May 8, 2014
17 mins read

በሬየን አልሸጥም – አጭር ወግ – በሄኖክ የሺጥላ*

አዲሱን (የነበረውን ግን ሰሞኑን የሾረውን) የ “ኦሮሞ ወጣቶች ” ግድያ። በነገራችን ላይ ለምንድን ነው “የኢትዮጵያ ወጣቶች ” የማንለው? ማለት ስለማንፈልግ? ወይስ ብንል ባንል ምን ይጠቅማል ( ምንስ ይጎዳል በሚል ሃሳብ?) ሁለቱንም ያዙልንና እንቀጥል።

ሰሞኑን አምቦ ላይ የተፈጸመውን ግድያ  ተከትሎ ወዳጆች ” ልጅ ሄኖክ በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር በል እንጂ “ጠላቶች ደሞ ” አንተ ምንትስ አማራ አሁን አማራ ቢሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ መከራ የደረሰበት አምሳ ገጽ ጽፈህ ፣ ነገሩን ለውጠሕና ለጥጠህ ባቀረብከው ነበር ” የሚሉ መልዕክቶችን አስቀምጠውልኛል። እኔም እንደ ለገዳዲ ሬዲዮ ” ጦማሪዎችች ሆይ ምልእክታችሁ  ደርሶኛል ለሁሉም እንደነገሩ ለመመለስ እንሆ–”

በነገራችን ላይ አማራ ስለመሆኔ እኔ በበኩሌ እርግጠኛ አይደለሁም ፣ ቢያንስ እርግጠኛ እስክሆን ብትታገሱኝ ምን ነበረበት ( ስለ-ኔ ከኔ በተሻለ መልኩ የምታውቀው እናቴ እንኩዋ እንዲህ በሙሉ አፍዋ “አንተ አማራ!”  ብላኝ  አታውቅም። ታዲያ የምታውቀው ነገር ቢኖራትም አይደል ? አለበለዚያ ማኛና ሰርገኛ በሚል ማህበረስብ ውስጥ አድጋ እኔን በደም ስሜ መጥራት ባልዳገታት ” እስኪ ለናቴ ጊዜ እንደሰጠሁዋት እናንተም ለኔ ጊዜ ስጡኝ ” ደሞ ለዘር ፣ እድሜ ለወያኔ እንኩዋን የሰው  የንብ ሰፈር እንኩዋ በታወቀበት ዘመን የምን መንገብገብ ነው!) ።  አቦ እናት ለዘላለም ትኑር ! ቀጣዩን ሃሳብ በሚቀጥለው መስመር ላይ ያንብቡት።

መልስ አንድ:  ለሞቱት ስንገጥም

 

ሲረግጡን ታግሰን

ሲሰድቡን ታግሰን

ይሄን ሁሉ ዘመን ብሶት ተንተርሰን

ሃዘን አኮራምቶን

መላ ቅጡ ጠፍቶን

ሁሉም ግራ ሆኖ

በሃሳብ ተውጠን

ከሥጋ ስማችን

ያፈሩ ከበደን ።

 

እና አይሆንም አልን

ሕጉ ይስተካከል

ይሞረድ ይቦረሽ ባለ ጥርሱ መድብል

ድንበሬን መልሱ ክብሬን እንዳሻችሁ

ነጻነቴን ቀሙኝ ስሜን እባካችሁ።

 

አልጻፍ አልናገር

አልሰለፍ ይቅር

ባልበላም ግድ የለም ዘመን ጾሜን ባድር

አይከፋኝም ከቶ ብሰደድ በገፋ

ሃገሬ ቢቆረጥ ታሪኬ ቢጠፋ

 

አይሞቅ አይበርደንም እኛ ግድ የለንም

ሰው ቢፈናቀል ቢራቆት ቢራብም

 

ወደብ አልባ ብሆን ወይም ወኔ አልባ

እሱ አይደልም ለኔ ከቁብ የሚገባ

 

እያልኩ ልቀጥል አሰብኩና ተውኩት።  እውነት እውነት እላችሁዋለሁ ሰው እንዳይከፋው እያሰቡ ለመጻፍ ከማሰብ የበለጠ  የሚከብድ ነገር ዕኔ በበኩሌ አላጋጠመኝም። ስለ መፈናቀል ጽፈ ሳልጨርስ ስለ አፈናቃዮች መጻፍ በጣም ይከብዳል፣ ስለ ዘረኛ ስርዓት ጽፈ ሳልጨርስ ስለ ዘረኛ ተጨቁዋኝ መጻፍ አሁንም ይከብዳል። ስለ ኢትዮጵያ ተናግሬ ሳልጨርስ ስለ መንዝ ወይም ስለ ኦሮሚያ መጻፍ ይደብታል። ስለ ትግሬ አምባገነን ተናግሬ ሳልጨርስ ስለ አማራ ወይም እሮሞ ታዳጊ አምባገነን ወግኖ መናገር ይከብዳል ።  የነገሩን ውስብስብነት ተረዱልኝ። በደላቸው፣  ስቃያቸው፣ መታሰር መገደላቸው፣ ሁሉም እውነትነት አለው። ግን   ሀሳባቸው ከደረሰባቸው በደል ያንሳል ፣ ስሜታቸው ካሳለፉት መከራ አንጻር ኢምንት ( ታልኢት) ነው፣ ጉልበታቸውን የማያውቁ በትንሽ ነገር የተጠመዱ ታጋዮች ሆኑብኝ፣ ወንድሞቻቸውን የሰዉለትና የምሰዉለት አላማ ከማንነታቸው ይደቃል፣ ጉዋዶች የተሻል ጥያቄ አለ ( ፍንጭ ልስጣችሁ አይደልም ኦሮሚያ  ኢትዮጵያ የኔ ነች የሚል )።   እስኪ አንድ ወደ ሁዋላ እንመለስና እናስብ። ስናስብ ደሞ በርጋታ እናስብ።

አንድ ወደ ሁ-ዋላ

በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ክፍላተ ሃገራት እንዴት ይካለሉ እንደነበር እናስብ ( ስለ ደርግ ጠቅላይ ግዛት አሰያየም  ብዙ ማውራት አልፈልግም፣ ማወቅ የፈለገ ያንብብ )  ፣ ከዚያ ” የዘመናት ብሶት የወረሰው ጀግናው የ ትግራይ ሰራዊት ( ስሙን ቀይሮ የ ኢህአዲግ የተባለው ) አዲስ አበባ ገባና ዔርትራን ለማስገንጠል የሚመች ሕግ አወጣ፣  በዚህም ሕጉ ኤርትራን  ብ ቻ ሳትሆን የልጅነት ( የእቃቃ ፍቅረኛዬም ) ከነ ኮካ ኮላ ኮርክያችን ( ጥሪታችን) ጋ አብራ ተገነጠለች (የሚገርመው ኮርኪ ሰለሆነ ነው መሰለኝ ይዘሽ መወጣት አትችይም አልተባለችም )። በመቀጠልም 70 ምናምን  ሺ  ሰው የጨረሰውና ያስጨረሰውን   ጦርነት አካሄአዱ ( በቴዲ አፍሮ ቁዋንቁዋ ” ሁለቱ ዝሆኖች”) በኔ ቁዋንቁዋ ዘ-ለቱ  እባብስ።

ያ ጦርነት አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ ለሰራው ሥራ የማህተም ማድረቂያ ካሳ ነበር።  ከዛ የመሃል ሀገር ሰው ጨዋተው የተጀመረ መስሎት በደስታ ፓርላማ ውስጥ ጨፈረ ( አንዳንዱ ኮፍያውና ሽርጡ እስከሚወልቅ ድረስ ) እና በየቤቱ የዘሩን ቆዳ የስል ጀመር። ጀግናው የኢህአዲግ ሰራዊት ግን ልጅነት ደጎሰ ጨዋታ ፈረሰ አለ ። ድሮስ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚሀብሄር ነሳ እንዳለው እዮብ ወያኔ ሰጠ ወያኔ ነሳ ሆነ  ( ስለዚህም ይህ የዘመን ብሶተኛ  ለኤርትራ በደም ለተቀረው ሕዝብ ደሞ በቾክ  ያሰመረውን ሕግ መርገጥ ጀመረ ) እና ከተሜ እንዴት ተደርጎ አለ። እኛ ስንት ነገር ስናስብ የምን ዘሎ መቀላቀል አይነት ነገርም አንዳንዶች ሲናገሩ ሰማናቸው። አንዳንዶቹ ልጆቻቸው በበሽታና በድንቁርና ከማለቃቸው የበለጠ የልጆቻቸው አማርኛ መማር አሳሰባቸው፣ በ 2006  መሬታቸውን ከቀማቸው ይልቅ ከመቶ ዓመት በፊት ቸፍጭፎናል የሚሉትን ሚኒልክን  መውቀስ ቀለላችው፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከመገንጠል በሚለው ይጠደሰጡት ፣ የአንድን ግለሰብ ሃሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብቱን ተቃወሙ እና በታንክ እና በ መትረይስ ከሚደበድባቸው ወያኔ ይበልጥ የቴዲ አፍሮ ዘፈን አመማቸው እና በጠራራ ጸሓይ እየተገደሉ  ወያኔ ይሙት ይላሉ ስል ” ቴዲ አፍሮ ይታሰርልን አሉ” ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ። ለዚያ ነው እየከፈሉት ያለው መስዋትነት ከያዙት ሃሳብ ይበልጣል ያልኩት ።  ነብሳቸውን አይማረውና የጎሳ ማይክሮ ባይሎጅስቱ ( መለስ )  ይህንን  ቆመው ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን ? እንደኔ እንደኔ ” አዋ ይሄኛው ባክቴሪያ ልክ እንደታሰበው ነው ሪ- አክት እያደረገ ያለው፣ ያኛው አሁንም ቢሆን ትንሽ ራይቦሶማል ትራይባል ሴንስ ኢንሰርት ሊደረግበት ያስፈልገዋል ” የሚሉ አይመስላችሁም? አይ እሳቸው ! አይ እኛ !

አንድ ወደ-ፊት 

የትግል ስያሜ ያላማ ግብር ይሆናል ማለት ዘበት ነው። ለምሳሌ ( የትግራይ ነጻ አውጪን እንመልከት)። በመጀመሪያ ትግራይ ማለት ከየት እስከየት ነው ? የመሃል ሃገሩን ትግራይ ይጨምር ነበር ? እንደዚያ ከሆነ የትግራይ ሕዝብ ሳይሆን የትግራይ ኑዋሪዎች ነጻ አውጪ ነበር መባል የነበረበት። ምክናይቱም ትግሬ ትግራይ ውስጥ ብቻ አይደልምና  የሚኖረው። ለምሳሌ የኛ ጎረቤት የነበሩት እማማ ሐዳስ ( እድሜ ለ ወያኔ የተንጣለለ ቤት ሰርተው ወደ ሳር ቤት ገቡ እንጂ ትግሬ ነበሩ። ግን ነጻ ስለመውጣታቸው እርግጠኛ አይደለሁም።

አሁንም ወደ ነገሬ ልመለስ ( ማንሽ አንቺ በዛሁ የጠፋሁ እንደሁ መልሽን )። ይሄ በተያያዘ ሃሳብ የመጥፋት ችግር አለብኝ ”

አሁንም የስያሜ ጦርነትን የሚቀድም ነገር ያለ ይመስለኛል ( እንዲሁ ሳስበው ፣ አያርገውና የኦሮሞ ሕዝብ ምናምን የሚባል ድርጅት አዲስ አበባን ” ፍንፍኔን በሸዋኛ ” ወይም ” ፊንፍኔ በኦሮምኛ” እዚህ ጋ ቶሎሳ እና ተሎሳ ብለው ሲጣሉ ስላየሁ ጥንቃቄ ቀድሜ ባረግ ብዬ ነው፣ ለማስመልስ ባደረጉት ጥረት ወያኔን ሳያስቡት ገለበጡት እንበል ( ልክ ወያኔ ሳያስበው አዲስ አበባ እንደደረሰ ) ከዛ ምን የሚሆን ይመስላችሁዋል ? እናንተ ለመመለስ ትፈሩ ይሆናል ሌኔ ግን የሞተው መለስ  በኦሮሞ ልጆች ስም; በኦሮሞ ልጆች ደም ፣ በኦሮሞ ልጆች አፈር ብቅ የሚል ይመስለኛል። ከስያሜ ማንነት ይቀድማል። ማንነታችንን ሳናስከብር ስለ ምንነታችን መናገር አንችልም ( ” መ ስፍን ወ/ማርያም እንዳሉት)።  መቼ ነው የነሱን ጨዋታ መጫወት የምናቆመው ? መቼ ?

 

ወግ

አንድ ገበሬ እጅግ የሚወደው በሬውን ሊሸጥ ገበያ ይዞ ይወጣና ሳይሸጥ  ይዞ ይመለሳል።

ዘመድ “ምነው ጃል በሬህን የሚገዛ ሰው አጣህ?”

ገበሬ ” አይ በሬዬን  ሊገዙ ከመጡት ሰዎች መሃል አንዳቸውም  ለበሬው የሚሆን ድርቆሽ ( መኖ ወይም ሳር ) አልነበራቸውም፣ ስለዚህ በሬየን ሽጬ በረሀብ ከምገልው ብዬ ነው ሳልሽጥ  ይዤው የተመለስኩ ”

እኔም እንዲህ ነው የሚታየኝ።  ወያኔ መውደቅ ስላለበት ተብሎ በሬዬን በርሃብ ለሚገል ገበያተኛ ነጻነቴን አልሸጥም። እንሱም (ወያኔዎችም) ቢሆን  ሲጠነሰሱ እርሾዋቸው ዘረኝነት ነበረና። በሬዬን ልተገዛ ከፈለክ መጀመሪያ ሳር ይኑርህ ፣ መጀመሪያ የሚገዛ ሃሳብ ይኑርህ፣ መጀመሪያ ስለ በሬ እወቅ።  አስራ ስምንት ሚሊዮን ጭቁን፣  አስራ ስድስት ሚሊዮን ጭቁን ቢጠላ ጥላቻው  ወተት አይወጣውም እሱንም የሚጠላውንም  ይዞ ይጠፋል እንጂ።  ብሬ መግዛቱ አይደልም ቁም ነገሩ ፣ ቁም ነገሩ እስክታርደው ድረስም በሬነቱን መገንዘብ ነው።

ገበያ ወጥቶ ሸማች መሆን አይደለም ቁም ነገሩ፣ ቀም ነገሩ ቢያንስ የሸማች ባህሪ ይዞ መገኘት ነው።

በአንድነት ለመቆም አንድ አይነት አመለካከት የግድ ሊኖር ይገባል በሚለው ሃሳብ ብስማማም በይበልጥ የሚያስማማኝ አንድ አይነት አላማ ሊኖር ይገባል የሚለው ነው።

እስከሚገባኝ የታጋይ ሃሳብ የጨቆኑትን ከማሸነፍ፣ የገደሉትን ከማንበርከክ፣ የበደሉትን ከመበደልም የራቀና የላቀ መሆን አለበት ብዬ አስባለው። በታጋይና በበቀልተኛ መሃከል ያለው ልዩነት ይሄም ይመስለኛል። ታጋይ አንድን ስርዓት ሲቃወም ወይም ሲታገል፣ ስርዓቱ ማድረግ የነበረበት ግን ያላደረገውን ነገር ለመለወጥ ይመስለኛል፣ አንድ ታጋይ አንድን ስርዓት ለመለወጥ ሲነሳ ፣ ኢ-ፍትሃውነትንም ሆነ የአስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እውቀቱና ብቃቱ እንዳለው አምኖ ያ እውቀቱና ብቃቱ ስልጣን ላይ ባለው ስራዓት ( ስርዓቱ በሚፈቅደው መንገድ ታግሎ ) እውቅናን ሲነፈግ ፣ ያ የሚያልመውን ለውጥ ለማምጣት እምቢ ያለ አካል ነው ብዬም አስባለሁ። በቀልተኛ ግን የድሮ ቁስሉንና ብሶቱን ከማሰብ እና ብድሩን እንዴት እንደሚመልስ ከማውተንተን ያለፈ ሕልም የለውም፣ ለሱ የሥርዓት ለውጥ ማለት የበደሉትን ( ወይም በድለውኛል በሎ የሚያምነውን) ማህበረሰብ መበደል ነው፣ ለሱ ትግል ቂሙን የሚወጣበት ፣ እልሁንና ቁጭቱን የሚገልጽበት አጋጣሚ መፈለግ ነው። ወያኔ የተፈጠረው በዚህ መንገድ ነው፣ ሌላውም በዚህ መንገድ መሄድ ይፈልጋል ፣ እንደ ዜጋ የተሻለ ሃሳብ ከሌለህ፣ ከቂመኛነት ወደ ታጋይነት፣ ከባለ አረርንት ወደ ባለ ር-አይነት መለወጥ ካልቻልክ በሬየን አልሸጥም።

ቸር ይግጠመን

 

 

 

* ገጣሚው

 

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop