከፋፈለው ነው:. የህህዋት/ኢህአዴግ ገና ወደ ስልጣን ብቅ ሲል በጦርነት ከደርግ የሚረከባቸውን ቦታዎች ፣ዳገትና ቀበሌዎች ሁሉ በቤተሰብ ሳይቀር እየከፋፈለ በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች እያሰረ ልዩነታቸውን ብቻ እያሳየ ሌላ አማራጭ ያልነበረው ህዝብ ሲቀበለው ቆይቶ አሁን በክልል በዞን በወረዳ በቀበሌ እና ሰፈር ድረስ በዘርና በጎሳ ከፋፍሎ ይህ ወያኔ ከደደቤት በረሃ ይዞት የመጣው የዘረኝነት ፖለቲካ መዘዝ ዘሬም በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቶ በየሰፈሩ አሁን የእንትን ሰፈር ልጅ ከእንትን ሰፈር ልጅ ጋር በጩቤ በድንጋይ ሲፈነካከት ሲተራረድ ማየት ምንም አዲስ ነገር አይደለም፡፡የአንዱን ወረዳ ነዋሪ ከሌላኛው ወረዳ ነዋሪ ጋር በሆነ ባልሆነው ሲኮራረፍ ሲገዳደል ሲቀጣቀጥ ማየት ምንም አዲስ አደለም፡፡ አንዱ ዞን ከሌላኛው ዞን ጋር በስራቸው በሚያስተዳድሩት ህዝብ ስም ጥቅም እየነገዱ አንዱን ከአንዱ አባትን ከልጁ እናትን ከልጇ ወንድምን ከወንድሙ ምን አለፋችሁ በቃ በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደምታዩት ጠላቶች ሆነን ስንጨራራስ ስንተራረድ እንገኛለን፡፡ሰው ከሰው ጋር ለምን ይጋጫል ለምን ይገዳደላል የሚለው እውነተ ውስጥ አልገባሁም እርሱ ራሱን የቻለ ተፈጥሯዊ ክስተት ስለሆነ፡፡በዛም አለ በዚህ የመከፋፈላችን የመጨረሻ ውጤትና ምክንያት ፍጅት ነው፡፡ ሆኖም ፍጅት ሲባል ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ሊነሳ የሚችለው ፍጅት እንደሁቱና ቱትሲ ይሆናል ብላችሁ ግን አታስቡት፡፡ መቸም ቢሆን ይህ ጉዳይ ሊከሰት አይችልም፡፡ በብሄር ግጭት ተነስቶ ኢትዮጵያ ሃገራችን ትጠፋለች አንድ ዘር ይጠፋል ማለት አይቻልም፡፡ ለዚህ ራሱን የቻሉ እውነተኛ ምክንያቶች አሉ፡፡ ሌላው ዓለም ላይ የሌሉ ሃገራችን ውስጥ ግን እንደ ዕድል ብቻ ሆኖ ያሉ ነገሮች ሕዝባችን ሳይማር ተፈጥሮ ብቻ አስተምራ ያኖረችው ትውልድና ትስስር በመሆኑ ብቻ አብረውን የሚኖሩ እውነቶች አሉ፡፡ወያኔ ኢህአዴግ ግን ከዞን እና ቀበሌ ባለፈ የመጨረሻ ሴራውን በክልል በቋንቋ፣ ዘር ፣ቀለም ወዘተ እያለ በባህል፣ በእምነት እያለ የሚታዩና የማይታንን ልዩነቶች እየፈጠረ በመካከላችን ምንም አይነት ችግርና ሳይኖር በፍቅር የኖረን ሆነን ሳለን ህህዋት ከጅምሩ ይዞ የተነሳውን በቋንቋና በዘር ልዩነት ላይ የተመሰረተው የፌደራል ሥርአትና ኢትዮጵያን የመሰነጣጠቅ ሴራው አሁን ላይ ስር እየሰደደ መጥቶ በኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድን የመሳሰሉ የመሳሰሉ የወያኔ አለቅላቂዎችና አሽከሩች ተጨምረውበት በእነዚህ የኢትዮፖያን ሕዝብ ደም መጣጭ ድርጅቶች በኩል እየተገበረ ያለውን ኢትዮጵያን የመሰነጣጠቅ እና ለአስተዳደር ለማመቻቸት በመሰለ ሴራና ተንኮል ህዝባችን አንድነቱ ፍርሶ ፣ አሞቱ ፈሶ ኢትዮጵያዊው ወኔ እንዲደርቅ በማድረግ ለራሳቸውየሚጠቅማቸውን ለህዝባችን እና ሃገራችን ግን ትልቅ የአንድነት ነቀርሳን ተክለውብን ምኞታቸውን እያሳኩ ይገኛሉ፡: ይህ የወያኔ የዘረኝነት ፖለቲካ መዘዝ ስር እየሰደደ በጣም በአሳሳቢ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ አስከፊና አሳዛኝ የሆኑ የተለያዩ ችግሮች እየወለደ፤ ጸብና ግጭቶችን እያበራከተ የዜጎችን ሕይወት በቀላሉ እየቀጠፈና የሕዝቦችን ሀብት በማውደም፣ቤቶችን በማቃጠል መጥፎ ክስተት እየተከሰተ ይገኛል። ከተለያዩ ምንጮች እንዳገኛውት ከሆነ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ደገሃቡርና ጅጅጋ፤ በምሥራቅ ሀረርጌ ጋራሙለታ፤ በደኖ አንስቶ በባሌና በአርሲ በሚገኙ አካባቢዎች በዘር ላይ የተመሰረቱ ግጭቶችና የሰው ሕይወትና ንብረት የወደሙበት በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። በምዕራብ ኢትዮጵያም ቢሆን በተለያዩ ወቅቶች በአሶሳ በባምባሲ፤ በሰሪ፤ በጋምቤላ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ፤ ነቀምት፤ አምቦም ለዚሁ አስከፊ ሁናቴ የሚጠቀሱ ናቸው። በአርሲ ክፍለ ሀገር በአርባጉጉ አውራጃ ውስጥ በሚገኙ ጎሎልቻ፤ ጨሌ፤ ጃጁ፡ መርቂ በተሰኙ ወረዳዎችና አካባቢዎች በርካታ መኖሪያ ቤቶች የወደሙበት፤ ሕይወት የጠፋበት፤ የሰው ልጅ እንድ ከብት አንገትና ጡቶች የተቆረጡበት አሰቃቂና አሳዛኝ በድሎች ተካሂደዋል። በሌላ ቦታ ደግሞ ከነ ነፍሰሕይወታቸው ወደገደል ተውርውረው እንዲፈጠፈጡ ተደርገዋል። በምንም መንገድ ከታሪካዊ አመጣጡም ቢሆን እንደተረዳነው ወያኔ ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ አንድነት ሳይሆን የታገለው አሁንም የሚሮጠው ለእነዚህ አላማዎች ብቻ ነው፡፡ አንድም ታላቋ ትግራይን መመስረትና የአማራውን ተሰሚነት አኮላሽቶ መቅበር ነው፡፡ለዚህም አማራውን ዝም ካልነው አያስቀምጠንም” የሚለው የመለስ መፈክር በቂ ምስክር ሲሆን ይህንን የሚያረጋግጡም በርካታ የምስልና የድምፅ ቅጅዎች በተለያዩ ነፃነት ናፋቂ የየትኛውም ብሄር ታጋዮች እጅ ይገኛል፡: ከዚህ በፊት ኢትዮጵያን ሲመሩ የነበሩት መሪዎች ሁሉ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በማስከበረ ሕዝቡም አንድነቱን ጠብቆ እንዲኖር ብዙ መስዋትነትን ከፍለዋል በወያኔ መንግስት እንደ አውሪ የሚቆጠረው ደርግ ሳይቀር ለኢትዮጵያ አንድነት ምሳሌ ናቸው ::ደርግ በርካታ አንቱ የሚያስብሉት ትግባራትን ፈፅሟል፡፡ በኋላም ለውድቀት የዳረገው በትክክል ደርግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠልቶት ሳይሆን በመካከላቸው በነበረው ተራ የስልጣን ሽኩቻ ምክንያት በነበራቸው የሃሳብ መለያየት፣ ውስጣዊ ሴራ እና አማራጭ በማጣት አንድን የደርግ ወታደር በሁለት ብር ሂሳብ ለወያኔ በሰጡ ባስጨረሱ ጀኔራሎች ሴራ እንጅ በወያኔ ጥንካሬ እንዳልሆነ እውን ነው፡፡ የሚገርመው ግን የኢትዮጵያን አንድነት ለማጥፋት አላማ ይዞ የመጣው ወያኔ ስልጣን እንደያዘ የጀመረው የደርግን ጅማሮዎችን በሙሉ ከምድረ ኢትዮጵያ ማጥፋት እና ማቃጠል ፣ አንድነቷና ዳር ድንበሯ ተከብሮ የቆየውን ሀገሪቷን መሸጥና መቆራራጥ ሀገሪቷን ወደብ አልባ በማድረግ ለታሪክ መጥፎ የሆነ ጠባሳ ማስቀመጥ ነበር ይህንንም ከሻቢያ ጋር በመሰማማት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ አድርጎታል:: ወያኔ ኢህአዴግ አሁን የያዘው ስትራቴጅ ደግሞ የማያዋጣው ማጥ ውስጥ ስለከተተው የሚከተለው እንደ ትግሉ በግልፅ ራሱን በመገንጠል አላማ ማለትም የመሄድ ዓላማ ሳይሆን ተቃራኒውን ነው፡፡ ይህም ማለት አሁን በምኑም በምኑም ምንያት የከፋፈለውን ህዝብ የበለጠ በመከፋፈልና የመለያያ ታሪኮችን እንደመልካም አስተማሪ ታሪክ በመምዘዝ እና አደባባይ በማውጣት /ሆኑ አልሆኑ የሚለው ባይታወቅም ምንጭ ባይኖረውም/ አንዱን ከአንዱ በማፋጀት እራሱ መሄዱን ሳይጀምር ሌሎች በየአቅጣጫው እንዲሄዱ በማድረግ የተዳከመች ኢትዮጵያ የተፈረካከሰች ኢትዮጵያ ስትቀር…በሉ እኔም የድርሻየን እናንተ ከሄዳችሁማ…ብሎ ለመነሳት ነው ያሰበው፡፡ ይህ አላማውን ለማሳካት ደግሞ አማራውን ከኦሮሞው አፋሩን ከሶማሌው ቀበሌን ከቀበሌ ፣ ዞንን ከዞን፣ ወረዳን ከወረዳ፣ ቋንቋን ከቋንቋ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ፣ ፓርቲን ከፓርቲ በማንኛውም ልዩነት አድርገው በወሰዱት መለያያ ሁሉ ለማፋጀት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ለዚህም በትንሹም ቢሆን የተሳካላቸው ይመስላሉ ዘላቂ አይደለም እንጅ፡፡ ለዚህ ማሳያም አማራው ከቀየው እየተፈናቀለ ቤት ንብረቱ በየሜዳው እየተቃጠለ እየተዘረፈ እየተገደለ ነው:: ዛሬ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በርካታ ሚሊዮን አማሮች በርካታ መቶ ሽህ ትግሬዎች ሶማሌዎች አፋሮች ደቡቦች ጉሙዞች ጋምቤላዎች ይኖራሉ ግን የነፃነታቸው ጉዳይ አጠያያቂ ነው፡፡የህህዋት የዘረኝነት ፓለቲካ ባመጣው መዘዝ ዛሬ ላይ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖሩ አማሮች ችግር ውስጥ ናቸው:: ከሰሞኑ እንዳየነው በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ በወያኔ መሰሪና ተንኮል የአካባቢው ተወላጆች የሆኑ ኦሮሞዎች በአማራው ተወላጅ ሕዝብ ላይ እያደረሱት ያለው ግፍና በደል ምስክር ሲሆን ብዙዎች ኢትዮጵያኖችን ያሳዘነና ሁላችንም ልናወግዘው የሚገባ ድርጊት ሲሆን አሁን ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ጊዛቶች ወያኔ ወደስልጣን ከገባ ጀምሮ አማሮች በኦሮሚያ ይገደላሉ ይታሰራሉ ንብረታቸው ይዘረፋል ይቃጠላል…ወዘተ ይህ ደግሞ የኦሮሚያ ህዝብ ለኢህአዴግ ሴራ ተገዥና ተጠቂ መሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን ይህን ሁሉ በደልና ግፍ የኦሮሚያ ህዝብ ኢህአዴግን ለመደገፍ ፈልጎ እንዳልሆነ ግልፅ ጉዳይ ነው ሆኖም ግን ስንት በርካታ ምሁራንን ያፈራው የኦሮሚያ ህዝብ ያላወቀው እና ለፀረ-ኢትዮጵያዊያን ተዘዋዋሪ አጋዥ ሆኗል ይህም ወያኔ ያመጣው የዘረኝነት ፖለቲካ መዘዝ ውጤት ነው:: አንድ ልናውቀው የሚገባ እውነት ይህች ሃገር በፍጹም ልትበታተንና ልትጠፋ አትችልም:: ይህንም ህህዋቶችና የወያኔ ተላላኪ፣ተለጣፊዎቹ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ ያወቁት አይመስለኝም ፡፡ ይህ ህዝብ አንድ ሆኗል በወያኔ ተንኳልና ሴራ አሁን ላይ በተለያዩ ነገሮች ቢጋጭም የተጋባ፣ የተዋለደ፣አብሮ የበላና ፣የጠጣ አብሮ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲል የታዋጋ ፣ የደማና የቆሰለ ሕዝብ ነው :: ይህ እውነታና ሚስጥር ያልገባቸው አንዳንድ የወያኔ ኢህአዴግ ሴራ ማስፈጸሚያና መጠቀሚያ መሆናቸውን ያላወቁ በስሜት የሚነዱ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ናቸው፡፡ስለሆነም የኦሮሞው፣የአማራው፣የአፋሩ፣የትግራዩ፣የጋምቢላው ……..ሕዝብ የወያኔ የዘር ፖለቲካ ማስፈጸሚያ እንዳይሆን ሊጠነቀቅ ይገባል እያልኩኝ እዚህ ላይ ላጠቃልል:: ውድቀት ለዘረኛው የወያኔ አገዛዝ !! የኢትዮጵያ አንድነት ለዘላለም ተጠብቆ ይኖራል!! [email protected]